“ግንቦት 6–12 (እ.አ.አ): “በጌታ ጥንካሬ” ሞዛያ 7–10፤ “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]
“ግንቦት 6–12 ሞዛያ 7–10 “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]
ግንቦት 6–12 : “በጌታ ጥንካሬ”
ሞዛያ 7–10
የንጉሥ ሞዛያ ሕዝብ በዛራሔምላ “[ባለማቋረጥ] ሰላም” እየተደሰቱ ሳለ (ሞዛያ 7፡1)፣ ሀሳባቸው ከብዙ አመታት በፊት በሌሂ-ኔፊ ምድር ይኖሩ ወደነበሩ ሌላ የኔፋውያን ቡድን ዞረ። ትውልዶች ቢያልፉም የሞዛያ ሰዎች ስለ እነሱ ምንም አልሰሙም። ስለዚህ፣ ሞዛያ የሄዱትን ኔፋውያንን ለማግኘት የፍለጋ ቡድን እንዲመራ አሞንን ጠየቀ። የፈላጊው ቡድን እነዚህ ኔፋውያን፣ “በክፋት ምክንያት” (ሞዛያ 7፡24)፣ በላማናውያን ግዞት ውስጥ እንደነበሩ አወቀ። ነገር ግን በአሞን እና በወንድሞቹ መምጣት በድንገት የመዳን ተስፋ ነበር።
አንዳንድ ጊዜ በኃጢአታችን ምክንያት እየተሰቃየን፣ እንዴት እንደገና ሰላም እንደምናገኝ እያሰብን እንደ እነዚህ የተማረኩ ኔፋውያን እንሆናለን። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እንደ አሞን ነን፣ ሌሎችን ለማግኘት በመነሳሳት እና በመጨረሻም “[ራሳቸውን እንዲያቀኑና እንዲደሰቱ በእግዚአብሔር እንዲታመኑ]” (ሞዛያ 7፡19) ጥረታችን እንዳነሳሳቸው እናገኛለን። ሁኔታችን ምንም ይሁን ምን፣ ሁላችንም ንስሀ መግባት እና “በሙሉ ልብ ወደ ጌታ መዞር አለብን፣ እናም እሱ… ያድነናል” (ሞዛያ 7፡33)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር ሀሳቦች
ኢየሱስ ክርስቶስ እኔን ለማዳን ኃይል አለው።
ከአሞን ጋር መገናኘት ለንጉሥ ሊምሂ ተስፋ ሰጠው፣ እናም ያንን ተስፋ ለህዝቡ ማስተላለፍ ፈለገ። ምናልባት የእሱ ቃላቶች ለእናንተም ተስፋ ሊሰጧችሁ ይችላሉ። ለዐውደ-ጽሑፍ፣ በሞዛያ 7፡20–25 ውስጥ ያለውን የሊምሂን ሰዎች ሁኔታ ለመገምገም አስቡ። ሞዛያ 7፡14–33 ስታነቡ እነዚህን ጥያቄዎች አስቡባቸው፡-
-
ሊምሂ የህዝቡን እምነት እና በክርስቶስ ላይ ያላቸውን ተስፋ ለማጠናከር ምን አለ?
-
ተስፋ እንዲሰማችሁ የሚረዱት የትኞቹ ሐረጎች ናቸው? (ቁጥር 19፣33 ይመልከቱ)።
-
እግዚአብሔር ሊያድን እንደሚችል እና እንደሚያድናችሁ እንድትተማመኑ የረዷችሁ የትኞቹ ተሞክሮዎች ናቸው?
በተጨማሪም “የእስራኤል አዳኝ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 6 ይመልከቱ።
“በአምላክ አምሳል” ተፈጥሬአለሁ።
በሞዛያ 7፡26–27፣ ሊምሂ አቢናዲ ያስተማረውን አንዳንድ እውነቶች አብራራ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የትኞቹን እውነቶች መለየት ትችላላችሁ? እነዚህ እውነቶች ለእግዚአብሔር እና ለራሳችሁ ባላችሁ አመለካከት ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ?
በተጨማሪ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “አካላችሁ፡ ለመንከባከብ ታላቅ ስጦታ [Your Body: A Magnificent Gift to Cherish]፣” ሊያሆና፣ ነሃሴ 2019 (እ.አ.አ)፣ 50–55 ይመልከቱ።
ጌታ ለሰው ልጆች ጥቅም ነቢያትን፣ ባለራዕዮችን እና ገላጮችን ይሰጣል።
ሊምሂ ጌታ ገላጩን እንዳስነሳ የአሞንን ምስክርነት በሰማ ጊዜ ሊምሂ “እጅግ ተደሰተና ለእግዚአብሔርን ምጋናውን አቀረበ” (ሞዛያ 8፡19)። ለምን እንዲህ የተሰማው ይመስላችኋል? በሞዛያ 8፡13–19 ውስጥ ከአሞን ቃል ስለ ገላጮች ምን ትማራላችሁ?
ዛሬ ላይ፣ የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋርያትን ቡድን እንደ ነብያት፣ ባለ ራእዮች እና ገላጮች እንደግፋለን። ለእናንተ “ጠቃሚ” የሆኑት እንዴት ነው? (ሞዛያ 18፥18)። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን አስተማሯችሁ?
እናንተ እንደ አሞን፣ ስለ ነቢያት፣ ባለ ራእዮች እና ገላጮች አስፈላጊነት በድፍረት እንዴት መናገር ትችላላችሁ? (ሞዛያ 8፡13–18ን ይመልከቱ)። ለምሳሌ፣ ስለምን ጉዳይ ለቤተሰባችሁ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ማጋራት ትችላላችሁ፡-
-
በእኛ ዘመን በጆሴፍ ስሚዝ እና በሌሎች የጌታ ነቢያት የተመለሱ እውነቶች (እንደ የእግዚአብሔር ተፈጥሮ፣ መለኮታዊ ማንነታችን፣ ወይም የቤተሰብ ዘላለማዊነት)። “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በሙላት መመለስ” ወይም “ቤተሰብ፡ ለዓለም አዋጅ (የወንጌል ቤተ መጻሕፍት) የሚለውን መከለስ ከእነዚህ እውነቶች አንዳንዶቹን እንድታስቡ ሊረዳ ይችላል።
-
የትእዛዛት ወይም የስርዓቶች በረከቶች (እንደ የጥበብ ቃል፣ የንፅህና ህግ፣ ወይም የቤተሰብ መታተም)።
ባለፈው ወር በአጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ ነቢያትን፣ ባለ ራእዮችን እና ገላጮችን አድምጠናል። ምን መልእክቶች አነሳሷችሁ? በተማራችሁት መሰረት የተለየ ምን ታደርጋላችሁ? የጌታ ባለ ራእዮች ወደ ፊት “ሊሆኑ [ስለሚችሉ] ነገሮች” ምን አሉ? (ሞዛያ 8:17)።
በተጨማሪም የወንጌል አርእስቶች፣ “ነቢያትን፣” የወንጌል ቤተ መጻሕፍት ላይ ተመልከቱ።
ፈተናዎቼን “በጌታ ጥንካሬ” መቋቋም እችላለሁ።
ዘኒፍ ስህተቶቹ ህዝቦቹን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳስገባ ተናግሯል። በኋላ ግን፣ ከላማናውያን ጋር በተደረገው ጦርነት፣ ህዝቡ በጌታ በማመን ተግዳሮቶቻቸውን እንዲጋፈጡ ረድቷቸዋል። ሞዛያ 9–10ን ስታነቡ የዜኒፍ ሰዎች እምነታቸውን ለማሳየት ያደረጉትን ፈልጉ። እግዚአብሄር ያበረታቸው እንዴት ነው? እናንተንስ እንዴት አበረታ? “በጌታ ጥንካሬ ”መውጣት ለእናንተ ምን ማለት ነው? (ሞዛያ 9:17፤ 10:10–11 )
የእኔ ምርጫዎች በትውልዶች ላይ ተጽዕኖ ሊፈጥሩ ይችላሉ።
ሞዛያ 10፡11–17ን ስታነቡ፣ የቀደሙት የላማናውያን ትውልዶች ድርጊት እና አመለካከቶች በኋላ ባሉት ትውልዶች ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንዳሳደሩ ለዩ። ይህ ምርጫችሁ ገና ያልተወለዱ ሰዎችን ጨምሮ ሌሎችን በመልካምም ሆነ በመጥፎ እንዴት እንደሚነካ ምን ያሳያል?
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
እግዚአብሔር ሰዎችን በቅዱሳት መጻሕፍት ረድቷል፣ እኔንም ሊረዳኝ ይችላል።
-
ህዝቦቹ ችግር ውስጥ በነበሩበት ጊዜ፣ ንጉስ ሊምሂ እምነታቸውን ለመገንባት ቅዱሳት መጻህፍትን አካፍሏል። ልጆቻችሁ እምነት እንዲኖራቸው ስለሚረዷቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ታሪኮች ወይም ገጸ ባህሪያት ጠይቋቸው። ከዚያም ሞዛያ 7፡19ን ልታነቡላቸው እና በዚህ ቁጥር ውስጥ የተጠቀሱትን ታሪኮች መገምገም ትችላላችሁ (“ፋሲካ” እና “እስራኤላውያን በምድረ በዳ” በብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 70–76 ተመልከቱ)። ምናልባት ልጆቻችሁ ሊተውኗቸው ይፈልጉ ይሆናል። ጌታ በእነዚህ ታሪኮች ውስጥ ያሉትን ሰዎች የረዳቸው እንዴት ነው? እኛን እንዴት ሊረዳን ይችላል?
-
ጌታ እንዴት እንደሚረዳን ተጨማሪ ምሳሌዎችን ለማግኘት ከልጆቻችሁ ጋር የ“መፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች” ወይም “የኔፊ ድፍረት” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 118–19፣ 120–21) የተወሰኑ ስንኞችን ለመዘመር ምረጡ። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ጌታ ሰዎችን እንዴት እንደረዳቸው እና እኛን እንዴት እንደሚረዳን እንዲያውቁ እርዷቸው።
እግዚአብሔር ነቢያትን፣ ገላጮችን እና ባለ ራዕዮችን ሰጥቶናል።
-
ስለ ገላጮች ለማስተማር አንዱ መንገድ የተሻለ እንድናይ ከሚረዱን እንደ መነጽር፣ ባይኖኩላር ወይም ማይክሮስኮፕ ካሉ ነገሮች ጋር ማነጻጸር ነው። ከዚያም ሞዛያ 8፡17ን ለልጆቻችሁ ስታነቡ፣ “ገላጭ” የሚለውን ቃል በሰሙ ቁጥር ልክ በባይኖኩላር እየተመለከቱ እንደሆነ በማስመሰል እጆቻቸውን ዓይኖቻቸው ላይ ማድረግ ይችላሉ። (በተጨማሪም ሙሴ 6:35–36ን ተመልከቱ) በአንድነት ጌታ ነቢያት “እንዲያዩ” ስለሚረዳቸው እኛ ግን ስለማናያቸው ነገሮች ተነጋገሩ። እንደ ጆሴፍ ስሚዝ ያሉ ነቢያቶቻችን ወይም ገላጮች ምን ገለጹልን?
-
ሞዛያ 8፡16–18ን ከልጆቻችሁ ጋር ካነበባችሁ በኋላ፣ ገላጭ ልክ እንደ … እኛ … ይረዳናል አይነት ዓረፍተ ነገርን የሚያሟሉበትን መንገዶች እንዲያስቡ መርዳት ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ ገላጭ ወደ ኢየሱስ እንደሚጠቁም የትራፊክ ምልክት ነው።
-
እንዲሁም በወረቀት የእግር ኮቴዎችን በመስራት ልጆቻችሁን ነቢያት፣ ባለ ራእዮች እና ገላጮች እንድንሰራ የመከሩንን ነገሮች እንዲስሉባቸው መጋበዝ ትችላላችሁ። ኮቴዎቹን በክፍሉ ዙሪያ ባለ መንገድ ላይ አስቀምጡና ልጆች በእነዚህ ኮቴዎች ላይ እንዲራመዱ አድርጉ። ገላጭ “ጠቃሚ” ሊሆነን የሚችለው እንዴት ነው? (ሞዛያ 8፡17–18 ተመልከቱ)።
እኔ ስደክም ጌታ ሊያበረታኝ ይችላል።
-
ልጆች ችግሮች ሲያጋጥሟቸው አንዳንድ ጊዜ ደካማ እና አቅመ ቢስ እንደሆኑ ይሰማቸዋል። ልጆቻችሁ በጌታ ብርታት እንዲታመኑ የምትረዷቸው እንዴት ነው? በአካል ለመጠንከር ምን እንደምናደርግ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። “[የሰዎች] ጥንካሬ” ማግኘት ሲባል ምን ማለት ነው? (ሞዛያ 10፡11 ተመልከቱ)። “[የጌታን] ጥንካሬ” ማግኘት ሲባልስ ምን ማለት ነው? ( ሞዛያ 9:17–18፤ 10:10 ተመልከቱ)። የጌታን ጥንካሬ እንዴት እንቀበላለን? ልጆቻችሁ የጌታን ብርታት እንዲቀበሉ የሚያግዟቸውን ነገሮች ምስል መሳል ይችላሉ።