“ነሐሴ 26–መስከረም 1፦ ’የአዳኛችን ዓለት’ ሔለማን 1-6፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])
“ነሐሴ 26–መስከረም 1 ሔለማን 1-6፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])
ነሐሴ 26–መስከረም 1፦ “የአዳኛችን ዓለት።”
ሔላማን 1–6
የሔለማን መጽሐፍ በኔፋውያን እና በላማናውያን ዘንድ የተከሰቱትን ድሎች እና አሳዛኝ ክስተቶች መዝግቦ ይዟል። “በኔፋውያን ህዝቦች መካከል ከባድ ችግር መሆን ጀመረ” (ሔለማን 1:1) በማለት ይጀምና ችግሮቹ በመላው ዘገባ መከሰታቸውን ይቀጥላሉ። በዚህ ውስጥ ስለፖለቲካ ሴራ፣ ስለዘራፊዎች ቡድን፣ ነቢያቶችን ስላለመቀበል እንዲሁም በመላ አገሪቱ ስለነበረው ኩራት እና እምነት ማጣት እናነባለን። ነገር ግን በመንፈሳዊ የተረፉትን ብቻ ሳይሆን የበለፀጉትን እንደ ኔፊ እና ሌሂ እንዲሁም “ትሁት የሆኑ ሰዎች[ን]” ምሳሌዎችም እናገኛለን (ሔለማን 3:34)። ይህን ያደረጉት እንዴት ነው? ሥልጣኔያቸው መውደቅ ሲጀምርና ሲፈራርስ እንዴት በጥንካሬ ዘለቁ? በተመሳሳይ መልኩ ማናችንም ሰይጣን “ሊመታን” በሚወረውረው “[በ]ኃይለኛው ውሽንፍር“ “አዳኝ በሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በክርስቶስ ዓለት ሰዎች ከገነቡበት ሊወድቁበት [በ]ማይችሉበት” በጥንካሬ እንቆማለን (ሔለማን 5:12)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ኩራት ከመንፈሱ እና ከእግዚአብሔር ከሚገኝ ጥንካሬ ይለየኛል።
ሔለማን 1–6ን ስታነቡ የኔፋውያንን ባህርይ የተለመደ መንገድ ልታስተውሉ ትችላላችሁ። ጻድቅ በሆኑ ጊዜ እግዚአብሄር ይባርካቸዋል እንዲሁም ይበለፅጋሉ። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ጥፋትና ሥቃይ የሚያመሩ ምርጫዎችን በማድረግ ኩራተኛ እና ክፉ ሆኑ። ከዚያም ትሁት ተደረጉ እንዲሁም ንስሐ ለመግባት ተነሳሱ እንዲሁም አሁንም እግዚአብሄር ባረካቸው። ይህ የተለመደ መንገድ ራሱን ይደግማል ስለዚህም ብዙውን ጊዜ አንዳንዶች ይህንን “የኩራት ዑደት” ብለው ይጠሩታል።
ሔለማን 1–6ን ስታነቡ የዚህን ኡደት ምሳሌዎች ፈልጉ። ይህን የተለመደ መንገድ እንድትገነዘቡ እንዲረዳችሁ አንዳንድ ጥያቄዎች እነሆ፦
-
በኔፋውያን መካከል ምን የኩራት ማሳያ ታያላችሁ? (ለምሳሌ ሔለማን 3:33–34፤ 4:11–13 ይመልከቱ)። ተመሳሳይ የኩራት ማሳያዎችን በራሳችሁ ላይ ታያላችሁ?
-
የኩራት እና የክፋት ውጤቶች ምን ምን ናቸው? (ሔለማን 4፥23–26 ይመልከቱ)። የትህትና እና የንስሐ ውጤቶች ምን ምን ናቸው? (ሔለማን 3:27–30, 35፤ 4:14–16 ይመልከቱ)።
-
ሞሮኒ ልጆቹ ምን እንዲያስታውሱ ፈለገ (ሔለማን 5:4–12 ይመልከቱ)። እነዚህ እውነቶች ኩራተኛ ከመሆን እንድትርቁ የሚረዷችሁ በምን በምን መንገዶች ነው?
በተጨማሪም “Chapter 18: Beware of Pride,” የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች: እሽራ ታፍት ቤንሰን (2014), 229–40 ይመልከቱ፤ “I Need Thee Every Hour,” መዝሙር፣ ቁጥር 98።
በክርስቶስ ማመን ነፍሴን በደስታ ይሞላል።
በሔለማን 3 ውስጥ ሞርሞን፣ ቤተክርስቲያኗ በጣም በመባረኳ መሪዎቹ ሳይቀሩ ስለተደነቁበት የደስታ ጊዜ ገልጿል። በቁጥር 24–32ውስጥ ከምታነቡት ተነስታችሁ ወደዚያ አስደሳች ሁኔታ የመራቸው ምን ይመስላችኋል? ሆኖም በደስታው የቀጠሉት ሁሉም አባላት አልነበሩም። በቁጥር 33-35 ውስጥ በተገለፁት ሰዎች መካከል የነበሩትን ልዩነቶች አስተውሉ። ከእነሱ ምሳሌ ምን ትማራላችሁ?
የአዳኙን ሥም ማክበር እችላለሁ።
ሔለማን 5:6–7ን ማንበብ የቤተሰብ ስምን ጨምሮ የተሰጧችሁን ስሞች እንድታስቡ ሊያነሳሳችሁ ይችላል። እነዚህ ሥሞች ለእናንተ ምን ምርጉም አላቸው? ልታከብሯቸው የምትችሉት እንዴት ነው? ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሆነው የአዳኙን ስም መሸከም ምን ማለት እንደሆነ አስቡ (ሞሮኒ 4:3)። ያንን ቅዱስ ሥም የምታከብሩት እንዴት ነው?
ኢየሱስ ክርስቶስን መሠረቴ ካደረግኩት ልወድቅ አልችልም።
“በአዳ[ኙ] ዓለት” ላይ “መሠረ[ትን] [መገንባት]” ማለት ለእናንተ ምን ማለት ነው? ሔለማን 5፥12። በህይወት አስቸጋሪ ፈተናዎች ውስጥ በኢየሱስ ክርስቶስ ጥበቃ ያገኛችሁት እንዴት ነው? ሔለማን 5፥12ን ስታነቡ ኔፊ እና ሌሂ እምነታቸውን በአዳኙ ዓለት ላይ በመገንባታቸው እንዴት ተባርከው እንደነበር ጥቀሱ።
አንዳንድ ሠዎች እያጠኗቸው ያሉትን ነገሮች በዓይነ ሕሊናቸው መመልከታቸው ጠቃሚ ሆኖ ያገኙታል። ሔለማን 5፥12ን በምሳሌ ለማሳየት በተለያየ ዓይነት መሠረቶች ላይ አነስተኛ ግንባታዎችን ማካሄድ ትችላላችሁ። ከዚያም በላዩ ላይ ውሃ በመርጨት እና አየር ማራገቢያን እንደ ነፋስ በመጠቀም “ኃይለኛ ውሽንፍር” መፍጠር ትችላላችሁ። መሠረታችሁን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ስለመገንባት ምን ግንዛቤዎችን ይሰጣችኋል? “A Secure Anchor” ከሚለው ቪዲዮ ሌላ ምን ነገር ትማራላችሁ? (የወንጌል ቤተመፃሕፍት)
ቁጥር 50 ላማናውያን የተቀበሏቸው “መረጃ[ዎች] ታላቅ ስለመሆ[ናቸው]” ይጠቅሳል። ሔለማን 5፥12–52ን ማንበብ እግዚአብሄር የሰጣችሁን መረጃዎች ወደ አዕምሯችሁ ሊያመጣ ይችላል። ለምሳሌ፣ ከመንፈስ የመጣ “ሹክሹክታ” ምናልባት በአዳኝ ላይ ያላችሁን እምነት አጠናክሮት ሊሆን ይችላል። ሔለማን 5፥30፤ በተጨማሪም ትምህርተ እና ቃል ኪዳኖች 88:66 ይመልከቱ። ወይም ምናልባት በታላቅ ጨለማ ውስጥ የነበራችሁ ልትሆኑና ለበለጠ እምነት ወደ እግዚአብሔር ጮኻችሁ የነበረ ሊሆን ይችላል። (ሔለማን 5፥40–47 ይመልከቱ)። ሌሎች ምን ተሞክሮዎች መሠረታችሁን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እንድትገነቡ ረድተዋችኋል?
በተጨማሪም ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “The Temple and Your Spiritual Foundation” ሊያሆና፣ ሕዳር 2021፣ 93-96፤ ሻን. ዳግላስ፣ “Facing Our Spiritual Hurricanes by Believing in Christ፣” ሊያሆና፣ ሕዳር 2021፣ 109-11፤ የወንጌል አርዕስቶች፦ “Faith in Jesus Christ፣” ወንጌል ቤተመፅአሕፍት ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
የሰማይ አባት ትሁት እንድሆን ይፈልጋል ።
-
ከላይ በተቀመጠው ንድፍ መሠረት ልጆቻችሁ የራሳቸውን “የኩራት ዑደት” እይታ እንዲስሉ መጋበዝን አስቡ። ከዚያም ሔለማን 3:24፣ 33–34 እና 4:11–15ን በጋራ ስታነቡ እነዚህ ጥቅሶች ወደሚገልጿቸው የኩራት ዑደት ክፍሎች ሊጠቁሙ ይችላሉ። ትሁት መሆንን መምረጥ—እና እንደዚያው በመሆን መቀጠል የምንችለው እንዴት ነው?
መሠረቴን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እገነባለሁ።
-
ሕንፃዎች ጠንካራ መሠረት ለምን እንደሚያስፈልጋቸው የተመለከተ ውይይት ለመጀመር የአንድን ቤተመቅደስ ምስል መጠቀምን አስቡ። ወይንም የቤታችሁን ወይም የቤተክርስቲያን ህንጻን መሠረት ልትመለከቱ ትችላላችሁ። በጠንካራ ዓለት ላይ ስለተጣለ መሠረት ጥንካሬ አፅንዖት ለመስጠት ልጆቻችሁ በላዩ ላይ ዓየር በማራገብ ድንጋዩን ለማንቀሳቀስ መሞከር ይችላሉ። ሔለማን 5፥12ን በጋራ ስታነቡ አኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ለህይወታችን “እርግጠኛ መሠረት” እንደሆነ ልጆቻችሁን ጠይቋቸው። ህይወታችንን በእርሱ ላይ መገንባት የምንችለው እንዴት ነው? (ሔለማን 3:27–29፣ 35 እና የእምነት አንቀጾች 1:4 ይመልከቱ)።
-
ልጆቻችሁ ጡቦችን ወይም ሌሎች ነገሮችን በመጠቀም እንደ ጥጥ ኳሶች ወይም ጠፍጣፋ ድንጋይ በመሣሠሉ በተለያዩ ዓይነት መሠረቶች ላይ ግንብ እንዲገነቡ ጋብዟቸው። ጠንካራ መሠረት እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሆነው እንዴት ነው? እርሱን ለመከተል ሊያደርጉ እንደሚችሉ ለሚያካፍሉት ለእያንዳንዱ ሃሳብ በግንባታው ላይ አንድ ጡብ ሊጨምሩ ይችላሉ።
መንፈስ ቅዱስ በ“አነስተኛ ለስላሳ ድምጽ” ይናገራል።
-
በሔለማን 5፥29–30፣ 45–47 ውስጥ የተገለፀው ድምጽ መንፈስ ቅዱስ እኛን የሚናገርበትን አንድ መንገድ ያስተምረናል። ልጆቻችሁ ይህንን እንዲገነዘቡ ለመርዳት “Chapter 37: Nephi and Lehi in Prison”ን (የመጽሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 99–102) ማንበብን አስቡ። ህዝቡ ሰምተውት ስለነበረው ድምጽ ስትናገሩ በለስላሳ ድምጽ ተናገሩ። ታሪኩን ለተወሰነ ጊዜ ደጋግሙት ከዚያም ልጆቹ ከእናንተ ጋር እንዲያንሾካሽኩ ጋብዟቸው። መንፈስ ቅዱስ ሊያናግረን የሚችልባቸውን ሌሎች መንገዶች እንዲያስቡ እርዷቸው። ይህንን መርህ ለማጠናከር “The Still Small Voice፣” የሚለውን መዝሙር ልትዘምሩ ትችላላችሁ (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣106–7)።
ንስሐ መንፈሳዊ ጨለማን በብርሃን ይተካል።
-
ሔለማን 5፥20–41 ስለጨለማ እና ብርሃን የሚያስተምረውን ለማጠናከር የእጅ ባትሪን እንደብርሃን በመጠቀም እነዚህን ጥቅሶች በጨለማ ውስጥ ማንበብን ወይም ማሳጠርን ሞክሩ። ልጆቻችሁ ጨለማው ይወገድ ዘንድ ህዝቡ ምን ማድረግ አስፈልጎት እንደነበር ማዳመጥ ይችላሉ። ከዚያም መብራቱን አብሩት እና ቁጥር 42–48 በጋራ አንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለንስሐ ምን ያስተምሩናል?