ቅድስናን ለእግዚአብሔር መስጠት
መስዋዕትነት ትንሽ “አሳልፎ መስጠት” እና የበለጠ ደግሞ ለ ጌታ “መስጠት” ነው።
ባለፈው ዓመት በእስያ ደቡብ አካባቢ አመራር ውስጥ ሳገለግል፣ በኤጲስ ቆጶስ አመራር ውስጥ ሁለተኛ አማካሪ ሆኜ እንዳገለግል ከፕሬዝዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን የስልክ ጥሪን ተቀበልኩኝ። ባለቤቴ ሎሪን ንግግሩን እንድትቀላቀል በቸርነት ጋበዟት። የስልክ ጥሪው ካበቃ በኋላ ባለቤቴ “የኤጲስ ቆጶስ አመራር ምን ስራ ነው የሚሰሩት” ብላ ስትጠይቅ ባለማመን ስሜት ውስጥ ነበርን። ከትንሽ ጊዜ ማሰላሰል በኋላ እንዲህ ብዬ መለስኩኝ፣ “በእርግጥ አላውቅም!”
ከአንድ ዓመት በኋላ—ጥልቅ ከሆነ የትህትና እና የምስጋና ስሜት በኋላ—የባለቤቴን ጥያቄ በታላቅ መረዳት መመለስ እችላለው። ከብዙ ነገሮች መካከል የኤጲስ ቆጶስ አመራር የቤተክርሰቲያኗን የደህንነት እና የሰብአዊ እርዳታ ስራ ይመለከታሉ። ይህ ስራ አሁን መላ ዓለምን ይሸፍናል እናም ከቀድሞ በበለጠ ሁኔታ ብዙ የእግዚአብሔርን ልጆች ይባርካል።
እንደ የኤጲስ ቆጶስ አመራር፣ በድንቅ የቤተክርቲያን ተቀጣሪዎች እና በሌሎች ከእኛ ጋር የቤተክርስቲያኗ ደህንነት እና እራስን መቻል አስፈፃሚ ኮሚቴ በሚያገለግሉ የአጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ አመራር እንታገዛለን። እንደ የዛ ኮሚቴ አባልነታችን በመላ አቅማችን የቀዳሚ አመራር እኔን—እንዲሁም ባለፈው ምሽት የተናገሩን እህት ሼረን ዩባንክንም ጨምሮ—የቤተክርቲያኗን የሰባዊ እርዳታ ሙከራዎች የቅርብ ለውጥ ከእናንተ ጋር እንድናካፍል ጠየቁኝ። በተለይ ጥልቅ የሆነ ምስጋናቸውን እንድንገልፅ ጠየቁ—ምክንያቱም፣ ወንድሞች እና እህቶች፣ እናነት ናችሁ እነዛን የሰባዊ እርዳታ ጥረቶች እውን ያደረጋችሁት።
የዓለም አቀፉን የኮቨድ–19ኝን ቀውስ የቀድሞ የኢኮኖሚ ውጤቶችን በጭንቀት ስንመለከት፣ ቅዱሳኑ የሚሰጡት የብር መዋጮው ይቀንሳል ብለን ልንጠብቅ እንችል ይሆናል። ሆኖም፣ የገዛ አባሎቻችን በወረርሽኝ እክሎች የሚገቱ አይደሉም። ተቃራኒውን ስንመለከት ስሜቶቻችን ምን እንደሚሆኑ አስቡ። በ2020 (እ.አ.አ) ውስጥ የሰባዊ እርዳት መዋጮ ከፍተኛው ሆኖ ተገኘ—እና በዚህ ዓመትም እየጨመረ ይገኛል። በቸርነታችሁ ምክንያት፣ ከ150 በላይ በሆኑ አገራት ውስጥ ከ1500 በላይ በሆኑ የኮቨድ–19 የእርዳታ ፕሮጀክቶች በኩል ቤተክርቲያኗ ከሰብአዊ እርዳታ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ በጣም ሰፊ ምላሹን መገንዘብ ችላለች። እራስ ወዳድ ባለመሆን ለጌታ የሰጣችሁት እነዚህ መዋጮዎች ማግኘት ለማይችሉ ሰዎች ሕይወት ለሚጠብቁ ምግቦች፣ ኦክስጂኖች፣ የመድሃኒት አቅርቦቶች እና ክትባቶች ተቀይረዋል።
ልክ ቁሳቁሶችን ማበርከት ጠቃሚ እንደሆነ ሁሉ ለሰብአዊ እርዳታ ጉዳዮች የቤተክርስቲያን አባሎች የሚያበረክቱት ጊዜ እና ጉልበት ጠቃሚ ነው። ወረርሽኙ በተባባሰበት ጊዜ እንኳን፣ የተፈጥሮ አደጋዎች፣ የእርስ በእርስ ግጭቶች እና የኢኮኖሚ አለመረጋጋት የማያቋርጡ ሆነዋል እናም በሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ከቤታቸው አፈናቅለዋል። የተባበሩት መንግስታት በዓለም ዙሪያ ከቦታቸው የተፈናቀሉ ከ82 ሚሊዮን በላይ የሚጠጉ ሰዎች መኖራቸውን አሁን ዘግቧል። 1 ሌሎች ለራሳቸው እና ለቤተሰባቸው የተሻለ ሕይወትን በመሻት ከድህነት ወይም ከጭቆና የተሰደዱትን እዚህ ላይ ጨምሩ እና የዚህን ዓለም ሁኔታ በትንሹ ለመረዳት ትችላላቹ።
ምስጋና በሚገባቸው በብዙ በጎ ፈቃደኞች ጊዜ እና ችሎታ፣ ቤተክርሰቲያኗ በዩናይትድ ስቴትስ እና በአውሮፓ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የስደተኛ እና የኢሚግሬሽን እንኳን ደህና መጣችሁ ማዕከሎችን ስለማንቀሳቀሷ ስዘግብ ደስተኛ ነኝ፣ ። እናም ምስጋና በሚገባቸው በእናንተ መዋጮዎች፣ ቁሳቁሶችን፣ ድጎማን እና በጎ አድራጊዎችን በዓለም ዙሪያ ተመሳሳይ ፕሮግራሞችን በሌላ ተቋሞች ለማንቀሳቀስ እንዲረዱ እንሰጣለን።
እነዚህን ስደተኞች እንዲቋቋሙ እና እራሳቸውን እንዲችሉ ለመመገብ፣ ለማልበስ፣ ጓደኛ ለማድረግ እና ለመርዳት ለቻሉት ለእነዛ ቅዱሳን ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ላበርክት።
ትላንትና ምሽት እህት ዩባንክ በዚህ ረገድ ላይ የቅዱሳኑን የተወሰኑ አስደናቂ ጥረቶች አካፈለች። በእነዚህ ጥረቶች ላይ ሳሰላስል ብዙ ጊዜ ሃሳቤ ወደ መስዋዕትነት መርህ እና ይህ መርህ እግዚአብሔርን ከመውደድ እና ጎረቤቶቻችንን ከመውደድ ከሁለቱ ታላቅ ትዕዛዛት ጋር ወዳለው ቀጥተኛ ግንኙነት ይዞራል።
በዘመናዊ አጠቃቀም፣ መስዋዕት የሚለው ቃል ነገሮችን ለጌታ እና ለእርሱ መንግስት “አሳልፎ መስጠት” የሚለውን ፅንሰ ሃሳብ ይይዛል። ይሁን እንጂ፣ በጥንት ቀናት ውስጥ፣ መስዋዕት የሚለው ቃል ትርጉም ከሁለት የላቲን ስሮች ጋር የበለጠ ይተሳሰራል፦ sacer [ሳሰር]፣ ማለትም ቅዱስ፣ወይም የተቀደሰ፣ እና facere [ፋሰር]፣ ማለትም “ማድረግ።” 2 ስለሆነም በጥንት ጊዜ መስዋዕት ማለት የሆነ ነገርን ወይም የሆነ ሰውን ቅዱስ ማድረግ ማለት ነበር። 3 እንደዚህ በመመልከት መስዋዕትነት ቅዱስ የመሆን እና እግዚአብሔርን የማወቅ ሂደት ነው፣ ነገሮችን ለጌታ የሚደረግ ክስተት ወይም በአምልኮ “አሳልፎ የመስጠት” አይደለም።
ጌታ እንዲህ አለ፣ “ከመስዋዕት ይልቅ [ልግስናን]፣ ከሚቃጠልም መስዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እሻለው።” 4 ጌታ ቅዱስ እንድንሆን፣ 5 ልግስና እንዲኖረን፣ 6 እና እርሱን እንድናውቀው ይፈልጋል። 6 ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳስተማረው፣ “ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ስጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።” 8 በመጨረሻ ጌታ ልባችንን ነው የሚፈልገው፤ በክርስቶስ አዲስ ፍጡር እንድንሆን ይፈልጋል። 9 ኔፋውያንን እንዳስተማረው፣ “ ለ እኔም መስዋእት የተሰበረ ልብና የተዋረደ መንፈስ ታቀርባላችሁ።” 10
መስዋዕትነት ትንሽ “ አሳልፎመስጠት” እና የበለጠ ደግሞ “ ለጌታ መስጠት” ነው። በእንዳንዱ የቤተመቅደስ መግቢያ ላይ “ቅድስናን ለእግዚአብሔር የእግዚአብሔር ቤት” የሚሉ የተቀረፁ ቃላት አሉ። ቃል–ኪዳናችንን በመስዋዕት ስንጠብቅ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ እና በቅዱስ ቤተመቅደስ መሰዊያዎች አማካኝነት በተሰበሩ ልቦች እና በተዋረዱ መንፈሶች ቅዱስ እንሆናለን፣ ቅድስናችንን ለጌታ እንሰጣለን። ሽማግሌ ኒል ኤ. ማክስዌል እንዲህ አስተማሩ፦ “የአንድን ሰው ፈቃድ [ወይም ልብ] አሳልፎ መስጠት 11 ] በእግዚአብሔር መሰዊያው ላይ የምናስቀምጠው ብቸኛ የተለየ ግላዊ ነገር ነው። … ይሁን እንጂ፣ እናንተ እና እኔ ግላዊ ፍቃዳችንን በእግዚአብሔር ፍቃድ እንዲዋጥ በመፍቀድ መጨረሻ ላይ እራሳችንን አሳልፈን ስንሰጥ ለ እርሱ የሆነ ነገር እየሰጠን ነው!” 12
ለሌሎች የምናደርገው የእኛ መሰዋዕትነት “አሳልፎ ከመስጠት” አንፃር ሲታዩ፣ እንደ ሸክም አድርገን ልንመለከታቸው እና መስዋዕትነታችን ሳይታዩ ወይም ሳይሸለሙ ሲቀሩ ተስፋ ልንቆርጥ እንችላለን። ይሁን እንጂ፣ ለጌታ “ከመስጠት” አንፃር ሲታይ፣ ለሌሎች የምናደርገው የእኛ መስዋዕቶቻችን ስጦታዎች ይሆናሉ እና በቸርነት በመስጠት የሚመጣው ደስታ ሽልማቱ ይሆናል። ፍቅርን፣ ማረጋገጫን ወይም አድናቆትን ከሌሎች ከመሻት ነፃ በመሆን፣ መስዋዕቶቻችን ለአዳኙ እና ለሰዎች ያለን የምስጋናችን እና የፍቅራችን ንፁ እና ጥልቅ መገለጫ ይሆናሉ። ማንኛውም እራስን መስዋዕት የማድረግ ኩራታማ አመለካከት፣ ለምስጋና፣ ቸርነት፣ እርካታ እና ደስታ ስሜቶች መንገድ ይሰጣል። 13
የሆነ ነገር ቅዱስ የሚሆነው—ሕይወታችን፣ ንብረታችን፣ ጊዜያችን ወይም ችሎታችን ቢሆንም—ይህን አሳልፈን በመስጠት ሳይሆን ነገር ግን ለጌታ በመቀደስ 14 ነው። የቤተክርቲያን የሰብአዊ ዕርዳታ ስራ እንዲህ አይነት ስጦታ ነው። ይህ ለእግዚአብሔር እና ለልጆቹ ያለን ፍቅር መገለጫ የሆነው የጋራ፣ የተቀደሱ የቅዱሳን መስዋዕቶች ውጤት ነው። 15
ስቲቭ እና አኒታ ካንፊልድ ለጌታ የመስጠት በረከቶችን በግላቸው የተለማመዱ የዓለም ዙሪያ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ተወካይ ናቸው። እንደ ደህንነት እና እራስን ስለመቻል ሚስዮኖች፣ ካንፊልዶች በመላው አውሮፓ በስደት ካምፖች እና በኢሚግሬሽን ማዕከሎች ዕርዳታ እንዲያቀርቡ ተጠይቀው ነበር። በስራ ሕይወቷ ውስጥ እህት ካንፊልድ ያማረ ቤታቸውን ለማሳመር ከሃብታም ባለ ጉዳዮች ጋር ውል የምትገባ አንጋፋ የውስጥ ዲዛይነር ነበረች። ከምድራዊ ንብረቶች አንፃር ሲታይ ሁሉንም ነገር ያጡ ሰዎችን በማገልገል በድንገት በሙሉ ተቃራኒ በሆነ ዓለም ውስጥ እራሷን አገኘች። በገዛ ቃላቶቿ “የበረዶ ሸክላ የእግር መንገድን በአፈር መሬት” ለወጠች፣ እና እንክብካቤያቸውን የሚሹትን ሰዎች—እሷ እና ባለቤቷ ጓደኛ ማድረግ ሲጀምሩ—እና ሲወዱ እና ሲቀበሉ ይህን በማድረግ ስፍር ቁጥር የሌለውን የማሳካት ስሜት አገኘች።
ካንፊልዶች እንዲህ አሉ፣ “ጌታን ለማገልገል ምንም ነገር ‘አሳልፈን የሰጠን’ መስሎ አልተሰማንም። ፍላጎታችን እኛን መጠቀም በሚፈልገው በማንኛውም መንገድ እንዲጠቀመን ጊዜያችንን እና ጉልበታችንን ልጆቹን ለመባረክ ለእርሱ ‘መስጠት’ ነበር። ከወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር ስንሰራ ማንኛውም የውጪ ገፅታ—በአስተዳደግ ወይም በንብረት ላይ ያለ ማንኛውም ልዩነት—ጠፋ እና የእርስ በእርስ ልቦችን ተመለከትን። እነዚህ ልምዶች በትሁት የእግዚአብሔር ልጆች መካከል ማገልገል የሰጠንን በረከት የሚስተካከል ምንም የስራ ውጤት ወይም ቁሳዊ ትርፍ የለም።”
የካንፊልዶች ታሪክ እና የእንደነሱ ዓይነት የሌላ ብዙዎች ታሪክ ቀላል የሆነ ነገር ግን ጥልቅ የሆነ የህፃናት መዝሙር ስንኞችን እንዳመሰግን እረድቶኛል።16
“ስጡ” አለ ትንሹ ወንዝ
ቁልቁለቱን በቶሎ ሲወርድ፤
“አቃለው እኔ ትንሽ ነኝ፣ ነገር ግን በምሄድበት ቦታ
መሬቶቹ አሁንም አረንጓዴ ይሆናሉ።”
አዎን፣ እያንዳንዳችን ትንሽ ነን፣ ነገር ግን በጋራ ለእግዚአብሔር እና ለሰዎች ለመስጠት ስንጣደፍ፤ በምንሄድበት ቦታ ሁሉ ሕይወቶች ይበለፅጋሉ እና ይባረካሉ።
የመዝሙሩ ሶስተኛው ጥቅስ ብዙም ታዋቂ አይደለም ነገር ግን በዚህ ተወዳጅ ግብዣ ይደመድማል።
ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ አቅማችንን ፣ ጊዜያችንን፣ እና አዎን ለራሳችን እንኳን በመስጠት፣ ለእግዚአብሔር እና ለሌሎች ስንኖር፣ ዓለምን ትንሽ አረንጓዴ አድርገን እየተውን፣ የእግዚአብሔርን ልጆች ትንሽ ደስተኛ እያደረግን፣ እና በሂደት፣ ትንሽ ቅድስና እየሆንን ነን።
በነፃ ለ እርሱ ለሰጣችሁት መስዋዕትነት ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ።
እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ እመሰክራለሁ። “ስሙ የቅድስና ሰው ነው።” 17 ኢየሱስ ክርስቶስ የእርሱ ልጅ እና የሁሉም መልካም ስጦታ ሰጪ ነው። 18 በእርሱ ፀጋ አማካኝነት እና በመስዋዕት ቃል–ኪዳኖቻችንን በመጠበቅ ቅዱስ እንሁን እናም የበለጠ ፍቅር እና ቅድስና ለጌታ እንስጥ። 19 በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።