አጠቃላይ ጉባኤ
መልሱን ውሰዱ
የጥቅምት 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


9:37

መልሱን ውሰዱ

ዘላቂ ለውጦችን እንድናደርግ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ብርታት ተሰጥቶናል። በትህትና ወደ እርሱ ስንዞር፣ እርሱ የመለወጥ አቅማችንን ያሳድጋል።

እህቶች፣ ከእናንተ ጋር መሆን አስደሳች ነው፡፡

በገበያ ሲከፈል

አንድ ነገርን ለመግዛት አንድ ሴት ወደ ገበያ ስትሄድ አስቡ። ለገንዘብ ያዥዋ እቃው ከሚገባው በላይ ከከፈለች፣ ገንዘብ ያዥዋ መልስ ትሰጣታለች።

መልስን መቀበል

ንጉስ ቢንያም በጥንት አሜሪካ ውስጥ የነበሩ ህዝቡን ከአዳኛችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የምናገኘውን ታላቅ በረከቶች አስተምሯል። እርሱ ሰማያትንና ምድርን እና እኛ የምንደሰትባቸውን ውበት ሁሉ ፈጠረ።1 በእርሱ አፍቃሪ የኃጢያት ክፍያ በኩል፣ ከሃጢያት እና ከሞት የምንድንበትን መንገድ ይሰጠናል።2 ትዕዛዛቱን በትጋት በመኖር ምስጋናችንን ስናሳየው፣ እርሱ ወዲያው ይባርከናል፣ በዚህም የእርሱ ባለዕዳ እንሆናለን።

እርሱ እጅግ ብዙ፣ እንዲያውም እኛ መልሰን ልንሰጠው ከምንችለው በላይ ዋጋ ያለውን ይሰጠናል። ስለዚህ ለሀጢያቶቻችን በዋጋ ሊተመን የማይችል ክፍያ ለከፈለው ምን ልንሰጠው እንችላለን? እኛ መልስልንሰጠው እንችላለን። መልሳችንንልንሰጠው እንችላለን። ምናልባት የሀሳብ መቀየር፣ የጸባይ መቀየር፣ ወይም የምንሄድበትን መንገድ መቀየር ሊሆን ይችላል። ለእያንዳንዳችን ለከፈለው ዋጋ አልባ ክፍያ በምላሹ ጌታ የልብ መቀየር እንዲኖረን ይጠይቀናል። ከእኛ የሚጠይቀው መለወጥ ለእርሱ ጥቅም ሳይሆን ለራሳችን ነው። ስለሆነም፣ ልክ እንደ ገበያ ያለው ገዢ መልስ ስንሰጠው ከሚወስደው ይልቅ የእኛ ቸር አዳኝ ግን መልሱን ለራሳችን እንድንይዝይጋብዘናል።

በንጉስ ቢንያም የተናገረውን ቃላት ከሰሙ በኋላ፣ ህዝቡ ልባቸው እንደተቀየረ እንዲህ አወጁ፣ ”ያለማቋረጥ መልካምን መስራት እንጂ ከእንግዲህ ኃጢያት ለመፈፀም ምንም ፍላጎት እንዳይኖረን ታላቅ ለውጥ ለእኛ … ሁሉን በሚገዛው በጌታ መንፈስ አማካኝነት ሆኗል”3 ቅዱሳን መጻህፍት ወዲያውኑ ፍጹም ሆኑ ሳይሆን ለመቀየር ያላቸው ፍላጎት ወደ ስራ ገፋፋቸው ይላሉ። የልባቸው መለወጥ ማለት ተፈጥሮአዊውን ወንድ ወይም ሴት አስቀርቶ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ የበለጠ ለመምሰል ስጥሩ ለመንፈስ ተገዢ መሆን ማለት ነው።

ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ እንዳስተማሩት፥ “እውነተኛ ለውጥ በታላቅ ጥረት እና የተወሰነ ህመም ጋር በእምነት መሻት ላይ ይወሰናል። ከዚያም ጌታ ነው የማንጻት እና የመቀየር ተአምራት … ለመሰጠት የሚችለው ።”4 ጥረታችንን አዳኙ እኛን ለመቀየር ካለው ችሎታ ጋር በማጣመር፣ አዲስ ፍጥረቶች እንሆናለን።

በልጅነቴ፣ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ግቤ ወደ ላይ፣ ቀጥ ያለ ጎዳና እየተጓዝኩ እራሴን በዓይነ ሕሊናዬ ተመልክቻለሁ። የተሳሳተ ነገር ባደረግሁ ወይም በተናገርኩ ቁጥር፣ ጉዞዬን በድጋሜ ለመጀመር ተንሸራትቼ መንገዶቼን ስወርድ ይሰማኛል። ከቦርዱ አናት ጀምሮ እስከ ጨዋታው መጀመሪያ ድረስ የሚንሸራትተው የህፃናት ጨዋታ መንሸራተቻ እና መሰላል ውስጥ በአንድ አደባባይ ላይ እንደ ማረፍ ነበር! ተስፋ የሚያስቆርጥ ነበር! ነገር ግን የክርስቶስን ትምህርት ስረዳ5 እና በሕይወቴ ውስጥ በየቀኑ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደምጀምር ማወቅ ስጀምር ተስፋ አገኘሁ።

የለውጥ ሂደት መፅናትንም ያካትታል።

ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለመቀየር ቀጣይ ንድፍ ሰጥቶናል። በእርሱ እምነትን እንድንለማመድ ይጋብዘናል፣ ይህም ንስሀ እንድንገባ ያነሳሳናል፣ ይህም “እምነትና ንስሃም በልባቸው ለውጥን ስለሚያመጣ።”6 ንስሃ ስንገባ እና ልባችንን ወደ እርሱ ስንመልስ፣ ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን ለመግባት እና ለመጠበቅ ታላቅ ፍላጎትን እናገኛለን። እስከ መጨረሻ የምንፀናው በሕይወታችን ሙሉ በቀጣይነት እነዚህን መርሆዎች ስንተገብር እና ጌታ እንዲቀይረን ስንጋብዝ ነው። እስከመጨረሻው መፅናት ማለት እስከመጨረሻ መቀየር ማለት ነው። አሁን በእያንዳንዱ ያልተሳካ ሙከራ እንደገና እንዳልጀመርኩ ተረድቻለሁ፣ ነገር ግን በእዚያ እያንዳንዱ ሙከራ፣ እኔ የለውጥ ሂደቴን እቀጥላለሁ።

በወጣት ሴቶች ጭብጥ መልእክት ውስጥ የሚናገር አነሳሽነት ያለው ሐረግ አለ፣ “የንስሀ በምግባት ስጦታን ከፍ አድርጌ እመለከተዋለሁ እናም በየቀኑ ለማሻሻል እሻለሁ።”7 ይህን ወብ ስጦታ ከፍ አድርገን እንድንመለከት እና ሆን ብለን ለውጥን የምንፈልግ እንድንሆን እጸልያለሁ። አንዳንድ ጊዜ ለማድረግ የምንፈልጋቸው ለውጦች ከከባድ ኃጢያት ጋር የተያያዙ ናቸው። ነገር ግን በአብዛኛው ጊዜ፣ እራሳችንን ከኢየሱስ ክርስቶስ ባህሪዎች ጋር ለማጣጣም ባህሪያችንን ለማጣራት እንጥራለን። የዕለት ተዕለት ምርጫችን እድገታችንን ይረዳል ወይም ያደናቅፋል። ትንሽ፣ ነገር ግን ቋሚ፣ ሆን ተብለው የሚደረጉ ለውጦች እንድንሻሻል ይረዱናል። ተስፋ አትቁረጡ። ለውጥ የዕድሜ ልክ ሂደት ነው። ለመለወጥ ባደረግነው ትግል ጌታ በእኛ ላይ ታጋሽ በመሆኑ አመስጋኝ ነኝ።

ዘላቂ ለውጦችን እንድናደርግ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ብርታት ተሰጥቶናል። በትህትና ወደ እርሱ ስንዞር፣ እርሱ የመለወጥ አቅማችንን ያሳድጋል።

ከአዳኛችን የኃጢያት ክፍያ የመለወጥ ኃይል በተጨማሪ ፣ ጥረታችንን ስናደርግ፣ መንፈስ ቅዱስ ይደግፈናል እንዲሁም ይመራናል። ምን ዓይነት ለውጦች ማድረግ እንዳለብን እንድናውቅ እንኳን ሊረዳን ይችላል። በክህነት በረከቶች፣ በጸሎት፣ በጾም፣ እና በቤተመቅደስ በመገኘት እርዳታ እና ማበረታቻ ማግኘት እንችላለን።

እንደዚሁም፣ የታመኑ የቤተሰብ አባላት፣ መሪዎች፣ እና ጓደኞች ለመለወጥ በምናደርገው ጥረት ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ። የስምንት ዓመት ልጅ እያለሁ፣ ታላቁ ወንድሜ ሊ እና እኔ ከጓደኞቻችን ጋር በጎረቤታችን አካባቢ በሚገኝ ዛፍ ቅርንጫፎች ላይ እየተጫወትን ጊዜ እናሳልፍ ነበር። በዚያ የዛፍ ጥላ ውስጥ በጓደኞቻችን ህብረት አብረን መሆንን እንወድ ነበር። አንድ ቀን ሊ ከዛፉ ላይ ወድቆ እጁን ሰበረ። በተሰበረ ክንዱ ምክንያት ወደ ዛፉ መውጣት ከባድ ሆነበት። ነገር ግን በዛፉ ውስጥ ያለው ህይወት ያለ እሱ ተመሳሳይ አልነበረም። ስለዚህ፣ አንዳንዶቻችን ከኋላ ሆነን እርሱን ስንገፋው ሌሎች ደግሞ በደህና እጁ ወደ ላይ ጎትቱት—እናም ያለ ብዙ ጥረት—ሊ ተመልሶ ወደ ዛፉ ወጣ። እጁ አሁንም ተሰብሮ ነበር፣ ነገር ግን በመፈወስ ላይ እያለ እንደገና ከእኛ ጋር አብሮ በወዳጅነትን ተደስቶ ነበር።

በብዛት በዛፍ ውስጥ የመጫወት ልምዴን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ የእኛ እንቅስቃሴ ዓይነት ጋር በማመሳሰል አስብበት ነበር። በወንጌል ቅርንጫፎች ጥላ ውስጥ፣ ከቃል ኪዳኖቻችን ጋር የተዛመዱ ብዙ በረከቶችን እናገኛለን። አንዳንዶች ከቃል ኪዳኖቻቸው ደህንነት ወድቀው ሊሆንን ይችላል እናም ተመልሰው ወደ ወንጌል ቅርንጫፎች ደህንነት ለመግባት የእኛን እርዳታ ይፈልጋሉ። በራሳቸው ተመልሰው መምጣት ለእነሱ ከባድ ሊሆንባቸው ይችላል። በእኛ ወዳጅነት እየተደሰቱ እያሉ ይድኑ ዘንድ እነሱን ለመርዳት በእርጋታ እዚህ ትንሽ መጎተት ትንሽ እዚያ ማንሳት እንችላለን?

በመውደቅ ላይ ጉዳት እየደረሰባችሁ ከሆናችሁ፣ እባካችሁ ወደ ቃል ኪዳኖቻችሁ እና ወደሚያቀርቡት በረከቶች እንድትመለሱ ሌሎች እንዲረዷችሁ ፍቀዱላቸው። በሚወዷችሁ ሰዎች ስትከበቡ አዳኙ እንድትፈወሱ እና እንድትቀየሩ መርዳት ይችላል።

ለብዙ ዓመታት ካላየኋቸው ጓደኞች ጋር አንዳንድ ጊዜ እገናኛለሁ። አንዳንድ ጊዜ “በጭራሽ አልተለወጥሽም!” ይላሉ። ያንን በሰማሁ ቁጥር ትንሽ እሸማቀቃለሁ ምክንያቱም ባለፉት ዓመታት እንደተለዋወጥኩ ተስፋ አደርጋለሁ። ከትናንት ለውጥ እንዳለኝ ተስፋ አለኝ! ትንሽ ደግ፣ በብዛት የማልፈርድ፣ እና የበለጠ ሩህሩህ እንደሆንኩ ተስፋ አለኝ። ለሌሎች ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት ፈጣን እንደሆንኩ ተስፋ አለኝ፣ እናም ተጨማሪ ትዕግስት ያለኝ እንደሆንኩ ተስፋ አለኝ።

ቤቴ አጠገብ ባሉ ተራሮች ላይ በእግር መጓዝ እወዳለሁ። ብዙውን ጊዜ ዱካውን በምጓዝበት ጊዜ በጫማዬ ውስጥ አንድ ትንሽ ድንጋይ አገኛለሁ። በመጨረሻም ቆም ብዬ ጫማዬን አራግፈዋለሁ። ነገር ግን ቆም ከማለቴ እና ይህን የሚበሳጭነገርን ከማውጣቴ በፊት፣ በህመም እያለሁ በእግር ለመጓዝ ምን ያህል እንደፈቀድኩ ያስደንቀኛል።

በቃል ኪዳኑ ጎዳና ስንጓዝ፣ አንዳንድ ጊዜ በደካማ ልምዶች፣ በኃጢአቶች ወይም በመጥፎ አመለካከቶች መልክ በጫማችን ውስጥ ድንጋዮችን እናነሳለን። በሕይወታችን ውስጥ በፍጥነት ስናወጣናቸው፣ የሟች ጉዞአችን የበለጠ ደስታ ይሆናል።

ለውጥን መጠበቅ ጥረት ይጠይቃል። አሁን ያስወገድኩትን የሚያበሳጭ እና የሚያሰቃይ ጠጠርን ወደ ጫማዬ ውስጥ ለማስገባት በመንገዱ መቆምን ማሰብ አልችልም። ቆንጆ ቢራቢሮ ወደ እጭ ሽፋኗ እንደማትመለስ ያህን እኔም እንደዚያ ለማድረግ አልፈልግም።

በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት መለወጥ እንደምንችል እመሰክራለሁ። ልምዶቻችንን ማስተካከል፣ ሀሳባችንን መለወጥ፣ እና እንደ እርሱ የበለጠ ለመሆን ባህሪያችንን ለማረም እንችላለን። እናም በእሱ እርዳታ ለውጡን መጠበቅእንችላለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።