አጠቃላይ ጉባኤ
ዝም በል፥ ፀጥ በል
የጥቅምት 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


11:0

ዝም በል፥ ፀጥ በል

አዳኙ ንፋሶች በዙሪያችን በጽኑ ሲነፍሱ እና ወጀቦች ተስፋችንን ለማስመጥ ሲያስፈራሩን እርሱ ሰላም እና ጸጥታ እንዲሰማን ያስተምረናል።

ልጆቻችን ወጣት ሳሉ፣ ቤተሰባችን በሚያምር ሀይቅ ላይ ጥቂት ቀናትን አሳልፍን። በአንድ ከሰአት በኋላ ላይ የተወሰኑ ልጆች ወደ ውሃው ከመዝለላችው በፊት የህይወት ጃኬት አጠለቁ። ትንሿ ሴት ልጃችን ወንድም እና እህቶቿን በጥንቃቄ በማጤን፣ በማመንታት ተመለከተች። ባላት ብርታት ሁሉ ተጠቅማ፣ በአንድ እጇ አፍንጫዋን ያዘች እና ዘለለች። በተደናገጠ ድምጽ ወዲያውኑ ብቅ አለች እና “እርዱኝ! እርዱኝ!” ብላ ጮኸች።

በህይወት አደጋ ላይ አልነበረችም በዚያ ሰአት፤ የህይወት ጃኬቷ ስራውን እየሰራ ነበር እናም በደህንነት እየተንሳፈፈች ነበር። በጥቂት ጥረት ወደ እርሷ ደርሰን እና ወደ ወለሉ ጎትተን መመለስ እንችል ነበር። ግን፣ በእርሷ እይታ፣ እርዳታ ያስፈልጋት ነበር። ምናልባትም የውሃው ቀዝቃዛነት ወይም ለተሞክሮው አዲስ ስለሆነች ይሆናል። የሆነው ሆኖ፣ ወደ ወለሉ ተመልሳ ወጣች፣ እዛም እኛ በደረቅ ፎጣ ጠቀለልናት እና ስለ ጀግንነቷ አሞገስናት።

ሽማግሌዎች እንሁን ወጣት፣ በጭንቀት ወቅቶች፣ አብዛኞቻችን እንደ “እርዱኝ!” “አድነኝ!” ወይም “እባክህ፣ ጸሎቴን መልስ!” አይነት የጥድፊያ ቃላቶችን እንላለን።

እንደዚህ አይነት ክስተት በኢየሱስ ምድራዊ አግልግሎት ጊዜ በደቀመዛሙርቱ ላይ ተከስቶ ነበር። በማርቆስ ውስጥ ኢየሱስ “በባሕር ዳር ሊያስተምር ጀመረ። እጅግ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ ስለ ተሰበሰቡ፤”1 ህዝቡ በጣም ከመብዛታቸው የተነሳ “በታንኳ ገብቶ”2 እና ከወለሉ ሆኖ ላይ ተናገረ። ህዝቡም ከዳርቻው እንደተቀመጡ እርሱ ሙሉ ቀን በምሳሌ አስተማራቸው።

“በዚያም ቀን በመሸ ጊዜ፣” ለደቀመዛሙርቱ “ወደ ማዶ እንሻገር አላቸው። ሕዝቡንም ትተው፣”3 ከዳርቻው ሄዱ እና ወደ ገሊላ ሀይቅ በመጓዝ ላይ ነበሩ። ከመርከቧ ኋለኛ ቦታ በማግኘት፣ ኢየሱስ ጋደም አለ እና እንቅልፍ በቶሎ ወሰደው። ብዙም ሳይቆይ “ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውኃ በመርከቧ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በመርከቧ ይገባ ነበር።”4

አብዛኞቹ የኢየሱስ ደቀመዛሙርቶች ልምድ ያላቸው አሳ አጥማጆች ነበሩ እና በማእበል ውስጥ ታንኳን እንዴት መቆጣጠር እንዳለባቸው ያውቁ ነበር። እነርሱ በእርግጥም የእርሱ ታማኞች፣ የተወደዱ ደቀመዛሙርቱ ነበሩ። ኢየሱስን ለመከተል ስራዎችን፣ የግል ህይወቶችን፣ እና ቤተሰብ ትተዋል። በመርከቧ መገኘታቸው በእርሱ ላላቸው እምነት ማሳያ ነበር። እና አሁን ታንኳቸው በማእበል መሀከል እና በመስመጥ ላይ ነበር።

ለምን ያህል ጊዜ መርከቧ በመንሳፈፍ እንድትቀጥል ለማድረግ እንደታገሉ አናውቅም፣ ግን እንዲህ በማለት በመደናገጥ ድምጽ ኢየሱስን ቀሰቀሱት፤

“መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን?”5

“ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን፣”6

“ጌታ፣” ብለው ጠሩት፣ በእርግጥም ጌታ ነው። እናም እርሱም “ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የሰማይና የምድር አባት፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ የሁሉም ነገር ፈጣሪ” ነው።7

ዝም በል፥ ፀጥ በል

በመርከቧ ከነበረበት ቦታ፣ ኢየሱስ ተነሳ እና ንፋሱን አዘዘው እናም የሚናጋውን ባህር እንዲህ አለው፣ “ዝም በል፥ ፀጥ በል። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ።8 የሁሌውም ጌታ መምህር፣ ኢየሱስ በሁለት ቀላል ነገር ግን ተወዳጅ ጥያቄዎች አስተማራቸው። እንዲህ ጠየቀኝ።

“እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምን ነው?”9

“እንዴትስ እምነት የላችሁም?”10

እራሳችንን በፈተናዎች፣ ችግሮች፣ ወይም መከራዎች ውስጥ ስናገኝ፣ ምድራዊ ግፊት አለ “መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አድነኝ።” ብሎ የሚያስጮህ። ጆሴፍ ስሚዝ እንኳ ከአስከፊው እስር ቤት ሆኖ ተማጸነ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፣ የት ነህ? እና የተሰወርክበትን ስፍራ የሚሸፍነው ድንኳን የት ነው?”11

በእርግጥም፣ የአለም አዳኝ ምድራዊ ገደቦቻችንን ያውቃል፣ ንፋሶች በዙሪያችን በጽኑ ሲነፍሱ እና ወጀቦች ተስፋችንን ለማስመጥ ሲያስፈራሩን እርሱ ሰላም እና ጸጥታ እንዲሰማን ያስተምረናል።

የተረጋገጠ እምነት፣ እንደ ልጅ የሚያምኑ ወይም በጣም ቅንጣት እንኳ እምነት ላላቸው12 ኢየሱስ እንዲህ በማለት ይጋብዛል “ወደ እኔ ኑ”፤13 “በስሜም እመኑ”14 “ከእኔ ተማር፣ እናም ቃላቴን አድምጥ።”15 እርሱ በርህራሄ ያዛል፣ “ንስሃ [ግቡ] እና በስሜ [ተጠምቁ]፣”16 “እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ”17 እናም “ሁልጊዜ እኔን እንድታስታውሱ።”18 ኢየሱስ በማረጋገጥ፣ ሲያብራራ፣ “በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲኖራችሁ ይህን ተናገሬአችኋለው። በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዧችሁ፤ እኔ አለምን አሸንፌአለሁ።”19

የኢየሱስ ክርስቶስን ደቀመዛሙርት በማእበል በምትናጠው መርከቧ ሆነው፣ እርዳታ በመፈለግ፣ ወጀቡ ከመርከቧ ወለሉ ጋር ሲጋጭ እና ውሃውን ወደ ላይ ሲያወጣው አትኩረው ሲመለከቱ የነብረውን መገመት እችላለሁ። ሸራዎቹን ሲይዙ እና በትንሿ የእጅ ስራቸው ላይ ሚዛናዊ ቁጥጥር እንዲኖር ሲሞክሩ በኣእምሮዬ መሳል እችላለሁ። የእነርሱ ትኩረት በዛች አፍታ ህይወታቸውን ማትረፍ ነበር፣ እና ለእርዳታ ተማጽኗቸው በአስቸኳይ ልባዊ ነበር።

አብዛኞቻችን በጊዜያችን ከዛ የተለየን አይደለንም። የቅርቡ በአለም ዙሪያ፣ በሀገራቶች፣ በማህበረሰባችን፣ እና ቤተሰቦች የነበሩት ክስተቶች ያልተጠበቁ ፈተናዎችን ደርድረውብናል። በጭንቀት ጊዜያት እምነታችን ከጽናታችን እና መረዳታችን ልክ ድረስ ሲዘረጋ ሊሰማን ይችላል። የፍራቻ ወጀቦች የእግዚአብሔርን መልካምነት እንድንረሳ በማድረግ፣ አመለካከታችንን አጭር እይታ እንዲኖረው እና ከትኩረት ውጪ ሆኖ እንዲቀር ያደርጋሉ። ገናም በእነዚህ አስቸጋሪ የውጥረት ጉዟችን ውስጥ ነው እምነታችን የሚሞከረው እናም የሚጠነክረው።

ሁኔታዎቻችን ምንም ይሁኑ፣ ሆን ብለን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነታችንን ለመገንባት እና ለማጎልበት ጥረት ማድረግ እንችላለን። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን እና እርሱ እንደሚወደን ስናስታውስ እምነታችን ይጠነክራል። የክርስቶስን ትምህርቶች በተቻለን መጠን ለመከተል በመሞከር፣ የእግዚአብሔርን ቃል በተስፋ እና ትጋት ስንለማመድ እምነታችን ያድጋል። ከመጠራጠር ይልቅ ለማመን፣ ከመፍረድ ይልቅ ይቅር ለማለት፣ ከማመጽ ይልቅ ንስሃ ለመግባት ስንመርጥ እምነታችን ይጨምራል። በቅዱሱ መሲህ መልካምነቶች፣ ምህረት፣ እና ጸጋ ላይ በትግስት ስንደገፍ እምነታችን ይታደሳል።20

“እምነት ፍጹም የሆነ እውቀት ባይሆንም፣” ሽማግሌ ኔይል ኤ. ማክስዌል እንዳሉት፣ “እውቀቱ ፍጹም ወደሆነው፣ በእግዚአብሔር ላይ ጥልቅ መተማመንን ያመጣል።”21 በአስቸጋሪ ጊዜያትም እንኳን፣ ጽኑ እና የሚቋቋም ነው። አላስፈላጊ ከሆኑ መሰናከያዎች እንድንጠራ ያግዘናል። በቃል-ኪዳኑ መንገድ ላይ በመጓዝ እንድንቀጥል ያበረታናል። እምነት ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ያበረታታናል እና የወደፊቱን በመፍትሄ እና በድፍረት እንድንጋፈጥ ያደርጋል። ወደ አብ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስንጸልይ ለመዳን እና እፎይታን እንድንጠይቅ ይገፋፋናል። ጸሎታዊ ተማጽኖዎች ያልተመለሱ ሲመስሉ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለን ጽኑ እምነት ትግስትን፣ ትህትናን፣ እና በማክበር “እንደ ፍቃድህ ይሁን” የሚሉትን ቃላት እንድንል አቅምን ያመንጭልናል።22

ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳስተማሩት፥

“ፍርሃቶቻችን እምነታችንን እንዲያዛቡት መፍቀድ የለብንም። እነዚያን ፍራቻዎች እምነታችንን በማጠንከር ማሸነፍ እንችላለን።

“ከልጆቻችሁ ጀምሩ። … እምነታችሁ እንዲሰማቸው አድርጉ፣ ከባድ ፈተናዎች ወደ እናንተ ቢመጡ እንኳ። በአፍቃሪ ሰማያዊ አባት እና በተወዳጅ ልጁ፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነታችሁን ያተኮር እንዲሆን አድርጉ፡፡… ውድ ወንድ እና ሴት ልጆች የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆኑ፣ በቅዱስ አላማ እና አቅም በአምሳሉ እንደፈጠራቸው አስተምሯቸው። ተግዳሮቶችን ለማሸነፍ እና እምነትን ለማጎልበት ነው እያንዳንዱ የተወለዱት።”23

በቅርብ “ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ነው የሚረዳን?” ለሚለው ጥያቄ ሁለት የአራት አመት ልጆች በመመልስ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት ሲያካፍሉ ሰማሁ። የመጀመሪያው ልጅ እንዲህ አለ፣ “ኢየሱስ እንደሚወደኝ አውቃለሁ ምክንያቱም ለእኔ ሞቷል። ጎልማሶችንም ይወዳል።” ሁለተኛው ልጅ እንዲህ አለ፣ “እኔ ሳዝን ወይም ነጭናጫ ስሆን ይረዳኛል። ስሰምጥ እርሱ ይረዳኛል።”

ኢየሱስ አወጀ፡ “ስለዚህ ንሰሃ የሚገባን እናም እንደህፃን ልጅ ወደ እኔ የሚመጣንም እቀበለዋለሁ፣ የእግዚአብሔር መንግስትም እንደነዚህ ላሉት ናትና።”24

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።25

በቅርብ፣ ፕሬዘዳንት ኔልሰን ቃል ገቡ “ በትክክል እንድትሰሙ፣ እንድትገነዘቡ እና የአዳኙን ቃላት ማዳመጥ” ስንጀምር “የፍራቻ መቀነስ እና የእምነት መጨመር ይከተላል።”26

ኢየሱስ ባህሩን ጸጥ ሲያደርግ

እህቶች እና ወንድሞች፣ አሁን ያለንበት ፈታኝ ሁኔታዎች የመጨረሻ ዘላለማዊ መድረሻችን አይደሉም። እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባልነታችን፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በቃል-ኪዳን በላያችን ላይ ወስደናል። በእርሱ የቤዛነት ሃይል ላይ እምነት አለን እና በታላቅ እና ውድ ቃልኪዳኖቹ ተስፋ እናደርጋለን። ለመደሰት ሁሉም ምክኒያቶች አሉን፣ ጌታችን እና አዳኛችን የእኛን ችግሮች፣ ሃሳቦች፣ ሀዘኖች በጥልቅ ያውቃል። ኢየሱስ ከድሮው ደቀመዛሙርቱ ጋር እንደነበረው ሁሉ፣ እርሱ በእኛም ታንኳ ላይ አለ። እናንተ እና እኔ እንዳንጠፋ እርሱ ህይወቱን እንደሰጠ እመሰክራለሁ። በእርሱ እንተማመን፣ ትዛዛቱን እንጠብቅ፣ እና በእምነት፣ “ዝም በል፥ ፀጥ በል።”27ሲል እናዳምጥ። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።