ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
መጋቢት 25–31 (እ.አ.አ)፦ “ፈውስን በክንፎቹ ይዞ ከሙታን ይነሳል።” ትንሳኤ


መጋቢት 25–31 (እ.አ.አ)፦ ‘ፈውስን በክንፎቹ ይዞ ከሙታን ይነሳል።’ ትንሳኤ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2023 (እ.አ.አ)]

“መጋቢት 25–31 (እ.አ.አ)። ትንሳኤ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2023 (እ.አ.አ)]

ከሞት የተነሳው ክርስቶስ ከሐዋርያቶቹ ጋር

ክርስቶስ እና ሐዋርያት፣ በዴል ፓርሰን

መጋቢት 25–31 (እ.አ.አ)፦ “ፈውስን በክንፎቹ ይዞ ከሙታን ይነሳል”

ትንሳኤ

የጥንት ሐዋርያት በኢየሱስ ክርስቶስ እና በትንሳኤው ላይ ባላቸው ምስክርነት ደፋሮች ነበሩ (የሐዋርያት ስራ 4፥33ን ይመልከቱ)። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ ያምናሉ እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተመዘገቡት በእነሱ ቃላት ምክንያት ሊከተሉት ይሞክራሉ። ነገር ግን የተወሰኑ ሰዎች፦ ኢየሱስ ክርስቶስ የአለም ሁሉ አዳኝ ከሆነ፣ የዓይን እማኞቹ በትንሽ ክልል ያሉ በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች የሆኑት ለምንድን ነው? በማለት ሊገረሙ ይችላሉ።

መፅሐፈ ሞርሞን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም አዳኝ እንደሆነ፣ “እራሱንም ለሁሉም ሀገሮች [እንደሚገልጽ]” (የመፅሐፈ ሞርሞን የርዕስ ገፅ) እና ወደ እርሱ ለሚመጡት ሁሉ ድህነት እንደሚሰጥ እንደ አሳማኝ ተጨማሪ ምስክር ሆኖ ቆሟል። በተጨማሪም፣ ይህ ሁለተኛ ምስክርነት ድህነት ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ ያደርጋል። ለዚህ ነው ኔፊ፣ ያዕቆብ፣ ሞርሞን እና ሁሉም ነቢያት “እነዚህን ቃላት በሰሌዳዎቹ ላይ ለመቅረፅ” —“ስለክርስቶስ [ስለማወቃቸው] … እናም የክብሩን ተስፋ” ለመጪ ትውልድ ለማወጅም ጭምር የተጉት (ያዕቆብ 4፥3–4)። በዚህ የፋሲካ ወቅት፣ መላ ዓለምን እና እናንተን ለማዳን፣ የአዳኙ ኃይል ለሁሉም ሲሆን እንዲሁም ግላዊ እንደሆነ፣ በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ ያሉ ምስክርነቶችን አሰላስሉ።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

የሴሚናሪ ምልክት
በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በትንሳኤ እነሳለሁ።

በትንሳኤ ወቅት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳት ማሰላሰል የተለመደ ነው። ነገር ግን ትንሳኤ ማድረግ ምን ማለት ነው? ስለ ትንሳኤ መፅሐፈ ሞርሞን ምን ዓይነት ሃሳቦችን ያስቀምጣል? ምን አልባትም በዚህ ወቅት ስለ ትንሳኤ በ2 ኔፊ 9፥6–15፣ 22አልማ 11፥42–4540፥21–253 ኔፊ 26፥4–5 ውስጥ የምታገኙትን እውነቶች መዘርዘር ትችላላችሁ።

እነዚህ የትንሳኤ እውነቶች በእናንተ ተግባር እና በምትኖሩበት መንገድ ላይ እንዴት ተፅዕኖ እንደሚያሳድሩ መመዝገብ ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ እነዚህን ዓረፍተ ነገሮች እንዴት እንደምትጨርሱ አስቡ፦ እነዚህን ነገሮች ባላውቅ ኖሮ … እና እነዚህን ነገሮች ስለማውቅ …

እንደ “አዳኜ እንደሚኖር አውቃለው [I Know That My Redeemer Lives]” (መዝሙር፣ ቁጥር 136) ያለ መዝሙር የአዳኙ ትንሳኤ ለእናንተ ለምን ጠቃሚ እንደሆነ እንድታስቡ ይረዳችኋል። ስትዘምሩ፣ ስታዳምጡ ወይም ስታነቡ፣ እናንተ ይህንን ጥያቄ ልትጠይቁ ትችላላችሁ፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በማድረጉ ምክንያት ህይወቴ እንዴት ነው የተለወጠው?”

Easter videos የጥናታችሁ ትርጉም ያለው አካል መሆን የሚችሉ የፋሲካ ቪድዮዎች ስብስብ አለው። ምናልባት ከእነዚህ አንድ ወይም ሁለት ቪድዮዎችን ማየት እና በአዳኙ ትንሳኤ ላይ ባላችሁ መረዳት ወይም አድናቆት ላይ ምን እንደሚጨምሩ ማሰላሰል ትችላላችሁ።

በተጨማሪም ሉቃስ 24፥36–43የሐዋርያት ስራ 24፥151 ቆሮንቶስ 15፥12–23፤ ሬይናኤል. አቡርቶ፣ “The Grave Has No Victory፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ) 85–86፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “ትንሳኤ፣” የወንጌል ቤተ መጽሐፍ፤ “ሞት፣ ሀዘን እና ማጣት” በ“የህይወት እርዳታ [Life Help]” ስብስብ በወንጌል ቤተ መጽሐፍ ውስጥ ይመልከቱ።

ኢየሱስ ክርስቶስ የእኔን ሃጢያቶች፣ ህመሞች እና ድክመቶች በራሱ ላይ ወስዷል።

መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሃጢያቶቻችን መስዋዕትን እንደከፈለ በግልፅ ያስተምራል። መፅሐፈ ሞርሞን የክርስቶስን መስዋዕትነት እና ስቃይ ጠቃሚ በሆኑ መንገዶች መረዳታችንን ያሰፋል። እነዚህን ትምህርቶች በሞዛያ 3፥715፥5–9አልማ 7፥11–13 ውስጥ ማግኘት ይቻላል። እነዚህን ምንባቦች ካነበባችሁ በኋላ፣ የምታገኙትን ነገር በእንደዚህ ዓይነት ሰንጠረዥ ላይ መመዝገብን አስቡ።

አዳኙ ምን ነበር ተሰቃየው?

ለምንስ ተሰቃየ?

ይህ ለእኔ ምን ትርጉም አለው?

እነዚህን ምንባቦች ለማጥናት ሌላኛው መንገድ ይኸውና፦ እነሱ ከሚያስተምሩት መልዕክቶች ጋር ይዛመዳሉ ብላችሁ የምታስቡትን መዝሙሮች ፈልጉ። ከመዝሙር መጽሐፉ ጀርባ ላይ ያለው “ቅዱሳት መጽሐፍት” መረጃ ጠቋሚ ሊረዳ ይችላሉ። ከእነዚህ መዝሙሮች እና ከቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ የአዳኙን መስዋዕትነት በጥልቀት እንድታደንቁ የትኞቹ ሃረጎች ይረዷችኋል?

በተጨማሪም ኢሳይያስ 53እብራውያን 4፥14–16፤ ጀራልድ ኮሴ፣ “የሕያው ክርስቶስ ህያው ምስክር [A Living Witness of the Living Christ]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ) 38–40 ይመልከቱ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያነፃኝ እና ፍፁም ሊያደርገኝ ይችላል።

መፅሐፈ ሞርሞን በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ስለተቀየሩ ሰዎች መዝገብ ነው ሊባል ይችላል። እነዚህን የተወሰኑ ልምዶች በሞዛያ 5፥1–227፥8–28አልማ 15፥3–1224፥7–19 ውስጥ ማንበብ ትችላላችሁ። ለማጥናት ሌሎች ምሳሌዎችን ማሰብ ትችላላችሁ። እነዚህን ልምዶች የሚያመሳስላቸውን ነገር ምን ታስተውላላችሁ? ምን ልዩነቶች ታስተውላላችሁ? አዳኙ እንዴት እንደሚለውጣችሁ እንደሚችል እነዚህ ልምዶች ምንን ያስተምሯችኋል?

በተጨማሪም አልማ 5፥6–1413፥11–1219፥1–1622፥1–2636፥16–21ኢተር 12፥27ሞሮኒ 10፥32–33 ይመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔት እትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ይህ እሁድ የወሩ አምስተኛ ሰንበት ስለሆነ የልጆች ክፍል አስተማሪዎች የመማሪያ አክቲቪቲዎችን በ“Appendix B: Preparing Children for a Lifetime on God’s Covenant Path” እንዲጠቀሙ ይበረታታሉ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት በመነሳቱ ምክንያት እኔም ከሞት እነሳለሁ።

  • ለልጆቻችሁ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ለመንገር “ምዕራፍ 53፦ ኢየሱስ ተሰቀለ” እና “ምዕራፍ 54፦ ኢየሱስ ተነሳ” (በአዲስ ኪዳን ታሪኮች፣ 136–38፣ 139–44) መጠቀም ትችላላችሁ። ወይም በነዚያ ምዕራፎች ውስጥ ያሉትን ምስሎች በመጠቀም ልጆቻችሁ ታሪኩን እንዲነግሯችሁ ፍቀዱ።

  • የተነሳው አዳኝ የአሜሪካ ጉብኝት የትንሳኤው ኃይለኛ ምስክር ነው። 3 ኔፊ 11፤ 17፤ መዝሙር “Easter Hosanna”፣ ወይም “የመጽሐፈ ሞርሞን ታሪኮች” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 68–69፣ 118–19) የመጨረሻ ጥቅስን በመጠቀም ለልጆቻችሁ ስለእርሱ መናገርን አስቡ። የኢየሱስን ቁስል መዳሰስ ምን ሊመስል እንደሚችል (3 ኔፊ 11፥14–15 ይመልከቱ) ወይም እርሱ ከባረካቸው ልጆች መካከል እንደ አንዱ እንደሆኑ ልጆቻችሁ እንዲያስቡ አበረታቱ (3 ኔፊ17፥21 ይመልከቱ)። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ትንሳኤው ያላችሁን ስሜት አንዳችሁ ለሌላው አካፍሉ።

  • መፅሐፈ ሞርሞን ስለ ትንሳኤ የሚያስተምረውን ልጆቻችሁ እንዲያውቁ ለመርዳት፣ እናንተ ስለ መፅሐፉ ምንም እንደማታውቁ አስመስሉ ከዚያም ስለ መፅሐፉ እንዲገልጹላችሁ መጋበዝ ትችላላችሁ። ለእንደነዚህ ዓይነት ጥያቄዎች መልሶች በ2 ኒፊ 9፥10–15አልማ 11፥41–45፤ እና አልማ 40፥21–23 ውስጥ እንዲመለከቱ እርዷቸው፦ ከሞት መነሳት ማለት ምን ማለት ነው? ከሞት ማን ይነሳል? እንዲሁም እንደ መልሳቸው አካል የአዳኙን ትንሳኤ ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ጋብዟቸው።

ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንደሚያፅናናኝ ያውቃል።

  • እንደ የሃጢያት ክፍያው አካል አዳኙ ያሳለፋቸውን የተወሰኑ ነገሮች ሞዛያ 3፥7 እና አልማ 7፥11 ይገልፃሉ። ከእነዚህ ጥቅሶች አንዱን ለልጆቻችሁ ማንበብ እና ኢየሱስ ምን እንደተሰቃየ የሚነግሯቸውን ቃላት እንዲያዳምጡ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ከዚያም ለምን እንደተሰቃየ ለማወቅ አልማ 7፥12ን ማንበብ ትችላላችሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያፅናናን ይችል ዘንድ ህመማችን እና በሽታዎቻችን ሁሉ እንደተሰማው መስክሩ።

  • ልጆቻችሁ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና የሃጢያት ክፍያው የሚወዱት መዝሙር አሏቸው? በጋራ መዘመር ወይም አዲስ መዝሙርን መማር ትችላላችሁ። በግጥሞቹ ውስጥ አዳኙ የሚሰጠንን መፅናናት እና ሰላም ስለሚያስተምሩት ቃላት ወይም ሃረጎች ተነጋገሩ።

ክርስቶስ በጌተሰማኔ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ

ጌተሰማኒ፣ በማይክልቲ. ማልም

ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያነፃኝ ይችላል እንዲሁም እንድቀየር ይረዳልኛል።

  • መፅሐፈ ሞርሞን በአዳኙ የሃጢያት ክፍያ አማካኝነት ስለተቀየሩ ብዙ ሰዎች ምሳሌዎችን ይሰጣል። ምናልባት ልጆቻችሁ ለመማር አንዱን መምረጥ ይችላሉ። ለምሳሌ ኢኖስ (ኢኖስ 1፥2–8 ይመልከቱ)፣ ወጣቱ አልማ (ሞዛያ 27፥8–24 ይመልከቱ)፣ ወይም በአንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች (አልማ 24፥7–19 ይመልከቱ)። ይሄ ግለሰብ ወይም ቡድን በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት እንዴት ነው የተቀየረው? የእነርሱን ምሳሌዎች እንዴት መከተል እንችላለን?

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ ንፁህ የሆነን ነገር እና ቆሻሻ የሆነ ነገርን በማነፃፀር ቆሻሻ ነገሮች እንዴት ንፁህ እንደሚሆኑ መነጋገር ትችላላችሁ። አልማ 13፥11–13ን በጋራ አንብቡ። ከሃጢያቶቻችን እንድንነፃ ኢየሱስ ምን አደረገ? ይሄ ስለ ሃጢያት ምን እንዲሰማን ያደርጋል? ስለ አዳኙስ ምን እንዲሰማን ያደርጋል?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

ለመንፈስ ምሪት ብቁ የሆነ ህይወትን ኑሩ። መንፈስ ቅዱስ እውነተኛ አስተማሪ ነው። የእርሱን ምሪት ስትሹ እና በብቁነት ስትኖሩ፣ የምታስተምሩትን ሰዎች ፍላጎት እንዴት ማሟላት እንዳለባችሁ ሃሳቦችን እና ግንዛቤዎችን ይሰጣችኋል።

ክርስቶስ ለኔፋውያን ሰላምታ ሲሰጥ

ክርስቶስ ከኔፋውያን ጋር ሆኖ የሚያሳይ ስዕል፣ በቤን ሶዋርድስ