ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሰኔ 17-23 ፡ “ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቦቹን ሊያድን ይመጣል” አልማ 8–12


“ሰኔ 17-23 ፡ “ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቦቹን ሊያድን ይመጣል” አልማ 8-12፤ “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“ሰኔ 17-23 አልማ 8-12 “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

አልማ እየሰበከ

እውነተኛ ትምህርት ማስተማር፣ በሚካኤል ቲ.ማልም።

ሰኔ 17–23፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቡን ለማዳን ይመጣል

አልማ 8–12

የእግዚአብሔር ስራ አይወድቅም። ነገር ግን በእሱ ስራ ለመርዳት የምናደርገው ጥረት አንዳንድ ጊዜ የሚከሽፍ ይመስላል—ቢያንስ የምንመኘውን ውጤት ወዲያውኑ ላናይ እንችላለን። በአሞኒሃ ወንጌልን ሲሰብክ እንደነበረ አልማ ትንሽ ሊሰማን ይችላል— አልተቀበሉትም፣ ተፉበት እንዲሁም አባረሩት። ነገር ግን መልአኩ ተመልሶ እንዲሄድ እና እንደገና እንዲሞክር ባዘዘው ጊዜ፣ አልማ በድፍረት “በፍጥነት ተመለሰ” (አልማ 8፡18)፣ እግዚአብሔርም በፊቱ መንገዱን አዘጋጀ። ለአልማ ምግብና ማረፊያ ቦታ ብቻ ሳይሆን አብሮት የሚሰራ፣ ቆራጥ የወንጌል ጠበቃ እና ታማኝ ጓደኛ አሙሌቅን አዘጋጀ፣። በጌታ መንግስት ውስጥ ስናገለግል እንቅፋቶች እና ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን፣ እግዚአብሔር አልማን እንዴት እንደደገፈ እና እንደመራው ማስታወስ እንችላለን፣ እንዲሁም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ስንሆን እግዚአብሔር እኛንም እንደሚደግፈን እና እንደሚመራን ማመን እንችላለን።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሀሳቦች

የሴሚነሪ መለያ

አልማ 8

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለማካፈል የማደርገው ጥረት ትዕግስት ይጠይቃል።

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለአንድ ሰው ለማካፈል ሞክራችሁ ነገር ግን ግብዣችሁ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ ያውቃል? አልማም ያ አጋጥሞታል። በአልማ 8፡13–16 ውስጥ ፈተናዎች እና ተቃውሞዎች ቢኖሩም ወንጌልን ስለመካፈል ከእርሱ ምን ተማራችሁ? ቁጥር 17-32ን ማንበብ ቀጥሉ እናም እናንተ የተሳካላችሁ ባይመስላችሁም ወንጌልን ማካፈል እንድትቀጥሉ የሚያነሳሷችውን ሀረጎች ፈልጉ።

ነቢያት እና ሐዋርያት የክርስቶስ ልዩ ምስክሮች ናቸው። ስለዚህ ስለ እርሱ ስለመመስከር በመንፈስ አነሳሽነት የተሞላ ምክር አላቸው። ሽማግሌ ዲዬተር ኤፍ. ኡክዶርፍ “ከባድ ከሆነስ? [But What If It’s Hard?]” የሚለውን (በ“የሚስዮናውያን ሥራ፡ በልባችሁ ያለውን ማካፈል [Missionary Work: Sharing What Is in Your Heart]፣ ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 18 ውስጥ ያለ ክፍል) ወይም ሽማግሌ ጋሪ ኢ. ስቲቨንሰን በ”መውደድ፣ ማጋራት፣ መጋበዝ [Love, Share, Invite]” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 84–87) ያጋሩትን ይመልከቱ። እዚያ ወንጌልን ለማካፈል ተስፋ መቁረጥ የጀመረን ሰው ሊረዳ የሚችል ምን ታገኛላችሁ?

ወንጌልን ስለመካፈል እዚህ የተማራችሁትን ሁሉ ወደ አንድ ወይም ሁለት አበረታች መግለጫዎች እንዴት ታጠቃልላላችሁ? እናንተ (እና ሌሎች) መሞከር እንድትቀጥሉ የሚያነሳሱ የግድግዳ ላይ ጽሁፎች ወይም ሚም ለመስራት አስቡ።

በተጨማሪም “በመነሳሳት እንዳስተምር እርዳኝ [Help Me Teach with Inspiration]፣” መዝሙሮች፣ ቁ. 281; “አልማ ወደ አሞኒሃህ እንዲመለስ በመልአክ ታዘዘ [Alma Is Commanded by an Angel to Return to Ammonihah]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “ሁሉንም የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲቀበሉ መጋበዝ”፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት ላይ ይመልከቱ።

አልማ 9፡14–23

የእግዚአብሔር በረከቶች ከታላቅ ኃላፊነት ጋር ይመጣሉ።

በአሞኒሃ የነበሩት ኔፋውያን የጌታን አገልጋዮች የያዙበትን መንገድ ስታነቡ፣ በአንድ ወቅት በወንጌል እንደኖሩ እና “በጌታ የተወደዱ ሰዎች” (አልማ 9:20) እንደነበሩ መርሳት ቀላል ነው። እግዚአብሔር ለኔፊ ሰዎች ስለሰጣቸው ታላቅ በረከቶች ስታነቡ (በተለይ አልማ 9፡14–23 ተመልከቱ)፣ እርሱ የሰጣችሁን ታላቅ በረከቶች አስቡ። ከእነዚህ በረከቶች ጋር ምን ኃላፊነቶች ይመጣሉ? እነዚህን ኃላፊነቶች ለመጠበቅ ምን እያደረጋችሁ ነው?

በተጨማሪ ትምህርት እና ቅል ኪዳኖች 50፥2482፥393:39ን ይመልከቱ።

አልማ 11–12

የእግዚአብሔር እቅድ የመዳን እቅድ ነው።

አልማ 11–12፣ አልማ እና አሙሌክ የእግዚአብሔርን እቅድ የመዳን እቅድ በማለት ጠቅሰዋል። እነዚህን ምዕራፎች ስታነቡ ቤዛ የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን እቅድ ለመግለጽ ለምን ጥቅም ላይ እንደዋለ አስቡ። አልማ እና አሙሌቅ ስለሚከተሉት የእቅዱ ገጽታዎች ያስተማሩትን አጭር ማጠቃለያ ለመጻፍ አስቡ፡-

  • ውድቀት

  • አዳኙ

  • ንስሀ መግባት

  • ሞት

  • ትንሳኤ

  • ፍርድ

የአሙሌቅ ቃል በሰዎች ላይ ያሳደረውን ተጽእኖ አስተውሉ (አልማ 11፡46 ይመልከቱ)። ስለ እግዚአብሔር እቅድ ማወቃችሁ እንዴት ተጽዕኖ ያሳድርባችኋል?

በተጨማሪም ዳሊን ኤች ኦክስን፣ “ታላቁ እቅድ”፣ ሊያሆና፣ ግንቦት 2020ን፣ 93–96ን፣ “አሙሌክ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክራል [Amulek Testifies of Jesus Christ]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት ላይ ይመልከቱ።

አልማ 12፡8–18

ልቤን ካላደነደንኩ የእግዚአብሔርን ቃል የበለጠ መቀበል እችላለሁ።

አንዳንድ ሰዎች የሰማይ አባት ለምን ሁሉንም ነገር እንደማያሳውቅ ያስቡ ይሆናል። በአልማ 12፡9–14 ላይ፣ አልማ አንድ ሊሆን የሚችልበትን ምክንያት ይገልጻል። እነዚህ ጥያቄዎች እሱ ያስተማረውን እንድታሰላስሉ ሊረዱ ይችላሉ፡-

  • ልብን ማደንደን ምን ማለት ነው? የልብ መደንደን ምን ያስከትላል? (በተጨማሪም አልማ 8፡9–119፡5፣ 30–31፤ እና 10፡6፣ 25ን ይመልከቱ)።

  • ልብን ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ምን ማድረግ ትችላላችሁ? (ኤርምያስ 24:7አልማ 16:16ሔለማን 3:35 ይመልከቱ)።

  • የእግዚአብሔር ቃል “[በእናንተ] ውስጥ [እንደሚገኝ]” ለማረጋገጥ ምን ማድረግ ትችላላችሁ? (( አልማ 12፡13 ). የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ውስጥ ካለ፣ “[በቃሎቻችሁ]፣” “[በሥራዎቻችሁ]” እና “[በአስተሳሰባችሁ]” ላይ ምን ተጽእኖ ይኖረዋል? (አልማ 12፡14).

መልካም ልብ ስለማግኘት የአሙሌቅ ልምድ ምን ያስተምራችኋል? ( አልማ 10፡1–11 ይመልከቱ)።

በተጨማሪም “አልማ ዘኢዝሮምን አስጠነቀቀ” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት ላይ ይመልከቱ።

ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ወር የሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች እትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

አልማ 8–10

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ማካፈል እችላለሁ።

  • የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ ለልጆቻችሁ በአልማ 8-10 ያሉትን ክስተቶች ለማጠቃለል ሊረዳችሁ ይችላል። አልማ እና አሙሌቅን ጥሩ ሚስዮናውያን ያደረጋቸውን መርሆች እንዲያገኙ እርዷቸው። ለምሳሌ፣ ተስፋ አልቆረጡም (አልማ 8፡8–13 ተመልከት)፣ ስለ ክርስቶስ መስክረዋል (አልማ 9፡26–27 ይመልከት)፣ እንዲሁም አብረው ሰርተዋል (አልማ 10፡12 ይመልከቱ)።

  • እንደ “አሁን ሚሲዮናዊ መሆን እፈልጋለሁ” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 168) ያሉ ስለ ሚሲዮናዊ ስራ የተዘመሩ መዝሙሮችን ልጆቻችሁ ለጓደኞቻቸው ወንጌልን ማካፈል ስለሚችሉባቸው መንገዶች ሀሳቦችን ሊሰጡ ይችላሉ። የሚያገኟቸውን ሃሳቦች እና ወንጌልን ሊያካፍሏቸው የሚችሉ ሰዎችን እንዲዘረዝሩ ጋብዟቸው። እንዲያውም የሚናገሩትን ወይም የሚያደርጉትን በማስመሰል እንዲጫወቱ ልትፈቅዱላቸው ትችላላችሁ።

ተሳትፎን አበረታቱ። ለማስተማር ስትዘጋጁ፣ ነገሮችን ለማለት ከማቀድ ይልቅ፣ “ልጆቹ ለመማር ምን ያደርጋሉ?” ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ። ልጆች በንቃት ሲሳተፉ በተሻለ ሁኔታ ይማራሉ እንዲሁም የበለጠ ያስታውሳሉ።

አልማ 11–12

የእግዚአብሔር እቅድ የመዳን እቅድ ነው።

  • ምናልባት ልጆቻችሁ እንደ አዳምና ሔዋን ውድቀት፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ፣ ንስሃ፣ ሞት፣ ትንሳኤ እና ፍርድ ያሉ የቤዛነት እቅድ መርሆዎችን የሚወክል ስዕል ሊስሉ ይችላሉ። ከዚያም ሥዕሎቻቸውን በአልማ 11-12 ውስጥ ስለእነዚህ መርሆዎች ከሚያስተምሩ ጥቅሶች ጋር እንዲያዛምዱ መርዳት ትችላላችሁ።

አልማ 8፡18–22

ጥሩ ጓደኛ መሆን እችላለሁ።

  • አልማ 8፡18–22 ያለውን ታሪክ ስትናገሩ አንድ ልጅ አሙሌቅን፣ ሌላው ደግሞ አልማን መስሎ እንዲታይ መጋበዝ ትችላላችሁ። አሙሌቅ ለአልማ ጥሩ ጓደኛ የሆነው እንዴት ነበር? ከዚያም ልጆቻችሁ አንድ ሰው ለእነሱ ጓደኛ እንዴት እንደነበረ እና ያ ተሞክሮ ምን እንዲሰማቸው እንዳደረጋቸው ማካፈል ይችላሉ።

  • ምናልባት የጓደኝነት የሚገጣጠም ምስል ልትፈጥሩ ትችላላችሁ፡ ጓደኝነትን የሚወክል ምስል ፈልጉ ወይም ሳሉና ወደሚገጣጠሙ ቁርጥራጮች ቁረጡት። በእያንዳንዱ ቁራጭ ጀርባ ላይ፣ አልማ እና አሙሌቅ ያደረጓቸውን ነገሮች ጨምሮ ጥሩ ጓደኛ ለመሆን ማድረግ የምንችሉትን ነገር ፃፉ። ጀርባው ላይ የተጻፈውን ስታነቡ ልጆቻችሁ በየተራ አንድ ቁራጭ መርጠው ወደሚገጣጠመው ምስል ሊጨምሩት ይችላሉ። ጓደኝነታችንን ማን ይፈልጋል?

ሁለት ሴት ልጆች እየሳቁ

ለሌሎች ጥሩ ጓደኛ መሆን እንችላለን።

አልማ 11፡43–44

በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በትንሳኤ እነሳለሁ።

  • ስለ ትንሣኤ ለማስተማር ይህን የመሰለ የተግባር ትምህርት ተመልከቱ፡ እጃችሁ መንፈሳችሁን፣ ጓንት ደግሞ ሰውነታችሁን ሊወክል ይችላል። መንፈሳችን እና አካላችን በሞት እንደሚለያዩ ለማሳየት እጃችሁን ከጓንት ውስጥ አውጡ። ከዚያም መንፈሳችን እና ሰውነታችን በትንሳኤ ዳግም እንደሚገናኙ ለማሳየት እጃችሁን ወደ ጓንት መልሳችሁ አስገቡ። አልማ 11፡43ን በምታነቡላቸው ጊዜ ልጆቻችሁ ተራ በተራ ጓንት እያደረጉ ያውጡ። ከሞት የተነሳውን አዳኝ ምስል አሳዩ (የወንጌል ጥበብ መጽሐፍ ቁ. 59 ይመልከቱ) እና ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉም ሰው እንዲነሳ እንዳስቻለ መስክሩ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

አልማ ከአሙሌቅ ጋር እየበላ

አልማ ከአሙሌቅ ጋር እየበላ የሚያሳይ ምስል፣ በዳን በር