የተፈተነ፣ የተረጋገጠ እና የጸዳ
በፈተናዎቻችን ወቅት ለቃል ኪዳኖቻችን ታማኝ መሆናችንን ስናሳይ የሚመጣው ትልቁ በረከት በተፈጥሮአችን ላይ ለውጥ ይሆናል።
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ዛሬ እናንተን ለማነጋገር ምስጋና ይሰማኛል። ተስፋዬ ሕይወት በተለይ አስቸጋሪ እና እርግጠኛ ያልሆነ በሚመስልበት ጊዜ ማበረታቻ መስጠት ነው። ለአንዳንዶቻችሁ ያ ጊዜ አሁን ነው። ካልሆነ ደግሞ ያ ጊዜ ይመጣል።
ይህ ጨለምተኛ እይታ አይደለም። ምክንያታዊ ነው ፣ ነገር ግን ብሩህ ነው - - እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ፍጥረት ውስጥ ካለው ዓላማ የተነሳ። ያ ዓላማ ለልጆቹ አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ ትክክለኛውን መምረጥ መቻላቸውን እና ፈቃደኝነታቸውን ለማሳየት እድል ለመስጠት ነበር። ይህንን በማድርግ ባህሪያቸው ይቀየራል ፤ የበለጠ እሱን እየምሰሉ ይመጣሉ። በእርሱ የማይናወጥ እምነት መኖርን እንደሚጠይቅ ያውቅ ነበር።
አብዛኛው የማውቀው ነገር የመጣው ከቤተሰቦቼ ነው። እድሜዬ ስምንት አመት ገደማ ስሆን፣ ብልኋ እናቴ እኔን እና ወንድሜን በቤተሰቦቻችን የጓሮ አትክልት ውስጥ አብረናት አረም እንድንነቅል ጠየቀችን። ይህ ቀላል ስራ ይመስላል ነገር ግን የምንኖረው በኒው ጀርሲ ውስጥ ነበር። አብዛኛውን ጊዜ ይዘንባል። አፈሩ በጣም ሸክላማ ነበር። አረሞቹ ከአትክልቶቹ በበለጠ ፍጥነት አድገዋል።
አረሞቹ ሥሮቻቸው በከባድ ጭቃ ላይ ተጣብቀው፣ በእጆቼ ውስጥ ሲሰባበሩ ብስጭቴን አስታውሳለሁ። እናቴ እና ወንድሜ ብዙ ቀድመውኝ ነበር። በጣም በሞከርኩ መጠን የበለጠ ወደ ኋላ ቀረሁ።
“ይህ በጣም ከባድ ነው!” ብዬ ጮህኩ።
እናቴ ርህራሄን ከመስጠት ይልቅ ፈገግ ብላ “ሃል፣ በእርግጥ ከባድ ነው። መሆንም ነበርበት። ህይወት ፈተና ነች” አለች ።
በዚያች ቅጽበት፣ የተናገረችው እውነት እንደሆነ እና ለወደፊትም እውነት ሆኖ እንደሚቀጥል አውቄ ነበር።
የሰማይ አባት እና የተወደደው ልጁ ፣ ይህንን ዓለም የፈጠሩበትን አላማ እና ለመንፈስ ልጆች የምድራዊ ህይወት እድልን ስለመስጠታቸው ሳነብ፣ የእናቴ የፍቅር ፈገግታ ምክንያቱ ከዓመታት በኋላ ግልጽ ሆነልኝ።
“እና ጌታ አምላክ የሚያዛቸውን ማናቸውንም ነገሮች ሁሉ እንደሚያደርጉ ለማየት፣ በዚህ እንፈትናቸዋለን፤
“እና የመጀመሪያ ሁኔታቸውን የጠበቁትም ይጨመርላቸዋል፤ እና ይህን የመጀመሪያውን ሁኔታቸውን ያልጠበቁትም ከዚህ አይነት መንግስት ውስጥ የመጀመሪያው ሁኔታቸውን ከጠበቁት ጋር ክብር አይኖራቸውም፤ እና ሁለተኛ ሁኔታቸውን የጠበቁትም በራሳቸው ላይ ክብር ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ይጨመርላቸዋል።”1
እኔ እና እናንተ ለመፈተን እና ከእንግዲህ ከሰማይ አባታችን ፊት በማንኖርበት ጊዜ የእግዚያግሔርን ትእዛዛት ለመጠበቅ እንደምንመርጥ ለማሳየት ጥሪውን ተቀበልን።
ከሰማዩ አባታችን የፍቅር ግብዣ ቢኖርም፣ ሰይጣን አንድ ሶስተኛው የመንፈስልጆች እንዲከተሉት በማሳመን ለእድገታችን የሚሆነውን የአብን እቅድ እና የዘላለማዊ ደስታ ውድቅ አደረገው። ሰይጣን በአመጹ ምክንያት ፣ ከተከታዮቹ ጋር ተባረረ። አሁን ፣ በሚሞተው ህይወት ውስጥ ከእግዚአብሄር እንዲርቁ ለማድረግ የቻለውን ሁሉ ይሞክራል።
ትእዛዙን የተቀበልነው፣ አዳኛችን እና ቤዛችን ለመሆን በቀረበው በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት ምክንያት ነው። ምንም እንኳን ድክመቶች ቢኖሩብንም እና ምንም አይነት ክፉ ሃይል በእኛ ላይ ቢሆን፣ በዚያን ጊዜ የመልካም ሃይሎች እንደሚበልጡ አምነን ነበር ማለት ነው።
የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ያውቁሃል እናም ይወዱሃል። ወደ እነሱ እንድትመለስ እና እንደነሱ እንድትሆን ይፈልጋሉ። የእናንተ ስኬት የእነሱ ስኬት ነው። እነዚህን ቃላትቶች ስታነቡ ወይም ስትሰሙ በመንፈስ ቅዱስ የተርጋገጠው ፍቅር ይሰማችኋል። ፥ “እነሆ፣ የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት ማምጣት ስራዬ እና ክብሬ ይህ ነው።”2
እግዚያብሄር መንገዳችንን የማቅለል ኃይል አለው። የእስራሄል ልጆች ወደ ቃል ኪዳኑ ምድር ሲጓዙ መናን መገባቸው። ጌታ በምድራዊ አገልግሎቱ ድውያንን ፈውሷል፣ ሙታንን እስነስቷል፣ ባህሩንም አረጋግቷል። ከትንሳኤው ብኋላ፣ ለታሰሩት በሩን ከፈተ።”3
ሆኖም ከታላላቆች ነቢዮቹ አንዱ የሆነው ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በእስር ቤት ውስጥ መከራን ተቀብሎ በተደጋጋሚ የእምነት ፈተናዎቻችን ውስጥ ሁላችንም የምንጠቀምበትን እና የምንፈልገውን ትምህርት አስተማረ ፡፡እና ወደ ጉድጓድ ወይም በገዳዮች እጅም ብትጣል፣ እና የሞት ፍርድ ቢተላለፍብህ፤ ወደ ጥልቁም ብትጣል፤ ወደፊት እና ወደኋላ የሚገፋው ውሀ በአንተ ላይ ቢያድም፤ አደገኛው ነፋስም ጠላትህ ቢሆን፤ ሰማያትም ጭለማን ቢሰበስቡ፣ እና ንጥረ-ነገሮች ሁሉ መንገድህን ለማሰናከል ቢጣመሩ፤ እና ከሁሉም በላይ፣ የሲኦል መንጋጋም አፍዋን በሰፊው ብትከፍትብህ፣ ልጄ ሆይ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ለአንተ ልምድ እንደሚሰጡህ እና ለአንተ ጥቅም እንደሆኑም እወቅ።4
አፍቃሪ እና ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ የምድራዊ ህይወታችን ፈተና በጣም ከባድ እንዲሆን ለምን እንዳደርገ ተገርማችሁ ይሆናል። ለዘላለም በእሱ መገኛ በቤተሰቦች ውስጥ መኖር እንድንችል በመንፈሳዊ ንጽህና እና ብቃት ማደግ እንዳለብን ስለሚያውቅ ነው። ያንን ማድረግ እንድንችል ፣ የሰማይ አባት በእምነት ትእዛዛቱን ለመጠብቅ እናም ንስሃ እንድንገባ እናም ወደእርሱ እንድንመጣ አዳኝ እና ለራሳችን የመምርጥ ሃይል ሰጥቶናል።
የአብ የደስታ እቅድ ያተኮረው እንደ ተወዳጁ ልጁ ፣ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆን እንድንችል ነው። በማንኛውም ነገር ፣ የእየሱስ ክርስቶስ ምሳሌነት ጥሩ መመሪያችን ነው። እርሱ እራሱን ከማረጋገጥ አስፈላጊነት አላመለጠም ነበር። ለሰማይ አባት ልጆች ፣ የሃጥያታችንን ዋጋ በመክፈል ጸና። ወደ ስጋ ለመጡ እና ለሚመጡት ሰዎች ሁሉ ተሰቃየ።
ምን ያህል ስቃይ በጥሩ ሁኔታ መቋቋም እንደምትችሉ በገረማችሁ ጊዜ ፣ እርሱን አስታውሱ። እንዴት እንደሚያነሳችሁ ያውቅ ዘንድ መከራችሁን ተቀብሏል። ሸክሙን ላያስወግደው ይችላል ፣ነገር ግን ጥንካሬን ፣ መፅናናትን እና ተስፋን ይሰጣችኋል። እርሱ መንገዱን ያውቀዋል። መራራ ጽዋውን ጠጥቷል። የሁሉንም ስቃይ ታገሰ።
ፈተና በሚገጥማችሁ ጊዜ ፣ እንዴት እንደሚታደጋችሁ በሚያውቅ በአፍቃሪው አዳኝ እየተመገባችሁ እናም እየተጽናናችሁ ነው። አልማ እንዳስተማርው
“እናም በመከራና በሁሉም ዓይነት ህመምና ፈተናዎች በመሰቃየት ይሄዳል፤ የህዝቡን ህመምና በሽታ በራሱ ላይ ይወስዳል የሚለውን ቃል ይፈፀም ዘንድ ይህ ይሆናል።
እናም ህዝቡን ያሰረውን የሞት እስር ይፈታ ዘንድ ሞትን በራሱ ላይ ይወስዳል፣ እናም በስጋ አንጀቱ በምህረት ይሞላ ዘንድ፣ በስጋ ህዝቡን ከድካሙ እንዴት እንደሚረዳ ያውቅ ዘንድ ድካማቸውን በራሱ ላይ ያደርጋል።5
እናንተን የሚደግፍበት አንዱ መንገድ ሁል ጊዜ እሱን እንድታስታውሱ እና ወደ እርሱ እንድትመጡ በመጋበዝ ይሆናል። አበረታቶናል።
“እናንተ ደካሞች ሸከማችሁ የከበደ ሁሉ፤ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
“ቀንበሬንም በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝ፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።“6
ወደ እርሱ ለመምጣት የሚቻልበት መንገድ ቃሉን መመገብ ፣ ንሰሃ በመግባት እምነታችንን መለማመድ ፣ መጠመቅ እና በተፈቀደለት አገልጋዩ ማረጋገጥ እና ከዚያ ቃል ኪዳኖቻችሁን ከአምላክ ጋር መጠበቅ ነው። አብሮህ ፣ አፅናኝ እና መመሪያ እንዲሆንህ መንፈስ ቅዱስን ይልካል። እሱም መመሪያ፣ መጽናናትን፣ እና እኛን ለማበረታታት መንፈስ ቅዱስን ይልካል።
ለመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ብቁ ሆናችሁ ስትኖሩ፣ መንገዱን ማየት በማይችሉበት ጊዜም እንኳን ጌታ ደህንነት ወዳለበት ቦታ ሊመራችሁ ይችላል። ለእኔ ፣ እሱ ብዙውን ጊዜ የሚቀጥለውን ወይም የሚወስደውን ሁለት እርምጃ አሳይቷል። ስለ ሩቅ ጊዜ በጥቂቱ ፍንጭ ሰጥቶኛል ፣ ነገር ግን እነዚያ አልፎ አልፎ የሚታዩ ዕይታዎች በዕለት ተዕለት ሕይወት ምርጫዬን ውስጥ ይመሩኛል።
ጌታ እንዲህ አለ፤
ከዚህ በኋላ ስለሚመጡት ነገሮች አምላካችሁ ያቀደውን፣ እናም … ብዙ መከራን ተከትሎ የሚመጣውን ክብር፣ በእዚህ ጊዜ በተፈጥሮ አይኖቻችሁ ልታዩ አትችሉም።
ከብዙ መከራ በኋላ በረከቶች ይመጣሉና።”7
በፈተናዎቻችን ወቅት ለቃል ኪዳኖቻችን ታማኝ መሆናችንን ስናሳይ የሚመጣው ትልቁ በረከት በተፈጥሮአችን ላይ ለውጥ ይሆናል። ቃል ኪዳኖቻችንን ለመጠበቅ በመምረጣችን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል እና የእርሱ የኃጢያት ክፍያ በረከቶች በእኛ ውስጥ ሊሠሩ ይችላሉ። ልባችን ለፍቅር ፣ ይቅር ለማለት እና ሌሎች ወደ አዳኙ እንዲመጡ ለመጋበዝ ሊራራ ይችላል። በጌታ ያለን መተማመን ይጨምራል። ፍርሃታችን ይቀንሳል።
ምንም እንኳን አሁን በመከራ ውስጥ ቃል የተገቡ በረከቶች ቢሆኑም ፣ እኛ መከራን አንፈልግም ፡፡ በምድራዊ ሕይወት ልምድ ውስጥ የበለጠ እንደ አዳኙ እና የሰማይ አባታችን ለመሆን ከባድ ፈተናዎችን ለማለፍ እራሳችንን ለመፈተሽ በቂ እድሎች ይኖሩናል።
በተጨማሪም ፣ የሌሎችን መከራ ማስተዋል እና ለመርዳት መሞከር አለብን። እኛ እራሳችንእየተፈተንን ሳለ ይሄ የበለጠ ለእኛ ከባድ ይሆናል። ነገር ግን የሌላውን ሸክም በመጠኑም ቢሆን ስናነሳ፣ጀርባዎቻችን ይጠንክራሉ እናም በጨለማ ብርሃን ሲሰማን እናገኛለን።
በዚህ፣ ጌታ ምሳሌአችን ነው። የእግዚያብሔር እንድያ ልጅ ባይሆን ኖሮ እንኳን በጎልጎታ መስቀል ላይ፣ በጣም በከባድ ህመም እየተሰቃየ ሊሞት ይችል ነበር፣ ወደሰቃዮቹ ተመልክቶ እንዲህ አለ፣ አባት ሆይ “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው።”8 በሕይወት ለሚኖሩ ሁሉ እየተሰቃየ ከመስቀሉ ላይ ሆኖ ወደ ዮሃንስ እና ወዳዘነችው እናቱ ተመለከተ እናም በመከራዋ አገለገላት።
ኢየሱስም እናቱን፣ ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ ፣ እናቱን አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት።
ለደቀመዝሙሩም፣ እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።9
በእነዚያ እጅግ በተቀደሱ ቀናት ላይ ባደረጋቸው ድርጊቶች ፣ እርሱ በዚህ ሕይወት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሚመጣው ጊዜም የዘላለምን ሕይወት በመስጠት ፣ ሕይወቱን ለእያንዳንዳችን በፈቃደኝነት ሰጠ።
በአስፈሪ ፈተናዎች ውስጥ ታማኝ በመሆን አስደናቂ ነግሮችን ያከናወኑ ሰዎች አይቻለሁ። ዛሬ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያሉ ሁሉ ምሳሌዎች ናቸው። ሰዎች በመከራ ውስጥ ትሁት ሆነዋል። በታማኝ ጽናታቸው እና ጥረታቸው፣ እንደ አዳኙ እና የሰማይ አባታችን መምሰል ይችላሉ።
ከእናቴ ሌላ ትምህርትን ተማርኩ። በልጅነቷ ዘጊ አናዳ ነበረባት እናም ልትሞት ተቃርባ ነበር። በመቀጠል የአከርካሪ ገትር በሽታ ገጠማት። አባቷ በልጅነቷ ስለሞተ እናቴ እና ወንድሞቿ እናታቸውን ይርዱ ነበር።
በህይወት ዘምኗ ሁሉ፣ የሕመም ፈተናዎችን ውጤቶች ተሰማት። በመጨረሻዎቹ 10 ዓመታት ሕይወቷ ውስጥ ብዙ ቀዶ ጥገናዎችን አስፈልጓት ነበር። ያም ሆኖ ግን፣ የአልጋ ቁራኛ እንኳን ሆና፣ ለጌታ ታማኝ መሆኗን አሳይታለች፣ በመኝታ ቤቷ ግድግዳ ላይ ያለው ብቸኛ ስዕል የአዳኙ ነበር። በሞት አፋፍ ላይ ሳለች ለእኔ የነበራት የመጨረሻ ቃሎቿ እነዚህ ነበሩ፤ “ሃል ጉንፋን የያዘህ ይመስላል። እራስህን መጠበቅ አለብህ።”
በቀብር ሥነ ሥርዓቷ ላይ የመጨረሻው ተናጋሪ ሽማግሌ ስፔንሰር ደብሊው ኪምቦል ነበር። ስላሳለፈችው ፈተና እና ታማኝነቷ ከተናገር በኋላ፣በዋነኛነት ግን እንዲህ አለ፤ “ሚልሬድ ለብዙ ጊዜና እና ለረዥም ጊዜ ለምን እንደተሰቃየች አንዳንዶቻችሁ ይገርማችሁ ይሆናል። ለምን እንደሆን እነግራችኋልሁ። ምክናያቱም ጌታ ለፈትናት ስለፈለጋት ነበር።”
ጌታ እንደዘጋጁ በፈገለገ መጠን በጽኑ እምነት ሸክሞቻቸውን የተሸከሙ እና ሌሎች ሸክማቸውን እንዲሸከሙ ለሚረዱ ለእየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በርካታ ታማኝ አባላት ምስጋናዬን አቀርባልሁ። እነሱም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው እንዲህ ያሉ ፈታኝ ሁኔታዎችን ተቋቋሙው በአለም ዙሪያ ላሉ ሌሎችን ለሚያገልግሉ አገልጋዩች እና መሪዎች ፍቅሬንና እድናቆቴን እገጻለሁ።
የሚወደን የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን እመሰክራለሁ። ፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰን ለሁላችንም ያለው ፍቅር ይሰማኛል። የአሁኑ አለም የጌታ ነብይ ነው። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም እመሰክራለሁ ፣ አሜን።