ተደሰቱ
በተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ትምህርት ላይ ያለን የማይነቃነቀው እምነታችን እርምጃዎቻችንን ይመራል እንዲሁም ደስታን ይሰጠናል።
በምድራዊ ሕይወቱ መጨረሻ ቀናት ውስጥ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያቶቹ ስለሚያጋጥማቸው ስደቶችና ችግሮች ነገራቸው።1 በዚህ ታላቅ ማረጋገጫ ደመደመው፤ “በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ” (ዮሐንስ 16፥33)። ያ አዳኙ ለሁሉም የሰማይ አባት ልጆች ያለው መልዕክት ነው። በምድዊ ሕይወታችን ውስጥ ያ ለእያንዳንዳችን የመጨረሻው መልካም ዜና ነው።
ትንሳኤ ያደረገው ክርስቶስ ሐዋርያቶቹን በላካቸው ዓለም ውስጥም “ተደሰቱ” የሚለው የሚያስፈልግ ማረጋጋጫ ነበር። በኋላም ሐዋሪያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች “በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፣ እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፣ እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፣ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም” ሲል ነገራቸው(2 ቆሮንቶስ 4፥8–9)።
ከሁለት ሺህ ዓመታት በኋላ እኛም “በሁሉም እንገፋለን ” ስለዚህም ተስፋ እንዳንቆርጥ ነገር ግን እንድንደሰት ያንን ተመሳሳይ መልዕክት እንሻለን። ጌታ ለውድ ሴት ልጆቹ ለየት ያለ ፍቅር አለው እንዲሁም ያስብላቸዋል። ለመኖር የግድ የሚያስፈልጓችሁን፣ቀሪዎቹን የምትፈልጓቸውን ነገሮች እና ፍርሃቶቻችሁን ያውቃል። እግዚአብሔር ሃያል ነው። እመኑት።
ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ “የእግዚአብሔር ስራ፤ ጥበብ፤ እና ዓላማ ሊከሸፍም ሆነ ከንቱ ሊሆን [ እንደማይችል]” ተምሯል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3፥1)። በትግል ላይ ላሉት ልጆቹ፣ ጌታ እነዚህን ታላላቅ ማረጋገጫዎች ሰጠ።
“እነሆ፣ አገልጋዮቼ ሆይ፣ ይህም ለእናንተ የተሰጠ የጌታ ቃል ኪዳን ነው።
“ስለዚህ፣ ተደሰቱ፣ እናም አትፍሩ፣ እኔ ጌታ ከእናንተ ጋር ነኝና፣ እናም ከጎናችሁ እቆማለሁና፣ እና ስለ እኔም፣ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የህያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆንኩኝ፣ እስቀድሜም እንደነበርኩኝ፣ ህያውም እንደሆንኩኝ፣ እናም ዳግምም እንደምመጣ ትመሰክራላችሁ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥5–6)።
ጌታ ከአጠገባችን በመቆም እንዲህ ይላል፦
“ለአንዱ የተናገርኩትን ለሁሉ እንደምናገር ነው፣ ህጻናት ሆይ፣ ተደሰቱ፤ በመካከላችሁ ነኝ፣ እናም አልተውኳችሁምና” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 61፥36)።
“ከብዙ መከራ በኋላ በረከቶች ይመጣሉና” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥4)።
እህቶች፣ በስደቶች እና በግላዊ ሃዘኖች መሃል የተሰጡት እነዚህ ተስፋዎች ለእያንዳንዳችሁ የዛሬ አስጨናቂ ሁኔታዎቻችሁ ተግባራዊ እንደሚሆኑ እመሰክራለሁ። በምድራዊ ተግዳሮት ውስጥ ወደፊት ስንጓዝ እንድንደሰት እና በወንጌል ሙላት ደስታ እንዲኖረን እያንዳንዳችንን ያስታውሱናል እንዲሁም ውድ ናቸው።
መከራ እና ተግዳሮቶች የተለመዱ የምድራዊ ሕይወት ልምዶች ናቸው። ተቃውሞ እንድናድግ የመርዳት መለኮታዊ ዕቅድ አስፈላጊ አካል ነው፣2 እናም በዛ ሂደት መሃከል በዘላለም ረጅም እይታ ውስጥ ተቃውሞ ሊረታን እንዲችል እንደማይፈቀድለት የእግዚአብሔር ማረጋገጫ አለን። በእርሱ እርዳታ እንዲሁም በእኛ ታማኝነት እና ጽናት አማካኝነት እናሸንፋለን። የእርሱ ክፍል በመሆናቸው ልክ እንደምድራዊ ሕይወት ፣ ሁሉም መከራዎች ጊዜያዊ ናቸው። ከአስከፊ ጦርነት በፊት በነበሩት ውዝግቦች ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት አብርሐም ሊንከን “ይህም ያልፋል” የሚል የጥንት ጥበብን በብልሃት ለአድማጮቹ አስታወሰ።3
እንደምታውቁት፣ ደስተኛ መሆንን አስቸጋሪ የሚያደርጉት—እየተናገርኩ ያለሁት ምድራዊ መከራዎች—በኮቨድ-19 ወረርሽኝ ከብዙ አስከፊ ውጤቶች መሃከል በተወሰኑ ትግሎች ውስጥ አሁን እያለፉ እንዳሉት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ በተለመደ መልኩ ከሌሎች ብዙ ነገሮች ጋር ወደኛ ይመጣሉ። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሁልጊዜ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫን አስታኮ የሚመጣ በሚመስል መልኩ በጠላትነት እና በክርክር የመከራ ወቅት ላይ ናቸው፣ ነገር ግን በዚህ ጊዜ ብዙዎቻችን አዛውንቶች እስከዛሬ ከምናስታውሰው በጣም የከፋ ነው።
ግላዊ በሆነ መልኩ፣ እያንዳንዳችን በብዙ ምድራዊ መከራዎች ለምሳሌ በራሳችን ወይም በሌሎች—ድህነት፣ ዘረኝነት፣ ህመም፣ ስራ ማጣት ወይም ብስጭት፣ ዓመፀኛ ልጆች፣ መጥፎ ትዳር ወይም ትዳር ማጣት እንዲሁም የሃጢያት ውጤቶች በየግል እንታገላለን።
ነገር ግን፣ በዚህ ሁሉ መሃል፣ እንድንደሰት እና በወንጌል መርሆዎችና ቃል ኪዳኖች እና በስራችን ፍሬዎች ደስታን እንድናገኝ ያ ሰማያዊ ምክር አለን።4 ያ ምክር ለነብያት እና ለእኛ ሁሌም ተመሳሳይ ነው። ይህንን ከቀዳሚዎቻችን ተሞክሮዎች እና ጌታ ለእነሱ ከተናገራቸው እናውቃለን።
የነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ ሁኔታዎችን አስታውሱ። በመከራዎች የማጉያ መነጽር አማካኝነት ሲታይ፣ ሕይወቱ ከድህነት፣ ከስደት፣ ከብስጭት፣ ከቤተሰብ ሃዘን እና ከመጨረሻ መሰዋትነት አንዱ ነበረ። በእስር ላይ ሳለ፣ ባለቤቱና ልጆቹ እንዲሁም ሌሎች ቅዱሳን ከምዙሪ ሲሰደዱ የማይታመን መከራ አጋጠማቸው።
ጆሴፍ ለእፎይታ በሚለምንበት ሰዓት ጌታ እንዲህ ብሎ መለሰ፦
“ልጄ፣ ለነፍስህ ሰላም ይኑርህ፤ ጭንቀትህ እና ስቃይህ ለጥቂት ጊዜ ቢሆን ነው፤
“ከዚያም፣ በመልካም ይህን ብትጸና፣ እግዚአብሔርም ወደ ላይ ዘላለማዊ ክብር ይሰጥሃል፤ ጠላቶችህንም በሙሉ ታሸንፋቸዋለህ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥7–8)።
ይህ ግላዊ ዘላለማዊ ምክር ነበር ነብዩ ጆሴፍ የደስተኝነት ፀባዩን እና ለህዝቡ የነበረውን ፍቅርና ታማኝነት እንዲጠብቅ የረዳው። እነዚህ ተመሳሳይ ባህሪዎች የተከተሏቸውን መሪዎች እና መስራቾች አጠንክረዋል እናንተንም ማጠንከር ይችላሉ።
የቀድሞ አባሎችን አስቡ! በተደጋጋሚ ከቦታ ወደ ቦታ እየተሰደዱ ነበር። በመጨረሻም ቤታቸውንና ቤተክርስቲያኗን በበረሃ ላይ የመመስረት ተግዳሮቶች አጋጠማቸው።5 የመጀመሪያ መስራቾች በታላቁ የሶልት ሌክ ሸለቆ ከደረሱ ከሁለት ዓመት በኋላ፣ በዛ አሁንም ድረስ አስጨናቂ በሆነው አካባቢ መስራቾቹ ኑሮን ለመቋቋም የሙጥኝ ማለታቸው አሁንም አደገኛ ነበር። አብዛኛዎቹ አባላት ከሜዳዎቹ ባሻገር አሁንም በመንገድ ላይ ነበሩ ወይም ያንን ለማድረግ ግብአቶችን ለማግኘት እየታገሉ ነበር። ነገር ግን መሪዎች እና አባሎች አሁንም በተስፋና በደስታ ተሞልተው ነበር።
ምንም እንኳን ቅዱሳናቱ በአዲሱ ቤታቸው ባይረጋጉም፣ በጥቅምት 1849 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ አዲስ የሚስዮኖች ማዕበል ወደ ስካንደኔቪያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ እና ደቡብ ፐስፊክ ተላኩ።6 ዝቅተኛ ተብሎ ሊገመት ከሚችለው ቦታ መስራቾቹ ወደ አዲስ ከፍታ ተሸጋገሩ። ከሶስት ዓመት በኋላ የተበታተኑ እስራኤላውያንን ለመሰብሰብ ሌሎች 98 ሰዎች ተጠሩ። አንድ የቤተክርስቲያን መሪ እነዚህ የሚስዮን አገልግሎቶች “በአጠቃላይ ለረጅም ጊዚያት እንደማይሆኑ፤ ማንኛውም ሰው ከቤተሰቡ ውጪ ምናልባት ከ3 እስከ 7 ዓመት ድረስ አንደሚቆይ” ገለፁ።
እህቶች፣ የቀዳሚ አመራሩ ስለተግዳሮታችሁ ይጨነቃል። እንወዳችኋለን እንዲሁም እንጸልይላችኋለን። በተመሳሳይ ሁኔታ የመሬት መንቀጥቀጥን፣ የእሳት አደጋን፣ ጎርፍን እና አውሎ ነፋሶችን ሳይጨምር—የአካላዊ ተግዳሮቶቻችን—ብዙውን ጊዜ ከኛ የቀደሙት ካጋጠማቸው ችግሮች ያነሱ በመሆናቸው ምስጋናን ዘወትር እናቀርባለን።
በችግሮች ውስጥ፣ መለኮታዊው ማረጋገጫ ሁሌም “ተደሰቱ፣ እንደሚገባችሁ እመራችኋለሁና። መንግስት የእናንተ ናት እናም በእዚያም ያሉ በረከቶች የእናንተ ናቸው፣ እናም የዘለአለም ባለጠግነትም የእናንተ ናቸውና” የሚለው ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥18)። ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል? ለመስራቾቹ እንዴት ሊሆን ቻለ? ለእግዚአብሔር ሴት ልጆች ዛሬ እንዴት ሊሆን ይችላል? ትንቢታዊ መመሪያን በመከተላችን፣ “የገሃነም መዝጊያዎች እንደማያሸንፉን” ጌታ በሚያዝያ 1830 (እ.አ.አ) ራዕይ ተናገረ። “አዎን፣” እርሱ እንዲህ አለ፣ “… ጌታ አምላክ የጭለማን ኃይል ከላያችሁ ላይ ይገፋል እናም ለእናንተ ጥቅም እና ለስሙ ክብር ሰማያት እንዲንቀጠቀጡ ያደርጋል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 21፥6)። “አትፍሩ፣ እናንት ትንሽ መንጋዎች፣ መልካምን አድርጉ፤ ምድርና ገሀነም ቢቀናጁባችሁም፣ በእኔ ዐለት ላይ ከተገነባችሁ ሊቋቋሟችሁ አይችሉምና” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥34)።
በጌታ ቃል ኪዳኖች “ልቦቻችንን ከፍ እናደርጋን እንዲሁም እንደሰታለን” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥13)፣ እናም “በደስተኛ ልብና ፈገግታ በተሞላበት ገፅታ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥15)፣ በቃልኪዳን መንገድ ላይ ወደፊት እንጓዛለን። አብዛኞቻችን የማይታወቅ መሬትን ለመመስረት ቤታችንን ትተን እንደመሄድ አይነት ታላቅ ድርሻ ያላቸው ውሳኔዎች አያጋጥሙንም። ውሳኔዎቻችን ብዙውን ጊዜ በሕይወት የዕለት ተዕለት ነገሮች ላይ ነው፣ ነገር ግን ጌታ እንደነገረን፣ “መልካም ስራን ትሰሩ ዘንድ አትታክቱ፣ የታላቅ ስራን መሰረት እየገነባችሁ ነውና። እናም ከትንንሾቹ ነገሮች ታላቅ የሆነው ይወጣል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥33)።
በተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ትምህርት ውስጥ ገደብ የሌለው ኃይል አለ። በዛ ትምህርት ላይ ያለን የማይነቃነቀው እምነታችን እርምጃዎቻችንን ይመራል እንዲሁም ደስታን ይሰጠናል። አዕምሮአችንን ያበራዋል እንዲሁም ለተግባራችን ጥንካሬንና መተማመንን ይሰጣል። ይህ ምሪት እና መገለጥ እንዲሁም ኃይል ቃል የተገቡ ከሰማይ አባታችን የተቀበልነው ስጦታዎች ናቸው። በመረዳትና የንስሃ መለኮታዊ ስጦታን ጨምሮ ሕይወታችንን ከዛ ትምህርት ጋር ስናስማማ፣ እራሳችንን በዘላለማዊ ዕጣ ፈንታ መንገድ ላይ ስንጠብቅ ደስተኛ መሆን እንችላለን—ከአፍቃሪ የሰማይ ወላጆቻችን ጋር እንደገና ለመገናኘት እና ከፍ ለማትም ችንችላለን።
ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ. ስኮት እንዲህ አስተማሩ፣ “ከመጠን በላይ የሆኑ ተግዳሮቶች ሊያጋጥሟችሁ ይችላሉ፣” “መቆጣጠር ከምትችሉት አቅም የበለጠ መስለው እስኪሰሟችሁ ድረስ አንዳንድ ጊዜ በጣም የተከማቹ፣ በጣም የማያቋርጡ ናቸው። ዓለምን ብቻችሁን አትጋፈጡ። ‘በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህ ማስተዋል አትደገፍ’ [ምሳሌ 3፥5]። … ሕይወት ተግዳሮት እንዲኖረው የታቀደ ነው፣ እንድትወድቁ ሳይሆን፣ ነገር ግን በማሸነፍ ስኬታማ እንድትሆኑ እንጂ።”8
ለሰማያዊ መዳረሻችን ሁላችንም እንድንጸና ስጸለይ የእግዚአብሔር አብ እና የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ዕቅድ አካል ስለመሆኑ እመሰክራለሁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።