አንድ ፐርሰንት የተሻለ
ለመለወጥ የምናደርገው ሁሉም ሙከራ ምንም ያህል ትንሽ ብትመስለንም በሕይወታችን ውስጥ ታላቁን ለውጥ ልታመጣ ትችላለች።
ከአንድ ክፍለ ዘመን ለሚበልጡ ጊዜያት የታላቋ ብሪታንያ የብሔራዊ ብስክሌት ተወዳዳሪ ቡድኖች የብስክሌት ዓለም መሳለቂያ ሆነው ነበር። ለብዙ ጊዜያት በችግር ሁኔታዎች ውስጥ በመሳተፍ፣ የብሪታንያ ብስክሌተኞች በ100 ዓመታት የኦሎምፒክ ውድድሮች ውስጥ ማግኘት የቻሉት የተወሰኑ ወርቆችን ብቻ ነበር፤ እንዲሁም በብስክሌት ማርኬ ክስተት ውስጥ ለ110 ዓመታት የብሪታንያ ብስክሌተኞች ማሸነፍ ያልቻሉበት 3 ሳምንትን የሚፈጀው አሰቃቂ የቱር ደ ፍራንስ ውድድር ላይ ከመጠን በላይ ተሰላችተው ነበር። የብስክሌት አምራቾች በጥንካሬ የተገኘ ዕውቅናቸው እስከመጨረሻ እንዳያበላሽባቸው በመፍራት ለብሪታኒያውያን ብስክሌት መሸጥን መከልከላቸው ለብሪታኒያ ብስክሌተኞች ችግር ነበር። ምንም እንኳን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ላይ እና ዘመናዊ የስልጠና ልምምዶች ላይ ብዙ ግብዓቶችን ቢያፈሱም ምንም መፍትሄ አላመጣም።
የብሪታኒያን የብስክሌት አቅጣጫ እስከመጨረሻው የቀየረ ትንሽ በአብዛኛው ልብ ያልተባለ ለውጥ እስከተከሰተበት እስከ 2003 (እ.አ.አ) ድረስ ምንም ነገር አልነበረም። ያ አዲሱ አቀራረብ—ቃል የተገባለት—ብዙ ጊዜ እራሳችንን ለማሻሻል በሚደረገው ግራ የሚያጋባ ምድራዊ ተልዕኮን የተመለከተ የዘላለም መርሆንም ይገልፃል። ስለዚህ የተሻልን የእግዚአብሔር ሴት እና ወንድ ልጆች ለመሆን ግላዊ ፍለጋችን ታላቅ ጥቅም ሊሆነን የሚችል በብሪታንያ የብስክሌት ስፖርት ውስጥ ምን ተከሰተ?
በ2003 (እ.አ.አ) ውስጥ ሰር ዴቭ ብሬልስፎርድ ተቀጠረ። ፈጣን ፣ ያልተጠበቁ በአንድ ጀምበር ለውጥን ለማምጣት ከሞከሩ የድሮ አስልጣኞች ይልቅ፣ ሰር ዴቭ ብሬልስፎርድ በምትኩ “የትንንሽ ውጤቶች ድምር” ብሎ የጠራውን ስትራቴጂ ተከተለ። ይህ ማለት በእያንዳንዳቸው ነገሮች ላይ ትንንሽ ማሻሻያዎችን ማድረግ ያካትታል። ያ ማለት በተደጋጋሚ ቁልፍ የሆኑ ስታቲስቲክሶችን መለካት እና የተለየን ድክመት ማሻሻል ማለት ነበር።
ከላማናውያኑ ነብዩ ሳሙኤል ሁኔታ ጋር ተመሳሳይነት አለው “በጥንቃቄ ይራመዳሉ” ብሎ እንደጠራው ነው። 1 ይህ ሰፋ ያለ በይበልጥ ሁሉን አቀፍ የሆነ ዕይታ በመያዝ ግልፅ የሆነ ችግር ወይም ሃጢያት ላይ የማተኮር ወይም አርቆ መመልከት ያለመቻል ወጥመድን ያስወግዳል። ብሬልስፎርድ እንዲህ ብሏል፣ “ሙሉ መርሆው ብስክሌት ከመንዳት ጋር ይያያዛል ብላችሁ የምታስቧቸውን ነገሮች ብትከፋፍሏቸው እና እነሱን በ1 ፐርሰንት ብታሻሽሏቸው፣ ሁሉንም በአንድ ላይ ስታደርጓቸው ትርጉም ያለው መሻሻል ታገኛላችሁ ከሚለው ሃሳብ የመጣ ነው።” 2
የእሱ አቀራረብ 99 ፐርሰንትን መስዋዕት በማድረግም ቢሆን—የ1 ፐርሰንትን ወሳኝነት ካስተማረን ከጌታ አቀራረብ ጋር በደምብ ይስተካከላል። በእርግጥ ፍላጎት ያላቸውን ግለሰቦች ለመፈለግ የሚጠቅምን የወንጌል ትዕዛዝ እያስተማረ ነበር። ነገር ግን ያንን ተመሳሳይ መርሆ በጣፋጩ በሁለተኛው የወንጌል መርሆ ማለትም በንስሃ ላይ ተግባራዊ ብናደርገውስ? በሁከት፣ ተስፋ የሚያስቆርጥ ጩኸት እና በሃጢያት እና በንስሃ መካከል ባለው አስገራሚ መለዋወጥ ከምንናደድ አቀራረባችን ትኩረታችንን ማጥበብ ቢሆንስ—እያሰፋነው እያለንም እንኳን? ሁሉንም ነገር ፍፁም ለማድረግ ከመጣር ይልቅ አንድን ነገር ብናከናውንስ?
ለምሳሌ፣ በአዲሱ ሰፋ ያለ ግንዛቤያችሁ መጽሐፈ ሞርሞንን በየቀኑ ማንበብ መርሳታችሁን ብትገነዘቡስ? ሁሉንም 531 ገፆች በአንድ ምሽት አንብቦ ለመጨረስ ከመሞከር ይልቅ 1 ፐርሰንቱን ለማንበብ ብትወስኑስ—ያም ማለት በቀን አምስት ገፆችን—ወይም በወቅታዊ ሁኔታችሁ ውስጥ ለእናንተ የሚቻል የሚመስላችሁን ሌላ መጠን ብታነቡስ? ትንሽ ነገር ግን ቀጣይነት ያላቸውን ትንንሽ ውጤቶች በሕይወታችን ውስጥ መደመር በመጨረሻ በእኛ ግላዊ ድክመቶቻችን ላይ ወደ ድል የሚወስድ ጎዳና ይሆን? ይህ የጉርሻ መጠን ያለው አቀራረብ በእውነት ለእንከኖቻችን ይሰራልን?
አንጋፋው ደራሲ ጄምስ ክሊር ይህ ስትራቴጂ ስሌቱን በቀጥታ ለእኛ ጥቅም ያውላል ብሏል። “ልምዶች ራስን የማሻሻል ‘የፍላጎት ውህደት’ ናቸው ሲል ያስቀምጣል። በየቀኑ በአንድ ነገር በአንድ ፐርሰንት ብቻ የተሻላችሁ ብትሆኑ፣ በዓመቱ መጨረሻ ላይ 37 እጥፍ የተሻላችሁ ትሆናላችሁ።” 3
የብሬልስፎርድ ትንሽ ለውጦች በግልፅ በመሳሪያ፣ በጨርቃጨርቆች እና የስልጠና ሂደቶች ጀመረ። ነገር ግን የእሱ ቡድን እዛ አላቆመም። 1 ፐርሰንት ማሻሻያዎችን እንደ አመጋገብ፣ እና ጥገና በመሳሰሉት ችላ በተባሉ እና ባልተጠበቁ ስፍራዎች ማግኘታቸውን ቀጠሉ። ከጊዜ በኋላ እነዚህ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ጥቃቅን ማሻሻያዎች ማንም ሰው ካሰበው በላይ በፍጥነት ወደ አስገራሚ ውጤት ይደመራሉ። “በትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ፣ በስርአት ላይ ስርአት፣ ጥቂት በዚህ፣ ጥቂት በዚያ” በእርግጥ በዘላለማዊ መርሆ ላይ ነበሩ። 4
ትንንሽ ማስተካከያዎች የምትሹትን ያንን “ታላቅ ለውጥ” ያመጣሉ? 5 በትክክል ከተተገበሩ እንደሚሰሩ 99 ፐርሰንት እርግጠኛ ነኝ። ነገር ግን በዚህ አቀራረብ አንዱ ማስጠንቀቂያ ትንንሽ ውጤቶች ለእኛ እንዲደመሩ ዘለቄታ ያለው የቀን ተቀን ሙከራ ሊኖር ይገባል። እናም ምንም እንኳን ፍፁማን ባንሆንም፣ ተስፋ አለመቁረጥነን በትዕግስት ለማንፀባረቅ መወሰን ይኖርብናል። ያንን አድርጉ እና የሚያድግ ጽድቅ ጣፋጭ ሽልማቶች የምትሹትን ደስታ እና ሰላም ያመጣሉ። ፕሬዝዳንት ኔልሰን እንዳስተማሩት፦ “ዘወትር እና በየቀኑ ንስሃ ላይ ትኩረት ከማድረግ ይበልጥ ነጻ የሚያወጣ፣ ይበልጥ ከፍ ወዳለ ክብር የሚያደርስ እና በግለሰብ ደረጃ ለምናደርገው እድገት ጠቃሚ የሆነ ነገር የለም። ንስሃ አንድ ጊዜ የሚደረግ ክስተት ሳይሆን ሂደት ነው። ለደስታ እና ለአእምሮ ሰላም ዋናው ቁልፍ ነው። ከእምነት ጋር ሲጣመር ንስሃ የእየሱስ ክርስቶስን የሃጥያት ክፍያ ሃይል እንድናገኝ በሩን ይከፍትልናል።” 6
ንስሃ የእምነትን ቅድመ ሁኔታ መሆኑን በተመለከተ ቅዱሳት መጻህፍት ግልፅ ናቸው። በመጀመሪያ የሚያስፈልገው ነገር ትንሽ “የእምነት ቅንጣት” ነው። 7 እናም ይህን “የሰናፍጭ ዘር” 8 አስተሳሰብ መሰብሰብ ከቻልን እኛም የማይጠበቁትን እና ልዩ የሆኑትን ለውጦች በሕይወታችን ውስጥ መጠበቅ እንችላለን። ነገር ግን በአንድ ምሽት ከአቲላ ዘሃን ወደ እማሆይ ትሬዛ ለመቀየር እንደማንሞክር ሁሉ የመሻሻል ሂደታችንን ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚጨምር እንዲሆን ማስተካከል ይኖርብናል። በሕወታችሁ ውስጥ የሚያስፈልጉት ለውጦች የጅምላ ቢሆኑም እንኳን፣ ትንሽ በሆነ መለኪያ ጀምሩ። ያ በተለይ መጨናነቅ ወይም ተስፋ መቁረጥ የሚሰማችሁ ከሆነ እውነተት ነው።
ይህ ሂደት ሁሌም በቀጥተኛ መንገድ አይከናወንም። የበለጠ ቆራጥ በሚመስሉ መካከል እራሱ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህንን ብስጭት በገዛ ሕይወቴ ውስጥ ስላየሁት አንዳንዴ 1 ፐርሰንት ወደፊት እንዲሁም 2 ፐርሰንት ወደኋላ የሆነ ያህል እንደሚሰማ አውቃለሁ። ቀጣይነት ባለው መልኩ እነዛን የ1 ፐርሰንት ውጤቶች በማሰባሰብ ተስፋ ሳንቆርጥ በቆራጥነት ከቆየን፣ እርሱ “ሃዘናችንን የተሸከመው” 9 በእርግጠኛነት ይሸከመናል።
እንደሚታወቀው፣ በአሳዛኝ ሃጢየቶች ውስጥ ከተሳተፍን፣ ጌታ ግልፅ እና ቀጥተኛ ነው፣ ማቆም አለብን፣ ከኤጲስ ቆጶስ እርዳታ መቀበል እና ይህንን የመሰሉ ድርጊቶችን በፍጥነት መተው አለብን። ነገር ግን ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር እንዳስተማሩት፣ “ትንሽ፣ የተረጋጋ፣ የሚያድግ መንፈሳዊ ማሻሻያዎች ጌታ እንድንወስዳቸው የሚፈልጋቸው እርምጃዎች ናቸው። በእግዚአብሔር ፊት ካለምንም እንከን ለመራመድ መዘጋጀት በስጋዊ ህይወት እና በሕይወት ዘመን ፍለጋ ውስጥ ካሉት ዋነኛ አላማዎች ውስጥ አንዱ ነው፤ አልፎ አልፎ የሚፈጥን ኃይል ያለው የሃይለኛ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ውጤት አይደለም።” 10
ስለዚህ ይህ ትንሽ የንስሃ እና የእውነተኛ ለውጥ አቀራረብ በእርግጥ ይሰራልን? ማስረጃው ያለው ከፔዳል አጠቃቀሙ ላይ ነውን? የብሪታኒያ ብስክሌት ስፖርት ይህንን ፍልስፍና ተግባራዊ ካደረገ በኋላ ባሉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ ምን እንደተከሰተ አስቡ። አሁን የብሪታኒያ ብስክሌተኞች የሚነገርለትን የቱር ደ ፍራንስ ስድስት ጊዜ አሸንፈዋል። ባለፉት አራት የኦሎምፒክ ጨዋታዎች፣ ታላቋ ብሪታኒያ በመላው የብስክሌት ዘርፎች ውስጥ በጣም ውጤታማ አገር ሆናለች። በቅርቡ በተጠናቀቀው የቶኪዮ ኦለምፒክ፣ ዩኬ በብስክሌት ከሌሎች አገራት በላቀ ሁኔታ ብዙ ውርቆችን አገኘች።
ነገር ግን ከዓለማዊ ነሃስ ወይም ከወርቅ በጣም ደምቆ የሚታየው ወደ ዘላለም በሚመራን መንገዳችን ላይ የእኛ ውድ ቃልኪዳን “በክርስቶስ ድል” ማድረጋችን ነው። 11 እናም ትንሽ ነገር ግን ቀጣይነት ያለውን ለውጥ ለማድረግ ስንወስን “የማያልፈው የክብር አክሊል” ቃል ተገብቶልናል። 12 በዛ በማይደበዝዝ የብርሃን ጸዳል ታጌጡ ዘንድ ሕይወታችሁን እንድትፈትሹ እና በቃልኪዳን መንገዱ ላይ እዛው እንድትቀሩ እና እያዘገያችሁ ያለውን ነገር እንድትመለከቱ እጋብዛችኋለሁ። ከዛ በስፋት ተመልከቱ። የመለወጥ ጣፋጭ ደስታ ውጤትን የሚያመጡ መጠነኛ ነገር ግን በሕይወታችሁ ውስጥ ሊደረጉ የሚችሉ ለውጦችን ማድረግን እሹ።
ዳዊት የማይበገረውን ግዙፍ ለመጣል አንድ ትንሽ ድንጋይን እንደተጠቀመ አስታውሱ። ነገር ግን ሌሎች አራት ድንጋዮችም ነበሩት። በተመሳሳይ መልኩ፣ የወጣቱ አልማ የክፋት ስሜት እና ዘላለማዊ እጣ ፈንታ የተቀየረው በአንድ ቀላል ጉልህ ሃሳብ ነበር—ይሄውም አባቱ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ፀጋ የሰጠው ትምህርት ትውስታ ነበር። እንዲሁም ለአዳኛችንም ተመሳሳይ ነው ሃጢያት አልባ ቢሆንም፣ “ሙላትን በመጀመሪያ አልተቀበለም፣ ነገር ግን ሙላትን እስከሚቀበል ድረስ ከጸጋ ወደ ጸጋ ቀጠለ።” 13
በደቂቃ ላይ የሚያተኩርን ወፍ መቼ እንደሚወድቅ እንዲሁም በሕይወታችን ውስጥ ያሉትን ወሳኝ ክስተቶች የሚያውቀው እርሱ ነው እናም ከዚህ ጉባኤ የሚወጣውን የእናንተ የአንድ ፐርሰንት ፍለጋ ምንም ይሁን ምን እናንተን ለማገዝ አሁን ዝግጁ ነው። ለመለወጥ የምናደርገው ሁሉም ሙከራ ምንም ያህል ትንሽ ብትመስለንም በሕይወታችሁ ውስጥ ታላቁን ለውጥ ልታመጣ ትችላለች።
ለዚህ አላማ ሽማግሌ ኒል ኤ. ማክስዌል እንዲህ አስተማሩ፣ “የእያንዳንዱ የጽድቅ ፍላጎት ማረጋገጫ፣ የእያንዳንዱ የማገልገል ተግባር እና የእያንዳንዱ የአምልኮ ተግባር ምንም እንኳን ትንሽ እና አእየጨመረ የሚሄድ ቢሆንም መንፈሳዊ ሃይላችንን ይጨምራል።” 14 እውነትም በትንሽ፣ ቀላል እና አዎ በ1 ፐርሰንት ነገሮች፣ ታላቅ ነገሮች ይከናወናሉ። 15 በጌታችን እና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል፣ መልካምነት እና ምህረት አማካኝነት “ማድረግ የምንችለውን ሁሉንም ካደረግን በኋላ” የመጨረሻው ድል 100 ፐርሰንት እርግጠኛ ይሆናል። 16 ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።