Book of Mormon 2024
መስከረም 9–15፦ “የታላቅ ደስታ የምስራች“ ሔለማን 13–16


“መስከረም 9–15፦ ‘የታላቅ ደስታ የምስራች‘ ሔለማን 13-16፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

“መስከረም 9–15። ሔለማን 13-16፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

Samuel the Lamanite teaching on the wall [ላማናዊው ሳሙኤል በግንብ ላይ እያስተማረ

ላማናዊው ሳሙኤል በግንብ ላይ፣ በአርኖልድ ፍሪበርግ

መስከረም 9–15፦ “የታላቅ ደስታ የምስራች“

ሔለማን 13–16

ላማናዊው ሳሙኤል በዛራሔምላ “የምስራች” ለማካፈል በሞከረበት በመጀመሪያው ጊዜ (ሔለማን 13–17)፣ ተቀባይነትን አላገኘም ነበር እንዲሁም ልበ ደንዳና በሆኑ ኔፋውያን ተባሮ ነበር። በልባቸው ዙሪያ የሳሙኤልን መልእክት ከመቀበል ያገዳቸው ሊታለፍ የማይችል ግንብ የገነቡ ይመስል ነበር ልትሉ ትችላላችሁ። ሳሙኤል የሰጠውን መልዕክት አስፈላጊነት ተረድቷል እንዲሁም “እንዲመለስ እናም [እንዲተነብይ] ” የተሰጠውን የእግዚአብሄርን ተዕዛዛት በመከተል እምነትን አሳይቷል (ሔለማን 13:3)። እንደ ሳሙኤል ሁሉ እኛም “የጌታን መንገድ [ስናቀና]” (ሔለማን 14:9) እና ነቢያትን ለመከተል ስንጥር ግንቦች ይገጥሙናል። እናም እንደ ሳሙኤል ሁሉ እኛም “በርግጥ [ስለ]ሚመጣው” ስለአኢየሱስ ክርስቶስ እንመሰክራለን እንዲሁም “ ሁሉም በስሙ [እንዲያምኑ]” እንጋብዛለን (ሔለማን 13:614:13)። ሁሉም ላይቀበል ይችላል እንዲሁም አንዳንዶች በንቃት ሊቃወሙን ይችላሉ። ነገር ግን በክርስቶስ በማመን ይህን መልዕክት የሚያምኑ “የታላቅ ደስታ የምስራች“ (ሔለማን 16:14) እንደሆነ ያውቃሉ።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ሔለማን 13

እግዚአብሔር እውነትን በነብያቶቹ አማካኝነት ማስጠንቀቂያ ይሰጣል።

በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ፣ አንዳንድ ጊዜ ነቢያት በግንብ ወይም በሠገነት ላይ በመሆን አደጋ ሲመጣ ከሚያስጠነቅቁ ጠባቂዎች ጋር ይነጻጸራሉ (ኢሳይያስ 62:6ሕዝቅኤል 33:1–7 ይመልከቱ)። በሔለማን 13ውስጥ ያሉትን የሳሙኤልን ቃላት ስታጠኑ እርሱ እንዴት ለናንተ እንደ ጠባቂ እንደሆነ አስቡ። ለዘመናችን የሚሆን የሚመስል ምን ተናገረ? (በተለይ ቁጥር 8፣ 21–22፣ 26–29፣ 31፣ እና 38 ይመልከቱ)። ለምሳሌ ሳሙኤል ስለንሥሐ፣ ስለትህትና እና ሃብት “ክፋትን በመፈጸም” ደስታን ስለመፈለግ ምን አስተማረ?

በዘመናችን ነቢያት በኩል ጌታ የሰጣቸውን ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያዎች ለማግኘት የቅርብ ጊዜ ከሆኑ የጉባኤ መልዕክቶች ውስጥ መፈለግም ትችላላችሁ። ስለነዚህ ማስጠንቀቂያዎች ምን ለማድረግ እንደምትነሳሱ ይሰማችኋል?

ንድፎችን ፈልጉ። ንድፍ አንድን ሥራ ለማከናወን እንደ መመሪያ የሚያገለግል ዕቅድ ወይም ሞዴል ነው። በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ህዝቡን ለማስጠንቀቅ አገልጋዮቹን እንደመላክ ያሉ ጌታ ሥራውን እንዴት እንደሚሠራ የሚያሳዩ ንድፎችን እናገኛለን።

ቤተሰብ አጠቃላይ ጉባኤን እየተመለከተ

ነቢያትን ስናዳምጥ ወደኢየሱስ ክርስቶስ ይጠቁሙናል።

ሔለማን 13–15

seminary icon
እግዚአብሄር ንስሐ እንድገባ ይጋብዘኛል።

ሳሙኤል ስለእግዚአብሔር ፍርድ የሰጣቸው ማስጠንቀቂያዎች በሁሉም ሁኔታዎች ንስሐ የመግባትን የምህረት ግብዣ ያካትታሉ። እነዚህን ግብዣዎች በመላው ሔለማን 13–15 (በተለይም ሔለማን 13:6–1114:15–1915:7–8 ይመልከቱ) ፈልጉ። ከእነዚህ ጥቅሶች ስለንሥሐ ምን ትማራላችሁ? አንዳንድ ሰዎች ንስሐን ሊሸሹት እንደሚገባ እንደ አስከፊ ቅጣት ይመለከቱታል። በእናንተ አመለካከት ሳሙኤል፣ ኔፋውያን ንሥሐን እንዲመለከቱ የፈለገው እንዴት ነበር?

ጥናታችሁን ለማጠናከር የራስል ኤም ኔልሰንን፣ “የተሻለ ማድረግ እንችላለን እንዲሁም የተሻልን መሆን እንችላለን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 67) ልታነቡ ትችላላችሁ። ንሥሐን የተረጎመው እንዴት ነው? በእርሱ መልዕክት ውስጥ ከልባዊ ንሥሐ የሚመጡ ምን በረከቶችን ታገኛላችሁ? ነቢዩ እንድንቀይራቸው የጋበዘንን የተለዩ ነገሮችን ልትፈልጉም ትችላላችሁ። መንፈስ ቅዱስ ልትቀይሩ እንደሚገባ የሚነግራችሁ ነገር ምንድን ነው? የተቀበላችሁትን የግል መገለጥ መፃፍን አስቡ።

ንስሐ መግባት ባህሪህን ከመቀየር የሚለየው በምንድን ነው? እግዚአብሄር ንሥሐ ስለመግባት ያቀረበውን ግብዣ መቀበል አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድን ነው? ይህንን በምታሰላስሉ ጊዜ ይህንን ግብዣ የሚገልፅ መዝሙር ልትዘምሩ ወይም ልታዳምጡ ትችላላችሁ፣ ለምሳሌ “How Gentle God’s Commands” (መዝሙር፣ 125)።

በተጨማሪም “Jesus Christ Will Help You,” For the Strength of Youth: A Guide for Making Choices፣ 6–9፤ “Repentance: A Joyful Choice፣” “Principles of Peace: Repentance” (ቪዲዮዎች)፣ ወንጌል ላይብረሪ፤ የወንጌል አርዕስቶች “Repentance፣” ወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

ሔለማን 1416:13–23

እግዚአብሄር ስለአዳኙ ውልደት እና ሞት ለመመስከር ምልክቶችን እና አስደናቂ ነገሮችን ልኳል።

ሳሙኤል በሔለማን 14 ውስጥ “መምጣቱን ታውቁ ዘንድ” እና “በስሙም እንድታምኑ” ጌታ ስለአዳኙ ውልደት እና ሞት ምልክት እንደሰጠ አብራርቷልን(ሔለማን 14:12)። ሔለማን 14ን ስታጠኑ በቁጥር 1–8 ውስጥ የአዳኙን ውልደት ምልክቶች እንዲሁም በቁጥር 20–28 የሞቱን ምልክቶች አስተውሉ። እነዚህ ምልክቶች የኢየሱስ ክርስቶስን ውልደት እና ሞት ለማመልከት ለምን በቂ የሆኑ ይመስላችኋል?

ሌሎች ይበልጥ ግላዊ የሆኑ እንዲሁም ብዙም አስገራሚ ያልሆኑ ምልክቶች “በ[አዳኙ] ስም እንድታምኑ” ሊረዷችሁ ይችላሉ። በእርሱ ላይ ያላችሁን እምነት ለማጠናከር ምን አድርጓል?

ሔለማን 16፥13-23 ውስጥ ስለምልክቶች ምን ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል? በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተገለጹትን ሰዎች ዝንባሌዎች እንዴት ማስወገድ ትችላላችሁ?

በተጨማሪም አልማ 30፥-43–52፤ ሮናልድ ኤ. ራዝባንድ “By Divine Design፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ) 55–57 ይመልከቱ።

ሔለማን 15፥3

ከጌታ የሚመጣ ተግሣፅ የፍቅሩ ምልክት ነው።

የሳሙኤል ቃላት ብዙ ጠንከር ያሉ ተግሣጾችን ይዘዋል፤ ነገር ግን ሔለማን 15:3 ከጌታ ስለሚመጣ ተግሣጽ እይታ ይሰጠናል። ከጌታ የሚመጣ ተግሣፅ የፍቅሩ ምልክት ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው። በሳሙኤል ትንቢቶች እና ማስጠንቀቂያዎች ውስጥ ስለጌታ ፍቅር እና ምሕረት ምን ማስረጃ ታያላችሁ?

በተጨማሪም የመለኮታዊ ተግሣጽን ሶስት አላማዎች እየፈለጋችሁ የዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰንን፣ “እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻለሁ እና እቀጣለሁ፣” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2011(እ.አ.አ)፣ 97-–100) ማጥናትን አስቡ። እግዚአብሄር በህይወታችሁ በዚህ መንገድ ሲሰራ ያያችሁት መቼ ነው?

ሔለማን 16

ነቢያት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ይጠቁሙኛል።

ሔለማን 16 ውስጥ የሳሙኤልን ትምህርቶች ከተቀበሉ ሰዎች ምን ትማራላችሁ? እርሱን ካልተቀበሉት ሰዎች ምን ትማራላችሁ? በህይወት ያሉ ነቢያትን መከተላችሁ እንዴት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመቅረብ እንደረዳችሁ አስቡ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ሔለማን 13፥2–5

እግዚአብሄር በልቤ ሊናገረኝ ይችላል።

  • እግዚአብሔር ለሳሙኤል እንደተናገረው በልባችን ሊናገረን እንደሚችል ልጆቻችሁን ልታስተምሯቸው የምትችሉት እንዴት ነው? ምናልባት ምንም ድምፅ ሳያወጡ ለመነጋገር የሚያስችሉ የተለያዩ መንገዶችን እንዲያሳዩዋችሁ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ይህ የሰማይ አባት ከእኛ ጋር ስለሚነጋገርባቸው የተለያዩ መንገዶች ውይይት ወደ ማድረግ ሊመራ ይችላል። እንደዚህ ውይይት አካል፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ የላማናዊውን የሳሙኤልን ምስል መመልከት እና (ይህ መዘርዝር ሁለቱን ይዟል) ልጆቻችሁ ሳሙኤል ምን ማለት እንዳለበት እግዚአብሔር እንዴት እንደነገረው እየሰሙ እያሉ ሔለማን 13:2–5ን ማንበብ ትችላላችሁ።

  • ብዙዎቻችን—በተለይ ልጆች—እግዚአብሄር እንዴት እና መቼ እንደሚያነጋግረን ለማወቅ እርዳታ ያስፈልገናል። እግዚአብሔር ምን እንድታደርጉ ወይም እንድትናገሩ እንደሚፈልግ በልባችሁ ታውቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ስለረዳችሁ ጊዜ ለልጆቻችሁ ልትነግሯቸው ትችላላችሁ። እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር እየተነጋገረ እንደነበረ እንዴት እንዳወቃችሁ ግለፁ፡፡ ምናልባት ልጆቻችሁ ስለነበራቸው ማንኛውም ተመሳሳይ ተሞክሮዎች ሊያካፍሉም ይችላሉ፡፡

ሔለማን 14፥2–7፣ 20–25

ነቢያት ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምራሉ፡፡

  • Samuel Tells of the Baby Jesus” (የልጆች የመዝሙር መፅሃፍ፣ 36) በአንድነት መዘመር ሳሙኤል ስለክርስቶስ ያስተማረውን ለልጆቻችሁ ለማስተማር ጥሩ መንገድ ሊሆን ይችላል፡፡ “Chapter 40: Samuel the Lamanite Tells about Jesus Christ” (የመፅሃፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 111–13) ማካፈል ሌላው መንገድ ነው፡፡ ሣሙኤል ስለአዳኙ ምን አስተምሯል? ምናልባት እናንተም የዘመናችን ነቢያት ስለእርሱ ምን እንደሚያስተምሩ ልታካፍሉም ትችላላችሁ፡፡ ቃላታቸው በእርሱ ላይ ያለንን እምነት የሚገነቡት እንዴት ነው?

ሔለማን 16፥1–6

ነቢዩን ስከተል እባረካለሁ።

  • ታማኘ የነበሩ ሰዎችን ምሳሌዎች በማሳየት ልጆቻችሁ በነቢዩ ላይ ያላቸውን እምነት ልትገነቡ ትችላላችሁ። ከእነዚህ አንዳንዶቹ በሔለማን 16፥1፣ 5 ይገኛሉ። በምታነቡበት ጊዜ ልጆቻችሁ፣ ህዝቡ የሳሙኤልን ቃላት ባመኑ ጊዜ ያደረጉትን ነገር ሲሰሙ ሊቆሙ ይችላሉ። ከዚያም ቁጥር 2 እና 6 በምታነቡበት ጊዜ ልጆቻችሁ፣ ህዝቡ ባላመኑ ጊዜ ያደረጉትን ነገር ሲሰሙ ሊቀመጡ ይችላሉ። በህይወት ያሉ ነቢያትን ቃላት እንደምናምን እንዴት ማሳየት እንችላለን? በእርሱ ነቢያት በኩል የሚመጣውን የጌታ ምክር ስትከተሉ እንዴት እንደተባረካችሁ ለልጆቹ ንገሯቸው።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ላማዊው ሳሙኤል

ላማናዊወ ሳሙኤል፣ በ ሌስተር ዮከም