ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
መጋቢት 4–10 ፦ “በክርስቶስ እንደሰታለን።” 2 ኔፊ 20–25


መጋቢት 4–10 (እ.አ.አ)፦ ‘በክርስቶስ እንደሰታለን።’ 2 ኔፊ 20–25፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“መጋቢት 4–10 2 ኔፊ 20–25፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

ቤተሰብ እያጠና

መጋቢት 4–10 ፦ “በክርስቶስ እንደሰታለን”

2 ኔፊ 20–25

የኢሳይያስ ጽሁፎች ጠንካራ ማስጠንቀቂያዎችን የያዙ ቢሆኑም ተስፋ እና ደስታም ይሰጣሉ። ኔፊ በመዝገቡ ውስጥ ያካተተበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው፦ “ይህንን ቃል የሚያይ ልብን ከፍ እንዲያደርጉና ሰዎች ሁሉ ይደሰቱ ዘንድ ከኢሳይያስ ቃል በጥቂቱ እፅፋለሁ” (2 ኔፊ 11፥8)። በተወሰነ መልኩ፣ የኢሳያስን ጽሑፎች የማንበብ ግብዣ የደስታ ግብዣ ነው። ልክ እንደ ኔፊ፣ በኢሳይያስ ትንቢቶች ስለ እስራኤል መሰብሰብ፣ ስለ መሲሁ መምጣት እና ለጻድቅ ስለተገባው ቃል ኪዳን ልትደሰቱ ትችላላችሁ። ጌታ “ለሀገሮች ምልክትን [በሚያቆምበት]፣ ከእስራኤልም የተሰደዱትን [በሚሰበስብበት]” በተተነበየው ቀን ውስጥ በመኖራችሁ ልትደሰቱ ትችላላችሁ (2 ኔፊ 21፥12)። ስለ ጽድቅ ስትጠሙ “ውኃንም ከመዳን ጉድጓዶች በደስታ [መቅዳት]” ትችላላችሁ(2 ኔፊ 22፥3)። በሌላ አባባል፣ “በክርስቶስ መደሰት” ይቻላችኋል ማለት ነው (2 ኔፊ 25፥26)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

2 ኔፊ 21–22

በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን ማግኘት እችላለሁ።

የሌሂ ልጆች የጸብ ችግር ነበረባቸው። ወደ መከፋፈል፣ ምርኮ፣ ሀዘን እና ጥፋት በመምራት ችግሩ በመጪው ትውልድ ላይ ተባባሰ። ጸብ ዛሬም ችግር መሆኑን ቀጥሏል።

ይህን ሁሉ ግምት ውስጥ በማስገባት በ2 ኔፊ 21–22 ውስጥ ያሉትን ትንቢቶች አስቡ። አዳኙ እነዚህን ትንቢቶች እንዴት እየፈፀመ እንደሆነ ይመልከቱ። ተኩላው “ከበጉ ጋር ይኖራል” የሚለው ትንቢት ለእናንተ ምን ማለት ነው? (2 ኔፊ 21፥6)። ሰላም ፈጣሪ ለመሆን ምን ማድረግ እንደምትችሉ አሰላስሉ።

ዴል ጂ. ረንለንድ፣ “የክርስቶስ ሰላም ጠላትነትን ያስወግዳል [The Peace of Christ Abolishes Enmity]፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2021 (እ.አ.አ) 83–85 ይመልከቱ።

2 ኔፊ 21፥9–12

እግዚአብሔር ህዝቦቹን እየሰበሰበ ነው።

ኔፊ እና ቤተሰቡ ለእስራኤል መበተን ምስክሮች ነበሩ (2 ኔፊ 25፥10ይመልከቱ)። አሁን በእስራኤል መሰብሰብ ላይ መሳተፍ ትችላላችሁ (2 ኔፊ21፥12 ይመልከቱ)። 2 ኔፊ 21፥9–12ን ስታነቡ እነዚህ ጥቅሶች የሚገልፁትን ትንቢቶች ለመፈፀም እንዴት መርዳት እንደምትችሉ አስቡ።

ለምሳሌ፣ የእግዚአብሔርን ህዝብ ለመሰብሰብ ስለሚነሳው “ሰንደቅ አላማ” (መደበኛ ወይም ባነር) ስታነቡ እግዚአብሔር በአካል እና በመንፈሳዊ ሕዝቡን ሲሰበስብ እንዴት እንዳያችሁ አስቡ። ሰዎችን ወደ ጌታ እና ወደ ቤተክርስቲያኑ ምን ይስባቸዋል?

የእግዚአብሔርን ህዝብ ለመሰብሰብ ለመርዳት ምን ለማድረግ መነሳሳት ይሰማችኋል?

2 ኔፊ 23–24

የባቢሎን ዓለማዊነት ይወድቃል።

የባቢሎን መንግስት ለጥንት እስራኤል ኃይለኛ የፖለቲካ እና የጦር ስጋት ነበር። ነገር ግን ለኔፊ ህዝብ እንዲሁም ለኛ ዛሬ ላይ ታላቁ ስጋት ባቢሎን የሚወክለው ነገር ነው፦ ዓለማዊነት እና ሃጢያት። በ2 ኔፊ 23–24 ውስጥ ያሉ ማስጥንቀቂያዎች የባቢሎንን ሀብትና ኃይል የፈሩ ወይም ያደነቁ ወይም ያመኑ ሰዎች ላይ እንዴት ተፅዕኖ እንደፈጠሩ አስቡ (ለምሳሌ 23፥6–9፣ 11፣ 19–2224፥10–19 ይመልከቱ)። ዛሬ ልንፈራቸው ወይም ልናደንቃችው የምንችላቸው ወይም የምናምነው አንዳንድ ተመሳሳይ ነገሮች ምንድን ናቸው? በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ለእናንተ የአዳኙ መልእክት ምን ሊሆን እንደሚችል ይሰማችኋል? “[በጌታ] ታላቅነት [እንደምትደሰቱ]” እንዴት እንደምታሳዩ አስቡ (2 ኔፊ 23፥3)።

የሴሚነሪ መለያ

2 ኔፊ 25፥19–29

“ስለ ክርስቶስ እንናገራለን … በክርስቶስ እንደሰታለን።”

ኔፊ እምነቱን —በተለይም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለውን ምስክርነት ሲያካፍል በግልጽ ነበር። 2 ኔፊ 25ን በምታጠኑበት ጊዜ ሁሉ፣ ኔፊ “[የእርሱ] ልጆች በክርስቶስ እንዲያምኑና ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁ ለማሳመን” ስለነበረው ምኞት አስቡ (ቁጥር 23)። ኔፊ ሰዎች ስለ አዳኙ ምን እንዲያውቁ ፈለገ? (ቁጥር 12–13፣ 16 ይመልከቱ)። ኔፊ ሰዎች በእርሱ እንዲያምኑ ለማሳመን እንዴት ሞከረ? (ቁጥር 19–29 ይመልከቱ)። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ በኢየሱስ ክርስቶስ እንድታምኑ እና እንድትከተሉ ያሳመኗችሁን ምንባቦች አስተውሉ።

ስለ ክርስቶስ ለማውራት አንዳንዶቻችን እንደ ኔፊ ድፍረት ላይሰማን ይችላል። ነገር ግን ስለ እርሱ ከሌሎች ጋር በግልጽ እንድትነጋገሩ የሚያነሳሳችሁን ምናልባት በ2 ኔፊ 25፥23–26 ውስጥ ካሉት የኔፊ ትምህርቶች የሆነ ነገር ልታገኙ ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ “በክርስቶስ እንደሰታለን” የሚለው የኔፊ መግለጫ አዳኙ እንዴት ደስታን እንደሚያመጣላችሁ—እናም ያንን ደስታ ለሌሎች እንዴት ማካፈል እንደምትችሉ ሊያነሳሳችሁ ይችላል።

ስለ ክርስቶስ እንናገራለን [We Talk of Christ]” (ሊያሆና፣ ህዳር 2020 እ.አ.አ 88–91) በተሰኘው መልዕክታቸው ውስጥ ሽማግሌ ኒል ኤል. አንደርሰን በተለያዩ ሁኔታዎች ስለ ክርስቶስ እንዴት በግልፅ መናገር እንደምንችል ጠቁመዋል። የትኞቹ ሃሳቦች ለእናንተ ጎልተው ይታያሉ? ስለ ክርስቶስ ከሌሎች ጋር ለመነጋገር ምን ዓይነት እድሎች አሏችሁ?

ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሌሎች ለመንገር ምን መነሳሳት ይሰማችኋል? የተወሰኑ ሃሳቦችን ከፈለጋችሁ “ህያው ክርስቶስ፦ የሐዋሪያት ምስክርነት” (የወንጌል ቤተ መጽሐፍት) ልታስሱ ትችላላችሁ። እንደ “I Believe in Christ[በክርስቶስ አምናለሁ]” (መዝሙር, no. 134) ተጨማሪ ሃሳቦችን ሊሰጣችሁ ይችላል።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች እትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

2 ኔፊ 21፥1–5

ኢየሱስ ክርስቶስ በጽድቅ ይፈርዳል።

  • ልጆቻችሁ እነዚህን ጥቅሶች በምናባቸው እንዲመለከቱ ለመርዳት፣ የተቆረጠ ዛፍን ወይም ከዛፍ የሚያድግን ቅርንጫፍ ለማግኘት ሞክሩ (ወይም ከታች ያለውን ምስል ይጠቀሙ)። በ2 ኔፊ 21፥1 ውስጥ “ቅርንጫፉ” ኢየሱስ ክርስቶስን ከወከለ፣ ቁጥር 2–5 ስለ እርሱ ምን የሚያስተምር ይመስላችኋል?

ከዛፍ ግንድ የሚበቅል ትንሽ ተክል

2 ኔፊ 21፥6–9

ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እና ደስታን ያመጣል።

  • 2 ኔፊ 21፥6–9 ሁሉም ሰዎች አዳኙን ቢከተሉ ምን ሊከሰት እንደሚችል ያስተምራል? (በተጨማሪም 4 ኔፊ 1፥15–18 ይመልከቱ)። ቤታችንን የበለጠ እንደዚህ ማድረግ እንዴት እንችላለን? ልጆቻችሁ በቁጥር 6–7 ውስጥ የተጠቀሱትን እንስሳት ስዕሎች —ብዙ ጊዜ ጠላት የሆኑ ኢየሱስ ዳግም ሲመጣ ግን እርስ በእርስ የማይጎዳዱ እንስሳትን በመመልከት ሊደሰቱ ይችላሉ (የዚህን ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ ይመልከቱ)። ልጆቻችሁ ራሳቸው እና እነዚህ እንስሳት ከኢየሱስ ጋር በሰላም ሲኖሩ የሚያሳይ ስዕልን መሳል ይችላሉ።

2 ኔፊ 21፥11–12፤ 22

እግዚአብሔር ህዝቦቹን እየሰበሰበ ነው።

  • ሰዎች ወደ እርሱ እንዲሰበሰቡ ለመርዳት ጌታ “ለሀገሮች ምልክትን” እንደሚያዘጋጅ ኢሳያስ ተናሯል (2 ኔፊ 21፥11–12 ይመልከቱ)። ልጆቻችሁ ምልክት እንደ ባንዲራ እንደሆነ እንዲገነዘቡ እርዷቸው። ምናልባት የራሳቸውን ባንዲራ በመሳል ሊደሰቱ ይችላሉ። ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ወደ ቤተክርስቲያኑ የሚመጡበትን ምክንያት የሚወክሉ ምስሎችን ወይም ቃላትን ሊያካትቱ ይችላሉ። ስለ ባንዲራቸው እንዲያወሩ ፍቀዱላቸው እንዲሁም ሌሎችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ “እንዲሰበሰቡ” እንዴት እንደሚያግዙ እንዲያስቡ እርዷቸው።

  • 2 ኔፊ 22፥4–5ን በጋራ ካነበባችሁ በኋል፣ ጌታ ስላደረገው “ታላቅ ስራ” ከልጆቻችሁ ጋር መነጋገር ትችላላችሁ። መናገር የምንችላቸው ጌታ “በመካከላችን የሚያደርጋቸው” የተወሰኑ ነገሮች ምንድን ናቸው? ልጆቻችሁ ስለዚህ ጥያቄ እንዲያስቡ ለመርዳት፣ ስለ አዳኙ በጋራ እንደዚህ ዓይነት መዝሙርን መዘመር ትችላላችሁ፣ “በክርስቶስ አምናለሁ [I Believe in Christ]” (መዝሙር፣ ቁጥር 134)። ተራ በተራ እንደሚከተልው ዓይነት አረፍተ ነገርን ለመጨረስ ሞክሩ፦ “በክርስቶስ አምናለሁ፣ እርሱ ።” አዳኙ ምን እንዳደረገልን ሌሎች ሰዎች እንዲያውቁ እንዴት መርዳት እንችላለን?

2 ኔፊ 25፥26

“በክርስቶስ እንደሰታለን።”

ስለ ክርስቶስ መስክሩ። ቤተሰባችሁ ስለ አዳኙ ያላችሁን ስሜት ያውቃሉ ብላችሁ አትገምቱ። ንገሯቸው እንዲሁም ስለ አዳኙ ያላችሁ ስሜት ከእነሱ ጋር ባላችሁ ግንኙነት ላይ ተፅዕሮ እንዲያደርግ ፍቀዱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

ሚስዮናውያን ቤተሰብን ሲያስተምሩ

እንድሄድ የምትፈልግበት ቦታ እሄዳለሁ [I’ll Go Where You Want Me to Go]፣ በራሞን ኤሊ ጋርሲያ ሪቫስ