ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
አባሪ ሐ፦ ለመጀመሪያ ክፍል—የመዝሙር ጊዜ እና የልጆች የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ፕሮግራም የማቅረብ መመሪያዎች


“አባሪ ሐ፦ ለመጀመሪያ ክፍል—የመዝሙር ጊዜ እና የልጆች የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ፕሮግራም የማቅረብ መመሪያዎች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 ( እ.አ.አ)]

“አባሪ ሐ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ልጆች እየዘመሩ

አባሪ ሐ

ለመጀመሪያ ክፍል—የመዝሙር ጊዜ እና የልጆች የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ዝግጅት የማቅረብ መመሪያዎች

የተቀደሰ መዝሙር ልጆቻችሁ ስለሰማይ አባት የደስታ እቅድ እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መሰረታዊ እውነቶችን እንዲማሩ ለመርዳት ሃይለኛ መሳሪያ ነው። ልጆች ስለወንጌል መርሆዎች ሲዘምሩ፣ መንፈስ ቅዱስ ስለ እውነትነታቸው ይመሰክራል። ቃላቱ እና ሙዚቃው በልጆቹ ልብ እና አዕምሮ ውስጥ በመላ ህይወታቸው ይቀመጣል።

ወንጌልን በሙዚቃ አማካኝነት ለማስተማር በምትዘጋጁበት ጊዜ የመንፈስን መመሪያ እሹ። ስለምትዘምሯቸው እውነቶች ያላችሁን ምስክርነት አካፍሉ። ልጆቹ፣ ሙዚቃው በቤት እና በመጀመሪያ ክፍሎች ውስጥ ከሚማሩት እና ከሚያጋጥሟቸው ነገሮች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ እንዲመለከቱ እርዷቸው።

የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ዝግጅት የማቅረብ መመሪያዎች

በኤጲስ ቆጶሱ አመራር፣ የልጆች የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ዝግጅት የሚቀርበው በተለምዶ በአራተኛው ሩብ አመት ነው። እንደ የመጀመሪያ ክፍል አመራር እና የሙዚቃ መሪ፣ ዝግጅቱን ለማቀድ የመጀመሪያ ክፍልን በበላይነት ከሚቆጣጠረው የኤጲስ ቆጶስ አማካሪ ጋር አብራችሁ ስሩ።

ፕሮግራሙ፣ ልጆቹ በዓመቱ ውስጥ የዘመሯቸውን የመጀመሪያ ክፍል መዝሙሮች ጨምሮ፣ ልጆቹ እና ቤተሰቦቻቸው ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች በቤት እና በመጀመሪያ ክፍል ውስጥ የተማሩትን እንዲያቀርቡ የሚፈቅድ መሆን ይገባዋል። ፕሮግራሙን ስታቅዱ ተሰብሳቢዎቹ በአዳኙ እና በትምህርቶቹ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ሊረዳ ስለሚችልባቸው መንገዶች አስቡ።

አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ልጆችን የያዙ የቤተክርስቲያኗ ክፍሎች፣ የቤተሰብ አባላት ከልጆቻቸው ጋር መሳተፍ የሚችሉባቸውን መንገዶች ሊያስቡ ይችላሉ። አንድ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል ስብሰባውን አጠር ባለ ንግግር ሊዘጋ ይችላል።

ፕሮግራሙን ለማቅረብ ስትዘጋጁ፣ የሚከተሉትን መመሪያዎች አስታውሱ፦

  • በልምምዶች ጊዜ ከመጀመሪያ ክፍል ወይም ከቤተሰባቸው እንዲለዩ የሚያደርግ አላስፈላጊ ጊዜ መኖር የለበትም።

  • የእይታ ማስተማሪያዎችን፣ አልባሳትን፣ እና ሚዲያዎችን በቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች ላይ መጠቀም ትክክል አይደለም።

አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል፣ 12.2.1.2፣ የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ልጆች እየዘመሩ

የመዝሙር ጊዜ መመሪያዎች

5 ደቂቃ (የመጀመሪያ ክፍል አመራር)፦ መክፈቻ ፀሎት የቅዱሳት መጻህፍት ወይም የእምነት አንቀጾች እና አንድ ንግግር

20 ደቂቃ (የሙዚቃ መሪ)፦ የመዝሙር ጊዜ

የመጀመሪያ ክፍል አመራር እና የሙዚቃ መሪ፣ ልጆች በትምህርት ክፍሎች እና በቤት እየተማሯቸው ያሉትን መርሆዎች ለማጠናከር የሚረዱ ለእያንዳንዱ ወር የሚሆኑ መዝሙሮችን ይመርጣሉ። እነዚህን መርሆዎች የሚያጠናክሩ መዝሙሮች ዝርዝር በዚህ መመሪያ ውስጥ ተካተዋል።

መዝሙሮችን ለልጆቹ በምታስተምሩበት ጊዜ፣ መዝሙሮቹ ስለሚያስተምሯቸው ታሪኮች እና ትምህርታዊ መርሆዎች የተማሩትን እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። በመዝሙሮቹ ውስጥ ስለሚገኙት እውነቶች ያላቸውን ሃሳቦች እና ስሜቶች እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው።

በመጀመሪያ ክፍል ውስጥ መዝሙርን በተመለከተ መሰረታዊ ግብአት የሚሆነው የልጆች መዝሙር መጽሃፍ ነው። በመዝሙር መጽሃፍ ውስጥ ያሉ መዝሙሮች እና በጓደኛ ውስጥ ያሉ ሙዚቃዎች ተገቢ ናቸው። ማንኛውንም ሌላ ሙዚቃ በመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ለመጠቀም፣ ከኤጲስ ቆጶስ አመራር ፈቃድ መገኘት አለበት (አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ፣ 12.3.4)።

ለመዝሙር ጊዜ የሚሆን ሙዚቃ

ጥር

  • Follow the Prophet [ነቢዩን ተከተሉ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 110፟–11

  • Search, Ponder, and Pray [ፈልጉ፣ አሰላስሉ እና ጸልዩ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 109

የካቲት

  • Dare to Do Right [ትክክለኛውን ለማድረግ ድፈሩ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 158

  • A Child’s Prayer [የልጅ ጸሎት]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 12–13

መጋቢት

  • Every Star Is Different [እያንዳንዷ ኮኮብ ልዩ ናት]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 142

  • When I Am Baptized [እኔ ስጠመቅ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 103

ሚያዝያ

  • When He Comes Again [እንደገና ሲመጣ]፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 82–83

  • Did Jesus Really Live Again? [በእውነት ኢየሱስ እንደገና ወደህይወት ተመልሷል?]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 64

ግንቦት

  • ‘Give,’ Said the Little Stream [‘ስጥ፣’ አለች ትንሿ ዥረት]፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 236

  • Shine On [አብሩ]፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 144

ሰኔ

  • The Holy Ghost [መንፈስ ቅዱስ]፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 105።

  • I Want to Be a Missionary Now [አሁን ሚስዮን ለመሆን እፈልጋለሁ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 168

ሐምሌ

  • Stand for the Right [ትክክለኛውን ለማድረግ ድፈሩ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 159

  • He Sent His Son [እርሱ ልጁን ላከ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 34–35

ነሐሴ

  • I’m Trying to Be like Jesus [እንደ ኢየሱስ ለመሆን እጥራለሁ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 78–79

  • I Feel My Savior’s Love [የአዳኜ ፍቅር ይሰማኛል]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 74–75

መስከረም

  • I Love to See the Temple [ቤተመቅደስን ማየት እወዳለሁ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 95

  • To Think about Jesus [ስለኢየሱስ ማሰብ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 71

ጥቅምት

  • Family History—I Am Doing It [የቤተሰብ ታሪክ—እየተገበርኩት ነኝ]፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 94።

  • The Church of Jesus Christ [የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 77

ህዳር

  • Keep the Commandments [ትዕዛዛቱን ጠብቁ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 146–47

  • To Be a Pioneer [መስራች ለመሆን]፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 218፟–19

ታህሳስ

  • I Am a Child of God [የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ]፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 2–3 ተመልከቱ።

  • O Little Town of Bethlehem [አቤቱ ትንሿ የቤተልሔም ከተማ]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 208

ትምህርትን ለማስተማር ሙዚቃን መጠቀም

የመዝሙር ጊዜ ልጆች የወንጌልን እውነት እንዲማሩ ለመርዳት የታሰበ ነው። በመዝሙሮች እና በመጀመሪያ ክፍል መዝሙሮች ውስጥ የሚገኙትን የወንጌል መርሆዎች ለማስተማር የሚያስችሉ መንገዶችን ስታቅዱ የሚከተሉት ሀሳቦች ሊያነሳሷችሁ ይችላሉ።

ተያያዥ ቅዱሳት መጻህፍትን አንብቡ።የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ እና በመዝሙር መጽሃፍ ውስጥ ለሚገኙ ለአብዛኞቹ መዝሙሮች ተያያዥ የሆኑ የቅዱሳት መጻህፍት ማጣቀሻዎች ተዘርዝረዋል። እነዚህን አንዳንድ ምዕራፎች እንዲያነቡ እርዷቸው እንዲሁም ቅዱሳት መጻህፍቱ ከመዝሙሮቹ ጋር እንዴት እንደሚገናኙ ተናገሩ። ጥቂት የቅዱሳት መጻህፍት ማጣቀሻዎችን በሰሌዳው ላይ ልትዘረዝሩ እና ልጆቹ እያንዳንዱን ማጣቀሻ ከአንድ መዝሙር ወይም ከመዝሙሩ አንድ ሥንኝ ጋር እንዲያዛምዱ መጋበዝ ትችላላችሁ።

ባዶውን ቦታ ሙሉ። ብዙ ቁልፍ ቃላት የጎደሉትን የመዝሙሩን አንድ ሥንኝ በሰሌዳው ላይ ጻፉ። ከዚያም ልጆቹን፣ በባዶው ቦታ ውስጥ የሚሞሉትን ቃላት እያዳመጡ መዝሙሩን እንዲዘምሩ ጠይቋቸው። እያንዳንዱን ባዶ ቦታ በሚሞሉበት ጊዜ ከጎደሉት ቃላት ምን ዓይነት የወንጌል መርሆዎችን እንደምትማሩ ተወያዩ።

ልጆች እየዘመሩ

መስክሩ። በመጀመሪያ ክፍል መዝሙሮች ውስጥ ስለሚገኙ የወንጌል እውነቶች ለልጆቹ አጭር ምስክርነት ስጡ። መዘመር ምስክርነት ሊሰጡ የሚችሉበት እና መንፈሱ እንዲሰማቸው የሚያደርግ አንድ መንገድ እንደሆነ እንዲገነዘቡ ልጆቹን እርዷቸው።

ምስክር ሆናችሁ ቁሙ። ልጆች በየተራ በመቆም እየዘመሩት ካለው መዝሙር ምን እንደተማሩ ወይም መዝሙሩ ስለሚያስተምረው እውነት እንዴት እንደሚሰማቸው እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። መዝሙሩን በሚዘምሩበት ጊዜ እንዴት እንደሚሰማቸው ጠይቋቸው እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስን ተፅዕኖ እንዲለዩ እርዷቸው ።

ሥዕሎችን ተጠቀሙ። በመዝሙሩ ውስጥ ካሉ ጠቃሚ ቃላት ወይም ሀረጎች ጋር የሚሄዱ ምስሎችን በመፈለግ ወይም በመፍጠር እንዲረዷችሁ ልጆቹን ጠይቋቸው። ሥዕሎቹ ከመዝሙሩ ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ እና መዝሙሩ ምን እንደሚያስተምር እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። ለምሳሌ “When He Comes Again [እንደገና ሲመጣ]” (መዝሙር፣ ቁጥር 82–83) የሚለውን መዝሙር እያስተማራችሁ ከሆነ (እንደ መላዕክትበረዶ፣ እና ኮከብ የመሳሰሉ) በመዝሙሩ ውስጥ ያሉ ጠቃሚ ቃላትን የሚያሳዩ ሥዕሎችን በክፍሉ የተለያዩ ቦታዎች ማስቀመጥ ትችላላችሁ። መዝሙሩን አብራችሁ በምትዘምሩበት ጊዜ፣ ልጆቹ ሥዕሎቹን እንዲሰበስቡ እና በትክክለኛው ቅደም ተከተል ከፍ አድርገው እንዲይዟቸው ጠይቋቸው።

ተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮችን አካፍሉ። ስለመዝሙሩ ውይይት ለማነሳሳት ተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገር መጠቀም ትችላላችሁ። ለምሳሌ “‘Give,’ Said the Little Stream [‘ስጥ፣’ አለች ትንሿ ዥረት]” (የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 236) የሚለውን መዝሙር ስትዘምሩ፣ እንደፈሳሽ፣ ሳር እና አበቦች ያሉ ነገሮችን ምሥሎች ለልጆቹ ልታሳዩአቸው ትችላላችሁ። ይህም፣ ትናንሽ የአገልግሎት ተግባራት እንኳን ሌሎችን በአስፈላጊ መንገዶች እንዴት እንደሚባርኩ ወደሚደረግ ውይይት ሊያመራ ይችላል።

የግል ተሞክሮዎችን ማካፈልን ጋብዙ። ልጆቹ መዝሙሩ የሚያስተምራቸውን መርሆዎች በእነዚህ መርሆዎች ላይ ካላቸው ተሞክሮዎች ጋር እንዲያዛምዱ እርዷቸው። ለምሳሌ “I Love to See the Temple [ቤተመቅደስን ማየት እወዳለሁ]” (የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 95) የሚለውን መዝሙር ከመዘመራችሁ በፊት፣ ልጆቹ ቤተመቅደስ አይተው የሚያውቁ ከሆነ እጃቸውን እንዲያወጡ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። በሚዘምሩበት ጊዜ ቤተመቅደስን ሲያዩ ምን እንደሚሰማቸው እንዲያስቡ ጋብዟቸው።

ጥያቄዎችን ጠይቁ። መዝሙሮችን በምትዘምሩበት ጊዜ ልትጠይቋቸው የምትችሏቸው ብዙ ጥያቄዎች አሉ። ለምሳሌ ልጆቹ በመዝሙሩ ውስጥ ካሉ ከእያንዳንዱ ሥንኞች ምን እንደተማሩ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። መዝሙሩ የሚመልሳቸውን ጥያቄዎች እንዲያስቡ ልትጠይቋቸውም ትችላላችሁ። ይህም መዝሙሩ ስለሚያስተምራቸው እውነቶች ውይይት ወደ ማድረግ ሊያመራ ይችላል።

ቀላል የእጅ እንቅስቃሴዎችን ተጠቀሙ። ልጆቹ የአንድን መዝሙር ቃል እና መልዕክት ለማስታወስ እንዲረዳቸው ቀላል የእጅ እንቅስቃሴዎችን እንዲያስቡ ጋብዟቸው። ለምሣሌ፣“Search, Ponder, and Pray [ፈልጉ፣ አሰላስሉ እና ጸልዩ]” (የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 109)፣ የሚለውን መዝሙር በምትዘምሩበት ጊዜ፣ በቅዱሣት መፃህፍት ውስጥ ስለመፈለግ በሚዘምሩበት ጊዜ ወደ ዓይኖቻቸው እንዲጠቁሙ፣ ስለማሰላሠል በሚዘምሩበት ጊዜ ወደ ጭንቅላታቸው እንዲጠቁሙ እንዲሁም ስለፀሎት በሚዘምሩበት ጊዜ እጆቻቸውን እንዲያጣጥፉ መጋበዝ ትችላለህ።