ትእግስት ፍጹም ስራዋ ይኑራት፣ እና ደስታ ትቆጠር!
ትዕግስትን ስንለማመድ እምነታችን ይጨምራል። እምነታችን ሲጨምር፣ ደስታችንም እንደዛው ነው።
ከሁለት አመታት በፊት፣ ታናሽ ወንድሜ፣ ቻድ፣ ወደዚያኛው መጋርጃ ተሻገር። ወደዚያኛው አለም መሻገሩ በአማቴ፣ ስቴፋኒ፣ በሁለቱ ትንሽ ልጆቻቸው፣ ብሬደን እና ቤላ፣ እናም በተቀረው ቤተሰብ ልብ ላይ ክፍት ቦታን ትቶ ነበር። ቻድ ከመሞቱ ከሳምንት በፊት ሽማግሌ ኒል ኤል. አንደርሰን በአጠቃላይ ጉባኤ ላይ ባሉት ቃላት ተጽናንተን ነበር፥ “በምድራዊ አስከፊ ፈተናዎች፣ በትእግስት ወደፊት እንግፋ፣ እናም የአዳኝ የመፈወስ ኃይል ብርሃን፣ መረዳትን፣ ሰላምና ተስፋን ያመጣላችኋል” [“ተቆስሎ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 85]።
በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እመነት አለን፤ ቻድን ዳግም እንደምንቀላቀለው እናውቃለን፣ ግን የአካላዊ አብሮነቱን ማጣት ይጎዳል። ብዙዎች ወዳጆቻቸውን አጥተዋል። መታገስ እና ዳግም እስክንቀላቀላቸው መጠበቅ ከባድ ነው።
ከህልፈቱ አንድ አመት በኋላ፣ የጨለማ ዳመና የሸፈንን ያህል ተሰማን። ቅዱሳት መጻህፍቶቻችንን በማጥናት፣ በበለጠ ሀይል በመጸለይ፣ እና በቤተመቅደስ በብዛት በመካፈል መሸሸግን አሻን። በጊዜው የዚህ መዝሙር ስንኞች ስሜቶቻችንን ሳቡ፤ “የቀኑ ጎህ እየፈታ ነው፣ አለም እየነቃ ነው፣ የምሽቱ ጨለማ ዳመናዎች እየሸሹ ናቸው” (“The Day Dawn Is Breaking,” መዝሙር፣ ቁጥር 52)።
ቤተሰባችንም 2020 (እ.አ.አ) የሚያድስ አመት ይሆናል ብለን ወሰንን! በህዳር 2019 (እ.አ.አ) መጨረሻ ላይ ከ ኑ፣ ተከተሉኝ ውስጥ ከአዲስ ኪዳን የያዕቆብ መጽሐፍን እያነበብን ሳለን ጭብጥ መልክት ወደ እኛ ተገለጠልን። ያዕቆብ መእራፍ 1 ቁጥር 2 እንዲህ ይነበባል፣ “ወንድሞቼ ሆይ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት” (የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ 1፥2 [በ ያዕቆብ 1፥2፣ ውስጥ፣ የግርጌ ማስታወሻ a])። አዲስ አመትን፣ አዲስ አስርት አመትን በደስታ ለመክፈት በመፈለጋችን፣ 2020 (እ.አ.አ) “እንደ ሙሉ ደስታ ለመቁጠር” ወሰንን። በጣም በጥንካሬ ስለተሰማን ያለፈው ገና ላይ ለወንድሞቻችን እና እህቶቻቸን በትልቁ “እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት” የተጻፈበት ሸሚዝ ሰጠኛቸው። የ2020 (እ.አ.አ) አመት በእርግጥም የደስታ እና የሃሴት አመት ይሆናል።
ይኸው ላይ ነን፣ 2020 ዓመተ ምህረት ከዛ ይልቅ በመላው አለም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ ማህበራዊ አለመረጋጋት፣ የበለጠ የተፈጥሮ አደጎች እና የኢኮኖሚ ፈተናዎችን አመጣ። የሰማይ አባታችን እንድናሰላስል እና ስለ ትእግስት ያለንን መረዳት እና ደስታን ለመምረጥ ያለንን ምርጫ እንድናስብበት ጊዜን እየፈቀደልን ይሆናል።
ከዛ ጀምሮ የያዕቆብ መጽሐፍ አዲስ ትርጉምን ሰጥቶናል። ያዕቆብ ምእራፍ 1 ቁጥሮች 3 እና 4 ቀጥለውም፥
“የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ።
“ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም።”
በፈተናዎቻችን መሀል ደስታን ለማግኘት ባለን ጥረት፣ እነዚያ ፈተናዎች ለመልካም እንዲሰሩልን ለማድረግ የሚቻልበት የትእግስት መኖር መሆኑን ዘንግተን ነበር።
ንጉስ ቢንያም ተፈጥሮአዊ ሰውነትን እንዲተው “በጌታ በክርስቶስ የኃጥያት ክፍያ አማካኝነት ቅዱስ [እንዲሆን]፣ እንደልጅ ሁሉን የሚቀበል፣ የዋህ፣ ትሁት፣ ትዕግስተኛ፣ በፍቅር የተሞላ፣ ልጅ ከአባቱ ተቀባይ እንደሚሆን፣ ሁሉንም ነገሮች ለመቀበል ፈቃደኛ” (ሞዛያ 3፥19) እንድንሆን አስተማረን።
ወንጌሌን ስበኩ ምዕራፍ 6 እኛ መከተል የምንለውን የክርስቶስን ዋና ጸባይ ያስተምራል፥ “ትዕግሥት ሳይቆጣ፣ ሳይበሳጭ፣ ሳይጨነቅ መዘግየትን፣ ችግርን፣ ተቃውሞን ወይም መከራን የመቋቋም አቅም ነው። የእግዚያብሔርን ፍቃድ ለማድረግ እና የእርሱን ጊዜ የመቀበል አቅም ነው። ታጋሽ በምትሆኑበት ጊዜ፣ ችግርን ትቋቋማላችሁ እናም በእርጋታ እና በተስፋ ችግርን መጋፈጥ ትችላላችሁ” (Preach My Gospel: A Guide to Missionary Service [ወንጌሌን ስበኩ፥ የሚስዮን አገልግሎት መመሪያ]፣ rev. ed. [2019]፣ 126)።
የትእግስት ፍጹም ስራ በክርስቶስ የቀድሞ ደቀመዝሙር፣ ቃነናዊው ሲመኦን፣ ህይወት ውስጥ መታየት ይችላል። ቀናተኞች የሮሜ ህግን አጥብቀው የአይሁድ ብሄርተኛ ቡድኖች ነበሩ። የቀናተኞች ንቅናቄ በሮሜ ላይ፣ በአይሁድ አጋሮቻቸው ላይ፣ እና ሰዱቃውያን ላይ ወረራ በማድረግ እና ምክንያታቸው የሚደግፍ ነገር ሁሉ በማድረግ ጥቃት ማድረስን ይደግፋል ( Encyclopedia Britannica, “Zealot,” britannica.com ተመልከቱ)። ከነዓናዊው ሲሞን ቀናተኛ ነበር ( ሉቃስ 6፥15ተመልከቱ)። ሲሞን የጦር መሳሪያ እንዲወስድ፣ የወታደራዊ ቡድን እንዲመራ ወይም በኢየሩሳሌም ረብሻን እንዲያስነሳ ክርስቶስን ሊያሳምን ሲሞክር አስቡት እስቲ። ኢየሱስ እንዲህ አስተማር፥
“እናም የዋሆች ብፁአን ናቸው፣ ምድርን ይወርሳሉና። …
“እናም ምህረትን የሚያደርጉ ብፁአን ናቸው፣ ምህረትን ያገኛሉና። …
“እናም የሚያስተራርቁ ሁሉ ብፁአን ናቸው፣ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና” (ማቴዎስ 5፥5፣ 7፣ 9)።
ሲሞን ፍልስፍናውን በትጋት እና ስሜት ይወድ እና ይሟገትለት ይሆናል፣ ነገር ግን ቅዱሳት መጻህፍት እንደሚያስረዱት በአዳኝ ተጽእኞ እና ምሳሌ ትኩረቱን ቀየረ። የክርስቶስ ደቀመዛሙርትነቱ የህይወቱ ጥረቶች መሃከላዊ ትኩረት ሆኑ።
ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳኖችን ስንገባ እና ስንጠብቅ፣ “በድጋሚ መወለድ፤ አዎን፣ ከእግዚአብሔር በመወለድ፣ ከስጋዊና ከወደቁበት ሁኔታ፣ ወደ ፃድቁ መንገድ በእግዚአብሔር በመዳን፣ የእርሱም ወንድና ሴት ልጆች በመሆን [ለመለወጥ]” አዳኝ ይረዳናል (ሞዛያ 27:25)።
በጊዜያችን ከሚገኙት የቀናተኛ ሙሉ ማህበራዊ፣ ሀይማኖታዊ፣ እና ፖለቲካዊ ክስተቶች በሙሉ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙርነት የበለጠ ይታወቅ እናም ማረጋገጫ ይሁን። “ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁ ደግሞ በዚያ ይሆናልና” (ማቴዎስ 6፥21)። ታማኝ ደቀመዛሙርቱ “የእግዚአብሔርን ፍቃድ” ካደረጉም በጓላ፣ እነርሱም “ትእግስት [ያስፈልጋቸው]” (ዕብራውያን 10፥36) እንደነበር እናስታውስ።
የእምነት መሞከር በእኛ ላይ ትግስትን እንደሚሰራው ሁሉ፣ ትእግስትን ስንለማመድ፣ እምነታችን ይጨምራል። እምነታችን ሲጨምር፣ ደስታችንም እንደዛው ነው።
ባለፈው መጋቢት፣ ሁለተኛዋ ሴት ልጃችን፣ ኤማ፣ ልክ እንደአብዛኛው በቤተክርስቲያን እንዳሉ ወንጌል ሰባኪዎች፣ ወደ ግዴታ ተነጥላ መቀመጥ ነበረባት። ብዙ ወንጌል ሰባኪዎች ወደቤት መጡ። ብዙ ወንጌል ሰባኪዎች አዲስ ሃላፊነትን ጠበቁ። አብዛኞች ወደ ስራቸው ቦታ ከመሄዳቸው በፊት የቤተመቅደስ በረከቶችን አልተቀበሉም ነበር። እናመሰግናችኋለን፣ ወንድሞች እና እህቶች። አንወዳችሗለን።
በኔዘርላንድ ውስጥ ኤማ እና አጋሯ በመጀመሪያዎቹ ብዙ ሳምንታት ውስጥ ተወጣጥረው ነበር—በአብዛኛው ሁኔታዎ እስኪያነቡ ድረስ ተወጣጥረው ነበር። በአካላዊ ግንኙነት ጥቂት እድሎች ብቻ እና የተገደቡ ከቤት ውጪ ግንኙነቶች ቢኖሩም፣ ኤማ በእግዚአብሔር የነበራት መመካት ጨመረ። በማህበራዊ ድረገጽ አብረናት ጸለይን እና እንዴት ልንረዳ እንደምንችል ጠየቅን። በማህበራዊ ድረገጽ እያስተማረችው ከነበሩ ጓደኞች ጋር እንድንገናኝ ጠየቀችን።
አንድ በአንድ፣ በኔዘርላንድ ካሉት ከኤማ ጓደኞች ቤተሰባችን በድረገጽ መገናኘት ጀመሩ። ሳምንታዊ፣ የማህበራዊ ድረገጽ ኑ፣ ተከተሉኝ ጥናት ከቤተሰቦቻችን ጋር እንዲቀላቀሉ ጋበዝናቸው። ፍሎር፣ ሎራ፣ ሬንስኬ፣ ፍሪይክ፣ ቤንጃሚን፣ ስታል፣ እና ሙሓመድ ሁሉም ጓደኞቻችን ሆኑ። የተወሰኑት ጓደኞቻችን ከኔዘርላንድ በ“ጠባቡ ደጅ” ገቡ (3 ኔፊ 14፥13)። ሌሎችም “ለሰዎች ልጆች የጎዳናውን ቀጥተኝነትና፣ እነርሱ በዚያ መግባት ያለባቸው በሩን ጥበት አሳይቷቸዋል” (2ኔፊ 31፥9)። በክርስቶስ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ናቸው። በቃል ኪዳናችን እድገት ላይ አብረን ስንሰራ በእያንዳንዱ ሳምንት እኛ “ደስታን እንቆጥራለን”።
እንደ የአጥቢያ ቤተሰብ ለአንድ ወቅት በአካል ለመገናኘት ባለመቻላችን ውስጥ እኛ “ትግስት ፍጹም ስራዋን እንድትሰራ” (ያዕቆብ 1፥4) አደረግን። ነገር ግን በአዲስ ቴክኖሎጂ እና በ ኑ ተከተሉኝ መጽሐፈ ሞርሞን ጥናት የቤተሰቦቻችን እምነት ሲጨምር እንደ ደስታ እንቆጥራለን።
ፕሬዝዳንተ ረስል ኤም ኔልሰን እንዲህ ቃል ገቡ፣ “በዚህ ስራ ላይ ውጤታማ ያልሆናችሁ መስሎ ሲሰማችሁ እንኳን የእናንተ ቀጣይነት ያለው ጥረታችሁ፣ ሕይወታችሁን፣ የቤተሰባችሁን ሕይወት እንዲሁም ዓለምን ይቀይራል” (“Go Forward in Faith፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 114)።
ከእግዚአብሔር ጋር ቅዱስ ቃል ኪዳን የምንገባበት ቤተመቅደስ ለጊዜው ተዘግቷል። ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳናችንን የምንጥብቅበት ቤታችን ግን ክፍት ነው። በቤት ውስጥ በልዩ ሁኔታ ውብ የሆኑት የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን ለማጥናት እና ለማሰላሰል እድሉ አለን። በአካላዊ ቅዱስ ቦታ መግቢያ በሌለበት፣ “[የእኛ] ልቦች …ለሚፈሱት የበረከቶች ውጤት በታላቁ ሀሴት እናደርጋለን” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥9)።
ብዙዎች ስራዎችን አጥተዋል፤ ሌሎች እድሎችን አጥተዋል። ሆኖም፣ በቅርብ እንዲህ ካሉት ፕሬዘዳንት ኔልሰን ጋር እንደሰታለን፥ “ከአባላቶቻችን የሚገኙ ፍቃደኛ የጾም በኩራት፣ እንዲሁም ለበጎ አድራጎት የምናደርግውም ፈቃደኛ ልገሳም እንደዚያው ጨምረዋል። … በአንድነት ይህን አስቸጋሪ ጊዜ እናሸንፋለን። ሌሎችን በመባረክ ስትቀጥሉ ጌታ ይባርካችኋል” [የራስል ኤም. ኔልሰን የፌስቡክ ገጽ ከነሀሴ 16 ቀን 2020 (እ.አ.አ)፣ facebook.com/russell.m.nelson]።
“ተደሰቱ” የእግዚአብሔር ትእዛዝ “ተደሰቱ” እንጂ በፍራቻ ሁኑ አይደለም (ማቴዎስ 14፥27)።
አንዳንዴ “ሁሉንም ነገር ትክክል ነው ያደረኩት” ብለን ስናስብ እና የምንፈልጋቸውን በርከቶችንም ሳንቀበል ስንቀር ትግስት እናጣለን። እርሱ እና ህዝቦቹ ከማረጋቸው በፊት ሄኖክ ከእግዚአብሔር ጋር ለ365 አመታት ተጓዘ። ሶስት መቶ እና ስልሳ አምስት አመታት ሁሉንም መልካም ለማድረግ በመጣር እና ከዛም ተከናወነ! ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥49ተመልከቱ።)
የወንድማችን ቻድ ህልፈት የመጣው የዩታ ኦግደን ሚሰዮንን ከመምራት ከተመለስን ጥቂት ወራት በኋላ ነበር። በደቡብ ካሊፎርኒያ በምንኖርበት ጊዜ፣ በ2015 (እ.አ.አ) ልንመደብባቸው ይችሉ ከነበሩት 417 ወንጌል ሰባኪዎች ሁላ፣ በሰሜን ዩታ መመደባችን ተአምራዊ ነበር። የሚስዮን ቤቱ ከቻድ ቤት የ30 ደቂቃ የመኪና መንገድ ነበር። የቻድ ቀንሰር የተገኘው እኛ የሚሰዮን ጥሪያችንን ከተቀበልን በኋላ ነበር። እጅግ በሚፈትኑ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳ፣ የሰማይ አባታችን እንደሚያውቅ እና ደስታን እንድናገኝ እንደሚረዳን እናውቅ ነበር።
የአዳኙን የኢየሱስ ክርስቶስን ቤዛዊ፣ ቅዱሳዊ፣ ትሁት፣ እና አስደሳች ሀይል እኔ እመሰክራለሁ። ለሰማይ አባታችን በኢየሱስ ስም ስንጸልይ፣ እርሱ እንደሚመልስልንም እመሰክራለሁ ። የጌታን ድምጽ እና ህያው ነቢዩን፣ ፕሬዘዳንት ረሴል ኤም. ኔልስንን ስንሰማ፣ ስንከተል እና ልብ ስንል፣ “ትእግስት ፍጹም ስራዋ ይኑራት፣” እና “ደስታ [እንድትቆጠር]” ማድረግ እንደምንችል እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።