ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 22–28 )፡ “በእግዚአብሄርና በሁሉም ሰዎች ፍቅር [መሞላት]” ሞዛያ 1–3


“ሚያዝያ 22–28 (እ.አ.አ)፡ “በእግዚአብሄርና በሁሉም ሰዎች ፍቅር [መሞላት]” ሞዛያ 1-3 ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስትያና፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2024 (እ.አ.አ))

“ሚያዝያ 22-28 ። ሞዛያ 1-3 ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስትያና፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ)

ንጉስ ቢንያም ህዝቦቹን እያስተማረ

የንጉሥ ቢንያም ትምህርቶችን መቀበል በማሪያ አሌሃንድራ ጊል

ሚያዝያ 22–28 ፡ “በእግዚአብሄርና በሁሉም ሰዎች ፍቅር [መሞላት]”

ሞዛያ 1–3

ንጉሥ የሚለውን ቃል ስትሰሙ አክሊሎችን፣ አገልጋዮችን እና ዙፋኖችን ልታስቡ ትችላላችሁ። በሞዛያ 1–3 ውስጥ፣ ስለ ሌላ ዓይነት ንጉስ ታነባላችሁ። ንጉስ ቢንያም በህዝቡ ድካም ከመኖር ይልቅ “በእጁ [ሰርቷል]” (ሞዛያ 2፡14)። ሌሎች እንዲያገለግሉት ከማድረግ ይልቅ፣ ህዝቡን “ጌታ [ለእርሱ] በሰጠው ኃይል፣ አእምሮ እና ብርታት አገልግሏል]” (ሞዛያ 2፡11)። ይህ ንጉሥ ሕዝቡ እንዲሰግዱለት አልፈለገም፤ ይልቁንም የሰማይ ንጉሣቸውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያመልኩ አስተማራቸው። ንጉሥ ቢንያም “ሁሉንም የሚገዛው ጌታ” (ሞዛያ 3፡5)፣ “ከሰማይ [የመጣው]” “በስሙ በማመን ደህንነት ለሰው ልጆች ይመጣ ዘንድ” እንደሆነ ተረድቷል (ሞዛያ 3፡5፣ 9)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ሞዛያ 1፥1-7

“[ቅዱሳን መጻህፍትን] በትጋት መመርመር”

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ፣ ቅዱሳት መጻህፍት የንጉሥ ቢንያምን ሕዝብ እንዴት እንደባረኩ ተመልከቱ። ቅዱሳት መጻህፍት በመኖራቸው ህይወታችሁ እንዴት የተሻለ ሆነ?

የሴሚነሪ መለያ

ሞዛያ 2:10–26

እኔ ሌሎችን ሳገለግል ጌታንም እያገለገልኩ ነው።

ንጉሥ ቢንያም በሙሉ “[ኃይሉ፣ አእምሮው እና ብርታቱ]” ለምን እንዳገለገለ ብትጠይቁት ምን የሚል ይመስላችኋል? (ሞዛያ 2:11) ሞዛያ 2፡10–26 ስታነቡ ይህን አስቡ። ንጉስ ቢንያም ሌሎችን ይበልጥ ትርጉም ባለው መንገድ እንድታገለግሉ የሚያነሳሳችሁን ምን አስተማረ? ለምሳሌ ሌሎች ሰዎችን ስታገለግሉ እግዚአብሄርንም እያገለገላችሁ እንደሆነ ማወቅ ለእናንተ ምን ማለት ነው? (ሞዛያ 2፡17 ይመልከቱ)። በዚህ ሳምንት የሆነን ሰው እንዴት ማገልገል እንደምትችሉ መነሳሳትን ፈልጉ።

ሌሎችን ማገልገል እንዳለብን እያወቅንም አንዳንድ ጊዜ ፈተናዎች ያጋጥሙናል። ሌላው ሞዛያ 2፡10–26ን የምታጠኑበት መንገድ፣ ንጉስ ቢንያም ያስተማራቸውን ከማገልገል የሚከለክሏችሁን ተግዳሮቶችን እንድታሸንፉ የሚረዱ እውነቶች በመዘርዘር ነው። ንጉሥ ቢንያም ያስተማረው እውነት መሆኑን የሚያሳዩ ምን ተሞክሮዎች አሏችሁ?

ፕሬዘደንት ጆይ ዲ. ጆንስ ሌሎችን፣ ለማገልገል ያላትን አመለካከት የለወጠ ኃይለኛ ተሞክሮ አካፍለዋል። ስለእዚያ በ“ለእሱ[For Him]” (ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 50–52) ላይ አንብቡ እና ሌሎችን ለማገልገል ስላላችሁ እድሎች አስቡ። እንዲያውም ጥቂቶቹን መዘርዘር እና የፕሬዘዳንት ጆንስ መልእክት ከሞዛያ 2፡17 ጋር እነዚህን እድሎች በምትጠቀሙበት መንገድ ላይ እንዴት ተጽእኖ እንደሚያሳድር ማሰብ ትችላላችሁ። እንደ “መንገደኛ ድሃ የሀዘን ሰው [A Poor Wayfaring Man of Grief]” (መዝሙሮች፣ ቁ. 29) ወይም እንደ “የድሮ ጫማ ሰሪ” (ወንጌል ቤተ-መጽሐፍት) ያለ ቪዲዮ ተጨማሪ ግንዛቤዎችን እንድታገኙ ሊረዳ ይችላል።

በተጨማሪም ማቴዎስ 25:40፤ ““የፌዝ ሙሬይ ታሪክ፡ መከራን በአገልግሎት ማሸነፍ [Faith Murray’s Story: Overcoming Adversity through Service]፣” “ንጉሥ ቢንያም አምላክን ስለማገልገል ያስተምራል [King Benjamin Teaches about Serving God]” (ቪዲዮዎች)፣ ፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት፤ JustServe.org; የወንጌል ርዕሰ ፣ “አገልግሎት የወንጌል ቤተ መጻሕፍት ላይ ይመልከቱ።

ሁለት ሴቶች ሲተቃቀፉ

እኔ ሌሎችን ሳገለግል ጌታንም እያገለገልኩ ነው።

ሞዛያ 2፡38–41

ደስታ የሚመጣው የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በመጠበቅ ነው።

እግዚአብሔርን በመታዘዝ የሚገኘውን ደስታ እንዴት ትገልጻላችሁ? በሞዛያ 2፡38–41 ውስጥ ለምን ትእዛዛቱን እንደምትጠብቁ ለማስረዳት የሚረዱ ሀረጎች አሉ?

ሞዛያ 3፥1-20

በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ቅዱስ መሆን እችላለሁ።

ንጉስ ቢንያም እንደሌሎች ነቢያት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቡ “[የኃጢአታቸውን ስርየት እንዲያገኙ] እና በታላቅ ደስታ ሃሴት” (ሞዛያ 3:13) እንደሚያደርጉ መስክሯል። በሞዛያ 3፡1–20 ላይ የንጉሥ ቢንያምን የአዳኙን ምስክርነት ስታነቡ ልታሰላስሏቸው የሚገቡ አንዳንድ ጥያቄዎች እዚህ አሉ፡

  • ከእነዚህ ጥቅሶች ስለ አዳኙ እና ስለ ተልእኮው ምን እማራለሁ?

  • ቅዱስ መሆን ምን ማለት እንደሆነ ከሞዛያ 3፡18–19 ምን እማራለሁ?

  • ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአትን እንዳሸንፍ፣ ተፈጥሮዬን እንድቀይር እና ቅዱስ እንድሆን የረዳኝ እንዴት ነው?

ሞዛያ 3፡5–21

“ሁሉንም የሚገዛ ጌታ… ከሰማይ… የሚመጣበት ጊዜ ይመጣል”።

የኤሌክትሪክ ሃይል ምን መስራት ያስችላችኋል? ያለ ኤሌክትሪክ ሕይወት እንዴት የተለየ ይሆናል? እነዚህ ጥያቄዎች አዳኙ ወደ ህይወታችሁ ሊያመጣ የሚችለውን የበለጠውን ሃይል እንድታስቡ ሊረዱ ይችላሉ።

ለንጉሥ ቢንያም የተገለጠው መልአክ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን “ሁሉን የሚገዛ” ሲል ጠርቶታል፣ ይህም ማዕረግ ሁሉን ቻይ ማለት ነው። አዳኙ ያን ኃይል እንዴት እንደሚጠቀም ከሞዛያ 3፡5–21 ምን ተማራችሁ? በህይወታችሁ እና በአካባቢያችሁ ባሉ ሰዎች ህይወት ውስጥ የአዳኙን ሀይል አይታችኋል? ኃይሉ ምን እንድትሰሩ እና እንድትሆኑ ያስችላችኋል? ያለ ኤሌክትሪክ ሕይወት እንዴት የተለየ ይሆናል?

ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ወር የሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶችን እትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ሞዛያ 2:11–18

እኔ ሌሎችን ሳገለግል ጌታን እያገለገልኩ ነው።

  • የዚህ ሳምንት የተግባር ገጽ ልጆቻችሁ ሊሰሩ የሚችሉት ቀላል አክሊል አለው። ሞዛያ 2–3 ላይ የሚገኙትን ንጉስ ቢንያም ለህዝቡ ያስተማረውን አንዳንድ ነገሮችን ስታካፍሉ፣ ተራ በተራ ወንበር ወይም በርጩማ ላይ ቆመው ንጉስ ቢንያምን በመምሰል መተወን ሊፈልጉ ይችላሉ። እንዲሁም የንጉሥ ቢንያምን ትምህርቶች አጠቃላይ እይታ ለመስጠት “ምዕራፍ 12፡ ንጉሥ ቢንያም”ን (የሞርሞን ታሪኮች፣ 32–35) ማካፈል ትችላላችሁ።

  • ሞዛያ 2፡17 ልጆቻችሁ እንዲማሩ ጥሩ ጥቅስ ሊሆን ይችላል። በአንድ ጊዜ ጥቂት ቃላትን እንዲደግሙ ልትረዷቸው ትችላላችሁ። ወይም ጥቅሱን በመጻፍና ብዙ ቁልፍ ቃላቶችን በመሰረዝ ከዚያም ልጆች የጎደሉትን ቃላት እንዲፈልጉ ጠይቁ። ከዚያም እግዚአብሄር አንዳችን ሌላችንን እንድናገለግል የሚፈልገው ለምን እንደሆነ ከልጆቻችሁ ጋር መነጋገር ትችላላችሁ።

  • ንጉሥ ቢንያም ሌሎችን ለማገልገል ምን እንዳደረገ ለማወቅ ልጆቻችሁ ሞዛያ 2፡11–18 እንዲያስሱ መርዳት ትችላላችሁ። ከዚያም ልጆቻችሁ የቤተሰብ አባላትን ማገልገል የሚችሉበትን አንዳንድ መንገዶች በቁራጭ ወረቀት ላይ ሊጽፉ ይችላሉ። ወረቀቶቹን እንደ ቦርሳ ወይም ማሰሮ አይነት ነገር ውስጥ አስቀምጡ፤ ከዚያም ልጆቻችሁ በየቀኑ አንዱን መርጠው በማንሳት ያንን አገልግሎት ለአንድ ሰው እንዲያደርጉ አድርጉ።

ልጆች ከድግግሞሽ ይጠቀማሉ። በተለይ ከትንንሽ ልጆች ጋር ብዙ ጊዜ ለመደጋገም አትፍሩ። ድግግሞሽ ልጆች የተማሩትን እንዲያስታውሱ ይረዳቸዋል።

ልጆች ቁራጭ ጨርቅ እያጠፉ

ሌሎችን በማገልገል እግዚአብሔርን ማገልገል እንደምንችል ንጉሥ ቢንያም አስተምሯል።

ሞዛያ 2:19–25

በረከቶቼ ሁሉ ከሰማይ አባት ይመጣሉ።

  • ንጉሥ ቢንያም ለሕዝቡ ያቀረበው አገልግሎት ለእግዚአብሔር ካለው ጥልቅ ምስጋና የተነሳ ነበር። በልጆቻችሁ ውስጥ ተመሳሳይ ስሜቶችን እንዴት ማነሳሳት ትችላላችሁ? ሞዛያ 2፡21ን አብራችሁ አንብባችሁ የሰማይ አባት የሰጠውን በረከቶች ዝርዝር ማውጣት መጀመር ትችላላችሁ። ከዚያ ምናልባት ልጆቹ የሚያስቧቸውን ሌሎች በረከቶች ወደ ዝርዝሩ ማከል ይችላሉ።

  • ልጆቻችሁ የሰማይ አባትን በረከቶች እንዲያውቁ ለማገዝ ሊጫወቱ የሚችሉት ጨዋታ እነሆ። ልጆች ስለ ምስጋና መዝሙር ሲዘምሩ ወይም ሲያዳምጡ የአዳኙን ምስል ሊቀባበሉ ይችላሉ (በ የልጆች መዝሙር መጽሐፍ የርእሶች ማውጫ ውስጥ ያለውን “ምስጋና” ይመልከቱ)። መዘመርን ወይም ሙዚቃውን በየጊዜው በማቆም ምስሉን የያዘ ሁሉ አመስጋኝ ስለሆነበት በረከት እንዲናገር ጋብዙ። በሞዛያ 2፡22–24 መሠረት፣ ለበረከቶቻችን አመስጋኞች መሆናችንን እንዴት ማሳየት እንችላለን?

ሞዛያ 5–10, 19

ኢየሱስ ክርስቶስ ይበልጥ እርሱን እንድመስል ይረዳኛል።

  • አንድ መልአክ ለንጉሥ ቢንያም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትና አገልግሎት ጠቃሚ እውነቶችን ነገረ። ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ በሞዛያ 3፡5–10 ውስጥ የተጠቀሱትን አንዳንድ ክስተቶች ምስሎችን ልትፈልጉ ትችላላችሁ (ለምሳሌ የወንጌል ጥበብ መጽሐፍ ቁጥር 30414257፣ 59 ይመልከቱ)። ሞዛያ 3፡5–10ን ስታነቡ፣ ልጆቻችሁ ከምስሎች መካከል በአንዱ ላይ ከሚታየው ውስጥ የሆነ ነገር ሲሰሙ እጃቸውን ማንሳት ይችላሉ።

  • ልጆቻችሁን የምግብ አዘገጃጀት መመሪያ ተጠቅማችሁ ምግብ በማዘጋጀት ረድታችሁ ታውቃላችሁ? ምናልባት ስለዚያ ተሞክሮ በመናገር እና ሞዛያ 3፡19ን በመጠቀም ኢየሱስ ክርስቶስን መምሰል የምንችልበትን “አዘገጃጀት መመሪያ” ማውጣት ትችላላችሁ። ኢየሱስ እርሱን እንድንመስል የሚረዳን እንዴት ነው?

ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

ንጉሥ ቢንያም ለሕዝቡ እየሰበከ

ንጉስ ቢኒያም ንግግር በጄረሚ ዊንቦርግ