ነሐሴ 19-25፦ “በእግዚአብሄር አስደናቂ ሃይል መጠበቅ።” አልማ 53-63፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])
“ነሐሴ 19–25 (እ.አ.አ)። አልማ 53-63፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])
ነሐሴ 19-25፦“በእግዚአብሄር አስደናቂ ሃይል መጠበቅ።”
አልማ 53–63
ከላማናውያን ሠራዊት ጋር ሲወዳደር፣ የሄለማን የወጣት ወንዶች “ትንሽ ሠራዊት” አልማ 56–33 የማሸነፍ ዕድል አልነበራቸውም። በቁጥር ትንሽ ከመሆናቸውም በላይ የሄለማን ወታደሮች “ሁሉም … ወጣቶች” እና “ፈጽሞ ተዋግተውም [የሚያ]ውቁ” አልነበሩም (አልማ 56:46–47)። በተወሰኑ መንገዶች በኋለኛው ቀን ከሰይጣንና ከክፉ ኃይላት ጋር በምናደርገው ውጊያ አንዳንድ ጊዜ በቁጥር እንደምንበለጥ ለሚሰማን ሰዎች ያሉበት ሁኔታ የተለመደ ሊመስል ይችላል።
ሆኖም የሄለማን ሠራዊት ከላማናውያን ሠራዊት ይልቅ ከቁጥርም ሆነ ከወታደራዊ ብቃት ጋር ዝምድና የሌላቸው አንዳንድ ጠቃሚ ጎኖች ነበሩት። ነቢይ የሆነውን ሄለማንን እንዲመራቸው መረጡት( አልማ 53:19 ይመልከቱ)፤ “ጥርጣሬ ከሌለባቸው እግዚአብሄር እንደሚጠብቃቸው በእናቶቻቸውም ተምረዋል” (አልማ 56:47)፤ እንዲሁም “በተማሩት ታላቅ እምነት” ነበራቸው። በውጤቱም፣ “በእግዚአብሔር አስደናቂው ኃይል” ጥበቃ አግኝተው ነበር (አልማ 57:26)። ስለዚህ የህይወት ውጊያዎች በሚገጥሙን ጊዜ ድፍረት ማግኘት እንችላለን። የሄለማን ሠራዊት “ጻድቅ እግዚአብሄር እንዳለና ማንም ካልተጠራጠረ በእግዚአብሄር አስደናቂው ኃይል እንደሚጠበቅ” ያስተምረናል (አልማ 57:26)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
አልማ 53:10–22፤ 56:43–49, 55–56፤ 57:20–27፤ 58:39–40
በእግዚአብሄር ማመን ፍርሃትን እንድቋቋም ይረዳኛል።
እምነት ባይኖራቸው ኖሮ የሔለማን ብላቴና ሠራዊት ፍርሃት ይሰማቸው ዘንድ በቂ ምክንያት ነበራቸው። ሆኖም በእምነታቸው ምክንያት ደፋር ለመሆን የበለጠ ምክንያት ነበራቸው። በአልማ 53፥58 ውስጥ ስለእነርሱ ስታነቡ በክርስቶስ በማመን ፍርሃቶቻችሁን እንድትጋፈጡ የሚረዷችሁን ነገሮች ፈልጉ። በሚከተሉት ጥቅሶች ላይ ማተኮርን አስቡ፦ አልማ 53:10–22፤ 56:43–49፣ 55–56፤ 57:20–27፤ እና 58:39–40። ይህ ሰንጠረዥ የምታገኙትን እንድትመዘግቡ ይረዳችኋል።
የሄለማን ብላቴና ወታደሮች ባህርያት፦ | |
በክርስቶስ ያላቸው እምነት ጠንካራ ሊሆን የቻለበት ምክንያቶች፦ | |
በክርስቶስ ያላቸውን እምነት ለመጠቀም ምን አደረጉ፦ | |
እግዚአብሄር እንዴት ባረካቸው፦ |
መንፈሳዊ ውጊያዎቻችንን ለማሸነፍ የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይልም እንፈልጋለን። እንዴት ኃይሉን መጠቀም ትችላላችሁ? መልሶቹን በራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የኢየሱስ ክርስቶስን ሀይል ወደ ህይወታችን መሳብ፣” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 39-42) ውስጥ ፈልጉ። የእርሱን ምክሮች የሄለማን ወታደሮች ካደረጓቸው ነገሮች ጋር ልታነጻጽሩ ትችላላችሁ።
እነዚህን ነገሮች ካጠናችሁ በኋላ ስለራሳችሁ መንፈሳዊ ውጊያዎች አስቡ። በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላችሁን እምነት ለመጠቀም ምን ለማድረግ እንደተነሳሳችሁ የተሰማችሁን ጻፉ።
በተጨማሪም ኒል ኤል. አንደርሰን፣ “Wounded,” ሊያሆና፣ ሕዳር 2018፣ 83–86፤ “True to the Faith,” መዝሙር፣ ቁ. 254፤ “Drawing upon the Power of God in Our Lives” (ቪዲዮ), ወንጌል ቤተመፃህፍት የወንጌል አርዕስቶች፣ “Faith in Jesus Christ,” ወንጌል ቤተመፃህፍት።
የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች በቀላሉ አይናደዱም።
ሄለማን እና ፓሆራን የተናደዱባቸው ምክንያቶች ነበሯቸው። ሄለማን ለሠራዊቱ ድጋፍ እያገኘ አልነበረም፣ፓሆራን ደግሞ ያንን ድጋፍ ከልክሏል በሚል በሞሮኒ በሀሰት ተከሶ ነበር። ( አልማ 58:4–9, 31–32፤ 60)። በአልማ 58:1–12, 31–37 እና አልማ 61ውስጥ ስለሰጡት ምላሾች ምን ያስደንቃችኋል? በዚህ መንገድ ምላሽ የሰጡት ለምን ይመስላችኋል?
ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር ፓሆራን የየዋህነት ምሳሌ እንደሆነ ጠቁመዋል እንዲሁም “እጅግ ታላቅ የሆኑ እና ትርጉም ያላቸው የየዋህነት ምሳሌዎች በራሱ በአዳኙ ሕይወት ውስጥ ይገኛሉ” ሲሉ አስተምረዋል (“Meek and Lowly of Heart,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 32)። አዳኙ የዋህነትን ያሳየው እንዴት ነው? ለምሳሌ ማቴዎስ 27:11–26፤ ሉቃስ 22:41–42፤ ዮሃንስ 13:4–17 ይመልከቱ። ምሳሌውን እንዴት መከተል ትችላላችሁ?
በዙሪያዬ ያሉትን ሰዎች እንዲደሰቱ የማድረግ ሀላፊነት አለብኝ፡፡
የኔፋውያን ሰራዊት የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች እያወቀ ችላ ብሎ ከሆነ እግዚአብሔር ፓሆራንን ተጠያቂ እንደሚያደርገው ሞሮኒ ጽፏል። እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ስለመንከባከብ ከአልማ 60:7-14 ምን ትማራላችሁ? የሌሎችን ፍላጎት በበለጠ ለማወቅ እና ለማሟላት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
ትሁት ከሆንኩ፣ የህይወት ፈተናዎች ልቤን ወደእግዚአብሔር ሊመልሱ ይችላሉ።
ፈተና በሚገጥማችሁ ጊዜ “ለስላሳ” ወይም “ጠንካራ” መሆንን እንዴት መምረጥ እንደምትችሉ ለማሰብ ይረዳችሁ ዘንድ ያልበሰለ እንቁላል እና ድንች በፈላ ውሃ ውስጥ ጨምሩ። እንቁላላችሁ እና ድንቻችሁ በመብሰል ላይ እያለ አልማ 62፥39–51ን አጥኑ እንዲሁም ከላማናውያን ጋር ካደረጉት ረጅም ጦርነት በኋላ ሕዝቡ ለሄለማን አገልግሎት እንዴት ያለ ምላሽ እንደሰጡ አስተውሉ። ከዚያም ይህንን ከ13 ዓመታት ቀደም ብሎ ለወንጌል ትምህርቱ ሰጥተውት ከነበረው ምላሽ ጋር ማነጻጸር ትችላላችሁ ( አልማ 45:20-24 ይመልከቱ)። ኔፋውያን በዚያው ተመሳሳይ መከራ በተለየ ሁኔታ የተነኩት እንዴት ነው? እንቁላሉ እና ድንቹ በደንብ ሲበስሉ እንቁላሉን ላጡ ድንቹንም ክፈሉት። የፈላው ውሃ በተለያየ መንገድ ተፅዕኖ ያደረገባቸው እንዴት ነው። ለፈተና ምላሽ ለመስጠት መምረጥ ስለምንችልባቸው መንገዶች ምን እየተማራችሁ ነው? በፈተናዎቻችሁ ወቅት ፊታችሁን ወደ እግዚአብሄር ልመልሱ የምትችሉት እንዴት ነው?
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
እንደ ሔለማን ብላቴና ሠራዊት ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን እችላለሁ።
-
“ምዕራፍ 34: ሔለማን እና 2,000 ወጣት ሠራዊት” (የመጽሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 93–94) የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገፅ ልጆቻችሁ እንደ ሔለማን ሠራዊት ሊሆኑ ስለሚችሉባቸው መንገዶች እንዲያስቡ ሊረዳቸው ይችላል። ከአልማ 53፧20–21 የብላቴና ሠራዊት አንዳንድ ባህሪያትን ማካፈልን አስቡ። “We’ll Bring the World His Truth፣” የሚለውን መዝሙር (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣172) አብራችሁ መዘመርም ትችላላችሁ።
ወላጆቼ በፅድቅ ለሚያስተምሩኝ ነገር ታማኝ ልሆን እችላለሁ።
-
የሔለማን ብላቴና ሠራዊት ታላቅ ፈተና በገጠማቸው ጊዜ ወደእናቶቻቸው እምነት ተመለከቱ። ምናልባት አልማ 56፥45–48ን ከልጆቻችሁ ጋር ለታነቡና የእነዚህ ብላቴናዎች እናቶች ስለእምነት ያስተማሯቸውን እንዲሰሙ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። ከወላጆቻቸው—ወይም ከሌሎች ታማኝ አዋቂዎች—ስለአዳኙ ምን እንደተማሩ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። “በትክክል” መታዘዝ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? (አልማ 57፥21)።
-
ልክ እንደ ብላቴና ሠራዊት እናቶች ልጆቻችሁ በእግዚአብሄር ላይ ያላችሁን እምነት እንደሚያውቁ ማረጋገጥ የምትችሉት እንዴት ነው? አንደኛው መንገድ እምነታችሁ ህይወታችሁን እንዴት እንደሚነካው ማካፈል ነው። ለምሳሌ “ባልተጠራጠራችሁ” ጊዜ “ያዳናችሁ” እንዴት ነው?
ከሰማይ አባት ጋር የገባኋቸውን ቃልኪዳኖች መጠበቅ እችላለሁ?
-
ልጆቻችሁ አንድ ሰው ከእነርሱ ጋር ቃል ገብቶ ስለነበረበት እና ቃሉን ስለጠበቀበት ጊዜ መናገር ይችሉ ይሆናል። የተገባው ቃል በተፈፀመ ጊዜ ጊዜ ምን ተሰማቸው? አልማ 53፥10–18ን ልታነቡና ሔለማን፣ የአሞን ሕዝቦች እና የአሞን ሕዝቦች ልጆች ቃል የገቧቸውን ወይም ቃል ኪዳኖቻቸውን እንዴት እንደጠበቁ እንዲመለከቱ ልጆቻችሁን መጋበዝ ትችላላችሁ። ቃል ኪዳኖቻችሁን ስትጠብቁ የሰማይ አባት እንዴት እንደሚባርካችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ፡፡
ቁጡ ላለመሆን መምረጥ እችላለሁ።
ያላደረጉትን ነገር አድርገዋል ተብለው የተከሰሱበትን ጊዜ እንዲያስቡ ልጆቻችሁን መጋበዝን አስቡ። ይህ ፓሆራን ላይ እንዴት እንደተከሰተ ንገሯቸው (አልማ 31:60-61 (በተጨማሪም “ምዕራፍ 35: ካፒቴን ሞሮኒ እና ፓሆራን፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 95-97 ይመልከቱ)። ፓሆራን ምላሽ ስለሰጠበት መንገድ ለማወቅ ከአልማ 61:3–14 በየተራ አንብቡ። ሞሮኒ በከሰሰው ጊዜ ፓሆራን ምን አደረገ? (አልማ 61፥2-3፣ 8–9 ይመልከቱ)። ከአዳኙ ምሳሌ ስለይቅርታ ምን እንማራለን? (ሉቃስ 23፥34)።