በትክክል ተግብሩ፣ ምህረትን ውደዱ እና ከእግዚአብሔር ጋር በትህትና ተጓዙ
በትክክል መተግበር ማለት በክብር መስራት ማለት ነው። በትህትና ከእግዚአብሔር ጋር ስንጓዝ አብረነው በክብር እንተገብራለን። ምህረትን በመውደድ ከሌሎች ጋር በክብር እንተገብራለን።
እንደ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች እና እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳናት፣ የተሻለን ለመስራትና የተሻለ ለመሆን እንጥራለን እንዲሁም እንድንጥር እንበረታታለን።1 “በቂውን እያደረኩኝ ይሆን?” እንዴ ብላችሁ ምናልባት እንደ እኔ ተገርማችሁ ሊሆን ይችላል። “ሌላስ ምን ማድረግ ይገባኛል?” ወይም “ፍፁም እንዳለመሆኔ ‘ፍፃሜ በሌለው ደስታ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር’ እንዴት ብቁ ልሆን እችላለሁ?”2
የብሉይ ኪዳን ነቢይ ሚክያስ ጥያቄውን በእንደዚህ ዓይነት መልኩ ጠየቀ፥ “ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ?”3 ሚክያስ በምጸት ከመጠን በላይ የሆነ ስጦታዎች ለሃጢያት መካሻ በቂ ይሆን ብሎ እንዲህ በማለት ተገረመ፣ “እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጎች ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? የበኩር ልጄን ስለበደሌ … ሃጢያት እሰጣለሁን?”4
መልሱ አይደለም ነው። መልካም ስራዎች በቂ አይደሉም። ደህንነት የተገኘ አይደለም።5 ሚክያስ የማይቻል መሆናቸውን የተገነዘበው ሰፊ መስዋእት እንኳን ትንሹን ኃጢአት ቤዛ ሊያደርግ አይችልም። ራሳችን በምናደርገው ብንተው፣ ወደ እግዚአብሔር መገኛ የመመለስ አላማው ተስፋ ቢስ ነው።6
ያለሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ በረከቶች፣ በቂ ማድረግም ሆነ በራሳችን በቂ መሆን አንችልም። መልካሙ ዜና ግን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በቂ መሆን መቻላችን ነው።7 ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ጸጋ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ በኩል ከስጋዊ ሞት ይድናሉ።8 ልባችንን ወደ እግዚአብሔር ከመለስን፣ “በኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ አማካኝነት … ለወንጌል ህግጋቶቹና ስነስርዓቶቹ በመታዘዝ” ከመንፈሳዊ ሞት መዳን መቻል ለሁሉም የተሰጠ ነው።9 ከእግዚአብሔር ፊት ለመቆም የሃጢያት ስርየት ማግኘት እንችላለን። ሚክያስ እንደገለፀው፣ “ሰው ሆይ መልክሙን ነግሮሃል እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድን ነው፣ ፍርድን ታደርግ ዘንድ ምህረትንም ትወድ ዘንድ ከአምላክህም ጋር በትህትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?”10
ልባችንን ወደ እግዚአብሔር ስለመመለስ እና ለደህንነት ብቁ ስለመሆን ሚክያስ ያጠቆመው ሶስት አብረው የተያያዙ ንጥረ ነገሮች አሉት። በትክክል መተግበር ማለት ከእግዚአብሔርና ከሌሎች ሰዎች ጋር በክብር መተግበር ማለት ነው። በትህትና ከእግዚአብሔር ጋር ስንጓዝ አብረነው በክብር እንተገብራለን። ምህረትን በመውደድ ከሌሎች ጋር በክብር እንተገብራለን። ስለዚህ በትክክል መተግበር “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ” የሚለውን የመጀመሪያውና የሁለተኛው ታላቅ ትዕዛዝ ተግባራዊ ማመልከቻ ነው።11
በትክክል መተግበር እና በትህትና ከእግዚአብሔር ጋር መጓዝ ከበደል እጃችንን ማንሳት፣ በህጎቹ መጓዝ እና በእውነት ታማኝ መሆን ማለት ነው።12 ቸር ግለሰብ ፊቱን ከሃጢያት ያዞራል ወደ እግዚአብሔር ደግሞ ይዞራል፣ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳኖችን ያደርጋል እንዲሁም እነዚያን ቃል ኪዳኖችም ያከብራል። ቸር ሰው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለማክበር ይመርጣል፣ ሲሳሳት ንስሃ ይገባል እንዲሁም መሞከሩን ይቀጥላል።
ትንሳኤ ያደረገው ክርስቶስ ኔፋውያኖችን ሲጎበኝ፣ የሙሴ ህግ በከፍተኛ ህግ እንደተተካ ገለፀ። “መስዋዕትን እና የተቃጠለ ስጦታዎችን እንዳያቀርቡ” ነገር ግን “የተሰበረ ልብንና የተዋረደ መንፈስን” እንዲያቀርቡ አስተማረ። እንዲሁም ቃል ገባ፣ “ወደ እኔም በተሰበረ ልብና በተዋረደ መንፈስ የሚመጣ በእሳትና በመንፈስ ቅዱስ አጠምቀዋለሁ።”13 ከጥምቀት በኋላ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ስንቀበልና ስንጠቀም ዘለቄታ ያለውን የመንፈስ ቅዱስ አብሮነት እናጣጥማለን እናም ማድረግ ያለብንን ሁሉንም ነገር እንማራለን፣14 እንዴት በትህትና ከእግዚአብሔር ጋር መጓዝ እንዳለብን ጨምሮም።
የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት እና ከመንፈሳዊ ሞት የማዳን መስዋትነት የተሰበረ ልብና የተዋረደ መንፈስ ላላቸው ሁሉ የተሰጠ ነው።15 የተሰበረ ልብና የተዋረደ መንፈስ የበለጠ እንደ ሰማይ አባታችንና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድንሆን በደስታ ንስሃ እንድንገባ ያስታውሰናል። ይህን ስናደርግ የአዳኙን የሚያነፃ፣ የሚፈውስና የሚያጠነክር ኃይል እንቀበላለን። በትክክል መተግበርና ከእግዚአብሔር ጋር በትህትና መጓዝ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ የሰማይ አባትና ኢየሱስ ክርስቶስ ምህረትን መውደድንም ጨምሮ እንማራለን።
እግዚአብሔር በምህረት ይደሰታል እናም በዚህ መጠቀማችንን ይፈቅዳል። ሚክያስ ለያህዌ ባለው ቃላት “በደልን ይቅር የሚል እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው፣ … ምህረትን የሚወድ ” እና “ሃጢያታችንንም በባህሩ ጥልቅ የሚጥል።”16 እግዚአብሔር እንደሚያደርገው ምህረትን መውደድ ከሌሎች ጋር በትክክል ከመተግበርና እነርሱን ካለማጉላላት ጋር በማይለይ መልኩ ተያይዞ ይገኛል።
ሌሎችን ያለማጉላላት ጥቅም ከክርስቶስ በፊት በኖረው የአይሁድ ምሁር በሽማግሌ ሂለል ማስታወሻ ላይ ተሰምሯል። የሂለል አንድ ተማሪ በቶራህ ውስብስብነት፣ እንዲሁምአምስቱ የሙሴ መጽሐፎች ከ613 ትዕዛዛቸው ጋር እና አብሯቸው ባለ የራቢኒክ ፅሁፎች ተበሳጭቶ ነበር። ተማሪው ሂለልን በአንድ እግሩ ብቻ ለመቆም በሚችልበት ጊዜ ብቻ ስለቶራህን እንዲያብራራ ጠየቀው። ሂለል ራሱን ቀና በማድረግ መጠበቅ ባይችልም፣ ነገር ግን ውርርዱን ተቀበለ። ከዘሌዋውያን እንዲህ ሲል ጠቀሰ፣ “አትበቀልም በህዝብህም ልጆች ቂም አትያዝ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።”17 ሂለል ከዚያም እንዲህ በማለት ደመደመ፥ “ጥላቻ የሆነን ለጎረቤትህ አታድርግ። የቶራህ ሙሉ ነጥብ ይሄ ነው፣ ቀሪው ሐተታ ነው። ሂድና አጥና።”18
ሁልጊዜ ከሌሎች ጋር በክብር መስራት ምህረትን የመውደድ አካል ነው። በባልቲሞር፣ ሜሪላንድ ዩኤስኤ ውስጥ በሚገኘው በጆንስ ሀፕኪንስ ሆስፒታል በድንገተኛ ክፍል ውስጥ ከአስርተ ዓመታቶች በፊት የሰማሁትን ንግግር ተመልከቱ። ታማሚው አቶ ጃክሰን ትሁት፣ ደስ የሚል በጣም የታወቀ የሆስፒታል ሰራተኛ ነበር። ከመጠጥ ጋር ተያያዠነት ባለው በሽታ ከዚህ በፊት በሆስፒታል ለብዙ ጊዜ ሄዶ ያውቃል። በዚህ ወቅት አቶ ጃክሰን በመጠት አማካኝነት በሚመጣ የጣፊያ መለብለብ ስሜት ለመመርመር ወደ ሆስፒታል ተመለሰ።
የቀን ስራው ወደማለቁ አካባቢ በጣም ታታሪውና የተደናቂው ሐኪም ዶክተር ኮኸን፣ አቶ ጃክሰንን ከመረመረ በኋላ ሆስፒታል ውስጥ መታከም እንዳለበት ወሰነ። ዶክተር ኮኸን በልውውጥ ቀጥላ ያለችውን ሐኪም ዶክተር ጆንስን አቶ ጃክሰንን ተቀብላ ህክምናውን እንድትከታተል መደባት።
ዶክተር ጆንስ በታዋቂ የህክምና ትምህርት ቤት ገብተው የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን ሊጀምሩ ነበር። ይህ አሰቃቂ ሥልጠና ብዙውን ጊዜ ከእንቅልፍ እጦት ጋር ይዛመዳል፣ ይህም ምናልባት ለዶክተር ጆንስ አሉታዊ ምላሽ አስተዋጽኦ አድርጓል። በምሽቱ አምስተኛ ታማሚ ሰው ጋር በመጋፈጥ፣ እርሷም ከፍ በሚል ድምፅ ለዶክተር ኮኸን ቅሬታዋን አቀረበች። ምንም እንኳን አቶ ጃክሰን በራሱ ላይ ያመጣው ችግር ቢሆንም፣ ብዙ ሰዓታትን እሱን በመንከባከብ ማጥፋት ተገቢ አይደለም ብላ ተሰማት።
የዶክተር ኮኸን ምላሽ ሹክሹክታ በሚመስል ንግግር ነበር የተነገረው። እንዲህ አለ፣ “ዶክተር ጆንስ፣ ሐኪም የሆንሽው ሰዎችን እንድትንከባከቢ እና እነርሱን ለመፈወስ ለመስራት ነው። እነሱ ላይ ለመፍረድ አይደለም ሐኪም የሆንሽው። ልዩነቱን ካተረዳሽ፣ በዚህ ተቋም ውስጥ ለመለማመድ መብት የለሽም።” ይህንን ማስተካከያ ተከትሎ፣ ዶክተር ጆንስ አቶ ጃክሰንን በሆስፒታል ቆይታው ወቅት በትጋት ተከታተለች።
ከእዚያ ጊዜ በኋላ አቶ ጃክሰን ሞቷል። ሁለቱም ዶክተር ጆንስ እና ዶክተር ኮኸን በስራቸው አስደናቂ ነበሩ። ነገር ግን በልምምድ ወሳኝ ወቅቷ ውስጥ፣ ዶክተር ጆንስ በትክክል መተግበር፣ ምህረትን መውደድና አቶ ጃክሰንን ሳትፈርድ መንከባከብ እንዳለባት ማስታወስ አስፈልጓት ነበር።19
በዓመታት ውስጥ ከዚያ ማስታወሻ ተጠቃሚ ሆኛለሁ። ምህረትን መውደድ ማለት እግዚአብሔር የሚያበረክተውን ምህረት ብቻ እንወዳለን ማለት አይደለም፣ እግዚአብሔር ተመሳሳይ ምህረትን ለሌሎችም በማበርከቱ እንደሰታለን ማለት ነው። እናም የእርሱን ምሳሌ እንከተላለን። “በእግዚአብሔር ፊት ሁሉም አንድ ነው፣”20 እናም ለመረዳትና ለመፈወስ ሁላችንም መንፈሳዊ እንክብካቤን እንሻለን። ጌታ እንዲህ አለ፣ “እናንተ አንዱን ሰው ከሌላው አታስበልጡ፣ ወይም ማንም እራሱን ከሌላው በላይ ከፍ አያድርግ።”21
በትክክል መተግበርና ምህረትን መውደድ ምን ማለት እንደሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ አሳይቷል። በአክብሮት በመንከባከብ ከሃጢያተኞች ጋር በነፃ ተባበረ። የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የመጠበቅን ደስታ አስተማረ እንዲሁም የሚቸገሩ ሰዎችን ከመፍረድ ይልቅ ከፍ ለማድረግ አሻ። ብቁ አይደሉም ብለው ላሰቡት ሰዎች በማገልገል ስህተት እንደሚያደርግ ያስቡበትን ሰዎች ነቀፈ።22 እንዲህ ዓይነቱ ራስን ማመፃደቅ ቅር አሰኝቶታል አሁንም እንዲህ ያደርገዋል።23
ክርስቶስ መሰል ለመሆን፣ አንድ ግለሰብ በትክክል ይተገብራል፣ ከእግዚአብሔርና ከሌሎች ሰዎች ጋር በክብር ራሱን ይመራል። ትክክለኛ ሰው በቃሎቹና በተግባሩ ትሁት ነው እናም በአስተሳሰብ ወይም በእምነት መለያየት እውነተኛ ቅንነትን እና ጓደኝነትን እንደማይገታ ያስተውላል። በትክክል የሚተገብሩ ግለሰቦች “እርስ በእርስ ለመቆሳሰል አያስቡም፣ ነገር ግን በሰላም መኖርን እንጂ።”24
ክርስቶስ መሰል ለመሆን አንድ ግለስብ ምህረትን ይወዳል። ምህረትን የሚወዱ ሰዎች ፈራጆቸ አይደሉም፤ ለሌሎች ርህራሄን ያንፀባርቃሉ፣ በተለይም ላልቀናላቸው ለሌላቸው ሰዎች፤ ደግ፣ ቅን እና አክባሪ ናቸው። እነዚህ ግለሰቦች ዘርን፣ ፆታን፣ ሐይማኖትን፣ የፍቅር ስበትን፣ ገንዘብን፣ ነገድን፣ ወይም ሃገራዊ ልዩነትን ሳያካትት ሁሉንም በፍቅርና በመረዳት ይንከባከባሉ። እነዚህ በክርስቶስ መሰል ፍቅር የተተኩ ናቸው።
ክርስቶስ መሰል ለመሆን፣ አንድ ሰው እግዚአብሔርን ይመርጣል፣25 ከእርሱ ጋር በትህትና ይጓዛል፣ እርሱን ሊያስደስት ይሻል እናም ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳኖችን ይጠብቃል።. ከእግዚአብሔር ጋር በትህትና የሚጓዙ ግለሰቦች የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ለእነሱ ምን እንዳደረጉላቸው ያስታውሳሉ።
በቂ ነገር እያደረኩኝ ነውን? ሌላ ምን ማድረግ ይኖርብኛል? ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ የምንወስደው ተግባር ለዚህ ሕይወት እና ለዘለአለማዊነት ደስታችን ማዕከላዊ ነው። አዳኙ መዳንን ቀለል አድርገን እንድንወስድ አይፈልግም። ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን ከገባን በኋላ፣ “ከጸጋው ወድቀን ከህያው እግዚአብሔር” ለመለየት የሚያስችል ሁኔታ አለ። ስለዚህ፣ “ወደ ፈተና” መውደቅን ለማስወገድ “መስማት እና ሁሌም መጸለይ” ይኖርብናል።26
ነገር ግን በተመሳሳይ ሁኔታ የሰማይ አባታችንና ኢየሱስ ክርስቶስ በሟች ጉዟችን ወቅት ለመዳን እና ከፍ ለማለት በቂ ነገር ማድረጋችንን በማሰብ ቀጣይነት ባለው አለመረጋጋት እንድንንደነዘዝ አይፈልጉም። ንስሃ በገባነው ስህተቶች፣ እንደማይድኑ ቁስሎች በማሰብ፣27 ወይም በድጋም እንደናቀፋለን ብለን በመጨነቅ እንድንሰቃይ በፍፁም አይፈልጉም።
የራሳችንን መሻሻል መገምገም እንችላለን። “የምንከተለው የህይወት ጎዳና በእግዚአብሔር ፍቃድ እንደሆነ” ማወቅ የምንችለው28 በትክክል ስንተገብር፣ ምህረትን ስናፈቅር፣ እናከእግዚአብሔር ጋር በትህትና ስንጓዝ ነው። የሰማይ አባትንና የኢየሱስ ክርስቶስን ባህርያት እንለብሳለን እንዲሁም እርስ በእርስ እንዋደዳለን።
እነዚህን ነገሮች በምታደርጉበት ጊዜ የቃል ኪዳን መንገድን ትከተላላችሁ፣ እንዲሁም “ፍፃሜ በሌለው ደስታ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ትኖራላችሁ።”29 ነፍሳችሁ በእግዚአብሔር ክብር እና በዘለአለማዊ ህይወት ትሞላለች።30 ለመገለፅ በማይቻል ደስታ ትሞላላችሁ።31 እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ እና ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አዳኛችንና መዳኒታችን እንደሆነ፣ እናም እርሱም በፍቅር እና በደስታ ምህረቱን ለሁሉም እንደሚሰጥ እመሰክራለው። ይህስ የምትወዱት አይደለምን! በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።