ቤተመቅደስ እና መንፈሳዊ መሰረታችሁ
በሕይወታችሁ ውስጥ ሁከት ሲከሰት፣ በመንፈስ በደህንነት ቦታ ለመሆን የምትችሉበት ቢኖር በቤተመቅደስ ቃል ኪዳናችሁ ውስጥ መኖር ነው።
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በዚህ ጠዋት የልቤን ስሜቶች ለማካፈል ከእናንተ ጋር በመሆኔ አመስጋኝ ነኝ።
እንደምታውቁት፣ በታሪካዊው የሶልት ሌክ ቤተመቅደስ ላይ ታላቅ እድሳትን እያደረግን ነን። ይህ ውስብስብ ፕሮጀክት ከክፍለ ዘመን በላይ ባገለገለው የቀድሞ መሰረቱ ላይ ታላቅ ማጠናከር ማድረግን ያካትታል። ነገር ግን ይህ ቤተመቅደስ ረዘም ላለ ጊኤ መቆም አለበት። ባለፈው ግንቦት መጨረሻ ላይ የዚህን ግዙፍ ፕሮጀክት ሂደት ፈተሸኩኝ። ባለቤቴ ዌንዲ እና እኔ ያየነውን ለማየት ትፈልጋላችሁ ብዬ አሰብኩኝ። “መሰረቱ እንዴት ጥብቅ ነው” 1 የሚለው መዝሙር ለእኛ እንዴት አዲስ ትርጉም እንዳለው ታያላችሁ ብዬ እገምታለሁ።
የሶልት ሌክ ቤተመቅደስ እድሳት ቪድዮ፦ “የሶልት ሌክ ቤተመቅደስን የመጀመሪያ መሰረት እየተመለከትን ነን። የአትክልት ክፍል ከነበረው በታች ቆሚያለሁ። የዚህን መላ ህንፃ የእጅ ጥበብ ስመረምር፣ መስራቾች ባከናወኑት ነገር እደነቃለሁ። ይህን እፁብ ድንቅ ቤተመቅደስ የገነቡት ከክፍለ ዘመን በላይ በሆነ ጊዜ የነበራቸውን መሳሪያዎች እና ዘዴዎች ተጠቅመው መሆኑን ሳስብ ሙሉ በሙሉ እገረማለሁ።
“ይሁን እንጂ ይህ ከብዙ አስርተ ዓመታት በኋላ መሰረቱን ቀረብ ብለን ብንገመግም፣ የመሸርሸርን፣ በመጀመሪያው የድንጋይ ስራ ላይ የክፍተትን እና በስራው ላይ የተለያዩ የጥንካሬ ደራጃዎችን ውጤቶች ማየት እንችላለን።
“ያንን የመጀመሪያውን መሰረት ለማጠናከር አሁን ዘመናዊ ኢንጂነሮች፣ ቀያሾች እና የግንባታ ባለሞያዎች ምን መስራት እንደሚችሉ ስመለከት በጣም እደነቃለሁ። የእነሱ ስራ አስገራሚ ነው!
“የማንኛውም ህንፃ መሰረት፣ በተለይም እንደዚህ ግዙፍ የሆነ ህንፃ፣ የመሬት መንቀጥቀጥን፣ ዝገትን፣ ከፍተኛ ንፋስን እና ሁሉንም ህንፃችን የሚያጠቃውን መሰርጎድ ለመቋቋም ጠንካራ እና የሚቋቋም መሆን ይኖርበታል። አሁን በመካሄድ ላይ ያለው የማጠንከሩ የተወሳሰበ ስራ ይህን ቅዱስ ቤተመቅደስ የጊዜን ፈተና መቋቋም በሚችል መሰረት ያጠነክራል።”
ይህን ለተፈጥሮ ኃይል ተጋላጭ፣ እየሆነ የመጣውን የተከበረ ቤተመቅደስ እስከ መጪው ሺህ አመት ድረስ የሚቋቋም መሰረትን ለመስጠት ምንም ጥረት እየቀነስን አይደለም። ተመሳሳይ በሆነ መልኩ፣ እያንዳንዳችን አስደናቂ የሆኑ መስፈርቶችን—ምናልባት ግላዊ መንፈሳዊ መሰረታችንን ለማጠንከር—ከዚህ ቀደም ወስደናቸው የማናቃቸውን መስፈርቶች ለመውሰድ ሰዓቱ አሁን ነው። ታይተው የማይታወቁ ጊዜዎች ታይተው የማይታወቁ መስፈርቶችን ይጠይቃሉ።
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ እነዚህ የኋለኛው ቀናት ናቸው ። እናንተ እና እኔ የሚመጡ አደጋዎችን እና ኃይሎችን የምንቋቋም ከሆነ፣ እያንዳንዳችን በቤዛችን በኢየሱስ ክርስቶስ አለት ላይ ጥብቅ መንፈሳዊ መሰረት መገንባት እንደሚያስፈልገን ግልፅ ነው። 2
ስለሆነም እያንዳንዳችሁን እንዲህ እጠይቃለሁ፣ የእናንተ መሰረት ምን ያህል ጠንካራ ነው? እና ለእናንተ ወንጌል ምስክርነት እና መረዳት ምን ዓይነት ማጠናከሪያዎች ይስፈልጋሉ?”
ቤተመቅደስ እምነታችንን እና መንፈሳዊ ምሽጋችንን ለማጠንከር ማዕከላዊ ቦታ ላይ ይገኛል ምክንያቱም አዳኙ እና የእርሱ ትምህርት የቤተመቅደስ እምብርት ነውና። በመመሪያ እና በመንፈስ አማካኝነት፣ በቤተመቅደስ ውስጥ የሚስተላለፈው ሁሉም ትምህርት ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚኖረንን መረዳት ይጨምራል። በቅዱስ የክህነት ቃል ኪዳኖች አማካኝነት አስፈላጊዎቹ የእርሱ ስርዓቶች ከእርሱ ጋር ያጣምሩናል። ከዚያም በኋላ፣ ቃል ኪዳኖቻችንን ስንጠብቅ፣ በእርሱ ፈዋሽ፣ አጠንካሪ ኃይል ይባርከናል። 3 እና አቤቱ፣ የእርሱ ኃይል በወደፊት ቀናት እንዴት እንደሚያስፈልገን።
“ከተዘጋጀ[ን] [እኛ] እንደማንፈራ” ቃል ተገብቶልናል። 4 ይህ ማረጋገጫ ዛሬ ከፍተኛ ትርጉም አለው። ምንም እንኳን ዛሬ ታይተው የማይታወቁ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፣ መሰረታቸውን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ለሚገነቡ ሰዎች እና ኃይሉን መጠቀምን ለተማሩ ሰዎች፣ ለዚህ ዘመን የተለዩ ጭንቀቶች እጅ መስጠት እንደማይኖርባቸው ጌታ ተናግሯል።
የቤተመቅደስ ሥነ-ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች ጥንታዊ ናቸው። አዳምን እና ሔዋንን እንዲጸልዩ፣ ቃል ኪዳኖችን እንዲገቡ እና መስዋዕትን እንዲያቀርቡ ጌታ አዘዘ። 5 በእርግጥ፣ “ጌታ የእርሱን ቃል የሚታዘዙ ሰዎች በምድር ላይ ባሉ ጊዜ ቤተመቅደስን እንዲገነቡ ይታዘዛሉ።” 6 አራቱ ቅዱሳት መጻህፍት በቤተመቅደስ ትምህርቶች፣ አልባሳት፣ ቋንቋዎች እና የበለጠ ጋር በሚዛመዱ ማጣቀሻዎች የተሞሉ ናቸው። 7 እያንዳንዱ የምናምናቸው እና እግዚአብሔር ለቃል ኪዳን ህዝቦቹ የገባው እያንዳንዱ የተስፋ ቃል በቤተመቅደስ ውስጥ ይዋሃዳል። በማንኛውም ዘመናት፣ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪኖችን የሚገቡ እና የሚጠብቁ ሰዎች የቃል ኪዳን ልጆች እንደሆኑ ቤተመቅደስ ውዱን እውነታ አስምሮበታል።
ስለሆነም፣ በጌታ ቤት ውስጥ አብርሐም፣ ይስሐቅ እና ያዕቆብ እንደገቡት ተመሳሳይ ቃል ኪዳኖችን ከእግዚአብሔር ጋር መግባት እንችላለን። እናም ተመሳሳይ በረከቶችን መቀበል እንችላለን።
ቤተመቅደሶች ከመጀመሪያ ቀናት ጀምሮ የዚህ ክፍለ ዘመን አካል ሆነዋል። 8 ኤሊያስ የህትመት ስልጣን ቁልፎችን ለጆሴፍ ስሚዝ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ሰጠው። የክህነት ሙላት በናቩ ቤተመቅደስ ውስጥ በዳግም ተመለሰ። 9
እስከሞቱ ድረስ ጆሴፍ ስሚዝ የቡራኬ እና የህትመት ሥነ-ስራዓቶችን መመለስ የሚያሳድግ ራዕዮችን መቀበሉን ቀጠለ። 10 ይሁን እንጂ፣ ያ ቀጣይነት ያለው ማጣሪያ አስፈላጊ እንደሆነ ተገነዘበ። በግንቦት 1842 (እ.አ.አ) ውስጥ ቡራኬን ለብሪገም ያንግ ካገለገለ በኋላ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ለብሪገም እንዲህ ብሎ ነገረው፣ “ይህ በትክክል አልተስተካከለም፣ ነገር ግን ባለንበት ሁኔታ ውስጥ የተቻለንን የተሻለ ነገር አድርገናል እና ይህን ጉዳይ እንድትወስደው እና ሁሉንም ሥነ-ስርዓቶች እንድታስተካክላቸው እመኛለው።” 11
የነዩን ሞት ተከትሎ፣ ፕሬዚዳንት ያንግ የናቩ ቤተመቅደስን እንዲፈጸም፡አደረገ እና ከዚያም በኋላ በዩታ ድንበር ውስጥ ቤተመቅደሶችን ገነባ። 12 የሴይንት ጆርጅ ቤተመቅደስ የታችኛው ፎቆች ቡራኬ ላይ ብሪገም ያንግ በሙታን ምትክ የሚደረገውን የቤተመቅደስ ስራን አስቸኳይነት በኃይል እንዲህ ብሎ ተናገረ፣ “ስለዚህ ጉዳይ ሳስብ የሰባት ነጎድጓዶች ምላሶች ህዝቡን እንዲያነቁት እፈልጋለሁ።” 13
ከዛ ጊዜ አንስቶ የቤተመቅደስ ሥነ-ስርዓቶች ቀስ በቀስ ተሻሻሉ። ፕሬዚዳንት ሃሮልድ ቢ. ሊ ሂደቶች፣ ፖሊሲዎች እና የቤተመቅደስ ሥነ-ስርዓቶች አገልግሎት እራሱ በአዳኙ የተመለሰው ቤተክርስቲያን ውስጥ ለምን መለወጣቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ፕሬዝደንት ሊ እንዲህም አሉ፦ “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መርሆዎች መለኮታዊ ናቸው። በራዕይ አማካኝነት ከጌታ በቀር ማንም ሰው የቤተክርስቲያኗን መርሆዎች እና [ትምህርቶች] አይቀይርም። ነገር ግን የተነሳሳው መመሪያ በዚያ ጊዜ ለሚመሩት ሰዎች ሲመጣ ዘዴዎች ይቀየራሉ።” 14
ቅዱስ ቁርባንን ማካፈል በዓመታት ውስጥ እንዴት እንደተቀየረ አስቡ። በድሮ ጊዜ የቅዱስ ቁርባኑ ውኃ ለምዕመኑ ይሰጥ የነበረው በአንድ ትልቅ ማሰሮ ውስጥ ነበር። ሁሉም ሰው ከእሱ ይጠጣ ነበር። አሁን ለያንዳንዳችን ጥቅም ላይ ውለው የሚጣሉ ኩባያዎችን እንጠቀማለን። ሂደቱ ተቀየረ፣ ነገር ግን ቃል ኪዳኑ ተመሳሳይ ሆኖ ቆየ።
እነዚህን ሶስት እውነታዎች አሰላስሉ፦
-
ዳግም መመለሱ ክስተት ሳይሆን ሂደት ነው፣ እና ጌታ በድጋሚ እስከሚመጣ ድረስ ይቀጥላል።
-
እስራኤልን የመሰብሰብ የመጨረሻ አላማ 15 የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ በረከቶች ለአማኝ ልጆቹ ለማምጣት ነው።
-
ያንን አላማ የበለጠ ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዴት ማሳክት እንደምንችል ስንሻ፣ ጌታ የላቀ ግንዛቤዎችን ይገልፃል። ቀጣይነት ያለው መመለስ ቀጣይነት ያለው ራዕይን ይፈልጋ።
የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ምልዓተ ጉባኤ የቤተመቅደስን በረከቶች ለአማኝ ልጆቹ ለመውሰድ የተሻለ መንገድ ካለ ብለው ጌታን ብዙ ጊዜ ጠይቀውታል። ምንም እንኳን በቋንቋ እና በባህል ልዩነት ቢኖርም እንዴት ዓለም አቀፋዊ የሆነ ትክክለኛ እና የማይለዋወጥ የቤተመቅደስ መመሪያን፣ ቃል ኪዳኖችን እና ሥነ-ስርዓቶችን ለማረጋገጥ በተደጋጋሚ ምሪትን እንሻለን።
በጌታ ምሪት ስር እና ለጸሎታችን ምላሽ መሰረት ወቅታዊ የሂደት ለውጦች ተደርገዋል። እርሱ ነው በታላቅ ግልፅነት በእርግጥ ምን ለማድረግ ቃል ኪዳኖችን እንደምትገቡ እንድትረዱ የሚፈልገው። እርሱ ነው ሙሉ በሙሉ የእርሱን ቅዱስ ሥነ-ስርዓቶች እንድትለማመዱ የሚፈልገው። እርሱ መብታችሁን፣ ቃል ኪዳናችሁን እና ሃላፊነታችሁን እንድትረዱ ይፈልጋል። እርሱ ከዚህ ቀደም ኖሯችሁ የማያውቀውን መንፈሳዊ ግንዛቤዎች እና መነሳሳት እንዲኖራችሁ ይፈልጋል። የትም ብትኖሩም፣ እርሱ ለሁላችሁም የቤተመቅደስ አገልጋዮች ይህን ይፈልጋል።
በቤተመቅደስ ሂደቶች ውስጥ ወቅታዊ ማስተካከያዎች እና የሚከተሉት ሌሎች፣ ጌታ በንቁነት ቤተክርስቲያኑን እየመራ እንዳለ ቀጣይነት ያላቸው ማረጋገጫዎች ናቸው። ሕይወታችንን በእርሱ እና በቤተመቅደሱ ሥነ-ስርዓቶች እና ቃል ኪኖች ላይ በማተኮር መንፈሳዊ መሰረቶቻችን የበለጠ ለማጠናከር ለእያንዳንዳችን እድሎችን እየሰጠ ነው። የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያችሁን፣ የተዋረደ ልባችሁን እና የሚሻ አዕምሮን ወደ ጌታ የትምህርት ቤት ስታመጡ፣ እርሱ ያስተምራችኋል።
ርቀት፣ የጤና ችግር ወይም ሌሎች መሰናክሎች የቤተመቅደስ ተሳትፎአችሁን ለተወሰነ ወቅት ከከለከላችሁ፣ የገባችሁትን ቃል ኪዳኖች በአዕምሮአችሁ ውስጥ ለመደጋገም ቋሚ የሆነ ሰዓት እንድትመድቡ እጋብዛችኋለው።
በቤተመቅደስ የመካፈል ፍላጎታችሁ ገና እያደገ ከሆነ፣ ትንሽ ጊዜ ሳይሆን—ብዙ ጊዜ ሂዱ። በዚያም በጌታ በመንፈስ አማካኝነት እንዲያስተምራችሁ እና እንዲያነሳሳችሁ ፍቀዱለት። ከጊዜ በኋላ ቤተመቅደስ የደህንነት፣ የመፅናናት እና የራዕይ ቦታ እንደሚሆን ቃል እገባላችኋለሁ።
ከሁሉም ወጣቶች ጋር አንድ ለአንድ መነጋገር የምችል ቢሆን፣ በቤተመቅደስ ውስጥ አብራችሁ እትመት የምታደርጉትን ጓደኛ እንድትሹ እለምናችሁ ነበር። ይህ በሕይወታችሁ ውስጥ ምን ለውጥ ያመጣል ብላችሁ ልታስቡ ትችሉ ይሆናል። ሁሉንም ለውጥ እንደሚያመጣ ቃል እገባለው። በቤተመቅስ ውስጥ ስታገቡ እና በተደጋጋሚ ስትመላለሱ፣ በውሳኔዎቻችሁ ትጠነክራላችሁ እናም ትመራላችሁ።
እስካሁን ድረስ በቤተመቅደስ ውስጥ ህትመትን ካልፈፀሙ ከእያንዳንዱ ባሎች እና ሚስቶች ጋር መነጋገር ብችል፣ ያንን ዘውዳማ ሕይወት ቀያሪ ሥነ-ስርዓትን ለመቀበል አስፈላጊ እርምጃዎችን እንድትወስዱ እለምናችሁ ነበር። 16 ለውጥ ያመጣልን? ለዘለአለም ለማደግ ከፈለግን እና አብረን መሆን ከፈለግን ብቻ። ለዘለአለም አብሮ ለመሆንመፈለግ ብቻ ይህን አያሳካውም። ሌላ አከባበር ወይም ፊርማ ይህን አያሳካውም። 17
ጋብቻን ለሚሹ ነገር ግን የእሱን ወይም የእሷን የዘላለም ጓደኛ እስካሁን ላላገኙት ለእያንዳንዱ ሰው ወይም ሴት መናገር ብችል፣ በጌታ ቤት ውስጥ ቡራኬን ለመቀበል ጋብቻ እስክትፈጽሙ እንዳትጠብቁ አበረታታችኋለሁ። የክህነትን ኃይል መታጠቅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ መማርን እና መለማመድን አሁን ጀምሩ።
እና የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን ላደረጋችሁ ለእያንዳንዳችሁም፣ የቤተመቅደስን ቃል ኪዳኖች እና ሥነ-ስርዓቶች ለመረዳት—በጸሎት እና በተደጋጋሚ—እንድትሹ እለምናችኋለሁ። 18 መንፈሳዊ በሮች ይከፈታሉ። በምድር እና በሰማይ መካከል ያለውን መጋረጃው እንዴት መክፈት እንዳለባችሁ፣ የእግዚአብሔር መላዕክቶች እንዲጠብቋችሁ እንዴት መጠየቅ እንዳለባችሁ እና ከሰማይ ምሪትን እንዴት በተሻለ መልኩ እንደምትቀበሉ ትማራላችሁ። ይህን ለማድረግ ያላችሁ የእናንተ ያላሰለሰ ጥረት መንፈሳዊ መሰረታችሁን ያጠነክራል እናም ያበረታል።
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ የሶልት ሌክ በተመቅደስ እድሳት ሲጠናቀቅ፣ በሶልት ሌክ ሸለቆ ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ በሚኖርበት ጊዜ፣ ከቤተመቅደስ ውስጣዊ ክፍል የተሻለ ምንም ደህና የሚሆን ቦታ እይኖርም።
በተመሳሳይ መልኩ፣ በሕይወታችሁ ውስጥ ሁከት ሲከሰት፣ በመንፈስ በደህንነት ቦታ ለመሆን የምትችሉበት ቢኖር በቤተመቅደስ ቃል ኪዳናችሁ ውስጥ መኖር ነው።
መንፈሳዊ መሰረታችሁ በጥንካሬ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ሲገነባ፣ መፍራት አያስፈልጋችሁምስላችሁ እባካችሁን እመኑኝ። በቤተመቅደስ ለገባችሁት ቃል ኪዳናችሁ ታማኝ ስትሆኑ፣ በእርሱ ኃይል ትጠነክራላችሁ። ከዚያም መንፈሳዊ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲመጣ፣ ጠንክራችሁ መቆም ትችላላችሁ ምክንያቱም የመንፈሳዊ መሰረታችሁ ጠንካራ እና የማይነቃነቅ ስለሆነ።
እወዳችኋለሁ፣ ውድ ወንድሞች እና እህቶች። እነዚህን እውነታዎች አውቃለሁ፦ የእኛ የሰማይ አባት፣ እግዚአብሔር እናንተ ወደ እርሱ ወደ ቤት እድትመጡ ይፈልጋል። የእርሱ የዘለአለም እድገት ዕቅድ ውስብስ አይደለም፣ እናም ነፃ ምርጫችሁን ያከብራል። በሚመጣው ዓለም ውስጥ ማን እንደምትሆኑ—ከማን ጋር እንደምትሆኑ—ለመምረጥ ነፃ ናችሁ።
እግዚአብሔር ህያው ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ነው! ይህችም መለኮታዊ እጣ ፈንታችሁን ለማሟት እንድትረዳችሁ በዳግም የተመለሰችው የእርሱ ቤተክርሰቲያን ናት። ይህንን የምመሰክረው ቅዱስ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።