አጠቃላይ ጉባኤ
ወደፊትን በእምነት መታቀፍ
የጥቅምት 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ወደፊትን በእምነት መታቀፍ

ለተዘጋጁት እና በጌታ እጆች መሳሪያዎች ለመሆን ለሚዘጋጁት ወደፊቱ ግርማዊ ይሆናል።

ይህም ለመርሳት የማይቻል ምሽት ነበር። ውድ እህቶቼ፣ ከእናንተ ጋር በመገኘቴ ክብር ይሰማኛል። ባለፉት ጥቂት ወራት እናንተ በአዕምሮዬ ላይ ነበራችሁ። እናንተ በቁጥራችሁ ከስምንት ሚልዮን በላይ ናችሁ። እናንተ አለምን ለመለወጥ ቁጥሩ ብቻ ሳይሆን ግን መንፈሳዊ ሀይል አላችሁ። በወረርሸኙ ጊዜ ይህን ስታደርጉም ተመልክቻለሁ።

አንዳንዶቻችሁ በድንገት በደንብ የማይገኘው እቃ ወይም አዲስ ስራ እንደሚትፈልጉ ራሳችሁን አግኝታችኋል። ብዙዎችም ልጆችን በቤት አስተምረዋል እናም ጎረቤቶቻቸውን ረድተዋል። አንዳንድም ከጠበቁበት በፊት ሚስዮናቸውን ወደቤት አምጥተዋል፣ ሌሎችም ቤታችሁን ወደ ሚስዮን ማሰልጠኛ ቦታ ለውጣችኋል። ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር ለምገናኘት፣ ብቸኝነት የሚሰማቸውን ለማገልገል፣ እና ኑ፣ ተከተሉኝ ን ከሌሎች ጋር ለማጥናት ቴክኖሎጂን ተጠቅማችኋል። ሰንበትን አስደሳች ለማድረግም አዲስ መንገዶችን አግኝታችኋል። እና መከላከያ ጭምብሎችንም ሠርታችኋል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩም!

በልብ በሚሰማ ርህራሄ እና ፍቅር፣ የሚወዱት ለሞቱባቸው ብዙ ሴቶች ልቤ ይነካል። ከእናንተም ጋር እናለቅሳለን። እና እንጸልይላችኋለን። ያለድካሜ የሌሎችን ጤንነት ለመጠበክ ስለሚሰሩትም በሙሉ ሙገሳ እናቀርባለን እናም እንጸልያለን።

እናንተም ወጣት ሴቶች አስደናቂ ነበራችሁ። ምንም እንኳን ማህበራዊ አውታረ መረቦች በክርክር ጎርፍ ቢጣሉም፣ ብዙዎቻችሁ ሌሎችን ለማበረታታት እና የአዳኛችንን ብርሃን ለማካፈል መንገዶችን አግኝታችኋል።

እህቶች፣ እናንተ በፍጹም ጀግናዎች ናችሁ! በጥንካሬዎቻችሁ እና በእምነታችሁ እገረማለሁ። በአስቸጋሪ ጉዳዮች፣ በጀግንነት እንደምትቀጥሉም አሳይታችኋል። እወዳችኋለሁ፣ እናም ጌታ እንደሚወዳችሁና የምታከናውኗቸውን ታላቅ ስራዎች እንደሚመለከትም አረጋግጥላችኋለሁ። አመሰግናችኋለሁ! እንደገናም፣ እናንተ በእውነትም የእስራኤል ተስፋ እንደሆናችሁ አረጋግጣችኋል።

ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ ሒንክሊ ከ25 አመት በፊት በመስከረም 1995 (እ.አ.አ) አጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስብሰባ ላይ “ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ” 1 በሚያስተዋውቁበት ጊዜ የነበራቸውን ተስፋ እውን ያደረጋችሁ ናችሁ። ይህን አስፈላጊ አዋጅ ለቤተክርስቲያኗ እህቶች ለማስተዋወቅ መምረጣቸው ታላቅ ትርጉም ያለው ነው። ይህን በማድረግ፣ በጌታ እቅድ ውስጥ ሴቶች ለመተካት የማይችል ተፅዕኖን እንዳላቸው ፕሬዘደንት ሒንክሊ በጥብቅ ያስተዋውቁ ነበር።

አሁን፣ በዚህ አመት ምን እንደተማራችሁ ለማወቅ በጣም እፈልጋለሁ። ወደ ጌታ በጣም ቅርብ ሆናችኋልን፣ ወይስ ከእርሱ የራቻችሁ እንደሆናችሁ ይሰማችኋል? እና የወቅቱ ክስተቶች ስለ ወደፊቱ ጊዜ ምን እንዲሰማችሁ አድርገዋል?

ጌታ ስለ ዘመናችን ልብ ሊባል በሚችል ሁኔታ ተናግሯል። “የሰዎች ልብ [ይወድቅባቸዋል]” 2 እናም የተመረጡትም እንኳን በመታለል አደጋ ላይ ናቸው 3 ብሎ አስጠንቅቋል። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝን “ሰላም ከምደር ትወሰዳለች” 4 እናም መቅሰፍትም በሰው ዘር ላይ ይወርዳል 5 ብሎ ነግሮታል።

ነገር ግን ጌታ ይህ የጸመን ፍጻሜ እንዴት አስደናቂ እንደሚሆን ራዕይ ሰጥቷል። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝን እንዲህ እንዲያውጅ አነሳሳው “የመጨረሻዎቹ ቀናት ስራ፣ እጅግ ሰፊ ነው። … ክብሩ ለመግለጥ አስቸጋሪ፣ እና ታላቅነቱም ተወዳዳሪ የሌለው ነው።” 6

አሁን፣ ባለፉት ጥቂት ወሮች የነበሩትን ለመቅለፅ የምንጠቀብመት ቃል ታላቅነት ላይሆንም ይችላል። ስለ ዘመናችን የሚያሳዝኑ ትንቢቶችንም ሆነ የከበሩ ንግግሮችን እንዴት እንይዛቸው ? ጌታ በቀላል፣ ግን በሚያስደንቅ፣ ማረጋገጫ እንዲህ ነግሮናል፣ “ከተዘጋጃችሁ ፍርሀት አይኖራችሁም።” 7

እንዴት ያለ ተስፋ ነው! ይህም ወደፊታችንን የምንመለከትበትን ለመቀየር የሚችል ነው። በሶልት ሌክ ሸለቆ የምድር መንቀጥቀጥ ጋር ተዳምሮ ወረርሽኙ እንደታሰበው ዝግጁ እንዳልነበረች እንድትገነዘብ እንዳደረጋት አንዲት ሴት ጥልቅ ምስክር ስታቀርብ በቅርቡ ሰማሁ። ስለ ምግብ ማከማቸቷ ወይም ስለ ምስክሯ እየተናገረች እንደሆነ ስጠይቃት ፈገግ ብላ “አዎ!” አለችኝ።

ይህንን የዘመን ፍጻሜ እና የወደፊት ሕይወታችንን በእምነት ለመቀበል መዘጋጀት ቁልፋችን ከሆነ፣ እንዴት በተሻለ መዘጋጀት እንችላለን?

ለብዙ አመታት፣ የጌታ ነቢያት ለችግር ጊዜያት ምግብን፣ ውሀን፣ እና ገንዘብን እንድናከማች ገፋፍተውናል። የአሁኑ ወረርሽኝ የዚያን ምክር ጥበብ አጠናክረዋል። በአለማዊ ጉዳዮች ዝግጁ ለመሆን እርምጃ እንድትወስዱ አበረታታችኋለሁ። ነገር ግን በመንፈሳዊ እና ስሜታዊ ዝግጅታችሁ ላይ ነው ሀሳብ ያለብኝ።

ያንንም በሚነካ፣ ከሸምበል ሞሮኒ ብዙ ለመማር እንችላለን። እንደ ኔፋውያን ሰራዊት መሪ፣ እርሱም ጠንካራ፣ ብዙ ቁጥር ያላቸው፣ እና ክፉ የሆኑ ሰራዊቶችን ተጋፍጦ ነበር። ስለዚህ፣ ሞሮኒ፣ ህዝቡን በሶስት አስፈላጊ መንገዶች አዘጋጀ።

መጀመሪያ፣ እርሱ “የጥበቃ ስፍራ” ብሎ የጠራቸውን እነርሱ የሚጠበቁበትን ስፍራዎች ለማዘጋጀት ረዳቸው። 8 ሁለተኛ፣ “የሰዎችን አዕምሮ ለጌታ ለአምላካቸው ታማኝ እንዲሆኑ” 9 አዘጋጀ። እናም ሶስተኛ፣ ህዝቡን በሰውነት ወይም በመንፈሳዊነት ማዘጋጀትን አላቆመም። 10 እነዚህን ሶስት መሰረታዊ መርሆች እናስብባቸው።

መርህ ቁጥር አንድ፥ የጥበቃ ስፍራን ፍረጡ

ሞሮኒ እያንዳንዱን የኔፋውያን ከተማ በመከለያ፣ ምሽጎች እና ግድግዳዎች አጠናከረ። 11 ላማናውያን በእነርሱ ላይ ሲመጡባቸው፣ “ኔፋውያን የስፍራቸውን ደህንነትለማዘጋጀት ባደረጉት ጥበብ እጅግ ተደንቆ ነበር።” 12

እንደዚህም አይነት፣ ሁከታ በአካባቢያችን ይገኛል፣ እኛም በሰውነት እና በመንፈስ በደህንነት የምንጠበቅበትን ቦታ መፍጠር ያስፈልገናል። ቤታችሁ የግል የእምነት መሸሸጊያ ሲሆን፣ መንፈስ ሲገኝበትም፣ ቤታችሁ የመጀመሪያው መከላከያ ይሆናል።

እንደዚህም፣ የፅዮን ካስማዎች “ከህይወት ማዕበሎች መሰሰጊያ” 13 ናቸው ምክንያቱም እነርሱ የሚመሩት የክህነት ቁልፎች ባላቸው እና የክህነት ስልጣንን በሚለማመዱበት ነውና። ጌታ እንዲመሯችሁ ስልጣን የሰጣቸውን ምክሮች በመከተል ስትቀጥሉ፣ ታላቅ ደህንነት ይሰማችኋል።

የጌታ ቤት የሆነው ቤተመቅደስ ከሌሎች ነገሮች ልዩ የሆነ የጥበቃ ስፍራ ነው። በዚያም፣ እናንተ እህቶች በምትገቡት ቅዱስ የክህነት ቃል ኪዳኖች በኩል በክህነት ሀይል ትባረካላችሁ። 14 በዚያም፣ ቤተሰቦቻችሁ ለዘለዓለም ይተሳሰራሉ። ቤተመቅደሶቻችንን ለመግባት ግድብ ባለበት በዚህ አመትም፣ እናንተ ከእርሱ ጋር ቃል ክየገባችሁትን በምታከብሩበት ጊዜ የእናንተ መንፈሳዊ ስጦታዎች ለእግዚአብሔር ሀይል ዘወትር መዳረሻ ሰጥቷችኋል።

በቀላልም፣ የጥበቃ ስፍራ እናንተ የመንፈስ ቅዱስ መገኘትን ስሜት እና በእርሱ መመራት የሚሰማበት ማንኛውም ቦታ ነው። 15 መንፈስ ቅዱስ ከእናንተ ጋር ሲሆን፣ ከሰፈነው አስተሳሰብ ጋር የሚቃረን ቢሆንም፣ እውነትን ለማስተማር ትችላላችሁ። እናም በመገለጥ አከባቢ ውስጥም ስለወንጌል ቅን ጥያቄዎችን ማሰላሰል ትችላላችሁ።

ውድ እህቶቼ፣ የጥበቃ ስፍራ የሆነ ቤት እንድትፈጥሩም አጋብዛችኋለሁ። ስለክህነት ስልጣን እና ስለቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችና በረከቶች ያላችሁን እውቀት እንድታዳብሩም ግብዣዬን አሳድሳለሁ። ማፈግፈግ የሚትችሉባቸው የጥበቃ ሥፍራዎች መኖሩም የወደፊቱን በእምነት ለማቀፍ ይረዳዎችኋል።

መርህ ቁጥር ሁለት፥ አዕሞራችሁን ለእግዚአብሔር ታማኝ ለመሆን አዘጋጁ።

የሶልት ሌክ ቤተመቅደስን እድሜ እና አቅም ለማራዘም ታላቅ የመገንባት ስራ ጀምረናል።

ምስል
የሶልት ሌክ ቤተ መቅደስ ሲገነባ

አንዳንድም እንደዚህ አይነት ታላቅ ድርጊት አስፈላጊ እንደሆነም ጠይቀው ነበር። ሆኖም፣ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የሶልት ሌክ ሸለቆ በ5.7 መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በደረሰበት ጊዜ፣ የመልአኩ ሞሮኒ ሐውልት ላይ ያለው መለከት እስኪወድቅ ድረስ ይህ የተከበረው ቤተመቅደስ በጣም ተናወጠ! 16

ምስል
መላዕኩ ሞሮኒ ከወደቀው መለከቱ ጋር

ሶልት ሌክ ቤተመቅደስ አካላዊ መሠረት የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመቋቋም ጠንካራ መሆን እንዳለበት ሁሉ፣ የእኛ መንፈሳዊ መሠረቶቻችንም ጠንካራ መሆን አለባቸው። ከዚያም፣ በህይወታችን ላይ ምሳሌአዊው የምድር መንቀጥቀጥ ሲኖር፣ በእምነታችን ምክንያት “የሚጸኑና የማይነቃነቁ” ለመሆን እንችላለን። 17

ጌታ “ትምህርትን፣ እንዲሁም በጥናት እና ደግሞም በእምነት” 18 በመሻት እምነታችንን እንዴት ለማጠናከር እንደምንችል አስተምሮናል። የእርሱን ትእዛዛት ለመጠበቅ እና “እርሱን ሁልጊዜ ለማስታወስ” 19 በምንጥርበት ጊዜ በኢየሱስ ክርስቶች ያለን እምነት ይጠናከራል። በተጨማሪም፣ በእርሱ እምነታችንን በምንለማመድበት ጊዜ ሁሉ እምነታችን ይጨምራል። ያም በእምነት መማር ማለት ነው።

ለምሳሌ፣ በእግዚአብሔር ህግጋት ታዛዥ ለመሆን እምነት ባለን ጊዜ በሙሉ፣ የብዙዎች አስተያየት እኛን ሲያቃልል እንኳን፣ ወይም የቃል ኪዳኑን ማፍረስ የሚያከብሩ መዝናኛዎችን ወይም ርዕዮተ ዓለሞችን በምንቃወምበት ጊዜ ሁሉ፣ እኛ እምነታችንን እየተለማመድን ነን፣ በዚህም እምነታችን እየተጨመረ ነው።

በተጨማሪም፣ እንደ መፅሐፈ ሞርሞን መጥለቅለቅ አይነት እምነትን የሚገነቡ ትንሽ ነገሮች ናቸው ያሉት። ስለኢየሱስ ክርስቶስ በሀይል እና በግልፅ የሚመሰክር ሌላ ምንም መፅሐፍ የለም። በጌታ የተነሳሱት የዚያ ነቢያትም የእኛን ቀናት አይተው ነበር እናም እኛን የሚረዱ ትምህርቶችን እና እውነቶችን መረጡ። መፅሐፈ ሞርሞን የኋለኛው ቀናት የመዳን መመሪያ ነው።

በእርግጥም፣ ፍጹም ጥበቃ የሚመጣው ራሳችንን ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በቀንበር ስናያይዝ ነው። ህይወት ያለ እግዚአብሔር በፍርሀት የተሞላ ህይወት ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ህይወት በሰላም የተሞላ ህይወት ነው። ይህም የሚሆነው መንፈሳዊ በረከቶች ለታማኞች ስለሚመጣ ነው። የግል ራዕይን መቀበል ከእነዚያ በረከቶች ታላቁ ነው።

ጌታ ከጠየቅን “በራእይ ላይ ራዕይን” 20 እንደምንቀበል ቃል ገብቷል። ራዕይ ለመቀበል ያላችሁን ችሎታ ስታጠናክሩ፣ ጌታ ለህይወታችሁ ተጨማሪ መመሪያዎች እና ገደብ የሌላቸው መንፈሳዊ ስጦታዎች በመስጠት እንደሚባርካችሁ ቃል እገባላችኋለሁ።

መርህ ቁጥር ሶስት፥ መዘጋጀትን በምንም አታቁሙ።

ነገሮች መልካም ቢሆኑም፣ ሸምበል ሞሮኒ ህዝቡን በማዘጋጀት ቀጠለ። በምንም አላቆመም። እርሱም በምንም አልረካም።

ጠላትም በምንም ጥቃቱን አያቆምም። ስለዚህ፣ እኛም በምንም መዘጃገትን ለማቆም አንችልም። በስጋዊ፣ በስሜታዊ፣ እና በመንፈሳዊ ራሳችንን በተጨማሪ የምንችል ከሆንን፣ የሰይጣንን የማያቆም ጥቃት ለመቋቋም በተጨማሪ የተዘጋጀን እንሆናለን።

ውስ እህቶች፣ ለራሳችሁ እና ለምታፈቅሯቸው የጥበቃ ስፍራን በማዘጋጀት ልዩ ችሎታ ያላችሁ ናችሁ። በተጨማሪም፣ በሌሎች ላይ አሳማኝ በሆነ መንገድ እምነትን ለመገንባት የሚያስችል መለኮታዊ ስጦታ አላችሁ። 21 እናም እናንተ በምንም አታቁሙ። ያንንም እንደገና በዚህ አመት ውስጥ አሳይታችኋል።

እባካችሁ፣ ቀጥሉ! ቤቶቻችሁን በመጠበቅ እና በምትወዷቸው ሰዎች ልብ ላይ እምነት በመፍጠር ረገድ የነበራችሁ ጥንቃቄ ለመጪው ትውልድ ሽልማቶችን ያስገኛል።

ውድ እህቶቼ፣ እኛ ወደፊት የምንመለከታቸው እጅግ ብዙዎች አሉ። ጌታ አሁን በዚህ ያስቀመጣችሁ እናንተ በእነዚህ የኋለኛው ቀናት የመጨረሻ ክፍል ውስብስብ ነገሮችን ለመቋቋም አቅም እንዳላችሁ ስለሚያውቅ ነው። የስራውን ታላቅነት እንደምትገነዘቡ እናም ሆኖ እንዲመጣ በጉጉት እንደምትረዱ እርሱም ያውቃል።

ወደፊት የሚመጡት ቀናት ቀላል ይሆናሉ እያልኩኝ አይደለም፣ ነገር ግን ለተዘጋጁት እና በጌታ እጆች መሳሪያዎች ለመሆን ለሚዘጋጁት ወደፊቱ ግርማዊ እንደሚሆን ቃል እገባላችኋለሁ።

ውድ እህቶቼ፣ በዚህ ዘመን ውስጥ በመፅናት ብቻ አንቀጥል። ወደፊትን በእምነት መታቀፍእንቀበል። ረባሽ ጊዜያት በመንፈሳዊ ለማደግ እድሎች ናቸው። ተፅዕኖአችን ረጋ ካሉ ጊዜ በላይ ወደውስጥ የሚገቡበት ጊዜዎችም አሉ።

የጥበቃ ስፍራ ስንፈጥር፣ አዕምሮአችንን በእግዚአብሔር ታማኝ ለመሆን ስናዘጋጅ፣ እና ለመዘጋጀት በምንም ሳናቆም፣ እግዚአብሔር ይባርከናል። እርሱም፣ “እንደሚያድነን …፤ ለነፍሳችን ሰላምን [ነግሮናል]፣ ታላቅ እምነትንም [ሰጥቶናል]፣ እናም በእርሱም ለመዳናችን ተስፋ እንዲኖረን አድርጓል።” 22

የወደፊቱን በእምነት ለመቀበል ስትዘጋጁ፣ እነዚህ ተስፋዎች የእናንተ ይሆናሉ! እኔም ለእናንተ ያለኝን ፍቅርን እና በእናንተ ላይ ያለኝን እምነት እየገለፅኩኝ፣ ስለዚህ የምመሰክረው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም ነው፣ አሜን።

አትም