ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ነሃሴ 5–11፦ “ታላቅ የደስታ እቅድ” አልማ 39–42


“ነሐሴ 5–11፦ ታላቅ የደስታ እቅድ።’ አልማ 39-42፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

“ነሐሴ 5–11። አልማ 39–42፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

ኢየሱስ ከመቃብሩ እየወጣ

ተነስቷል፣ በዴል ፓርሰን።

ነሐሴ 5–11፦ “ታላቅ የደስታ እቅድ”

አልማ 39–42

የምንወደው ሰው ከባድ ስህተት ሲሠራ እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለብን ማወቅ ከባድ ሊሆን ይችላል። አልማ 39–42ን በጣም ውድ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል ከዚህ በፊት ንስሐ የሚገባበት የራሱ ከባድ ኃጢአቶች የነበሩበት የክርስቶስ ደቀ መዝሙር የነበረው አልማ አንድ ጊዜ ይህን የመሰለውን ሁኔታ የያዘበትን መንገድ ስለሚገልጽ ነው። የአልማ ልጅ ቆሪያንተን ፆታዊ ኃጢአት ፈጽሟል፤ አልማ ደግሞ በአገልግሎቱ ማድረግን እንደተማረው ለልጁ ዘላለማዊ እይታን ይሰጠው ዘንድ እንዲሁም ንስሐን ያበረታታ ዘንድ በእውነተኛው ትምህርት ኃይል ታምኗል ( አልማ 4:1931:5 ይመልከቱ)። በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ኃጢአትን በማውገዝ ረገድ አልማ ያሳየውን ድፍረት እና ለቆሪያንተን የነበረውን ርህራሄ እና ፍቅር እንመለከታለን። እንዲሁም በመጨረሻ አዳኙ “የዓለምን ኃጢያት ሊወስድ እንደሚመጣ፤ አዎን፣ ለዚህ ህዝብ የደህንነትን የምስራች ዜና ለማወጅ እንደሚመጣ“ አልማ የነበረውን ልበ ሙሉነት እንገነዘባለን (አልማ 39:15)። የቆሪያንተን ንስሃ መግባት እና በመጨረሻም ወደ አገልግሎት ስራው የመመለሱ እውነታ ( አልማ 49:30ን ይመልከቱ) ስለራሳችን ኃጢአት ወይም ስለምንወደው ሰው ኃጢአት በምንጨነቅበት ጊዜ የይቅርታ እና የየቤዛዊ መስዋዕት ተስፋ ሊሰጠን ይችላል ( አልማ 42:29 ይመልከቱ)።

በተጨማሪም “Alma Counsels His Sons” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ቤተመፃሕፍት ይመልከቱ።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

አልማ 39

seminary icon
ከጾታዊ ኃጢአት መራቅ እችላለሁ።

አልማ 39 ውስጥ ያለው አልማ ለልጁ ለቆሪያንተን የሰጣቸው ምክሮች የብልግና ምስልን ጨምሮ ስለጾታዊ ሃጢያት አውዳሚ ውጤቶች ለመማር ትልቅ ዕድል ይሰጣሉ። ምናልባትም ይበልጥ አስፈላጊ የሆነውን አዳኙ ንስሃ ለሚገቡ ሰዎች ያቀረበውን የይቅርታ እና የፈውስ ስጦታም እንድትገነዘቡ ሊረዳችሁ ይችላል። እነዚህን ጥያቄዎች እና አክቲቪቲዎች ሊረዱ ይችላሉ።

  • ቆሪያንተንን የንጽህናን ህግ ወደመጣስ የመሩት ስህተቶች ምንድን ናቸው (አልማ 39፥2-4 ይመልከቱ)። ድርጊቶቹ ምን አስከተሉ? ( ቁጥር 5-13 ይመልከቱ)። ቆሪያንተን ንስሐ ስለመግባቱ የሚያሳዩ ምን መረጃዎች አሉን አልማ 42፥3149:3048:18)። ከዚህ ተሞክሮ ስለአዳኙ ምን ትማራላችሁ?

  • For the Strength of Youth: A Guide for Making Choicesከገጽ 19-20 አንብቡ። ከዚያም የብልግና ምሥሎች ምን እንደሆኑ፣ ለምን አደገኛ እንደሆኑ እና በሚያጋጥሟችሁ ጊዜ ምን እንደምታደርጉ የራሳችሁን ማብራሪያ ጻፉ። (በተጨማሪም ማቴዎስ 5፥27–28 እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥16ይመልከቱ።)

  • የብልግና ምሥሎችን ማስወገድን እና የንጽህና ህግን መኖርን ለምን እንደመረጣችሁ ለጓደኛችሁ የምታስረዱት እንዴት ነው? በFor the Strength of Youth: A Guide for Making Choices ውስጥ ካለው Your Body Is Sacred (ገጽ 22–29) ምን ግንዛቤ ልታጋሩ ትችላላችሁ?

  • “To Look Upon” (ወንጌል ቤተመፃሕፍት) የሚለውን ቪዲዮ መመልከትን አስቡ። ዳዊት የተለየ ምርጫ ሊያድርግ ይችል የነበረበት ጊዜ ሲኖር ቪዲዮውን ለተወሰነ ጊዜ ቆም አድርጉት። ለዳዊት የቀረቡለት ምርጫዎች ሊያጋጥሟችሁ ከሚችሉት ምርጫዎች ጋር ሊመሳሰሉ የሚችሉት እንዴት ነው?

ለማሰላሰል ለተወሰነ ጊዜ ቆም አድርጉት። ለማስተማርም ሆነ በራሳችሁ ለማጥናት አንድን ቪዲዮ በምትመለከቱበት ጊዜ አልፎ አልፎ ቪዲዮውን ቆም እያደረጋችሁ “ምን እየተማርኩ ነው?” ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ። ይህ ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጣን ግንዛቤ ሊጋብዝ ይችላል።

በተጨማሪም ብራድሊ አር. ዊልኮከሰ፣ “Worthiness Is Not Flawlessness፣” ሊያሆናህዳር 2021(እ.አ.አ)፣ 61-67 “የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳይ ፎቶ ወይም ፊልም” በወንጌል ቤተመፃሕፍት “የህይወት እርዳታ” ስብስብ ውስጥ ይመልከቱ።

አልማ 40–41

ከሞትኩ በኋላ ምን ይሆናል?

ቆሪያንተን ከሞት በኋላ ሊሆኑ ሰለሚችሉት ነገሮች አንዳንድ ጥያቄዎች ነበሩት። የነበሩበት ሥጋቶች አልማ በአልማ 40–41 ውስጥ የሚገኙትን መርሆዎች ወደማስተማር መራው። በምታጠኑበት ጊዜ እንደ የመንፈስ አለም፣ ትንሳኤ እና ፍርድ ስለመሳሰሉ ነገሮች የምታገኛቸውን እውነቶች ዘርዝሩ። እነዚህን ምዕራፎች እንደ ቆሪያንተን ንስሀ መግባት ከሚያስፈልገው ሰው እይታ አንፃር ማንበብን አስቡ—ሲጀመር ይህ ለሁላችንም ያስፈልገናል።

አልማ 40

በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ለጥያቄዎቼ መልስ መፈለግ እችላለሁ።

አንዳንድ ጊዜ ነቢያት የእያንዳንዱን የወንጌል ጥያቄ መልስ ያውቃሉ ብለን እናስብ ይሆናል። ነገር ግን በምዕራፍ 40 ውስጥ ያሉትን አልማ የነበሩትን ያልተመለሱ ጥያቄዎች አስተውሉ። መልሶቹን ለማግኝት ምን አደረገ? መልሶችን ባላገኘ ጊዜስ ምን አደረገ? የአልማ ምሳሌ ሊረዳችሁ የሚችለው እንዴት ነው?

ሴት እየጸለየች

ፀሎት ለወንጌል ጥያቄዎች መልሶችን ልናገኝ የምንችልበት አንድ መንገድ ነው።

አልማ 42

የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ መዳንን እንዲቻል ያደርገዋል።

ቆሪያንተን የሃጢያት ቅጣት ተገቢ እንዳልሆነ ያምን ነበር( አልማ 42:1ይመልከቱ) በአልማ 42 ውስጥ ለሥጋቱ ምላሽ የሰጠው እንዴት ነው? በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያሉትን ምንባቦች “እግዚአብሔር ፍትህ ነው” እና “እግዚአብሔር መሐሪ ነው” በሚሉ በሁለት ቡድኖች ማደራጀት ትችላላችሁ። የአዳኙ የሃጢያት ክፍያ መስዋዕት ፍትህንም ይቅርታንም የሚቻል የሚያደርገው እንዴት ነው? “The Mediator” (ወንጌል ላይብረሪ) በሚለው ቪዲዮ ውስጥ ተጨማሪ ግንዛቤዎችን ፈልጉ።

በተጨማሪም “ጥበቡ እና ፍቅሩ እንዴት ታላቅ ነው፣” መዝሙር፣ ቁጥር 195 ይመልከቱ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

አልማ 39፥1፣ 10–11

የእኔ መልካም ምሳሌነት ሌሎችን ወደክርስቶስ ሊመራ ይችላል።

  • አልማ ለቆሪያንተን የሰጠው ምክር ልጆቻችሁ መልካም ምሳሌ የመሆንን አስፈላጊነት እንዲገነዘቡ ሊረዳቸው ይችላል። አልማ 39፥1ን በጋራ ማንበብን አስቡ። የቆሪያንተን ወንድም የሆነው ሺብሎን መልካም ምሳሌ የነበረው እንዴት ነው? ልጆቻችሁ በአልማ 38፧2-4ውስጥ ለእነዚህ ጥያቄዎች ተጨማሪ መልሶች ሊያገኙ ይችላሉ።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ ተራ በተራ አንዳችሁ ሌላችሁን የምትከተሉበትን ወይም የምታስመስሉበትን ጨዋታ መጫወትም ትችላላችሁ። ይህንን ጨዋታ፣ ድርጊቶቻችን ሌሎች መልካም ምርጫዎችን እንዲያደርጉ እንዴት እንደሚረዳቸው በምሳሌ ለማስረዳት ተጠቀሙበት። “I Am like a Star” (የልጆች መዝሙር መፅሃፍ፣ 163)፣ አብራችሁ ዘምሩ እንዲሁም ልጆቻችሁ መልካም ምሳሌ የሚሆኑበትን መንገድ እንዲያስቡ እርዷቸው።

  • የእጅ ባትሪ ብርሃንን ወይም የፀሐይን ምስል በመጠቀም ብርሃንን መልካም ምሳሌ ካለው ኃይል ጋር ማወዳደር ትችላላችሁ። አንተና ልጆቻችሁ ኢየሱስ መልካም ነገሮችን ሲያደርግ የሚያሳዩ ሥዕሎችን መመልከትና ለእኛ ስለተወልን ምሳሌ መነጋገር ትችላላችሁ። “Shine Your Light So Others May See” እና “Lessons I Learned as a Boy” የተሰኙት ቪዲዮዎች የልጆቻችሁ ምሳሌ ሰዎችን እንዴት ወደ ክርስቶስ እንደሚመራቸው እንዲወያዩ ሊረዳቸው ይችላል።

አልማ 39፥9–13

ሥህተት በምሰራበት ጊዜ በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ንስሐ መግባት እችላላችሁ።

  • ስለኃጢአቶቹ ዓይነት ዝርዝር ውስጥ ሳይገባ ቆሪያንተን የተሳሳተ ምርጫ እንዳደረገ ገለፀ። እርሱን ለመርዳት ምን ልንል እንችላለን? አልማ 39:9ን ለልጆቻችሁ ማንበብን አስቡ እንዲሁም ንስሐ መግባት እና መተው ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲገነዘቡ እርዷቸው። በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው አማካኝነት ንስሐ የሚቻል እንደሆነ መስክሩ።

  • በንስሐ የሚገኝን ደስታ ለመግለጽ የሚረዳ የተግባር ትምህርት እነሆ፦ አንድ ስህተት የሆነ ነገር ስለፈፀመ እና መጥፎ ስሜት ስለተሰማው ሰው ታሪክ በምትናገሩበት ጊዜ ለአንድ ልጅ የሚሸከመው ከባድ ነገር ስጡት። ሸክሙ ስህተት በምንሰራበት ጊዜ ሊኖረን ከሚችለው መጥፎ ስሜት ጋር እንደሚመሳሰል ለልጆቻችሁ ንገሯቸው። ሰማያዊ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ከባድ፣ መጥፎ ስሜቶችን ሊያስወግዱ እንደሚችሉ እና ንስሃ በምንገባበት ጊዜ የተሻልን እንድንሆን እንደሚረዱን እየመሰከራቸሁ ከባዱን ሸክም ከልጁ ላይ አውርዱ።

አልማ 40፧6–7፣ 11–14፧ 21–23

ከሞትን በኋላ እስከትንሳኤ እና የፍርድ ቀን ድረስ መንፈሶቻችን ወደ መንፈስ አለም ይሄዳሉ።

  • ከሞትን በኋላ ምን እንሆናለን ብሎ ማሰብ ተፈጥሯዊ ነው። የተነሳሱ መልሶች እንዲያገኙ ለመርዳት ምን ማድረግ ትችላላችሁ? ሞትየመንፈስ ዓለም (ገነት እና የመንፈስ እስር ቤት)ትንሳኤ፣ እና ፍርድ ብላችሁ በቁርጥራጭ ወረቀቶች ላይ ልትጽፉ ትችላላችሁ። የእነዚህ ቃላት ፍቺ ምን እንደሆነ ልጆቻችሁ እንዲገነዘቡ እርዷቸው። አልማ 40:6–7፣ 11–14፣ 21–23 በአንድ ላይ ሰታነቡ ልጆቻችሁ፣ ቃላቶቹ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ በሚገኙበት ቅደም ተከተል መሠረት ሊያስቀምጧቸው ይችላሉ።

  • ተለቅ ተለቅ ያሉ ልጆች በአልማ 40:6–7፣ 11–14፣ 21–23 ውስጥ በመፈለግና ለጥያቄዎች መልስ በማግኘት ሊጠቀሙ ይችላሉ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ምላሽ ሊያገኙ የሚችሉ ለምሳሌ “ከሞት ስነሳ ሰውነቴ ምን ዓይነት መልክ ይኖረዋል?” የመሰሉ ጥያቄዎችን ልጆቻችሁን መጠየቅን አስቡ። በተገቢዎቹ ጥቅሶች ውስጥ መልሶችን ለማግኘት እንዲፈልጉ ጋብዟቸው።

    ማርያም እና ኢየሱስ

    ማርያም እና ከሞት የተነሳው ጌታ፣ በሃሪ አንደርሰን

  • ልጆቻችሁ አንድ የሞተ ሰው ያውቃሉ? ምናልባት ስለዚያ ሰው ባጭሩ ልትናገሩ ትችላላችሁ። አንድ ቀን እርሱ ወይም እርሷ—እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ሁሉ—ባኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ከሞት እንደሚነሱ ምስክርነታችሁን አካፍሉ። አስፈላጊ ከሆነ ከሞት መነሳት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማስረዳት የዚህን ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ ተጠቀሙ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

አልማ እና ቆሪያንተን

This My Son፣ በ አኤልስፔት ካይትሊን ያንግ