አዲስ መደበኛ
ልባችሁን፣ አዕምሮአችሁን፣ እና ነፍሳችሁን በተጨማሪ፡ወደ ሰማይ አባታችን እና ወደ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትመለሱ እጋብዛችኋለሁ።
ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ እነዚህ የሁለት ቀን ጉባኤዎች ግርማዊ ነበሩ! ከሽማግሌ ጀፍሪ አር ሆላንድ ጋር እስማማለሁ። እርሱ እንዳጠቆመው፣ መልእክቶች፣ ጸሎቶች፣ እና መዝሙሮች በሙሉ በጌታ የተነሳሱ ነበሩ። በማንኛውም መንገድ ለተሳተፉትም አመሰግናለሁ።
በሂደቶቹ ሁሉ፣ ጉባኤውን ሲያዳምጡ በአእምሮዬ እናንተን እንደ ፎቶ አይቻችኋለሁ። የሚሰማችሁን፣ የምትጨነቁበትን ወይም ለመፍታት የምትሞክሩትን ለመረዳት እንዲረዳኝ ጌታን ጠይቄአለሁ። ይህ ጉባኤ ሲጠናቀቅ ጌታ ስለ መጪው ጊዜ ብሩህ ተስፋን የሚልክላችሁን ምን ማለት እችላለሁ ብዬ አስቤአለሁ።
ለብዙ መቶ አመታት ነቢያት አስቀድመው ባዩት በግርማዊ ዘመን ውስጥ እንኖራለን። ይህም ከጻድቃን ምንም መንፈሳዊ በረከት የማይገታበት የዘመን ፍጻሜ ነው።1 የዓለም ብጥብጥ ቢኖርም፣2 ጌታ የወደፊቱን “በደስታ በጉጉት እንድንጠብቅ” ይፈልጋል።3 በትላንትና ትዝታዎች አንጨነቅ። የእስራኤል መሰብሰብ ወደፊት ትጉዟል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የቤተክርስቲያኗን ጉዳዮች ይመራል፣ እናም መለኮታዊ ዓላማዎቹን ያሳካል።
ለእርናንተ እና ለእኔ ያለው ፈታኝ ሁኔታ እያንዳንዳችን የእርሱን ወይም የእሷን መለኮታዊ አቅም እንደምናሳካ ማረጋገጥ ነው። ዛሬ በአብዛኛው ስለ “አዲስ መደበኛ” እንሰማለን። በእውነት “አዲስ መደበኛ” ለመቀበል ከፈለጋችሁ፣ ልባችሁን፣ አዕምሮአችሁን፣ እና ነፍሳችሁን በተጨማሪ፡ወደ ሰማይ አባታችን እና ወደ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትመለሱ እጋብዛችኋለሁ። ያም ለእናንተ አዲስ መደበኛው ይሁንላችሁ።
አዲሱን መደበኛችሁን በየቀኑ ንስሀ በመግባት ተቀበሉ። በተጨማሪም ንጹህ ሀሳብን፣ ቃልን፣ እና ክስተትን እሹ። ሌሎችን አገልግሉ። ዘለአለማዊ አይታ ይኑራችሁ። ጥሪያሁን አጉሉ። ፈተናችሁ ምንም ቢሆን፣ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ እያዳንዱን ቀን እናንተ ከፈጠራችሁጋር ለመገናኘት ተጨማሪ ዝግጅት በማድረግ ኑሩ።4
ለዚህም ነውቤተመቅደሶች ያሉን። የጌታ ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች ከእግዚአብሔር በረከቶች ሁሉ ታላቅ ለሆነው ለዘለአለም ህይወት ያዘጋጁናል።5 እንደምታውቁት፣ የኮቪስ ወረርሸኝ የቤተመቅደሶቻችንን ጊዜአዊ መዘጋትን አስፈልገውበታል። ከዚያም በጥንቃቄ በተቀናጀ ሁኔታ እነዚህን ደረጃ በደረጃ እንደገና መክፈት ጀመርን። ደረጃ 2 አሁን በብዙ ቤተመቅደሶች ውስጥ ተከስትቶ፣ ባለፉት ጥቂት ወሮች ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥንዶች ታትመዋል፣ እና በሺዎች የሚቆጠሩ የራሳቸውን መንፈሳዊ ስጦታ ተቀብለዋል። ሁሉም ብቁ የቤተክርስቲያን አባላት እንደገና ቅድመ አያቶቻቸውን ለማገልገል እና በቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ ለማምለክ የሚችሉበትን ቀን በጉጉት እንጠብቃለን።
አሁን በሚቀጥሉት ቦታዎች ስድስት አዲስ ቤተመቅደሶችን ለመገንባት ስላለወቅድ በማስተዋወቅ እደሰታለሁ፥ ታራዋ፣ ኪሪባቲ፤ ፖርት ቪላ፣ ቫኑዓቱ፤ ሊንደን፣ ዩታ፤ ታላቁ የጓቲማላ ስቲ፣ ጓቲማላ፤ ሳዖ ፖሎ ምስራቅ፣ ብራዚል፤ እና ሳንታ ክሩዝ፣ ቦሊቪያ።
እነዚህን ቤተመቅደሶች ስንገነባ እና ስንንከባከብ፣ ወደ ቅዱስ ቤተመቅደስ ለመግባት ብቁ ትሆኑ ዘንድ፣ እያንዳንዳችሁ ራሳችሁን እንድትገነቡ እና እንድትንከባከቡ እንጸልያለን።
አሁን ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም እንድትሞሉ እባርካችኋለሁ። የእርሱ ሰላም ከሁሉም ሟቾች ግንዛቤ በላይ ነው።6 የእግዚአብሔርን ህግጋት ለማክበር ተጨማሪ ፍላጎት እና ችሎታ ይኖራችሁ ዘንድ እባርካችኋለሁ። ይህን ስታደርጉ፣ እርግጠኛ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ እንኳን፣ የበለጠ ድፍረትን፣ የግል መገለጥን፣ በቤታችሁ ውስጥ የበለጠ መግባባት እና ደስታን በሚያመጡ በረከቶች ትባረካላችሁ።
መለኮታዊ ሀላፊነታችንን፣ እንዲሁም ራሳችንን እና አለምን ለጌታ ዳግም ምፅዓት ማዘጋጀትን ለማሟላት በጋራ ወደፊት እንግፋ። ለእያንዳንዳችሁ ያለኝን ፍቅር በድጋሜ እየገልፅኩኝ፣ እንዲህም የምጸልየው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም ነው፣ አሜን።