አጠቃላይ ጉባኤ
የኢየሱስ ክርስቶስ የመፈወስ ኃይል
የጥቅምት 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


9:36

የኃጢያት ክፍያ የመፈወስ ኃይል

በእርሱ እምነትን በመለማመድ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ስንመጣ፣ ንስሃ ስንገባ እና ቃል ኪዳኖችን ስንገባ እና ስንጠብቅ፣ ስብራችን—ምንም ይፍጠረው ምንም—መፈወስ ይችላል።

ከዚህ ዓመት መጀመሪያ አንስቶ ብዙ ያልተጠበቁ ክስተቶችን አስተናግደናል። በዓለም ዙሪያ በተከሰተው ወረርሽኝ ምክንያት የሰው ሕይወት እና የገቢ መጥፋት በአለም አቀፍ ማህበረሰብ እና ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል።

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተከሰቱት የመሬት መንቀጥቀጦች፣ የእሳት አደጋዎች እና የጎርፍ አደጋዎች እንዲሁም ሌሎች ከአየር ሁኔታ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ አደጋዎች ሰዎች አቅመ ቢስ፣ ተስፋ ቢስ እና ልባቸው እንዲሰበር አድርገዋል፣ ህይወታቸው መቼም ቢሆን ተመሳሳይ ይሆን ወይ።

ስለ ስብራት የግል ታሪክ ልንገራችሁ።

ልጆቻችን ወጣት በነበሩበት ጊዜ የፒያኖ ትምህርት መውሰድ እንደሚፈልጉ ወሰኑ። ባለቤቴ ሩዲ እና እኔ ለልጆቻችን ይህንን እድል ለመስጠት ፈለግን ግን ፒያኖ አልነበረንም። አዲስ ፒያኖ መግዛት ስላልቻልን ሩዲ ያገለገለ አንድ መፈለግ ጀመረ።

በዚያ ዓመት ለገና፣ በፒያኖ ሁላችንንም አስገረመን፣ እና ባለፉት ዓመታት ልጆቻችን መጫወት ጀመሩ።

አሮጌ ፒያኖ

ወንዶች ልጆቻችን አድገው ከቤት ሲወጡ አሮጌው ፒያኖ ልክ አቧራ ሰብስቦ ሸጠነው። ጥቂት ዓመታት አለፉ እና የተወሰነ ገንዘብ አጠራቀምን። አንድ ቀን ሩዲ “አዲስ ፒያኖ የምናገኝበት ጊዜ አሁን ይመስለኛል” አለ።

“ሁለታችንም ሳንጫወት ሳንችል ለምን አዲስ ፒያኖ እናገኛለን” ብዬ ጠየቅኩ።

እሱ “ኦ፣ ግን እሱ ራሱ የሚጫወት ፒያኖ ማግኘት እንችላለን! አይፓድን በመጠቀም ከ 4000 በላይ መዝሙሮችን፣ የታበርናክል መዘምራን መዝሙሮችን፣ ሁሉንም የመጀመሪያ ደረጃ መዝሙሮችን እና ሌሎችንም ለማጫወት ፒያኖውን ፕሮግራም ማድረግ ይቻላል።”

ሩዲ በትንሹ ለመናገር ታላቅ የሽያጭ ባለሙያ ነወ።

አዲስ ፒያኖ

አንድ የሚያምር አዲስ ተጫዋች ፒያኖ ገዛን እና ከቀናት በኋላ ሁለት ትልልቅ ጠንካራ ሰዎች ወደ ቤታችን አስገቡልን።

የት እንደፈለግኩ አሳየኋቸው እና ከመንገዱ ተንቀሳቀስኩ።

ፒያኖውን ማጓጓዝ

አነስ የሚል የግራንድ ፒያኖ ነበር እናም በበሩ በኩል እንዲገጣጠም እግሮቹን አስወገዱ እና ፒያኖውን ይዘውት በሄዱት የእጅ ኩርኩር አናት ላይ ጎን ለጎን ማስቀመጥ ቻሉ።

ቤታችን በትንሽ ተዳፋት ላይ ተቀመጠ፣ እና በሚያሳዝን ሁኔታ በዚያ ቀን ቀደም ሲል በረዶ ነበር፣ ነገሮችን እርጥብ እና ለስላሳ ያደርጋቸዋል። ይህ ወዴት እንደሚሄድ ማየት ትችላላችሁ?

ወንዶቹ ፒያኖውን ወደ ትንሹ ተዳፋት ወደ ላይ ሲያነሱት ተንሸራተተ፣ እና በጣም ከፍተኛ ውድቀት ሰማሁ። ፒያኖው ከእጅ ኩርኩር ላይ ወድቆ መሬቱን በኃይል በመምታት በሣር ሜዳችን ላይ ትልቅ ቀዳዳ እንዲተው አድርጓል።

አልኩ፣ “ወይኔ ጉዴ። ደህና ናቹ?”

ደግነቱ ሁለቱም ሰዎች ደህና ነበሩ።

እርስ በእርሳቸው ሲተያዩ ዓይኖቻቸው ሰፊ ነበሩ፣ ከዚያ ወደኔ ተመለከቱ እና “በጣም እናዝናለን። ወደ ሱቁ እንመልሰውና አስተዳዳሪችን እንዲደውልልዎ እንጠይቃለን።

ብዙም ሳይቆይ ሥራ አስኪያጁ አዲስ ፒያኖ ለማድረስ ከሩዲ ጋር ተነጋገረ። ሩዲ ደግ እና ይቅር ባይ ነው እና ጉዳቱን ከጠገኑ እና ተመሳሳይ ፒያኖ ይዘው ቢመለሱ ጥሩ እንደሆነ ለአስተዳዳሪው ነግሮታል ግን ስራ አስኪያጁ አዲስ እናገኛለን በማለት አጥብቀው ጠየቁ።

ሩዲ መልስ ሰጠ፣ “ያን ያህል መጥፎ ሊሆን አይችልም። በቃ አስተካክላችሁ አምጡት።”

ሥራ አስኪያጁ፣ “እንጨቱ ተሰብሯል፣ አንዴ እንጨቱ ከተሰበረ በጭራሽ ተመሳሳይ ድምፅ ማሰማት አይችልም። አዲስ ፒያኖ ታገኛለህ።”

እህቶች እና ወንድሞች፣ ሁላችንም እንደዚ ፒያኖ፣ ትንሽ የተሰበርን፣ የተሰነጠቅን እና የተጎዳን እኛ ከእንግዲህ ወዲህ እንደማንሆን የተሰማን አይደለንም? ይሁን እንጂ፣ በእርሱ እምነትን በመለማመድ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ስንመጣ፣ ንስሃ ስንገባ እና ቃል ኪዳኖችን ስንገባ እና ስንጠብቅ፣ ስብራችን—ምንም ይፍጠረው ምንም—መፈወስ ይችላል። በሕይወታችን ውስጥ የአዳኙን የመፈወስ ኃይል የሚጋብዘው ይህ ሂደት ከዚህ ቀደም ወደነበርንበት አይመልሰንም ነገር ግን ከዚህ በፊት ከነበርነው የተሻልን ያደርገናል። በአዳኝ የኃጢያት ክፍያ በኩል ሁላችንም ልክ እንደ አዲስ ፒያኖ እንደ ተስተካከለ፣ ሙሉ እንድንሆን እና ቆንጆ እንደምንሆን አውቃለሁ።

ፕሬዘደንት ራስል ኤም ኔልሰን እንዳስተማሩት፤ “ከባድ ፈተናዎች ሲደርሱብን፣ በአምላክ ላይ ያለንን እምነት ጠልቀን፣ ጠንክረን ለመስራት እና ሌሎችን ለማገልገል ጊዜው አሁን ነው። ያኔ የተሰበረውን ልባችንን ይፈውሳል። እሱ የግል ሰላምን እና መፅናናትን ይሰጠናል። እነዚያ ታላላቅ ስጦታዎች በሞት እንኳ አይጠፉም።”1

ኢየሱስ እንዲህ አለ፤

“እናንተ ደካሞች ሸከማችሁ የከበደ ሁሉ፤ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።

ቀንበሬንም በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝ፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።

“ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና” (ማቴዎስ 11፥28–30)።

አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፤

ወደ እርሱ በመምጣት ስብራታችንን ለመጠገን በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ሊኖረን ይገባል። በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት መኖር ማለት ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ መመካት—በዘላለማዊ ኃይሉ … እና ፍቅሩ ማመን ማለት ነው። ትምርቶቹን ማመንንም ይጨምራል። የሚያደርጋቸውን ሁሉ መረዳት ባንችልም እንኳን ማመን ማለት ነው። ሁሉንም ህመማችንን፣ ስቃያችንን እና ድክመቶቻችን ስለተለማመደ ከቀን ተቀን ችግሮቻችን እንዴት ከፍ ሊረዳን እንደሚችል ያውቃል።”2

ወደ እርሱ ስንመጣ፣ “በደስታ፣ በሰላም፣ እና በመፅናኛ ለመሞላት እንችላለን። ስለሕይወት [ከባድ እና አስቸጋሪ] የሆኑት ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ትክክል ለመሆን ይችላሉ።”3 እንዲህ ብሎ አስተማረ፣ “ባሰባችሁት ነገር ሁሉ ወደ እኔ ተመልከቱ፤ አትጠራጠሩ፣ አትፍሩ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥36)።

በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ አልማ እና ህዝቦቹ በእነሱ ላይ በተጫነው ሸክሞች ሊጨፈለቁ ሲሉ ህዝቦቹ ለእፎይታ ተማፀኑ። ጌታ ሸክማቸውን አልወሰደም፣ በምትኩ እንዲህ ቃል ገባላቸው፤

“እናም ደግሞ በባርነት በነበራችሁ ጊዜም ቢሆን፣ በጀርባችሁም እንኳን ሊሰማችሁ እንዳይቻላችሁ፣ በትከሻችሁ ላይ ያለውን ሸክም አቃልልላችኋለሁ፤ እናም ይህንን የማደርገው ከዚህ በኋላ ለእኔ በምስክርነት እንድትቆሙ ነው፤ እናም እኔ ጌታ እግዚአብሔር በእውነት በመከራቸው ጊዜ ህዝቤን እንደምጎበኝ ታውቁ ዘንድ ነው።

“እናም አሁን እንዲህ ሆነ በአልማ እና በወንድሞቹ ላይ የተጫኑ ሸክሞች ቀላል ሆነላቸው፤ አዎን፣ ሸክማቸውን በቀላል ሸክም እንዲሸከሙ ጌታ አበረታታቸው፣ እናም ለጌታ ፈቃድ ሁሉ በደስታ እና በትዕግሥት አስረከቡ”።(ሞዛያ 24፥14–15)።

ስለአዳኙ የመፈወስ እና ሸክምን የማቅለል ችሎታ፣ ሽማግሌ ታድ አር ካልስተር እንዲህ አስተማሩ፤

“ከኃጢያት ክፍያ በረከቶች አንዱ የአዳኙን የመርዳት ኃይል መቀበል መቻላችን ነው። ኢሳይያስ ስለጌታ የፈውስ አረጋጊ ተፅዕኖ በተደጋጋሚ ተናገረ። አዳኙ ‘ለድሀው መጠጊያ፣ ለችግረኛው በጭንቁ ጊዜ መጠጊያ፣ ከውሽንፍር መሸሸጊያ ከሙቀትም ጥላ እንደሆነ መሰከረ’ (ኢሳይያስ 25፥4)። ለሚያዝኑ ሰዎች፣ ኢሳይያስ አዳኙ ‘የሚያዝኑትን ሁሉ የማጽናናት’ ኃይል እንዳለው ገልጽዋል። (ኢሳይያስ 61:2), እና ‘ከፊት ሁሉ እንባን ያብሱ’ (ኢሳይያስ 25:8; ራእይ7:17); ‘የትሑታንን መንፈስ ማደስ’ (ኢሳይያስ 57:15); እና ‘የተሰበሩትን ጠግኑ’ (ኢሳይያስ 61:1; ሉቃስ 4:18; መዝሙረ ዳዊት 147:3)። ስለሆነም የመርዳት ኃይሉ ‘በአመድ ፋንታ አክሊልን፣ በለቅሶ ፋንታ የደስታ ዘይትን፣ በሀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋና መጎናጸፊያን’ መቀየር እስኪችል ዘንድ ከፍተኛ ነበር (ኢሳይያስ 61፥3)።

“ኦ፣ በእነዚያ ተስፋዎች ውስጥ ምን ተስፋ ይወጣል! … መንፈሱ ይፈውሳል፤ ያጣራል፤ ያጽናናል፤ ተስፋ በሌላቸው ልቦች ውስጥ አዲስ ሕይወት ይተነፍሳል። በህይወት ውስጥ አስቀያሚ እና ጭካኔ የተሞላበት እና ዋጋ ቢስ የሆኑትን ሁሉ ወደ ከፍተኛ እና ክቡር ግርማ ወደሆነ ነገር ለመቀየር ኃይል አለው። እርሱ የሟችነትን አመድ ወደ ዘላለም ውበቶች የመለወጥ ኃይል አለው።”4

ኢየሱስ ክርስቶስ አፍቃሪ አዳኛችን፣ ቤዛችን፣ ዋና ፈዋሽ እና ታማኝ ጓደኛችን እንደሆነ እመሰክራለሁ። ወደ እርሱ ከተመለስን እርሱ ይፈውሰናል እንደገናም ሙሉ ያደርገናል። ይህ የእርሱ ቤተክርስቲያን እንደሆነ እመሰክራለሁ እናም በድጋሜ ወደዚች ምድር ተመልሶ በኃይል እና በክብር ለመግዛት እየተዘጋጀ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ረስል ኤም ኔልሰን “Jesus Christ—the Master Healer,” ሊያሆና፣ ታህሳስ 2005 (እ.አ.አ)፣ 87።

  2. Faith in Jesus Christ,” Gospel Topics, topics.ChurchofJesusChrist.org።

  3. Preach My Gospel: A Guide to Missionary Service, rev. ed. (2018), 52, ChurchofJesusChrist.org።

  4. Tad R. Callister, The Infinite Atonement (2000), 206–7።