“ሰኔ 3–9 (እ.አ.አ): ‘ፅኑ እና የማይነቃነቁ’ ሞዛያ 29-አልማ 4፤ “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]
“ሰኔ 3–9 ሞዛያ 29-አልማ 4፤ “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]
ሰኔ 3–9 (እ.አ.አ): “ፅኑ እና የማይነቃነቁ”
ሞዛያ 29–አልማ 4
አንዳንዶች ንጉሥ ሞዛያ ነገሥታትን በተመረጡ ዳኞች ለመተካት ያቀረበውን ሐሳብ እንደ ጥሩ የፖለቲካ ማሻሻያ አድርገው ይመለከቱት ይሆናል። ነገር ግን ለኔፋውያን፣ በተለይም በክፉው ንጉስ በኖህ ዘመን ለኖሩት ይህ ለውጥ መንፈሳዊ ትርጉም ነበረው። አንድ ዓመፀኛ ንጉሥ በሕዝቡ ላይ ምን ተጽዕኖ እንዳሳደረ አይተው ስለነበር ከዚህ ተጽዕኖ ነፃ ለመውጣት “እጅግ ጓጉ”። ይህ ለውጥ ለፅድቃቸው ተጠያቂ እንዲሆኑ እና “[ለራሳቸው] ኃጢአት ለመመለስ” (ሞዛያ 29፡38) ያስችላቸዋል።
እርግጥ ነው፣ የነገሥታት ንግሥና በማብቃቱ በኔፋውያን ማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ ችግሮች አበቁ ምለት አልነበረም። እንደ ኔሆር እና አምሊሲ ያሉ ተንኮለኞች ሰዎች የውሸት ሀሳቦችን አራመዱ፣ አማኞች ያልሆኑ ቅዱሳንን አሳደዱ እንዲሁም ብዙ የቤተክርስቲያኑ አባላት በኩራት ወደቁ። ነገር ግን “ትሑት የእግዚአብሔር ተከታዮች” በዙሪያቸው ምንም ቢከሰት “ጸኑ እና የማይነቃነቁ” ሆኑ (አልማ 4፡15፤ 1፡25)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሀሳቦች
በማህበረሰቤ ውስጥ አዎንታዊ ተጽእኖ መፍጠር እችላለሁ።
በመሳፍንት የንግሥና ዘመን አምስት ዓመታት ብቻ ቢያልፉም ብዙውን ጊዜ የሕዝብ ድምፅ ትክክል የሆነውን የሚመርጥበትን የሞዛንያ መግለጫ የሚፈትን ቀውስ ተፈጠረ (ሞዛያ 29፡26 ይመልከቱ)። ጉዳዩ ምን እንደነበር እና ኔፋውያን ምን እንዳደረጉ ለማወቅ አልማ 2፡1–7ን አጥኑ። “የቤተክርስቲያን ሰዎች” ድምጻቸውን ባያሰሙ ኖሮ ምን ሊሆን ይችል ነበር? ጌታ በማህበረሰባችሁ ውስጥ እንድትሳተፉ ስለሚፈልግበት መንገድ ከዚህ ታሪክ ሌላ ምን ትማራላችሁ? (በተጨማሪም ሞዛያ 29፡26–27ን ይመልከቱ)።
ማህበረሰባችሁ የሚያጋጥሟቸው አስፈላጊ ጉዳዮች ምንድን ናቸው? ልክ እንደ ኔፋውያን፣ የእናንተ ድምጽ “በህዝብ ድምጽ” ውስጥ መካተቱን እንዴት ማረጋገጥ እንደምትችሉ አስቡ። የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ እንደመሆናችሁ መጠን በማኅበረሰባችሁ ላይ መልካም ተጽዕኖ ማሳደር የምትችሉት በሌሎች በምን መንገዶች ነው?
በተጨማሪም ዳሊን ኤች ኦክስ፣ “ጠላቶችሁን ውደዱ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 26–29 ይመልከቱ።
የእግዚአብሔር ቃል ሃሰተኛ ትምህርቶችን እንዳውቅ ይረዳኛል።
ምንም እንኳን ኔሆር በመጨረሻ ያስተማረው ነገር ውሸት መሆኑን ቢናዘዝም፣ ትምህርቶቹ ግን በኔፋውያን ላይ ለብዙ አመታት ተጽእኖ ማሳደራቸውን ቀጥለዋል። ኔሆር ያስተማረውን ሰዎች የወደዱት ለምን ይመስላችኋል? በአልማ 1፡2–6 ውስጥ፣ በኔሆር ትምህርቶች ውስጥ ያሉትን ውሸቶች— እነዚያን ውሸቶች ለመደበቅ የተጠቀመባቸውን እውነቶችም ፈልጉ።
ጌዴዎን ኔሆርን “በእግዚአብሔር ቃል” ተቃወመው (አልማ 1፡7፣ 9)። የኔሆርን ውሸት የሚያስረዱ አንዳንድ ጥቅሶች እነሆ፡ ማቴዎስ 7፡21–23፤ 2 ኔፊ 26፡29–31፤ ሞዛያ 18:24–26፤ እና ሔለማን 12፡25–26። እያንዳንዱን ጥቅስ ለማጠቃለል ሞክሩ። በዘመናችን የሐሰት ትምህርቶችን ስህተት ማስረጃ ከሕያዋን ነቢያት ምን ተማራችሁ?
የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት “ትሑት የእግዚአብሔር ተከታዮች” ናቸው።
አልማ ምዕራፍ 1 እና 4 ቤተክርስቲያን የበለጸገችበትን ወቅት ነገር ግን የቤተክርስቲያኑ አባላት ለዚያ ብልጽግና በተለየ መንገድ ምላሽ መስጠታቸውን ይገልፃል። ለምሳሌ የቤተክርስቲያን አባላት በጥቂት አመታት ውስጥ እንዴት እንደተለወጡ ለማየት አልማ 1፡19–30ን ከአልማ 4፡6–15 ጋር አነጻጽሩ። ባነበባችሁት መሠረት እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች የተለያየ እምነት ስላላቸው ሰዎች ምን ይሰማቸዋል? እውነተኛ የክርስቶስ ተከታዮች ለሀብትና ብልጽግና ምን አይነት አመለካከት አላቸው? የራሳችሁን አመለካከት ለመለወጥ ምን ተነሳሽነት ይሰማችኋል?
የእኔ ምሳሌነት እና ምስክርነት ልብ ሊለውጥ ይችላል።
ምናልባት አልማ በህዝቡ መካከል እየሆነ ያለውን ነገር ሲመለከት የተሰማውን ሀዘን ልትረዱ ትችላላችሁ። በአልማ 4፡6–15 ውስጥ እሱ ያየውን ችግር ፈልጉ። ተመሳሳይ ችግሮችን አስተውላችኋል? ምናልባት የምትወዱት ሰው በእነዚህ ችግሮች ውስጥ በመሆኑ ተጨንቃችሁ ይሆናል። ለመርዳት ምን ማድረግ እንደምትችሉ አስባችሁ ታውቃላችሁ?
አንዳንዶች አልማ እንደ ዋና ዳኛ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ምርጡ ሰው ነበር ሊሉ ይችላሉ። ነገር ግን አልማ የተሻለ መንገድ እንዳለ ተሰማው። ከቁጥር 16–20 ስታነቡ ህዝቡን ለመርዳት ስላደረገው ሙከራ ምን ያስደንቃችኋል?
አልማ በእግዚአብሔር ቃል እና “ንጹህ ምስክር” (ቁጥር 19) ላይ ታላቅ እምነት ነበረው። የንጹህ ምስክርነት ኃይል ምን ምሳሌዎችን አይታችኋል? ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ወንጌሉ ምስክርነት መስጠት የምትችሉባቸውን የተለያዩ መንገዶች ስታሰላስሉ አልማ 4፡6–14ን ደጋግማችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ያሉ የቤተክርስቲያኑ አባላት ተግባር ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነታቸው እና ስለ ትምህርቶቹ ምን ያሳያሉ? ተግባሮቻቸው በራሳቸው እና በሌሎች ላይ ስለሚኖራቸው ተጽእኖ ምን አስተዋላችሁ? እንዲሁም በሌሎች ሰዎች በቃላት ወይም በድርጊት በተሰጠ ንጹህ ምስክርነት ስለተባረካችሁበት መንገዶች ልታስቡ ትችላላችሁ።
የኢየሱስ ክርስቶስን ምስክርነት በቃላት ወይም በተግባር ማካፈል የምትችሉባቸውን መንገዶች አስቡ። በእናንተ ምስክርነት ማን ሊጠቀም ይችላል?
በተጨማሪም ጋሪ ኢ ስቲቨንሰን፣ “ምስክርነትን መመገብ እና መስጠት [Nourishing and Bearing Your Testimony]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 111–14፤ “ምስክርነት”፣ መዝሙር፣ ቁ. 137 “ታናሹ አልማ ከዋና ዳኝነት ወረደ [Alma the Younger Steps Down as Chief Judge]” (ቪዲዮ)፤ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት፤ የወንጌል አርዕስቶች፣ “ራዕይ”፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት ላይ ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ጌታ የሐሰት ትምህርቶችን እንዳውቅ ሊረዳኝ ይችላል።
-
አልማ 1፡2–4ን ከልጆቻችሁ ጋር የምታጠኑበት አንዱ መንገድ ሐሰተኛው መምህር ኔሆር ያስተማረውን በመጠቀም የእውነት ወይም ሀሰት ጥያቄዎችን እንዲፈጥሩ በመርዳት ነው። ከዚያም ሰይጣን ብዙውን ጊዜ እውነትን ከውሸት ጋር የሚደባልቀው ለምን እንደሆነ ከእነሱ ጋር መነጋገር ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ አንዳንድ ምሳሌዎችን እንዲያስቡ እርዷቸው። በቁጥር 7–9 ላይ ጌዴዎን የኔሆርን ውሸቶች እንዴት ተቋቋመ? (በተጨማሪም “ምዕራፍ 20፡ አልማ እና ኔሆር፣ የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 54–55 ይመልከቱ።)
እንደ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል፣ ሌሎችን እወዳለሁ እንዲሁም አገለግላለሁ።
-
በአልማ ዘመን አንዳንድ የጌታ ቤተክርስቲያን አባላት ደጎች እና ለጋሾች፣ ሌሎች አባላት ደግሞ ደግነት የጎደላቸው እና ኩራተኞች ነበሩ። ልጆቻችሁ ከእነዚህ ተሞክሮዎች እንዲማሩ ለመርዳት አልማ 1፡27፣ 30ን አብራችሁ ማንበብ እና የጌታ ቤተክርስቲያን አባላት የረዷቸውን ሰዎች አይነት ዝርዝር ማውጣት ትችላላችሁ። “በችግር” (አልማ 1፡30) ውስጥ ያለ፣ የኛን ፍቅር እና እርዳታ የሚሻ የምናውቀው ሰው አለ? እንዲሁም ስለ ፍቅር እና አገልግሎት እንደ “ደግነት ከእኔ ይጀምራል” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 145) ያለን መዝሙር መዘመር እና ልጆች ከመዝሙሩ ጋር ሊሄዱ የሚችሉ ድርጊቶችን እንዲያስቡ እርዷቸው።
-
ሰዎች መልካም ሳይሆኑልን ሲቀሩ ምን ማድረግ አለብን? በአልማ 1፡19–20 ላይ የክርስቶስ ተከታዮች ምን እንደደረሰባቸው ከልጆቻችሁ ጋር ለማንበብ አስቡ። በቁጥር 22 እና 25 ላይ እንዴት ምላሽ እንደሰጡ ተናገሩ። ምናልባት ሌሎች ደግነት ሲጎድላቸው ምላሽ መስጫ መንገዶችን መለማመድ ትችላላችሁ።
የእኔ ምስክርነት ሌሎችን ሊያጠነክር ይችላል።
-
ብዙውን ጊዜ የልጅ “ንጹህ ምስክርነት” (አልማ 4፡19) በሌሎች ላይ ጠንካራ ተጽእኖ ሊኖረው ይችላል። ልጆቻችሁ ይህንን እንዲያውቁ ለመርዳት፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ እየተከሰቱ ያሉትን ችግሮች ለይተው እንዲያውቁ በመርዳት አልማ 4፡8–12፣ 15ን አብራችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። እነዚህን ችግሮች ለመፍታት አልማ ምን ማድረግ ይችላል? አልማ በአልማ 4፡16–20 ላይ ምን ለማድረግ እንደወሰነ እንዲያውቁ እርዷቸው። ምናልባት ሌላ ሰው ስለ ክርስቶስ የሰጠው ምስክርነት እንዴት እንዳበረታታችሁ አንዳችሁ ለሌላው ልታካፍሉ ትችላላችሁ።
-
ልጆቻችሁ ምሥክርነት ምን እንደሆነ ምሳሌዎችን የሚፈልጉ ከሆነ፣ በአጠቃላይ ጉባኤ ምስክርነት የሚሰጥ ተናጋሪን ቪዲዮ ክሊፕ ለማሳየት አስቡ። እንዲሁም የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽን መጠቀም ወይም እንደ “ምስክርነት” (መዝሙሮች፣ ቁ. 137) ያለ መዝሙር አብራችሁ መዘመር ትችላላችሁ። ከእነዚህ ምንጮች ስለ ምስክርነቶች ምን እንማራለን? ልጆቻችሁ ምስክርነታቸውን ማካፈል እንዲለማመዱ እድርጉ።