“ሚያዚያ 1–7 ፦ ‘በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ከእርሱ ታረቁ።’ ያዕቆብ 1–4፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]
“ሚያዝያ 1–7 ። ያዕቆብ 1–4፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]
ሚያዝያ 1–7 ፦ በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ከእርሱ ታረቁ
ያዕቆብ 1–4
ኔፋውያኖች ኔፊን እንደ “ታላቅ ጠባቂ” ይቆጥሩት ነበር (ያዕቆብ 1፥10 ይመልከቱ)። ከመንፈሳዊ አደጋዎችም ሃጢያት እንዳይሰሩ በማስጠንቀቅ እና ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ በማበረታታት ጠብቋቸዋል። ያ ስራ አሁን ኔፊ ካህን እና አስተማሪ እንዲሆን አድርጎ በቀባው በያዕቆብ ላይ ወደቀ (ያዕቆብ 1፥18 ይመልከቱ)። “ሃጢያትን መስራት [የጀመሩትን]” ያዕቆብ በድፍረት ለማስጠንቀቅ እንዲሁም በሌሎች ሰዎች ሃጢያቶች ምክንያት “የቆሰለውን ነፍስ” ለማፅናናት ሃላፊነት ተሰማው (ያዕቆብ 2፥5–9 ይመልከቱ)። ሁለቱንም ማድረግ የሚችለው እንዴት ነው? ሁለቱም ቡድኖች የአዳኙን ፈውስ ያስፈልጋቸው ስለነበር (ያዕቆብ 4 ይመልከቱ) ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጠቆም ነው። ልክ ከእሱ በፊት እንደነበረው እንደ ኔፊ መልዕክት የያዕቆብም ምስክርነት “በክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ [ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁ]” ጥሪ ማድረግ ነበር (ያዕቆብ 4፥11)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
“ከጌታ መልዕክት” አለኝ።
ለያዕቆብ የእግዚአብሔርን ቃል ማስተማር “የጌታ መልእክት” ስለነበር “ሃላፊነቱን ለማጉላት” በትጋት ሰራ (ያዕቆብ 1፥17፣ 19)። ያዕቆብ የተጠቀማቸው እነዚህ ቃላት ለእናንተ ምን ትርጉም አላቸው? አጉሊ መነጽር ምን እንደሚሰራ አስቡ። ያ ምን ሀሳብ ይሰጣችኋል? ያዕቆብ 1፥6–8፣ 15–19 እና 2፥1–11ን ስታሰላስሉ ጌታ ለእናንተ ሊኖረው የሚችለውን ተልእኮዎች አስቡ። እነዚያን “ለማጉላት” ምን ለማድረግ ተነሳሳችሁ?
በተጨማሪም “ጌታ የሚጠራውን ብቁ ያደርጋል [Whom the Lord Calls, the Lord Qualifies]፣” በየቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች፦ ቶማስ ኤስ. ሞንሰን (2022 እ.አ.አ)፣ 209–20፤ “ለጥሪያችሁ ብቁ ሁኑ [Rise to Your Cal]l” (ቪድዮ)፣ በወንጌል ቤተ መጽሐፍ ውስጥይመልከቱ።
“ይህ የልባችሁ ክፋት ነፍሳችሁን እንዲያጠፋ [አትፍቀዱ]!”
ኔፋውያ የኩራት እና ሃብት ላይ የማተኮር ችግር ነበረባቸው (ያዕቆብ 2፥13 ይመልከቱ)፣ እናም ያ ችግር ለእነሱ እና ለቀናቸው የተለየ አልነበረም። ጠላት ዛሬ የሀብትን ፍቅር የሚያበረታታው እንዴት ነው? ያዕቆብ 2፥12–21ን ካነበባችሁ በኋላ፣ እግዚአብሔር ቁሳዊ ሀብትን እንዴት እንድታዩ እንደሚፈልግ በራሳችሁ ቃላት ግለፁ። እንደ “ብዙ ስለተሰጠኝ [Because I Have Been Given Much]” (መዝሙር፣ ቁጥር 219) አይነት መዝሙር ተጨማሪ ሃሳቦችን ሊሰጥ ይችላል። ከምትማሩት ነገር ምን ለማድረግ መነሳሳት ይሰማችኋል?
እግዚአብሔር በንፅህና ይደሰታል።
ያዕቆብ 2፥22–35፤ 3፥10–12ን ስታነቡ ንፅህና ለእግዚአብሔር ለምን በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ለመረዳት የሚረዳችሁን ምን ታገኛለችሁ? በያዕቆብ እና በእኛ ዘመን አንዳንድ የብልግና አሉታዊ ውጤቶች ምንድን ናቸው? ንፁህ ህይወትን የመምራት በረከቶች ምንድን ናቸው?
ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር “ዘርን በመተካት ቅድስና ላይ በሚሳለቅ አለም ውስጥ” እንደምንኖር አስተምረዋል [“ንፁህ በመሆን እናምናለን [We Believe in Being Chaste]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2013 (እ.አ.አ) 41–44]። የንፅህናን ህግ ለምን እንደምትጠብቁ ሌሎች እንዲገነዘቡ እንዴት ትረዳላችሁ? “አካላችሁ ቅዱስ ነው [Your body is sacred]” በለወጣቶች ጥንካሬ፦ ውሳኔዎችን የማድረግ መመሪያ (ገጾች 22–29) ውስጥ ስለ ጾታዊ ስሜት እና ግንኙነት እግዚአብሔር ያወጣቸውን መሥፈርቶች ማብራራት ለመጀመር መልካም ቦታ ነው። የንጽህናን ህግ ለምን እንደምትኖሩ ለማብራራት የሚረዳችሁን በዚያ ምንጭ ውስጥ ምን ተጨማሪ ነገር ታገኛላችሁ?
ከላይ በተጠቀሰው የሽማግሌ ቤድናር መልዕክት ወይም በ “ነፁህ ለመሆን መምረጥ እችላለው [I Choose to Be Pure]” (የወንጌል ቤተ መጻሕፍት) ቪድዮ ውስጥ ተጨማሪ መልሶችን ማግኘት ትችላላችሁ።
የእግዚአብሔር የፆታዊ ንፅህና መለኪያ ከሚያጋጥሟችሁ ከሌሎች መልዕክቶች የሚለየው እንዴት ነው? ንፁህ ህይወትን የመምራት በረከቶች ምንድን ናቸው?
በተጨማሪም የወንጌል ርዕሶች፣ “ንጽህና [Virtue]፣” የወንጌል ቤተ መጽሐፍት፤ “የተመሳሳይ ፆታ ስበት [Same-Sex Attraction]” በ“የህይወት እርዳታ [Life Help]” በወንጌል ቤተ መጽሐፍት ስብስብ ውስጥ ይመልከቱ።
በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ እችላለሁ።
ያዕቆብ “በክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ [ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁ]” ህዝቡን ለመነ (ያዕቆብ 4፥11)። የመታረቅ አንዱ ትርጉም ወደ ወዳጅነት ወይም ስምምነት መመለስ ማለት ነው። የራሳችሁን ህይወት ስታሰላስሉ ከሰማይ አባት ርቃችሁ እንደነበር ስለተሰማችሁ ጊዜ አስቡ። ይህን ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ አዳኙ እንዴት ይረዳችኋል? በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር እንድትታረቁ የሚረዳችሁን ምን ምክር ማግኘት ትችላላችሁ? (ቁጥር 4–14 ይመልከቱ)።
ከማቴዎስ 5፥23–24 ምን ተጨማሪ ግንዛቤን ታገኛላችሁ? አዳኙ ከእግዚአብሔር እንዲሁም ከሌሎች ጋር እንድትታረቁ እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል?
በተጨማሪም 2 ኔፊ 10፥24 ይመልከቱ።
በአዳኙ ላይ በማተኮር መንፈሳዊ እውርነትን ማስወገድ እችላለሁ።
ያዕቆብ ህዝቡን የበለጠ ወደ ጌታ ለመመለስ ሲሰራ፣ በመንፈስ እውር እንዳይሆኑ እና የወንጌልን “ግልጽ ቃላት” እንዳይንቁ አስጠነቀቃቸው (ያዕቆብ 4፥13–14 ይመልከቱ)። በያዕቆብ 4፥8–18 መሰረት፣ መንፈሳዊ እውርነትን ለማስወገድ ምን ማድረግ እንችላለን?
በተጨማሪም ክውንተን ኤል. ኩክ፣ “ከምልክቱ ባሻገር ተመልከቱ [Looking beyond the Mark]፣” ኢንዛይን፣ መጋቢት 2003 (እ.አ.አ) 40–44 ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
እግዚአብሔር የቆሰለን ነፍስ ይፈውሳል።
-
“የቆሰለ ነፍስ” እንዴት መዳን እንደሚችል ለልጆቻችሁ ለማስረዳት፣ አካላችን እንዴት እንደሚቆስል እና እንዲፈወስ ምን እንደሚረዳ በጋራ ልትወያዩ ትችላላችሁ። ለምሳሌ ልጆቻችሁ ስለተጎዱበት ጊዜ እና ለመፈውስ ምን እንደረዳቸው ሊናገሩ ይችላሉ። እንደዚህ ውይይት አካል ፋሻ ወይም መድሃኒት ልታሳዩ ትችላላችሁ። ምናልባት መንፈሳችሁ ፈውስን ሲሻ አዳኙ እንዴት እንደረዳችሁ ለእነሱ ልታካፍሉ ትችላላችሁ።
በማካፈል የተቸገሩትን መርዳት እችላለሁ።
-
በያዕቆብ ዘመን የነበሩ አንዳንድ ሰዎች እጅግ ሀብታም የነበሩቢሆኑም ያላቸውን ለሌሎች ለማካፈል አይፈልጉም ነበር። በያዕቆብ 2፥17–19 ውስጥ የያዕቆብን ትምህርቶች ስታነቡ፣ ከእነዚህ ጥቅሶች ጋር የሚዛመዱ ምስሎችን ወይም ቁሶችን እንዲይዙ ለልጆቻችሁ መስጠት ትችላላችሁ። እነዚህን ቁሶች ለእነሱ እያካፈላችሁ እንደሆነ ልትገልጹ ከዚያም በኋላ ቁሶቹን ለእናንተ ወይም ለሌሎች እንዲያካፈሉ መጋበዝ ትችላላችሁ። ስታካፍሉ ምን እንደሚሰማችሁ ተናገሩ። ሌሎች ደስታ እንዲሰማቸው ለመርዳት ከእነሱ ጋር ምን መካፈል እንችላለን?
-
ያዕቆብ 2፥17ን በጋራ ካነበባችሁ በኋላ የሰማይ አባት ለእነሱ ያካፈለውን በረከቶች ልጆቻችሁ መዘርዘር ይችላሉ። እርሱ አንዳችን ለሌላችን እንድናካፍል ለምን ይፈልጋል?
በኢየሱስ ክርስቶስ እምነቴን ማጠንከር እችላለሁ።
-
ያዕቆብ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የነበረው እምነት ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ የመይነቃነቅ ነበር። እንደዚያ ዓይነት እምነትን እንዲገነቡ ልጆቻችሁን ለማስተማር፣ አካሎቻችንን ለማጠንከር የምናደርገውን ነገሮች እነሱን መጠየቅ ትችላላችሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እምነት ለማጠናከር ምን ማድረግ እንችላለን? ያዕቆብ እና ህዝቦቹ እምነታቸውን “የማይነቃነቅ” ለማድረግ ምን እንዳደረጉ ልጆቻችሁ እንዲያውቁ ለመርዳት ያዕቆብ 4፥6ን በጋራ አንብቡ።
-
በእምነት “የማይነቃነቁ” መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ልጆች እንዲገነዘቡ ለመርዳት ሌላኛው መንገድ፣ ትልቅ ዛፍን በማግኘት እና ቅርንጫፎችን አንድ በአንድ እንዲያነቃንቁ እነሱን በመጠየቅ ነው። ግንዱን እንዲያነቃንቁ አድርጉ። ግንዱን ለማነቃነቅ ለምንድን ነው የሚከብደው? በያዕቆብ 4፥6፣ 10–11 ውስጥ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለን እምነት የማይነቃነቅ እንዲሆን ምን ማድረግ እንደምንችል የትኞቹ ሃረጎች ይጠቁማሉ?
-
ልጆቻችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ስላለ የማይናወጥ እምነት ለማስተማር ለሌሎች ንጽጽሮች፣ ኒል ኤል አንደርሰንን ፣ “መፈሳዊ አውሎ ነፋስ [Spiritual Whirlwinds]” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2014 (እ.አ.አ)፣ 18–21፤ እና “መፈሳዊ አውሎ ነፋስ [Spiritual Whirlwinds]“) ቪድዮ ወይም “ብልሁ ሰው እና ሞኙ ሰው [The Wise Man and the Foolish Man]” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 281)ይመልከቱ፤በተጨማሪም ማቴዎስ 7፥24–27ን ይመልከቱ።