አጠቃላይ ጉባኤ
ብርሃናችሁን ከፍ አድርጋችሁ ያዙ
የጥቅምት 2021 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ብርሃናችሁን ከፍ አድርጋችሁ ያዙ

የዛሬው ግብዣዬ ቀላል ነው ወንጌልን አካፍሉ። እራሳችሁን ሁኑ እና ብርሃንን ከፍ አድርጉ።

ከጥቂት ዓመታት በፊት ወደ ፔሩ በረራ ላይ ሳለሁ፣ አምላክ የለሽ ነኝ ከሚል ግለሰብ አጠገብ ተቀመጥኩ። ለምን በእግዚአብሔር እንደማምን ጠየቀኝ። በዚህ አስደሳች ውይይት፣ ጆሴፍ ስሚዝ ስላየው በእግዚአብሔር እንዳመንኩ ነገርኩት—ከዚያም ስለእግዚአብሔር ያለኝ እውቀት እንዲሁ ከግል፣ ከእውነተኛ መንፈሳዊ ተሞክሮ የመጣ መሆኑን አክዬ ነበር። እኔ “ሁሉም ነገር እግዚአብሔር እንዳለ ያመላክታል” 1 የሚለውን እምነቴን አካፍዬ እናም በጠፈር ባዶነት ውስጥ ያለው የሕይወት ምሰሶ–ይህ ምድር ወደ ሕልውና እንዴት እንደመጣ–እንደሚያምን ጠየኩት። እሱ በቃላቱ “አንደ አጋጣሚ” ከዘመናት በላይ ሊከሰት እንደሚችል መለሰ። እንዲህ ዓይነቱን ወብት እና ስርአት ለመዘርጋት “አጋጣሚ” ለመሆን ምን ያህል የማይታሰብ እንደሆነ ሳብራራ፣ እሱ ለተወሰነ ጊዜ ዝም አለ እና ከዚያም በጥሩ ሁኔታ “አገኘኸኝ” አለ። መጽሐፈ ሞርሞንን እንዲያነብ ጠየቅሁት። እሱም አነበዋለሁ አለ፣ ስለዚህ አንድ ቅጂ ላኩለት።

ከአመታት በኋላ፣ በናይጄሪያ ሌጎስ አውሮፕላን ማረፊያ ሳለሁ አዲስ ጓደኛ አገኘሁ። ፓስፖርቴን በሚመለከትበት ወቅት ተዋወቅን። ስለ ሃይማኖቱ ጠየቅሁት፣ እናም በእግዚአብሔር ላይ ጠንካራ እምነትን እንዳለው ገለጸ።። በዳግም የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ደስታ እና ንቁነት አካፍዬ፣ ከሚስዮናውያን የበለጠ መማር ይፈልግ እንደሆነ ጠየቅሁ። እርሱም እሺ አለ፣ ተማረ፣ እናም ተጠመቀ። ከአንድ ወይም ከሁለት ዓመት በኋላ የላይቤሪያ አየር ማረፊያ ውስጥ ሳልፍ አንድ ድምፅ ስሜን ሲጠራ ሰማሁ። ዞር አልኩ፣ እናም ያው ወጣት በትልቅ ፈገግታ ቀረበ። እኛ በደስታ ተቃቀፍን እና እሱ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንደነበረ እና ከሚስዮናዊያን ጋር በመሆን የሴት ጓደኛውን እንደሚያስተምር አሳወቀኝ።

አሁን፣ አምላክ የለሽ ጓደኛዬ መፅሐፈ ሞርሞንን አንብቦ ወይም ወደ ቤተክርስቲያኗ መቀላቀሉን አላውቅም። ሁለተኛው ጓደኛዬ ተቀላቅሏል። ለሁለቱም፣ የእኔ ኃላፊነት 2 —ዕድሌ—አንድ አይነት ነበር፦ የወንጌልን ብርሃን ከፍ በማድረግ—በመደበኛ፣ በተፈጥሮአዊ መንገድ ለእያንዳንዱም ለመውደድ፣ ለማካፈል እና ለመጋበዝ ነው። 3

ወንድሞች እና እህቶች፣ ወንጌሉን የማካፈል በረከቶች አጋጥመቅኛል፣ እነሱም አስደናቂ ነበሩ። እነዚህም ጥቂቶቹ ናቸው፦

ወንጌልን መካፈል ደስታን እና ተስፋን ያመጣሉ

አስተውሉ፣ ወደዚህች ምድር ከመምጣታችን በፊት እኛ የሰማያዊ ወላጆቻች ልጆች ሆነን እንደኖርን 4 እና ምድር የተፈጠረችበት አላማ፣ እያንዳንዱን ሰው አካል እንዲያገኝ፣ ልምድን እንዲያገኝ፣ እንዲማር እና እንዲያድግ እንዲሁም የእግዚአብሔር ሕይወት የሆነውን ዘላለማዊነትን ለመቀበል እንዲቻል እንደሆነ እናንተ እና እኔ እናውቃለን። 5 የሰማይ አባት በምድር ላይ እንደምንሰቃይ እና ኃጢአት እንደምንሠራ ያውቅ ነበር፣ ስለዚህ “ተወዳዳሪ የሌለውን ሕይወቱን” 6 እና ማለቂያ የሌለውን የኃጢያት ክፍያ መሥዋዕት 7 የሆነውን ልጁን ልኮ ይቅርታ፣ መፈወስ እና ሙሉ መሆንን አስችሎናል። 8

እነዚህን እውነቶች ማወቅ ሕይወት ለዋጭ ነው። አንድ ሰው የከበረውን የሕይወት ዓላማ ሲማር፣ ክርስቶስ እርሱን የተከተሉትን ይቅር እንደሚል እና እንደሚረዳ ሲረዳ፣ እና ከዚያም በኋላ ክርስቶስን ወደ ጥምቀት ውሃ ለመከተል ሲመርጥ፣ የሕይወት ውጪአዊ ሁኔታዎች ባይለወጡም፣ ሕይወት ለተሻለ ሁኔታ ይለወጣል።

በናይጄሪያ ኦኒሻ ውስጥ ያገኘኋት አንጸባራቂ እህት አንዴ እውነትን ከተማረች እና ከተጠመቀች በኋላ እንዳለችው፣ “ሁሉም ነገር ለእኔ ጥሩ ነው። ደስተኛ ነኝ፡፡ እኔ በሰማይ ነኝ።” 9 ወንጌልን ማካፈል በሰጪውም ሆነ በተቀባዩ ነፍስ ውስጥ ደስታን እና ተስፋን ይጭራል። በእውነት ወንጌልን በምታካፍሉበት ጊዜ “ደስታችሁ እንዴት ታላቅ ይሆናል” 10 ወንጌልን ማካፈል በደስታ ላይ ደስታ፣ በተስፋ ላይ ተስፋ ነው። 11

ወንጌልን መካልፈል የእግዚአብሔርን ሀይል ወደ ህይወታችን ያመጣል

በተጠመቅን ጊዜ እያንዳንዳችን ከእግዚአብሔር ጋር ዘለአለማዊ 12 ቃል ኪዳን ገባን፣ ይህም “እርሱን ለማገልገልና ትዕዛዛቱን ለመጠበቅ” 13 ነው፣ በዚህም “ሁል ጊዜ እና በሁሉም ነገር እና በሁሉም ቦታ”11፣ እንደ እርሱ ምስክሮች” መቆንም የሚያካትተው ነው። 14 ይህንን ቃል ኪዳን በመጠበቅ “በእርሱ ውስጥ ስንኖር”፣ ቅርንጫፍ ከወይን ተክል ምግብ እንደሚቀበል አይነት፣ ህያው የሚያደርገው፣ የሚደግፈው፣ እና የሚያጸዳው የአምላካዊነት ኃይል ከክርስቶስ ወደ ሕይወታችን ይፈስሳል። 15

ወንጌልን መካፈል ከፈተናዎች ይጠብቀናል

ጌታ እንዲህ ሲል ያዘናል፦

“ስለዚህ፣ ለዓለም ያበራ ዘንድ ብርሃናችሁን ከፍ አድርጉ። እነሆ፣ እኔ ሳደርግ የተመለከታችሁትም፣ እናንተ ከፍ የምታደርጉት ብርሃን ነኝ።

“ … ትዳስሱና ትመለከቱ ዘንድ ወደ እኔ እንድትመጡ አዝዣችኋለሁ፤ በዚሁም ሁኔታ ለዓለም አድርጉ፤ እናም ይህንን ትዕዛዝ የሚያፈርስ ቢኖር ወደ ፈተናው ለመግባት ለራሱ ፈቅዷል።” 16

የወንጌልን ብርሃን ላለመያዝ መምረጥ ለፈተና ተጋላጭ ወደምንሆንበት ወደ ጥላዎች ይወስደናል። በአስፈላጊነት፣ ተቃራኒውም እውነት ነው፤ የወንጌልን ብርሃን ለማንሳት መምረጥ ወደዚያ ብርሃን እና ከፈተናዎች ለሚከልለው እንድንቀርብ ያደርገናል። ዛሬ በጨለማው ዓለም ውስጥ ይህ እንዴት ያለ ታላቅ በረከት ነው!

ወንጌልን መካፈል ፈውስን ያመጣል

እህት ቲፋኒ ማይሎአን ስለ እምነቷ ጥያቄዎችን ጨምሮ በጣም ከባድ የግል ትግል ቢኖርባቸውም ሚስዮናውያንን እንዲደግፉ ግብዣውን ተቀበሉ። እርሷም በቅርብ እንደነገረችኝ፣ ሚንስዮኖችን መደገፍ እምነቷን እና የደህንነቷን ስሜት አድሷል። በራሷ ቃላት፣ “የሚስዮናዊነት ሥራ በጣም ፈዋሽ ነው”። 17

ደስታ ተስፋ ከእግዚአብሔር የመጣ ኃይልን መደገፍ። ከፈተና ጥበቃ። ፈውስ ይህ ሁሉ—እና ከዚያ በላይ (የኃጢአት ስርየትን ጨምሮ) 15 —ወንጌልን ስንካፈል ከሰማይ በነፍሳችን ላይ ይሰክናል።

አሁን፣ ወደ ታላቅ እድላችን በመዞር

ወንድሞች እና እህቶች፣ “ከሁሉም… ፓርቲዎች፣ [ኑፋቄዎች] እና ቤተ እምነቶች… መካከል የት እንደሚያገኙትም ባለማወቃቸው ምክንያት እውነትን እንዳያገኙ የተደረጉ ብዙዎችም በምድር ላይ አሉ፡፡” 19 በሁሉም የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የእኛን ብርሃን ከፍ አድርጎ መያዝ የሚያስፈልግበት ከዚህ ጊዜ የሚበልጥ የለም። እና እውነቱ የበለጠ ተደራሽ ሆኖ አያውቅም።

በቡዲስት ያደገው ጂሚ ቶን ሕይወታቸውን በዩቱብ ላይ ባካፈሉ ቤተሰብ ተደነቀ። እነሱ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት መሆናቸውን ሲያውቅ፣ እሱ ራሱ በድህረ ገጽ ላይ ወንጌልን አጠና፣ መጽሐፈ ሞርሞንን በመተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ላይ አነበበ፣ እና በኮሌጅ ውስጥ ከሚሲዮናዊያን ጋር ከተገናኘ በኋላ ተጠመቀ። 20 ሽማግሌ ቶን አሁን የሙሉ ጊዜ ሚስዮናዊ ነው።

ነቢያችንን በመጥቀስ፣ እርሱ እና ሌሎች ሚስዮናውያን በዓለም ዙሪያ የጌታ ሻለቃ ናቸው። 21 እነዚህ ሚስዮናውያን የዓለምን መንገድ ተቃውመዋል፤ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጄን ዚ ትውልዶች ከእግዚአብሔር መንገድ እየራቁ ሲሆን፣ 22 የኛ የስትሪፕሊንግ ተዋጊዎች 23 ወንድ እና ሴት ሚስዮናውያን ግን ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር እየቀየሩ ነው። እና ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ የቤተክርስቲያኗ አባላት ሚስዮናውያን ወንጌልን በማካፈል፣ ብዙ ወዳጆች ወደ ክርስቶስ እና ወደ ቤተክርስቲያኗ እንዲመጡ በመርዳት ላይ ናቸው።

በላይቤሪያ ያሉ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን በሀገራቸው ውስጥ የሚያገለግሉ የሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያን ባልነበሩ 10 ወራት ውስጥ 507 ጓደኞቻቸውን ወደ ጥምቀት ውሃ እንዲገቡ ረድተዋል። በዚያ ካሉት አስደናቂ የካስማ ፕሬዘዳንቶቻችን አንዱ የሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያን ተመልሰው መምጣታቸውን ሲሰማ፣ “ኦ መልካም፣ አሁን በስራችን ሊረዱን ይችላሉ” አለ።

እርሱ ትክክል ነው፦ የእስራኤል መሰብሰብ የሆነው በምድር ላይ ትልቁ ምክንያት 24 የቃል ኪዳናችን ሃላፊነት ነው። እና ይህ የኛ ጊዜ ነው! የዛሬው ግብዣዬ ቀላል ነው ወንጌልን አካፍሉ። እራሳችሁን ሁኑ እና ብርሃንን ከፍ አድርጉ። ለሰማይ እርዳታ ጸልዩ እና መንፈሳዊ ምሪቶችን ተከተሉ። ሕይወታችሁን በመደበኛ እና በተፈጥሮአዊ ሁኔታ አካፍሉ፣ ሌላ ሰው እንዲመጣ እና እንዲያይ፣ እንዲመጣ እና እንዲረዳ፣ እና እንዲመጣ እና ከኛ ጋር እንዲሆን ጋብዙ። 25 እና ከዚያም እናንተ እና የምትወዷቸው ቃል የተገቡትን በረከቶች በመቀበል ተደሰቱ።

በክርስቶስ ይህ የምሥራች ለድሆች እንደሚሰበክ አውቃለሁ፤ በክርስቶስ ልባቸው የተሰበረ ይጠገናል። በክርስቶስ ለተማረኩትም ነጻነት ይታወጃል፤ እና በክርስቶስ፣ በክርስቶስ ብቻ፣ ለሚያለቅሱትም ከአመድ ፋንታ አክሊልን ሰጥቷቸዋል። 26 ስለዚህም ምክንያት እነዚህን ነገሮች ለማሳወቅ በጣም አስፈላጊ ነው! 27

ኢየሱስ ክርስቶስ የእምነታችን ጸሐፊ እና ፈጻሚ መሆኑን እመሰክራለሁ። 28 የወንጌልን ብርሃን በመያዝ የእምነታችንን ልምምድ — ምንም እንኳን ፍጹምነት የጎደለን ቢሆንም—ያጠናቅቃል። እርሱ የተአምራት አምላክ ነውና በሕይወታችን እና በሚሰበስበው ሁሉ ሕይወት ውስጥ ተአምራትን ያደርጋል። 29 በሚደንቀው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

አትም