“የካቲት 26–መጋቢት 3 (እ.አ.አ)፦ ‘ስሙም … የሠላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።’ 2 ኔፊ 11–19፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]
“የካቲት 26–መጋቢት 3 (እ.አ.አ)። 2 ኔፊ 11–19፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]
የካቲት 26–መጋቢት 3 ፦ “ስሙም … የሠላም አለቃ ተብሎ ይጠራል”
2 ኔፊ 11–19
በብረት ሰሌዳዎች ላይ መቅረጽ ቀላል አይደለም፤ በኔፊም ትንሽ ሰሌዳዎች ላይ ቦታ በጣም የተወሰነ ነበር። ስለዚህ ኔፊ የነቢዩ ኢሳይያስን ብዙ ጽሁፎች ወደ እሱ መዝገብ ለመቅዳት ለምን ጣረ? በኢየሱስ ክርስቶስ እንድናምን ፈልጎ ስለነበረ ነው። “የሚመጣውን ክርስቶስ እውነት ለህዝቦቼ በማረጋገጥ ነፍሴ ትደሰታለች” (2 ኔፊ 11፥4) ብሎ ፃፈ። በመጪው ትውልዶች ውስጥ በሕዝቦቹ ላይ ምን እንደሚሆን ኔፊ አይቶ ነበር። ብዙ በረከቶች ቢኖራቸውም ኩሩዎች፣ ጸበኞች እና ዓለማዊ እንደሚሆኑ ተመለከተ (1 ኔፊ 12፤ 15፥4–6 ይመልከቱ)። በዘመናችንም ተመሳሳይ ችግሮችን አይቷል (1 ኔፊ 14 ይመልከቱ)። የኢሳይያስ ፅሁፎች እንደዚህ ዓይነት ክፋትን አስጠንቅቀዋል። ነገር ግን ለኔፊ የወደፊት የክብር ተስፋም ሰጡት—የክፋት ፍጻሜ፣ የአማኞች መሰባሰብ እና “በጨለማ [ለተጓዙ]” ሰዎች “ታላቅ ብርሃን” መሆን (2 ኔፊ 19፥2)። ይሄ ሁሉ የሚከሰተው ጠብን ሁሉ ማቆም የሚችል “ህፃን [ስለተወለደ]፣” እርሱም “የሰላም አለቃ” ስለሆነ ነው (2 ኔፊ 19፥6)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
የኢሳይያስን ትምህርቶች በጥሩ ሁኔታ እንዴት መረዳት እችላለሁ?
“የኢሳይያስ ቃላት ለእናንተ ግልፅ አይደሉም” በማለት ኔፊ እውቅና ሰጥቷል (2 ኔፊ 25፥4)። ነገር ግን በኢሳይያስ ፅሁፎች ውስጥ ትርጉም እንድናገኝ እንዲረዳን ሃሳቡንም አካፍሏል፦
-
“የእሱን ቃላት [ከራሳችሁ ጋር] አመሳስሉ” (2 ኔፊ 11፥2)። ብዙዎቹ የኢሳይያስ ትምህርቶች ብዙ ትርጉሞች እና ትግበራዎች አሏቸው። ለምሳሌ በ2 ኔፊ 14:5–6 ውስጥ ስለ መኖሪያ ቦታዎች ስታነቡ፣ እነዚህ ጥቅሶች ለቤታችሁ እንዴት እንደሚተገበሩ አስቡ። ራሳችሁን ፣ “እግዚአብሔር ምን እንድማር ይፈልጋል?” በማለት ጠይቁ።
-
የኢየሱስ ክርስቶስን ምልክቶች ፈልጉ (2 ኔፊ 11፥4 ይመልከቱ)። ኢሳይያስ ስለ አዳኙ ያስተማራቸው ብዙዎቹ ትምህርቶች በምልክቶች የተገለፁ ናቸው። ለምሳሌ በ2 ኔፊ19፥2 ውስጥ አዳኙ የተወከለው እንዴት ነው ? ይህ ምልክት ስለ እርሱ ምን ያስተምራችኋል?
-
“በትንቢት መንፈስ ለመሞላት ፈልጉ” (2 ኔፊ 25፥4)። ስታጠኑ መንፈሳዊ ምሪት ለማግኘት ጸልዩ። መጀመሪያ ላይ ሁሉንም ነገር ላትረዱ ትችላላችሁ፣ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ማወቅ ያለባችሁን ነገር እንድታውቁ ሊረዳችሁ ይችላል።
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ጥናት ይረዳል [study helps]ን የግርጌ ማስታወሻዎችን፣ የምዕራፍ ርዕሶችን ጨምሮ የቅዱሳት መጻሕፍት መመሪያ [Guide to the Scriptures]ን መመልከት ጠቃሚ ሆኖ ልታገኙ ትችላላችሁ። መፅሐፈ ሞርሞን እና የብሉይ ኪዳን ኢኒስቲቲዩት መመርያ ስለ ኢሳይያስ ትምህርቶች ታሪካዊ አውድ እንድትማሩ የሚረዳችሁ ተጨማሪ መረጃዎች አሏቸው።
አሳይያስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መሰከረ።
ኢሳይያስ ምሳሌያዊ ቋንቋን በመጠቀሙ ምክንያት፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይለኛ ምስክርነቱን ችላ ማለት ቀላል ሊሆን ይችላል። በ2 ኔፊ 13፥13፤ 14፥4–6፤ 15፥1–7፤ 16፥1–7፤ 17፥14፤ 18፥14–15፤ 22፥2 ውስጥ አዳኙን ፈልጉ። እነዚህ ጥቅሶች ስለእርሱ ምን ያስተምሯችኋል?
በ2 ኔፊ 19፥6 ውስጥ ያለው ትንቢት በርካታ የኢየሱስ ክርስቶስን ስሞች ይገልፃል። እነዚህን ሚናዎች በህይወታችሁ ያሟላው እንዴት ነው?
በተጨማሪም ኡሊሴስ ስዋሬስ፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ፦ የነፍሳችን ተንከባካቢ [Jesus Christ: The Caregiver of Our Soul]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ) 82–84 ተመልከቱ።
ኩሩዎች እና ዓለማዊዎች ትሁት ይሆናሉ።
ኔፊ ኩራት የህዝቡን ውድቀት እንደሚያመጣ አስቀድሞ አይቶ ነበር (1 ኔፊ 12፥19ይመልከቱ)። ስለሆነም ኔፊ ለህዝቡ ኢሳይያስ ስለ ኩራት በተደጋጋሚ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ቢያካፍል አያሰደንቅም። በምዕራፍ 12 እና 13 ውስጥ፣ ኩራትን ለመግለፅ ኢሳይያስ የተጠቀመውን ቃላት ይመልከቱ፣ ለምሳሌ ከፍ ማድረግ እና ትዕቢተኛ። በ2 ኔፊ 15:1–24 ውስጥ፣ የኩራትን ውጤት የሚገልጽ ምሳሌያዊ ቋንቋን ፈልጉ። ከዚያም ያነበባችሁትን ነገር በራሳችሁ ቃላት ለማጠቃለል ሞክሩ። ትሁት ለመሆን እንዴት እንደምትመርጡም አስቡ።
በተጨማሪም “ምዕራፍ18፦ ከኩራት ተጠንቀቁ [Chapter 18: Beware of Pride]፣” የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፦ እዝራ ታፍት ቤንሰን (2014 እ.አ.አ)፣ 229–40 ይመልከቱ።
ቤተመቅደስ የጌታ ቤት ነው።
ኢሳይያስ ቤተ መቅደስን “የጌታ ቤት ተራራ” ብሎ ጠርቷል (2 ኔፊ 12፥2)። ተራራ ለቤተ መቅደስ ጥሩ ምልክት የሆነው ለምንድን ነው?
ቤተመቅደስ ለምን እንደሚያስፈልገን ለአንድ ሰው እንዴት ማስረዳት ትችላላችሁ? በ2 ኔፊ 12፥2–3 እና የፕሬዝዳንት ረስል ኤም. ኔልሰን “ቤተ መቅደስ እና የእናንተ መንፈሳዊ መሠረት [The Temple and Your Spiritual Foundation]” [ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 93–96] መልዕክት ውስጥ መልስ የሚሆኑ የተወሰኑትን ማግኘት ትችላላችሁ። ባነበባችሁት መሰረት፣ ጌታ በቅዱስ ቤቱ ውስጥ ምን እንድትማሩ እና እንድትለማመዱ ይፈልጋል? እዚያስ ምን ተሞክሮዎችን አግኝታችኋል?
የቤተ መቅደስ መግቢያ የመታወቂያ ቃለ መጠይቅ ጥያቄዎችን በለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ ገጽ 36–37 ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ። እያንዳንዱን ለማንበብ እና ራሳችሁን ስለ ጌታ ምን ያስተምረኛል በማለት ለመጠየቅ አስቡ። “በእርሱ መንገዶች [እንድጓዝ]” እንዴት ይረዳኛል?
በተጨማሪም የወንጌል ርዕሶች፣ “ቤተ መቅደሶች፣” የወንጌል ቤተ መጻሕፍት፤ “በተራራው ከፍታ ላይ [High on the Mountain Top፣” መዝሙር፣ ቁጥር 5 ይመልከቱ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቦቹን ያድናል።
የተመለከተው እየተመለከተ የነበረው ክፋት ቢሆንም፣ ኢሳይያስ ለወደፊት ተስፋን አየ። የሚከተሉትን እያንዳንዳቸውን ምንባቦች ማጥናትን አስቡ። እያንዳንዱ ምንባቦች ስለ ቀናችን የሚያስተምሩትን አንድ ወይም ብዙ እውነቶችን ጻፉ፦ 2 ኔፊ 12፥1–5፤ 14፥2–6፤ 15፥20–26፤ 19፥2–8። እነዚህ ምንባቦች እንድንገነዘባቸው አስፈላጊ የሆኑት ለምን ይመስላችኋል?
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ቤተመቅደስ የጌታ ቤት ነው።
-
ኢሳይያስ ቤተ መቅደስን “የጌታ ቤት ተራራ” በማለት ገልጿል። 2 ኔፊ 12፥2–3ን ስታነቡ ልጆቻችሁ ተራራ መውጣትን በማስመሰል ሊደሰቱ ይችላሉ። ለምን ቤተ መቅደሶች እንዳሉን የሚገልጹ ሃረጎችን በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንዲያገኙ እርዷቸው።
-
በ2 ኔፊ 12፥3 ውስጥ፣ “በጎዳናው እንራመዳለን” የሚለውን ለማስረዳት በወለል ላይ ወደ ቤተ መቅደስ ምስል የሚያመራ መንገድን መስራት ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ በመንገዱ ላይ ሲራመዱ በጌታ መንገዶች ላይ ለመራመድ ማድረግ የሚችሉትን ነገሮች መጥቀስ ይችላሉ።
-
ምናልባት ልጆቻችሁ እነሱ ወደ ቤተ መቅደስ ሲሄዱ የሚያሳይ ምስልን ሊስሉ ይችላሉ። ስለ ቤተመቅደስ መዝሙር ለመዘመር ወይም ማዳመጥም ይችላሉ፣ ለምሳሌ “ቤተመቅደስን ማየት እወዳለሁ” (የልጆች መዝሙር፣ 95)። በመዝሙሩ ውስጥ ቤተመቅደስ ምን እንደሆነ እና እዚያ ምን እንደምናደርግ የሚያስተምሩ ሃረጎችን እንዲያገኙ እርዷቸው።
ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኜ ነው።
-
በ2 ኔፊ 11፥4–7፤ 17፥14፤ 19፥6 ውስጥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ስሞች አሉ። ልጆቻችሁ እንዲያገኟቸው እና ምን ማለት እንደሆኑ እንዲናገሩ እርዷቸው። ለምሳሌ፣ “ክርስቶስ” ማለት “የተቀባው” ማለት ሲሆን “አማኑኤል” ማለት ደግሞ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ማለት ነው። እነዚህ ስሞች ስለ ኢየሱስ ምን ያስተምሩናል?
-
የተለያዩ ሰዎች ኢየሱስን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳዩት የሚያሳየውን “ልጁ ክርስቶስ [The Christ Child]” (የወንጌል ቤተ መጻሕፍት) የሚለውን ቪድዮ የተወሰኑ ክፍሎች አሳዩ። ቪድዮውን አቁሙና እነዚህ ሰዎች ስለተሰማቸው ስሜቶች ልጆቻችሁን ጠይቋቸው። እኛ እዚያ ብንሆን ምን ሊሰማን ይችል ነበር? እሱን እንደገና ስናየው እንዴት ሊሰማን ይችላል?
ሰይጣን ስለ መልካም እና መጥፎ ነገር ግራ ሊያጋባኝ ይሞክራል።
-
ለልጆቻችሁ መራራ ወይም ጎምዛዛ ነገርን ለምሳሌ የሎሚ ቁራጭን በከረሜላ መጠቅለያ ውስጥ አሳዩ። 2 ኔፊ 15፥20ን በጋራ አንብቡ። ሰይጣን መጥፎ ነገር ጥሩ እንደሆነ ለማስመሰል የሚሞክረው እንዴት ነው? እንዲሁም የመጀመሪያዎቹን 90 ሰከንዶች “የነፃ ይወጣሉ [You Will Be Freed]” (የወንጌል ቤተ መጻሕፍት) ቪዲዮን ማሳየት ትችላላችሁ። ዓሳ አጥማጁ ማጥመጃውን ለምን ይደብቃል? ሰይጣን ሃጢአትን ለምን ይደብቃል? ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ነው በሰይጣን እንዳንታለል የሚረዳን?