“አባሪ መ፦ ለአሮናዊ ክህነት ቡድን እና ለወጣት ሴቶች የትምህርት ክፍሎች—የስብሰባ አጀንዳዎች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 ( እ.አ.አ)]
“አባሪ መ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)
አባሪ መ
ለአሮናዊ ክህነት ቡድን እና ለወጣት ሴቶች የትምህርት ክፍሎች—የስብሰባ አጀንዳዎች
የሥብሰባ ቀን፦
የሥብሰባው አስተባባሪ (የትምህርት ክፍል ወይም የቡድን አመራር አባል)።
መክፈቻ
መዝሙር (እንደ አስፈላጊነቱ)፦
ጸሎት፦
የወጣት ሴቶችን ጭብጥ ወይም የአሮናዊ ክህነት ቡድንን ጭብጥ ከልሱ።
አብራችሁ ተመካከሩ
ሥብሰባውን በሚያስተባብረው ሰው በመመራት፣ የትምህርት ክፍሉ ወይም ቡድኑ ከ5 እስከ 10 ለሚሆኑ ደቂቃዎች በደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ላይ ስላላቸው ሀላፊነት በጋራ ይመካከራል። ይህም በአመራር ስብሰባዎች ወይም በአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ውይይት በተደረገባቸው ነገሮች ላይ የክፍል ወይም የቡድን አመራር ክትትል እንዲያደርጉ መልካም አጋጣሚን ይፈጥራል።
ስብሰባውን የሚያስተባብረው ግለሰብ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን ወይም ከአንድ በላይ ጥያቄዎችን ሊጠቀምም ይችላል፦
በወንጌል መኖር
-
ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ወንጌሉ ያለንን ምስክርነት ያጠናከሩልን የቅርብ ጊዜ ተሞክሮዎች የትኞቹ ናቸው?
-
ወደ አዳኙ ለመቅረብ ምን እያደረግን ነው? የበለጠ እርሱን ለመምሰል እየሞከርን ያለነው እንዴት ነው?
-
የጌታ ምሪት በህይወታችን ውስጥ የተሰማን እንዴት ነው?
የተቸገሩትን መንከባከብ
-
ማንን የመርዳት እና የማገልገል ምሪት ተሰምቶናል? የተቸገረን ሠው ለመርዳት ከኤጲስ ቆጶስ አመራሩ ምን የሥራ ድርሻ ተስጥቶናል?
-
የትምህርት ክፍል ወይም የቡድን አባላት ምን ዓይነት ፈተናዎችን እየተጋፈጡ ይገኛሉ? በሚያጋጥሙን አስቸጋሪ ነገሮች እርስ በእርስ መደጋገፍ የምንችለው እንዴት ነው?
-
በቅርቡ ወደ አጥቢያችን የተዛወረ ወይም ቤተክርስቲያኗን የተቀላቀለ ሰው አለ? መልካም አቀባበል እንደሚደረግላቸው እንዲሰማቸው መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?
ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ መጋበዝ
-
ሌሎች የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲሰማቸው ለመርዳት ምን ልናደርግ እንችላለን?
-
ጓደኞቻችን እንዲሳተፉ ልንጋብዝ የምንችልባቸው እየመጡ ያሉ ምን ዓይነት አክቲቪቲዎች አሉ?
-
በአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ ወንጌልን ማካፈልን የተመለከቱ ምን እቅዶች ውይይት ተደርጎባቸዋል? የትምህርት ክፍላችን ወይም ቡድናችን መሳተፍ የሚችለው እንዴት ነው?
ቤተሰቦችን ለዘለዓለም ማጣመር
-
ከአያቶቻቸን እንዲሁም ከአክስቶቻችን እና ከአጎቶቻቸን ጋር ጨምሮ፣ ከቤተሰብ አባላቶቻችን ጋር በተሻለ ሁኔታ የምንገናኝባቸው አንዳንድ መንገዶች ምን ምን ናቸው?
-
የቤተመቅደስ ሥርዓቶች የሚያስፈልጓቸው ቅድመ ዓያቶቻቸንን ሥም ለመፈለግ ምን እያደረግን ነው? ሌሎች የቅድመ አያቶቻቸውን ሥም እንዲያገኙ ለመርዳት ምን ልናደርግ እንችላለን?
-
በግለሰብ እንዲሁም በትምህርት ክፍል ወይም በቡድን ደረጃ በቤተመቀደስ ሥራ የበለጠ ለመሳተፍ የምንችለው እንዴት ነው?
አንድ ላይ ተማሩ
አንድ ጎልማሳ መሪ ወይም የቡድን ወይም የትምህርት ክፍል አባል የዚህን ሳምንት የኑ፣ ተከተሉኝ ንባብ ይመራል። በኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉትን የጥናት ሃሳቦች ይጠቀማሉ። ከዚህ ምልክት ጋር ያለው የጥናት ሃሳብ ከሴሚናሪ ጋር የተያያዘ ነው ስለዚህ በተለይ ለወጣቶች የሚሆን ነው። ሆኖም፣ የትኛውንም የጥናት ሃሳብ መጠቀም ይቻላል። ይህ የስብሰባው ክፍል በአጠቃላይ ከ35 እስከ 40 ደቂቃዎችን ይወስዳል።
መዝጊያ
ስብሰባውን የሚመራው ግለሰብ፦
-
ስለ መርሆዎቹ በተሰጠው ትምህርት ላይ ምስክርነቱን ይሰጣል።
-
ክፍሉ ወይም ቡድኑ የተማሩትን ነገር በቡድን ወይም በግል እንዴት በስራ ላይ እንደሚያውሉ ይወያያል።
ጸሎት፦