ታሪካችሁን ለመጻፍ ክርስቶስን ይጋብዙ
ምሳሌአችሁ የሆነውን አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ በመከተል፣ ትረካችሁ የእምነት ይሁን።
ለማሰላሰል የታሰቡ በርካታ ጥያቄዎችን በማቅረብ እጀምራለሁ፦
-
ለሕይወታችሁ ምን ዓይነት የግል ትረካ ትፈጽማላችሁሉ?
-
በታሪካችሁ ውስጥ የገለጻችሁት መንገድ ቀጥተኛ ነውን?
-
ታሪክካችሁ በጀመረበት ያበቃልን፣ እንዲሁም በሰማይ ቤታችሁ ውስጥ?
-
በታሪካችሁ ውስጥ ምሳሌአዊ የሆነ አለ—እና ያም አዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውን?
አዳኝ “የእምነታችንንም ራስ እና ፈጻሚ” መሆኑን እመሰክራለሁ። 1 የታሪካችሁ ደራሲ እና ፈፃሚ እንዲሆን ትጋብዙታላችሁን?
መጀመሪያውን ከመጨረሻው ያውቃል። እርሱ የሰማይና የምድር ፈጣሪ ነበር። ወደ ቤታችን፣ ወደ እርሱ እና ወደ ሰማያዊ አባታችን እንድንመለስ ይፈልጋል። እርሱ ሁሉንም ነገር በእኛ ላይ አውሏል እናም ውጤታማ እንድንሆን ይፈልጋል።
ታሪኮቻችንን ወደ እርሱ እንዳንሰጥ የሚከለክለን ምን ይመስልላችኋል?
ምናልባት ይህ ምሳሌ እራሳችሁን ለመገምገም ይረዳችኋል።
ውጤታማ የፍርድ ጠበቃ በጥያቄ ላይ መልሱን የማያውቀውን አንድ ጥያቄ ለምስክር እምብዛም መጠየቅ እንደሌለበት ያውቃል። እንደዚህ ዓይነቱን ጥያቄ መጠየቅ ምስክሩ ለእናንተ—እና ለዳኛው—የማታውቁትን ነገር እንዲነግሩ መጋበዝ ነው። እናንተ የሚገርማችሁን እና ለጉዳያችሁ ካዘጋጁት ትረካ ጋር የሚቃረን መልስ ልታገኙ ትችላላችሁ።
ምንም እንኳን መልሱን የማያውቁት ጥያቄን መጠየቅ ለጠበቃ በአጠቃላይ ጥበብ የጎደለው ቢሆንም፣ ለእኛ ተቃራኒ ነው። በምህረት አዳኛችን ስም አፍቃሪ የሆነውን የሰማያዊ አባታችንን ጥያቄዎች መጠየቅ እንችላለን፣ እናም ለጥያቄዎቻችን መልስ የሚሰጠን ምስክር፣ ሁል ጊዜ ስለ እውነት የሚመሰክረው፣ መንፈስ ቅዱስ ነው። 2 መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ፍጹም በሆነ አንድነት ስለሚሠራ፣ የመንፈስ ቅዱስ መገለጦች አስተማማኝ መሆናቸውን እናውቃለን። እውነት፣ በመንፈስ ቅዱስ የተገለጠልንን ይህን ዓይነት ሰማያዊ እርዳታ ለመጠየቅ አንዳንድ ጊዜ ለምን እንቃወማለን? ምስክሩ ወዳጃዊ ብቻ ሳይሆን ሁል ጊዜም እውነትን የሚናገር በሚሆንበት ጊዜ፣ መልሱን የማናውቀውን ጥያቄ ከመጠየቅ ወደኋላ የምንለው ለምንድን ነው?
ምናልባት እኛ የምናገኘውን መልስ ለመቀበል እምነት ስለሌለን ሊሆን ይችላል። ምናልባት በእኛ ውስጥ ያለው ተፈጥሯዊ ወንድ ወይም ሴት ነገሮችን ሙሉ በሙሉ ወደ ጌታ ለማዞር እና በእርሱ ሙሉ ለሙሉመታመን ስለሚቃወም ሊሆን ይችላል። ምናልባት ለዚያ ነው በሚመቸን በመጽሐፉ ደራሲ ያልተስተካከለ ታሪካችን፣ እንዲሁም እኛ ለራሳችን በጻፍነው ትረካ ለመቀጠል የምንፈልገው። እኛ ለራሳችን በምንጽፈው ታሪክ ውስጥ በትክክል የማይመጥን ጥያቄ መጠየቅ እና መልስ ማግኘት አንፈልግም።
እውነቱን ለመናገር፣ ጥቂቶቻችን ምናልባት የሚያጣሩንን ፈተናዎች በታሪኮቻችን ውስጥ እንጽፍ ይሆናል። ነገር ግን ተዋናይ ትግሉን ሲያሸንፍ ያነበብነውን የከበረ መደምደሚያ አንወደውምን? ሙከራዎች የእኛ ተወዳጅ ታሪኮች አስገዳጅ፣ ጊዜ የማይሽራቸው፣ እምነትን የሚያስተዋውቁ እና ለመናገር ብቁ የሚያደርጉት የእቅዱ አካላት ናቸው። በ የእኛ ታሪኮች ውስጥ የተፃፉት ውብ ትግሎች ወደ አዳኝ እንድንቀርበው የሚያደርገን እና እሱን እንድንመስል የሚያደርገን ነው።
ዳዊት ጎልያድን እንዲያሸንፍ፣ ብላቴናው ከግዙፉ ሰው ጋር መወዳደር ነበረበት። ለዳዊት ምቹ የሆነ ትረካ በጎችን ወደ መጠበቅ መመለስ ነበር። ግን ይልቁንም ጠቦቶችን ከአንበሳ እና ከድብ በማዳን ልምዱ ላይ አሰላስሏል። እናም በእነዚያ የጀግንነት ድርጊቶች ላይ በመገንባት፣ እግዚአብሔር ታሪኩን እንዲጽፍ እምነቱን እና ድፍረቱን ሰበሰበ፣ እንዲህም አወጀ፣ “ከአንበሳ መዳፍ እና ከድብ ያዳነኝ ጌታ እርሱ ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” 3 እግዚአብሔር እንዲያሸንፍ በመሻት፣ ለመንፈስ ቅዱስ ጆሮ፣ እና አዳኙ የታሪኩ ጸሐፊ እና ፍጻሜ እንዲሆን ፈቃደኛ በመሆን ብላቴናው ዳዊት ጎልያድን አሸንፎ ሕዝቡን አዳነ።
የነፃ ምርጫ የላቀ መርህ ቢኖር በእርግጥ የእኛን የግል ታሪኮች እንድንጽፍ ያስችለናል—ዳዊት በጎቹን ለማሰማራት ወደ ቤቱ መመለስ ይችል ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን እንደ መለኮታዊ መሣሪያዎች፣ በእጁ የተሳለ እርሳሶች፣ በመጠቀም ድንቅ ሥራን ለመጻፍ ዝግጁ ነው! እርሱን የምፈቅድለት እምነት ቢኖረኝ፣ ታሪኬን እንዲጽፍ ከፈቀደልኝ፣ በእጁ ውስጥ እንደ መሣሪያ፣ እኔን እንደ እርቃን እርሳስ፣ በምህረት ለመጠቀም ፈቃደኛ ነው።
አስቴር እግዚአብሔር እንዲያሸንፍ የሚደረግበት ሌላ ውብ ምሳሌ ናት። ራሷን ከመጠበቅ ጥንቃቄ የተሞላበት ትረካ ጋር ከመጣበቅ ይልቅ፣ ራሷን ሙሉ በሙሉ ለጌታ አሳልፋ በመስጠት እምነትን በተግባር አሳይታለች። ሐማ በፋርስ የነበሩትን አይሁዶች ሁሉ ለማጥፋት ያሴር ነበር። የአስቴር ዘመድ መርዶክዮስ ሴራውን ተገንዝቦ በሕዝቧ ስም ከንጉስ ጋር እንድታነጋግር ጽፎላት ነበር። እርሷም ሳትጠራ ወደ ንጉሡ የሚቀርብ ሰው ለሞት እንደሚዳረግ ትነግረዋለች። ነገር ግን በታላቅ የእምነት ተግባር መርዶክዮስን አይሁዶችን ሰብስቦ እንዲጾምላት ጠየቀችው። እርሷም “እኔና ገረዶቼም እንዲሁ እንጾማለን” አለች፣ “እናም እንደ ሕጉ ወደሌለው ወደ ንጉስ እገባለሁ፤ ብጠፋም እጠፋለሁ።” 4
አስቴር፣ በሟችነት መነጽር፣ መጨረሻው አሳዛኝ ሊሆን ቢችልም፣ አዳኝ ታሪኳን እንዲጽፍላት ፈቃደኛ ነበረች። በበረከትም፣ ንጉሱ አስቴርን ተቀበለ፣ በፋርስ የነበሩ አይሁዶችም ዳኑ።
በእርግጥ የአስቴር የድፍረት ደረጃ አይነት ከእኛ ብዙም ጊዜ አይጠየቅም። ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲያሸንፍ፣ የታሪኮቻችን ጸሐፊ እና ፈጻሚ እንዲሆን መፍቀድ፣ ትእዛዛቱን እና የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች እንድንጠብቅ ይጠይቃል። በመንፈስ ቅዱስ በኩል መገለጥን እንድናገኝ የግንኙነት መስመሩን የሚከፍትልን፣ ትእዛዛታችን እና የቃል ኪዳኑ መጠበቅ ነው። እናም የእኛን ታሪኮች ከእኛ ጋር ሲፅፍ የመምህሩን እጅ የምንመለከተው በመንፈስ መገለጫዎች በኩል ነው።
በሚያዝያ 2021 (እ.አ.አ)፣ ነቢያችን ፕሬዘደንት ረስል ኤም ኔልሰን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የበለጠ እምነት ቢኖረን ምን ማድረግ እንደምንችል እንድናስብ ጠየቁን። በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለን የበለጠ እምነት፣ መልሱን የማናውቀውን ጥያቄ መጠየቅ እንችላለን—እውነትን በሚመሰክር በመንፈስ ቅዱስ በኩል መልስ እንዲልክልን የሰማይ አባታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠየቅ እንችላለን። የበለጠ እምነት ቢኖረን፣ ጥያቄውን እንጠይቃለን እና ከዚያ እኛ የምንሰጠው መልስ ከሚመቸን ትረካ ጋር ባይስማማም እንኳን፣ ለመቀበል ፈቃደኞች እንሆናለን። እናም በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን በተግባር የሚመጣው የተስፋው በረከትምን፣ እንደ ጸሐፊያችን እና እንደ ፈጻሚያችን በእርሱ ላይ ያለንን የእምነት መጨመር ነው። ፕሬዘደንት ኔልሰን እንዳወጁት፣ “ተጨማሪ እምነት የሚያስፈልገውን ነገር በማድረግ እምነትን በጭማሬ ተቀበሉ”። 5
ስለዚህ፣ ልጅ አልባ የሆኑት ባለትዳሮች፣ ምንም እንኳን ለራሳቸው የጻፉት ትረካ ተአምራዊ ልጅ መወለድን ያካተተ ቢሆንም፣ በእምነት ልጆችን በጉዲፈቻ ለመቀበል ፈቃደኞች መሆናቸውን በእምነት ሊጠይቁ ይችላሉ።
ምንም እንኳን ለራሳቸው የጻፉት ትረካ በስራ ተጨማሪ ጊዜን ማሳለፍ ያካተተ ቢሆንም፣ አንድ ሸምገል ያሉ ጥንዶች ባተልእኮን ለማገልገል እና ለመሄድ ፈቃደኛ የሚሆኑበት ጊዜ እንደሆነ ይጠይቁም ይሆናል። ወይም ምናልባት መልሱ “ገና” ሊሆን ይችላል፣ እና ለምን ትንሽ ረዘም ላለ ጊዜ በቤት ውስጥ ለምን እንደተፈለጉ በታሪካቸው የኋለኛ ምዕራፎች ውስጥ ይማራሉ።
በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኝ ወጣት ወንድ ወይም ወጣት ሴት ስፖርት ወይም ትምህርት ወይም ሙዚቃ ሙያ ለመከታተል በጣም ዋጋ ያለው መሆኑን ወይም አለመሆኑን በእምነት ለመጠየቅ እና ፍጹም ምስክር የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ለመከተል ፈቃደኛ መሆን ይችላል ወይም ትችላለች።
አዳኝ የታሪኮቻችን ደራሲ እና ፈፃሚ እንዲሆን ለምን እንፈልጋለን? አቅማችንን በፍፁም ስለሚያውቅ፣ እኛን ወዳላሰብናቸው ቦታዎች ይወስደናል። እርሱም ዳዊት ወይም አስቴር ሊያደርገን ይችላል። እርሱ ያስፋፋናል እና እንደ እርሱ እንድንሆን ያጠራናል። በበለጠ እምነት ስንሠራ የምናገኛቸው ነገሮች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እምነት ይጨምራሉ።
ወንድሞች እና እህቶች፣ ልክ ከአንድ ዓመት በፊት ውድ ነቢያችን እንዲህ ጠየቁ፣ “እግዚአብሔር በህይወታችሁ እንዲያሸንፍ እናንተ ፍቃደኞች ናችሁን? … እርሱ እንድታደርጉ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ከሌላው ግብ ሁሉ በፊት ለማስቀደም ፈቃደኞች ናችሁን?” 6 በእነዚያ ትንቢታዊ ጥያቄዎች ላይ በትህትና እጨምራለሁ፣ “እግዚአብሔር የታሪካችሁ ጸሐፊ እና ፈጻሚ እንዲሆን ትፈቅዳላችሁን?
በራዕይ ውስጥ እንደ ሥራችን በእግዚአብሔር ፊት እንደምንቆም እና ከሕይወት መጻሕፍት እንደምንፈርድ እንማራለን። 7
በሕይወታችን መጽሐፍ እንፈርዳለን። ለራሳችን ምቹ የሆነ ትረካ ለመፃፍ መምረጥ እንችላለን። ወይም እኛ የምንፈልገው ሚና ከሌሎች ምኞቶች ይልቅ ቅድሚያ እንዲሰጠው በማድረግ ዋና ጸሐፊ እና ፈፃሚ የእኛን ታሪክ ከእኛ ጋር እንዲጽፍ መፍቀድ እንችላለን።
ክርስቶስ የታሪካችሁ ደራሲ እና ፈፃሚ ይሁን!
መንፈስ ቅዱስ ምስክራችሁ ይሁን!
በእግዚአብሔር ፊት ለመኖር ወደ ሰማያዊው ቤታችሁ በሚመራችሁ ጎዳና ላይ የሚሄዱበት መንገድ ቀጥተኛ የሆነበትን ታሪክ ፃፉ።
የእያንዳንዱ ጥሩ ታሪክ አካል የሆነው ፈተና እና መከራ ወደ እሱ የምትቀርቡበት እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ የምትመስሉበት መንገድ ይሁኑ።
ሰማያት ክፍት መሆናቸውን የምታውቁበትን ታሪክ ተናገሩ። እግዚአብሔርን ማወቅ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ፈቃዱን ለእርናንተ ለማሳወቅ ፈቃደኛ ስለሆነ መልሱን የማታውቁትን ጥያቄዎች ጠይቁ።
ምሳሌአችሁ የሆነውን አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ በመከተል፣ ትረካችሁ የእምነት ይሁን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።