ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 29–ግንቦት 5 ፡ “ታላቅ ለውጥ” ሞዛያ 4–6


“ሚያዝያ 29–ግንቦት 5 ፡ ‘ታላቅ ለውጥ’ ሞዛያ 4–6፡ “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“ሚያዝያ 29–ግንቦት 5 ሞዛያ 4–6፡ “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

ምስል
ንጉስ ቢንያም ህዝቦቹን እያስተማረ

እግዚአብሄርን ማገልገል፣ በዋልተር ሬን

ሚያዝያ 29–ግንቦት 5 ፡ “ታላቅ ለውጥ”

ሞዛያ 4–6

አንድ ሰው ሲናገር ሰምታችሁ ህይወታችሁን ለመለወጥ መነሳሳት ተሰምቷችሁ ያውቃል? ምናልባት እናንተ በሰማችሁት ነገር ምክንያት፣ በትንሽ— ወይም በጣም በተለየ መልኩ ለመኖር ወስናችሁ ይሆናል። የንጉሥ ቢንያም ስብከት እንደዚህ አይነት ስብከት ነበር፣ ያስተማረው እውነት በሰሙት ሰዎች ላይ እንዲህ አይነት ተጽእኖ ነበረው። ንጉስ ቢንያም መልአኩ “የክርስቶስ የደም ክፍያ”(ሞዛያ 4፡2) አስደናቂ በረከቶችን እንደሚያስችል ያስተማረውን ለህዝቡ አካፍሏል። በመልእክቱ ምክንያት፣ ለራሳቸው ያላቸውን አመለካከት ቀየሩ (ሞዛያ 4፡2 ይመልከቱ)፣ መንፈስ ፍላጎታቸውን ለወጠ (ሞዛያ 5፡2 ይመልከቱ)፣ ሁልጊዜም ፈቃዱን እንደሚያደርጉ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ገቡ (ሞዛያ 5፡5 ይመልከቱ)። የንጉሥ ቢንያም ቃላት ሕዝቡን የነካው በዚህ መንገድ ነበር። እናንተ ላይ እንዴት ተጽዕኖ ያሳድራሉ?

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር ሀሳቦች

ሞዛያ 4

በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የኃጢአቴን ስርየት መቀበል እና ማቆየት እችላለሁ።

አንዳንድ ጊዜ፣ ለኃጢያታችሁ ስርየት እንዳገኛችሁ ተሰምቷችሁ እንኳን ስሜቱን ለመጠበቅ እና በጽድቅ መንገድ ላይ ለመቆየት ልትቸገሩ ትችላላችሁ። ንጉስ ቢንያም ህዝቡን እንዴት የኃጢአት ስርየት መቀበል እና ማቆየት እንዳለባቸው አስተምሯል። ሞዛያ ምዕራፍ 4ን ስታጠኑ፣ እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ አስቡ፡-

ቁጥር 1-8እግዚአብሔር ለኃጢአታችሁ ስርየት የሚያደርግባቸውን መስፈርቶች ምንድን ናቸው? በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ንስሐ እንድትገቡ የሚያነሳሳ ምን ተማራችሁ? ንስሐ እንደገባችሁ እንዴት ማወቅ ትችላላችሁ?

ቁጥር 11-16በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት፣ በቁጥር 11 ላይ የተገለጹትን ነገሮች ብናደርግ በሕይወታችን ውስጥ ምን ይሆናል? እናንተ ወይም የምትወዱት ሰው እነዚህ ለውጦች እንዴት አጋጠሟቸው? እነዚህን ለውጦች በሞዛያ 3፡19 ከተገለጹት ለውጦች ጋር አወዳድሩ።

ቁጥር 16-30ያላችሁን ለሌሎች ማካፈል የኃጢአታችሁን ስርየት እንድታቆዩ እንዴት ሊረዳ ይችላል? ክርስቶስን ለመምሰል በምታደርጉት ጥረት ቁጥር 27ን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ ትችላላችሁ?

ሁላችንም በምን መልኩ ለማኞች ነን? በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት ሁሉንም የእግዚአብሔር ልጆች እንዴት ማየት አለብን? (ሞዛያ 4፡26 ይመልቱ)። የእናንተን እርዳታ የሚያስፈልገው ማነው?

በተጨማሪም ቤኪ ክራቨን፣ “ለውጡን ቀጥሉ”፣ ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 58–60 ይመልከቱ።

ምስል
የሴሚነሪ መለያ

ሞዛያ 4፡5–10

አምናለሁ በእግዚአብሔርም እታመናለሁ።

ንጉሥ ቢንያም በእግዚአብሔር ስለመታመን ያቀረበው ግብዣ በጥንት ጊዜ እንደነበረው ዛሬም አስፈላጊ ነው። ሞዛያ 4፡5–10ን ስታነቡ፣ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ ምክንያት የሚሰጣችሁን እውነት ፈልጉ። ንጉሥ ቢንያም በቁጥር 10 ላይ የሰጠውን ግብዣዎች ልብ በሉ። በእግዚአብሔር መታመን ንጉሥ ቢንያም የጋበዘውን ለማድረግ ቀላል የሚያደርገው ለምንድን ነው?

የእግዚአብሔርን ባሕርያት ዝርዝር ለማውጣት ከእነዚህ ተጨማሪ ጥቅሶች መካከል አንዳንዶቹን አስሱ፡- ኤርምያስ 32፡171 ዮሐንስ 4:82 ኔፊ 9፡17አልማ 32:22 ሞርሞን 9:9ኤተር 3:12ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፡1–388፡41 (በተጨማሪም “ክርስቶስን መሰል ባሕርያት”፣ የተሰኘውን ቪዲዮ በወንጌል ቤተ መጻሕፍት ይመልከቱ)። አንድን ዓረፍተ ነገር ለማጠናቀቅ የተለያዩ መንገዶችን ለማግኘት ዝርዝራችሁን እንደሚከተለው መጠቀም ትችላላችሁ፡- “እግዚአብሔር እንደሆነ ስለማውቅ በእርሱ ልተማመንበት እችላለሁ።

ከእግዚአብሔር ጋር ልምምዶች ሲኖሩን በእርሱ ላይ ያለን እምነት ይጨምራል። በሞዛያ 4፡1–3 ውስጥ፣ የንጉሥ ቢንያም ሰዎች “የእግዚአብሔርን ቸርነት ወደማወቅ” እንዲመጡ የረዳቸው ምንድን ነው? (ቁጥር 6) ከእግዚአብሔር ጋር ስለነበራችሁ ልምዶች አስቡ። እነዚህ ልምምዶች ስለ እሱ ምን አስተምሯችኋል? እምነታችሁን ለማጠናከር ወይም በእግዚአብሔር ለመታመን ምን እርምጃዎች እየወሰዳችሁ ነው (ወይንም ልትወስዱ ትችላላችሁ)?

በተጨማሪም ጄፍሪ አር. ሆላንድን “የእግዚአብሔር ታላቅነት [The Grandeur of God]”፣ .ሊያሆና፣ ህዳር 2003 (እ.አ.አ)፣ 70–73; የወንጌል አርእስቶች “እግዚአብሔር አብ [God the Father]”፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት፤ “አዳኜ እንዳለ አውቃለሁመዝሙሮች፣ ቁ. 302 ይመልከቱ።

የተቀደሱ ልምዶችን ማካፈል። አንዳንድ ልምዶች ለማጋራት በጣም የተቀደሱ ወይም ግላዊ ናቸው። ሌሎች ተሞክሮዎችን እንዲካፈሉ ስትጋብዙ፣ የማይፈልጉ ከሆነ እንዲያካፍሉ አትጫኗቸው።

ሞዛያ 4፥29–30

ሀሳቤን፣ ቃላቶቼን እና ድርጊቶቼን ማስተዋል አለብኝ።

እግዚአብሔር የኃጢአትን ዝርዝር ሁሉ አልሰጠንም። በሞዛያ 4፡29–30 መሰረት በምትኩ ምን ያደርጋል? የእናንተ ሃሳብ፣ ቃላቶች እና ድርጊቶች በእናንተ እና በሌሎችን ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ አስቡ። ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁን ግንኙነት እንዴት ይነካል? እንዴት ነው “[ራሳችሁን የምታስተውሉት]”?

ሞዛያ 5፡1–5

የጌታ መንፈስ በልቤ ውስጥ ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል።

የሰዎች “መለወጥ አልችልም፣ እኔ እንደዚህ ነኝ” ማለት የተለመደ ነው። በአንጻሩ፣ የንጉሥ ቢንያም ሕዝብ ተሞክሮ የጌታ መንፈስ ልባችንን እንዴት እንደሚለውጥ ያሳየናል። ሞዛያ 5፡1–5ን ስታነቡ፣ ወደ እውነተኛ መለወጥ የሚያመጣው “ታላቅ ለውጥ” በህይወታችሁ እንዴት እንደተከሰተ—ወይም ሊከሰት እንደሚችል አስቡ። ስለ አነስተኛ፣ ዝግመታዊ ለውጦች እና ስለ “ታላቅ” ልምዶች አስቡ። ፈተና በሚያጋጥመን ጊዜ እነዚህ ተሞክሮዎች እንዴት ይረዳሉ?

በተጨማሪም ሕዝቅኤል 36፡26–27አልማ 5:14፤ “የልብ ለውጥ [A Change of Heart]፣” “የንጉሥ ቢንያም ሕዝብ ቃል ኪዳን ገባ [The People of King Benjamin Make a Covenant]” (ቪዲዮዎች)፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት ላይ ይመልከቱ።

ምስል
ክርስቶስ የታመመች ሴትን እየፈወሰ

የፈውስ እጆች፣ በአደም አብራም

ሞዛያ 5፥5–15

ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን ስገባ የክርስቶስን ስም በራሴ ላይ እወስዳለሁ።

በራሳችን ላይ የክርስቶስን ስም መውሰድ ምን ማለት እንደሆነ ከሞዛያ 5፡7–9 ምን ተማራችሁ? የቅዱስ ቁርባን ጸሎቶች (ሞርሞን 4–5ን ይመልከቱ) ስለዚህ ምን ያስተምራሉ? እናንተ የአዳኙ መሆናችሁን እንዴት ማሳየት ትችላላችሁ?

በተጨማሪም ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን “Why the Covenant Path፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 116-19ን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ሞዛያ 4፥1-3፣ 10

ንስሐ ደስታን ያመጣል።

  • ስለ ንስሐ ደስታ ለማስተማር፣ ምናልባት ልጆቻችሁ እጃቸውን እንዲቆሽሹ መፍቀድ፣ ከእዚያም ከታጠቡ በኋላ ምን እንደሚሰማቸው ማስተዋል ትችላላችሁ። ከዚያም ያንን በሞዛያ 4፡1–3 ላይ የነበሩት ሰዎች ኃጢአታቸው ከመሰርየቱ በፊት እና በኋላ ከተሰማቸው ስሜት ጋር ማወዳደር ትችላላችሁ። መንፈሳዊ ንጽህና ስለሚሰጠን የአዳኙ ኃይል ምስክርነታችሁን አካፍሉ።

  • ልጆቻችሁ እንዴት በሙሉ እና ከልብ ንስሃ መግባት እንደሚችሉ ያውቃሉ? በሞዛያ 4፡1–3፣ 10 ውስጥ የንጉሥ ቢንያም ሰዎች ያደረጉትን እንዲያገኙ እርዷቸው። በተጨማሪም “ንስሐ፣ ንስሐ መግባት” የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ መከለስ ይችላሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ንስሐ መግባትን ያስቻለው እንዴት ነው?

ሞዛያ 4፡12–26

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሌሎችን በፍቅር እና በደግነት እንድይዝ ያነሳሳኛል።

  • ሌሎችን ማገልገል ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል። ምናልባት ልጆቻችሁ አንድን ሰው ስለወደዱበት ወይም ስላገለገሉበት ጊዜ እና ያ ተሞክሮ ምን እንዲሰማቸው እንዳደረጋቸው ሊናገሩ ይችላሉ። ሰዎች ሌሎችን ማገልገል የማይፈልጉበት አንዳንድ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? አንድን ሰው የተቸገሩ ሰዎችን እንዲረዳ ለመጋበዝ ምን ልንናገር እንችላለን? በሞዛያ 4፡16–26 ውስጥ ሃሳቦችን ፈልጉ።

  • ንጉሥ ቢንያም ወደ ክርስቶስ ስንመጣና የኃጢአታችንን ስርየት ስንቀበል፣ “በእግዚአብሔር ፍቅር እንደምንሞላ” (ሞዛያ 4፡12) አስተምሯል። ይህ ለሌሎች አፍቃሪ እና ደግ እንድንሆን ይመራናል። እናንተ እና ልጆቻችሁ ሞዛያ 4፡13–16፣ 26ን ማሰስ (ወይም እንደ “ከአንተ ጋር እራመዳለሁ”፣የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 140–41 ያለ መዝሙር) እና ሌሎችን እንዴት ማገልገል እንደምንችል የሚገልጹ ሀረጎችን ማግኘት ትችላላችሁ። ከዚያም እነዚህን ነገሮች መተወን ወይም ስዕሎቻቸውን መሳል እና ምን እንደሆኑ የሌላውን ሀረጎች መገመት ይችላሉ። በቤት፣ በትምህርት ቤት ወይም በቤተ ክርስቲያን ፍቅርና ደግነት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ምስል
ወጣት ልጅ ከሕፃን ጋር እየተጫወተች

ኢየሱስ ክርስቶስ ለሌሎች ደግ እንድንሆን አስተምሮናል።

ሞዛያ 5፥5–15

ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ስገባ፣ የክርስቶስን ስም በራሴ ላይ እወስዳለሁ።

  • ልጆቻችሁ “ኢየሱስ ክርስቶስ” የሚለውን ስም የሚያሳዩ ባጆችን በመፍጠር እና በልባቸው ላይ ማድረግ ያስደስታቸው ይሆናል (የዚህ ሳምንት የአክቲቪት ገጽን ይመልከቱ)። ይህን በሚያደርጉበት ጊዜ፣ ለእነርሱ ሞዛያ 5፡12 ማንበብ እናም ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳኖች መግባት የክርስቶስን ስም ሁልጊዜ “በልባችን [እንደመጻፍ]” እንደሆነ ማውራት ትችላላችሁ።

ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

ምስል
ክርስቶስ ወፎችን እየመገበ

በእሱ ቋሚ እንክብካቤ፣ በግሬግ ኬ. ኦልሰን

አትም