ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
አባሪ ለ፦ ለመጀመሪያ ክፍል—ልጆች ለእድሜ ልክ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ እንዲሆኑ ማዘጋጀት


“አባሪ ለ፦ ለመጀመሪያ ክፍል—ልጆች በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለእድሜ ልክ እንዲቆዩ ማዘጋጀት፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 ( እ.አ.አ)]

“አባሪ ለ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

አባሪ ለ

ለመጀመሪያ ክፍል—ልጆች ለእድሜ ልክ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ እንዲሆኑማዘጋጀት

አምስት እሁዶች ባሏቸው ወራት፣ የመጀመሪያ ክፍል አስተማሪዎች በአምስተኛው እሁድ መርሐ ግብር የተያዘውን የኑ፣ ተከተሉኝ መዘርዝር በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ በእነዚህ የትምህርት አክቲቪቲዎች እንዲተኩ ይበረታታሉ።

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መርሆዎች እና ሥርዓቶች

የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት እንዴት ወደ እግዚአብሔር እንደምንመለስ ያስተምረናል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ለአሜሪካ ህዝቦች በተገለጠ ጊዜ ትምህርቱን አስተምሯቸዋል። እምነት ቢኖረን፣ ንሥሐ ብንገባ፣ ብንጠመቅ፣ መንፈስ ቅዱስን ብንቀበል እና እስከመጨረሻው ብንፀና፣ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንደምንችል ተናግሯል (3 ኔፊ 11፥31–40፤ በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥29 ተመልከቱ)። ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት አክቲቪቲዎች እነዚህ መርሆዎች እና ሥርዓቶች በመላው ህይወታችን ወደ አዳኙ እንድንቀርብ እንደሚረዱን ልጆቹን ለማስተማር ይረዷችኋል።

ስለክርስቶስ ትምህርት የበለጠ ለመረዳት፣ 2 ኔፊ 31 ተመልከቱ።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ማድረግን፣ ንሥሐን፣ ጥምቀትን እና ማረጋገጫ መቀበልን የሚወክሉ ሥዕሎችን ለልጆቹ ስጧቸው (የወንጌል ስዕሎች መፅሐፍ፣ ቁጥር 1111103፣ እና 105ን ተመልከቱ)። አራተኛውን የእምነት አንቀፅ ከልጆቹ ጋር አንብቡ ወይም በቃላችሁ ያዙ፣ ከዚያም ያ መርህ ወይም ሥርዓት ሲጠቀስ ሥዕሎቻቸውን ከፍ አድርገው እንዲይዙ ጠይቋቸው። ልጆቹ እነዚህ መርሆዎች እና ሥርዓቶች እንዴት የበለጠ እንደ ሰማይ አባታችን እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድንሆን እንደሚረዱን እንዲገነዘቡ እርዷቸው።

    ምስል
    Frontal head and shoulders portrait of Jesus Christ. Christ is depicted wearing a pale red robe with a white and blue shawl over one shoulder. Light emanates from the face.
  • ልጆቹ እምነት፣ ንሥሐ፣ ጥምቀት እና ማረጋገጫ መቀበል የአንድ ጊዜ ተግባራት ሳይሆኑ በመላው ህይወታችን መንፈሳዊ እድገት ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድሩ እንዲገነዘቡ እንዴት ልትረዷቸው ትችላላችሁ? ለምሳሌ የአንድን ዘር እና የትልቅ ዛፍ ሥዕል ልታሳዩአቸው (ወይም እነዚህን ነገሮች በሰሌዳው ላይ ልትስሉ) ትችላላችሁ። ዘሩ ወደ ትልቅ ዛፍነት እንዲያድግ ስለሚረዱት እንደ ውሃ፣ አፈር እና የፀሐይ ብርሃን ያሉ ነገሮች እንዲያስቡ እርዷቸው። እነዚህ በመላ ህይወታችን ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የምናደርጋቸው በኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን እንደመግንባት፣ በየቀኑ ንሥሐ እንደመግባት፣ በጥምቀት ቃል ኪዳኖቻችን እንደ መኖር እና መንፈስ ቅዱስን እንደመስማት ያሉ ነገሮች መሆናቸውን እንዲያዩ እርዷቸው።

  • How Can Repenting Help Me Feel Happy? [ንስሀ መግባት ደስታ እንዲሰማኝ እንዴት ይረዳኛል?]” በሚል ርዕስ ሽማግሌ ዴል ጂ. ረንለንድ ያቀረቡትን ስለ ርችቶች የሚናገረውን ታሪክ ከልጆቹ ጋር ተወያዩ። (ጓደኛ፣ ታህሳስ 2017 (እ.አ.አ)፣ 12–13፣ ወይም ሊያሆና፣ ታህሳስ 2017 (እ.አ.አ)፣ 70–71፤ በተጨማሪም “Repentance: A Joyful Choice [ንስሀ መግባት፦ አስደሳች ምርጫ]” [የወንጌል ቤተ መጻህፍት] የሚለውን ቪዲዮ ተመልከቱ)። ሽማግሌ ረንለንድ በታሪኩ የተለያዩ ነጥቦች ላይ ምን ተሰምቷቸው የነበረ ሊሆን እንደሚችል እንዲያስቡ ልጆቹን ጋብዟቸው። ንሥሐ በምንገባበት ጊዜ ደስታ የሚሰማን ለምንድነው? የሰማይ አባት ይቅር እንዲላችሁ ጠይቃችሁ በነበረበት ጊዜ ተሰምቷችሁ የነበረውን ደስታ እና ፍቅር ለልጆቹ አካፍሉ።

ጥምቀት

ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ ለእኔ ምሳሌ ትቶልኛል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሃጢያት ያልነበረበት ቢሆንም ለሰማይ አባት ስለመታዘዝ ፍጹም ምሳሌ ይሆን ዘንድ ተጠመቀ (2 ኔፊ 31፥6–10 ተመልከቱ)።

ስለ ጥምቀት የበለጠ ለመማር፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥37፤ Topics and Questions[ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “ጥምቀት፣” የወንጌል ቤተ መጻህፍት ላይ ተመልከቱ።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • የአዳኙን ጥምቀት እና የአንድ ሌላ ሰውን የጥምቀት ምሥል አሳዩ (ወይም የወንጌል ስዕሎች መፅሐፍ፣ ቁጥር 35 እና ቁጥር 103 ወይም ቁጥር 104 ተመልከቱ)። በሁለቱ ሥዕሎች መካከል ምን ልዩነት እና ምን ተመሳሳይነት እንዳለ እንዲያካፍሉ ልጆቹን ጠይቋቸው። ማቴዎስ 3፥13–17 ወይም “Chapter 10: Jesus Is Baptized [ምዕራፍ 10፦ ኢየሱስ ተጠምቋል]” በአዲስ ኪዳን ታሪኮች፣ 26–29 ውስጥ (ወይም በየወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተዛማጅ ቪዲዮውን) አብራችሁ አንብቡ። ልጆቹ በንባቡ ውስጥ ወይም በቪዲዮው ላይ በተጠቀሱት ሥዕሎች ውስጥ ወዳሉት ነገሮች እንዲጠቁሙ አድርጓቸው። ለአዳኙ ያላችሁን ፍቅር እና እርሱን ለመከተል ያላችሁን ፍላጎት ለልጆቹ ንገሯቸው።

    ምስል
  • ለምሳሌ እንደ “A Child’s Prayer [የልጅ ጸሎት]” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 102) ያሉ ስለ ጥምቀት የሚያወሱ መዝሙሮችን አዳምጡ ወይም ዘምሩ። ከመዝሙሩ ስለ ጥምቀት ምን እንማራለን? 2 ኔፊ 31፥9–10 አንብቡ ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን እንደተጠመቀ እንዲያዳምጡ ልጆቹን ጋብዙ። የራሳቸውን የጥምቀት ቀን ምስል እንዲስሉ ጋብዟቸው።

ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት እና ለመጠመቅ መምረጥ እችላለሁ።

ለጥምቀት መዘጋጀት ለአንድ ፕሮግራም ከመዘጋጀት በብዙ የሚበልጥ ነገርን ይጠይቃል። ቃል ኪዳን ለመግባት መዘጋጀት ከዚያም ያንን ቃል ኪዳን ዕድሜ ልክ መጠበቅ ማለት ነው። ልጆቹ በሚጠመቁበት ጊዜ ለእነርሱ የሰጣቸውን ተስፋዎች እና ለእርሱ የሚገቧቸውን ቃል ኪዳኖች የሚያካትተውን ከሰማይ አባት ጋር የሚገቡትን ቃል ኪዳን ይገነዘቡት ዘንድ እንዴት ልትረዷቸው እንደምትችሉ አሰላስሉ።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • ቃል ኪዳን፣ ሰው እና የሰማይ አባት የሚገቡበት የተስፋ ቃል እንደሆነ አስረዱ። ለእግዚአብሔር የገባናቸውን የተስፋ ቃሎች ለመጠበቅ በምንጥርበት ጊዜ እግዚአብሔር እንደሚባርከን ቃል ገብቷል። በሰሌዳው ላይ ለእግዚአብሔር የገባኋቸው ቃል ኪዳኖች እና እግዚአብሔር ለእኔ የገባልኝ ቃል ኪዳኖች ብላችሁ ጻፉ። ሞዛያ 18፥10፣ 13 እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥37ን አብራችሁ አንብቡ፣ ከዚያም ልጆቹ የሚያገኟቸውን የቃል ኪዳኖች ዝርዝር በተገቢው ርዕስ ሥር እንዲዘረዝሩ አግዟቸው (በተጨማሪም ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “Your Baptism Covenant [በጥምቀት የምትገቡት ቃል ኪዳን]፣” ጓደኛ፣ የካቲት 2021 (እ.አ.አ)፣ 2–3 ተመልከቱ)። በጥምቀት የምትገቡትን ቃል ኪዳን ለመጠበቅ በምትጥሩበት ጊዜ የሰማይ አባት እንዴት እንደባረካችሁ አካፍሉ።

  • ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ እያገለገለ በነበረበት ጊዜ ያከናወናቸውን ነገሮች የሚያሳዩ ሥዕሎች ለልጆቹ አሳዩ (አንዳንድ ምሳሌዎችን ለማግኘት፣ የወንጌል ስዕሎች መፅሐፍ፣ ቁጥር 33–49 ተመልከቱ)። በእያንዳንዱ ሥዕል ውስጥ ኢየሱስ ምን እየሰራ እንደሆነ እንዲናገሩ አድርጉ። ሞዛያ 18፥8–10፣ 13ን አንብቡ፣ ከዚያም ልጆች ሲጠመቁ ለማድረግ ቃል የገቡትን ነገሮች እንዲሰሙ ጋብዟቸው (በተጨማሪም “The Baptism Covenant [የጥምቀት ቃል ኪዳን]፣” ጓደኛ፣ የካቲት 2019 (እ.አ.አ)፣ 7፣ ወይም ሊያሆና፣ የካቲት 2019 (እ.አ.አ)፣ F3 ተመልከቱ)። እነዚህ ተስፋዎች በዕለት ተዕለት ድርጊቶቻችን ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ? ልጆች ኢየሱስ እንደሚያደርገው ሌሎችን እየረዱ የሚያሳይ የራሳቸውን ምስል እንዲስሉ ጋብዟቸው።

    ምስል
    Jesus Christ depicted as a child with his mother Mary. Christ is kneeling beside Mary and resting His clasped hands on Mary's lap. Mary has her head bowed as she and the young Christ pray. There is an oil lamp burning on a table next to the mother and son.
ምስል
ጥምቀት

በምንጠመቅበት ጊዜ ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን እንገባለን፣ እርሱም ለእኛ ቃል ኪዳን ይገባልናል።

ማረጋገጫ መቀበል

ማረጋገጫ ስቀበል የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል እሆናለሁ።

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል መሆን፣ ልጆች በእግዚአብሔር ሥራ ንቁ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ የሚያስችሉ እድሎችን ጨምሮ ብዙ በረከቶችን ያመጣል።

ማረጋገጫ ስለመቀበል እና ስለመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የበለጠ ለመማር፣ ጌሪ ኢ. ስቲቨንሰን፣ “መንፈስ ቅዱስ እንዴት ይረዳችኋል?፣ ”ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 117–20፤ Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “መንፈስ ቅዱስ፣” የወንጌል ቤተ መጻህፍት ተመልከቱ።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • አንድ በቅርቡ የተጠመቀ እና ማረጋገጫ የተቀበለ ሰው ወደ ክፍል እንዲመጣና ማረጋገጫ መቀበል ምን እንደሚመስል እንዲያካፍል ጋብዙት። ይህን ሠው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርሰቲያን አባል መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲናገር ጠይቁት። ልጆቹ እንደ ቤተክርስቲያኗ አባላት የጥምቀት ቃል ኪዳናቸውን መጠበቅ የሚችሉባቸውን (ለምሳሌ ሌሎችን እንደማገልገል፣ ሌሎች ስለ ኢየሱስ የበለጠ እንዲማሩ እንደመጋበዝ፣ በስብሰባዎች ላይ ጸሎት እንደማቅረብ፣ ወዘተ) ያሉ መንገዶችን እንዲያስቡ እርዷቸው። እነዚህን ነገሮች ማድረግ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል በመሆን የሚገኘው ደስታ ይሰማችሁ ዘንድ እንዴት እንደረዳችሁ አካፍሉ።

  • በሞርሞን ውሃ አጠገብ የነበሩ ሰዎችን ሥዕል አሳዩ (የወንጌል ስዕሎች መፅሐፍ፣ ቁ. 76ን ተመልከቱ) ከዚያም ልጆቹ በሥዕሉ ውስጥ የሚያዩትን እንዲገልፁ ጠይቋቸው። አልማን እና ህዝቡ በዚያ እንደተጠመቁ ስለሚያወሣው ታሪክ ተናገሩ (ሞዛያ 18፥1–17፤ “Chapter 15: Alma Teaches and Baptizes [ምዕራፍ 15፦ አልማ አስተማረ እና አጠመቀ]፣” በየመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 43–44፣ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በየወንጌል ቤተ መጻህፍት ውስጥ ይመልከቱ)። ሞዛያ 18፥8–9 ከልሱ ከዚያም ህዝቡ እንደ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት ለማድረግ ፈቃደኛ የነበሩትን ነገሮች እንዲያስታውሱ የሚረዷቸውን ተግባራት እንዲፈፅሙ ልጆቹን ጋብዟቸው። ለምሣሌ፣ ሌሎች “ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት አንድ እርምጃ ወደፊት እንዲራመዱ” መርዳት የምንችለው እንዲት ነው? (ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Hope of Israel [የእስራኤል ተስፋ]” [ዓለም አቀፍ የወጣቶች የሀይማኖት ትምህርት]፣ ሰኔ 3፣ 2018 (እ.አ.አ)]፣ የወንጌል ቤተ መጻህፍት)። የቤተክርስቲያኗ አባላት በእነዚህ መንገዶች ሲያገለግሉ ያያችሁበትን አንድ ተሞክሮ አካፍሉ።

    ምስል
    The Book of Mormon prophet Alma baptizing Nephite converts in the Waters of Mormon. Other men and women are watching or waiting to be baptized. There are trees and mountains in the background. Scriptural reference: Mosiah 18:5-16

ማረጋገጫ በምቀበልበት ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን እቀበላለሁ።

በምንጠመቅበት እና ማረጋገጫ በምንቀበልበት ጊዜ የሰማይ አባት “የእርሱ መንፈስ ሁልጊዜ [እንደሚኖረን]” ቃል ገብቶልናል (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 20፥77)። ከእግዚአብሔር የሚመጣው ይህ አስደናቂ ስጦታ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ይባላል።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 33፥15ን አንብቡ፣ ከዚያም በምንጠመቅበት እና ማረጋገጫ በምንቀበልበት ጊዜ የሰማይ አባት ስለሚሰጠን ልዩ ስጦታ እንዲሰሙ ልጆቹን ጠይቋቸው። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንዴት እንደሚረዳቸው ይበልጥ እንዲማሩ ለመርዳት ዮሐንስ 14፥26ገላትያ 5፥22–232 ኔፊ 32፥53 ኔፊ 27፥20ን አብራችሁ ከልሱ። “The Holy Ghost Is …[መንፈስ ቅዱስ … ነው]” (ጓደኛ፣ ሰኔ 2019 (እ.አ.አ)፣ 24–25፤ ሊያሆና፣ ሰኔ 2019 (እ.አ.አ)፣ F12–F13) የሚለውን ፅሁፍ ልትከልሱም ትችላላችሁ።

  • የአንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ልጆችን ወላጆች የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስላላቸው እንዴት እንደተባረኩ በተማሪዎቹ ፊት እንዲያካፍሉ ጠይቋቸው። እንዴት ይረዳቸዋል? የእርሱን ድምፅ የሚሰሙት እንዴት ነው?

  • እንደ “The Holy Ghost [መንፈስ ቅዱስ]” (የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 105) የመሰለ ስለመንፈስ ቅዱስ የሚያወሳ መዝሙር አብራችሁ ዘምሩ። መንፈስ ቅዱስ ሊረዳን ስለሚችልበት መንገድ መዝሙሩ ምን እንደሚያስተምረን ልጆቹ እንዲገነዘቡ እርዷቸው።

መንፈስ ቅዱስ በተለያዩ መንገዶች ሊናገረኝ ይችላል።

የመንፈሱን ድምጽ ማወቅ የሚችሉ ልጆች በመላ ህይወታቸው ይመራቸው ዘንድ የግል መገለጥን ለመቀበል ይዘጋጃሉ። መንፈስ ቅዱስ ሊያናግረን የሚችልባቸው ብዙ መንገዶች እንዳሉ እንዲገነዘቡ እርዷቸው።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • ልጆቹ ሩቅ ከሚኖር ጓደኛ ጋር የምንነጋገርባቸውን እንደ ደብዳቤ መፃፍ፣ ኢሜል መላክ ወይም በስልክ ማናገር የመሳሰሉ የተለያዩ መንገዶችን እንዲያስቡ እርዷቸው። የሰማይ አባት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በተለያየ መንገድ ሊያናግረን እንደሚችል አስተምሯቸው። ልጆቹ መንፈስ ቅዱስ ለአዕምሮአችን እና ለልባችን የሚናገርባቸውን የተለያዩ መንገዶች እንዲገነዘቡ ለመርዳት የፕሬዚዳንት ዳለን ኤች.ኦክስን How Does Heavenly Father Speak to Us? [የሰማይ አባት እንዴት ያናግረናል]” (ጓደኛ፣ መጋቢት 2020 (እ.አ.አ)፣ 2–3፤ ሊያሆና፣ መጋቢት 2020 (እ.አ.አ)፣ F2–F3) የሚለውን መልዕክት ተጠቀሙ።

  • መንፈስ ቅዱስ እናንተን በአእምሮአችሁ በሃሳብ ወይም በልባችሁ በስሜት ያነጋገረበትን አንድ ተሞክሮ አካፍሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥22–238፥2–3 ተመልከቱ። በተጨማሪም ሄንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “Open Your Heart to the Holy Ghost [ልባችሁን ለመንፈስ ቅዱስ ክፈቱ]፣” ጓደኛ፣ ነሃሴ. 2019 (እ.አ.አ)፣ 2–3 ወይም ሊያሆና፣ ነሃሴ 2019(እ.አ.አ)፣ F2–F3) ተመልከቱ)። መንፈስ ቅዱስ በተመሳሳይ መንገድ ሊረዳቸው እንደሚችል ለልጆቹ መስክሩላቸው።

  • ልጆቹ መንፈሱ የተሰማቸውን ጊዜ እንዲያስቡ እርዷቸው—ለምሳሌ፣ ስለአዳኙ መዝሙር በሚዘምሩበት ወይም ለሌሎች መልካም ነገር በሚያደርጉበት ጊዜ። በተለይ ተግባራዊ እርምጃ እንድንወስድ በሚያነሣሣን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የሚያመጣቸውን መንፈሳዊ ስሜቶች እንዲያውቁ እርዷቸው። መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ስሜቶች የሚያመጣልን ለምን ይመስላችኋል? መንፈስ ቅዱስ ሲናገረን ለመስማት እንችል ዘንድ ማድረግ ያሉብንን ነገሮች እንዲያስቡ ልጆቹን እርዷቸው። ድምጹን በበለጠ ጥራት ለመስማት ምን እንደምታደርጉ ተነጋገሩ።

ቅዱስ ቁርባን

ቅዱስ ቁርባንን በምወስድበት ጊዜ የአዳኙን መስዋዕት አስታውሳለሁ እንዲሁም ቃል ኪዳኖቼን አድሳለሁ።

አዳኙ ለእኛ የከፈለውን መስዋዕት እንድናስታውስ እና ቃል ኪዳኖቻችንን ለማደስ እንዲረዳን ቅዱስ ቁርባንን ሰጠን።

የበለጠ ለመማር፣ ማቴዎስ 26፥26–30. 3 ኔፊ 18፥1–12ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77፣ 79 ተመልከቱ።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • ልጆቹ “Jesus Introduced the Sacrament to the Nephites [ኢየሱስ ቅዱስ ቁርባንን ለኔፋውያን አስተዋወቀ]” የሚለውን ስዕል እንዲቀቡ ጋብዟቸው፣ ይህም በየቅዱሳት መጻህፍት ታሪኮች ማቅለሚያ መጽሐፍ፦ መፅሐፈ ሞርሞን (2019 (እ.አ.አ)) 26 ውስጥ ይገኛል። በሥዕሉ ውስጥ ሰዎቹ እያሰቡት ወዳለው ነገር እንዲጠቁሙ እነርሱን ጠይቋቸው። በ3 ኔፊ 18፥1–12 ወይም “Chapter 45: Jesus Christ Teaches about the Sacrament and Prayer [ምዕራፍ 45፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለቅዱስ ቁርባን እና ስለጸሎት አስተማረ]፣” የሚገኘውን የተወሰነ ክፍል ለልጆቹ አንብቡላቸው፤ ይህ በየመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 126–27፣ ውስ ጥ ይገኛል (ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በChurchofJesusChrist.org ውስጥ ተመልከቱ)። በቅዱስ ቁርባን ወቅት ኢየሱስ ክርስቶስን ለማስታወስ ምን ማድረግ እንችላለን?

  • ልጆቹ ሁል ጊዜ ማድረግ እንደሚገባቸው ማስታወስ ያለባቸውን፣ ጫማቸውን እንደማሠር፣ ወይም ከመብላታቸው በፊት እጃቸውን እንደመታጠብ ያሉ አንዳንድ ነገሮችን እንዲነግሯችሁ ጠይቋቸው። እነዚህን ነገሮች ማስታወስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ሞሮኒ 4፥3ን ለልጆቹ አንብቡ፣ ከዚያም ቅዱስ ቁርባንን በምንወስድበት ጊዜ ምንን ሁል ጊዜ ለማስታወስ ቃል ኪዳን እንደምንገባ እንዲያዳምጡ ጋብዟቸው። ኢየሱስ ክርስቶስን ማስታወስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? ልጆቹ የቅዱስ ቁርባን ዳቦ እና ውሃ ኢየሱስ ለእኛ ያደረገልንን እንድናስታውስ እንዴት እንደሚረዱን እንዲገነዘቡ እርዷቸው (ሞሮኒ 4፥35፥2 ተመልከቱ)።

  • በሰሌዳው ላይ “…ለማድረግ ቃል እገባለሁ” የሚል ፅሁፍ ፃፉ። የቅዱስ ቁርባኑን ፀሎት ለልጆቹ አንብቡላቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77፣ 79 ተመልከቱ)። ለእግዚአብሔር የገባነውን አንድ ቃል ኪዳን ሲሰሙ፣ ለአፍታ ቆም በሉና በሰሌዳው ላይ ያለውን ዓረፍተ ነገር በሰሙት ቃል ኪዳን እንዲያሟሉ እርዷቸው። ቅዱስ ቁርባንን በምንወስድበት ጊዜ ስንጠመቅ የገባነውን ያንኑ ቃል ኪዳን እየገባንን እንደሆነ እንዲገነዘቡ እርዷቸው።

  • የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በላያችን ላይ መውሰድ ማለት ምን ማለት ነው? ልጆቹ ይህንን ጥያቄ እንዲመልሱ ለመርዳት ስሞቻችንን በላዩ የምናደርግበትን የአንድ ነገር ምሳሌ አካፍሉ። ስሞቻችንን በእነዚህ ነገሮች ላይ የምናደርገው ለምንድን ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙን በእኛ ላይ ማድረግ የሚፈልገው ለምንድን ነው? የፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰንን የሆነውን ይህን ማብራሪያ ማካፈልን አስቡ፦ “የአዳኙን ስም በላያችን ላይ መውሰድ—በስራዎቻችን እና በቃላቶቻችን—ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ለሌሎች ማወጅን እና መመስከርን ያካትታል” (“The Correct Name of the Church[የቤተክርስቲያኗ ትክክለኛ ስም]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 88)።

የክህነት ሃይል፣ ሥልጣን እና ቁልፎች

እግዚአብሔር ልጆቹን በክህነት ሃይል አማካኝነት ይባርካል።

ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች—ሴት እና ወንድ፣ ወጣት እና አዛውንት—ከእርሱ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን ሲጠብቁ፣ የእግዚአብሔርን ሃይል ይቀበላሉ። እንደጥምቀት ያሉ የክህነት ሥርዓቶችን ስንቀበል እነዚህን ቃል ኪዳኖች እንገባለን (አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል3.53.6፣ የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ)። የበለጠ ለማወቅ፣ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Spiritual Treasures[መንፈሳዊ ሀብቶች]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019፣ (እ.አ.አ)፣ 76–79፤ “Priesthood Principles[የክህነት መርሆዎች]፣” ምዕራፍ 3ን በአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ ውስጥ ተመልከቱ።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • ልጆቹ በክህነት ምክንያት የሚቀበሉትን በረከቶች እንዲያስተውሉ እርዷቸው። የተወሰኑ ሃሳቦችን ለመስጠት፣ “Blessings of the Priesthood [የክህነት በረከቶች]” (የወንጌል ቤተመፃህፍት) የተሰኘውን ቪዲዮ ልታሳዩ ትችላላችሁ። እነዚህን በረከቶች በሰሌዳው ላይ መዘርዘርን አስቡ። እነዚህ በረከቶች ለእኛ አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? እነዚህ በረከቶች ወደ እኛ የሚመጡት በኢየሱስ ክርስቶስ እና በእርሱ ክህነት ሥልጣን እንደሆነ መስክሩ።

  • እግዚአብሔር እኛን ለመባረክ ሃይሉን እንዴት እንደሚጠቀም የሚያሣዩ ምሥሎችን ፈልገው እንዲያገኙ እርዷቸው። ለምሣሌ፣ ለእኛ የፈጠረልንን ምድር ፣ የታመሙትን የመፈወስ ምሣሌዎችን እና ለእኛ የሰጠንን ቅዱስ ሥርዓቶች ምሥል ሊፈልጉ ይችላሉ (የወንጌል ስዕሎች መፅሃፍ፣ ቁ. 346104105107120 ተመልከቱ)። ለክህነት እና ለሚያመጣችው በረከቶች አመስጋኝ የሆናችሁት ለምን እንደሆነ አካፍሉ። ልጆቹ በእግዚአብሔር የክህነት ሃይል የተባረኩባቸውን ተሞክሮዎች እንዲያስቡ እርዷቸው።

    ምስል
    A girl with long brown hair, wearing a white jumpsuit, being baptized in a baptismal font by a man in a white shirt and tie.
  • በህይወታችን የእግዚአብሔርን ሀይል በረከቶች ከምንቀበልባቸው ዋና መንገዶች አንዱ በክህነት ሥርዓቶች በኩል ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥20 ተመልከቱ)። ልጆቹ ይህንን እውነት እንዲማሩ ለመርዳት የሚከተሉትን የቅዱሳት መፃህፍት ጥቅሶች በሰሌዳው ላይ መዘርዘር ትችላላችሁ፦ 3 ኔፊ 11፥21–26፣ 33 (ጥምቀት)፤ ሞሮኒ 2 (ማረጋገጫ መቀበል)፤ ሞሮኒ 4–5 (ቅዱስ ቁርባን)። ልጆቹ እያንዳንዳቸው ከእነዚህ ምንባቦች ውስጥ አንዱን ሊመርጡ እና የሚገልፀውን ሥርዓት ሊለዩ ይችላሉ። ልጆቹ የክህነት ሥርዓቶችን በመቀበላቸው እንዴት በግል እንደተባረኩ እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው።

  • ልጆቹ በሚጠመቁበት እና የጥምቀት ቃል ኪዳናቸውን በሚጠብቁበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ኃይል እንደሚቀበሉ እንዲገነዘቡ እርዷቸው። ይህ ኃይል ልጆቹን እንዴት ሊረዳቸው እንደሚችል ጠይቋቸው።

የእግዚአብሔር ሥራ የሚመራው በክህነት ቁልፎች ሲሆን የሚከናወነውም በክህነት ሥልጣን ነው።

አንድ ግለስብ ለአንድ ጥሪ ሲለይ ወይም በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ እንዲረዳ ሲመደብ፣ እሱ ወይም እሷ በውክልና የተሠጣቸውን የክህነት ስልጣን መጠቀም ይችላሉ። በተጨማሪም፣ ብቁ የሆኑ ወንድ የቤተክርስቲያኗ አባላት በክህነት ክፍል ሊሾሙ ይችላሉ። በቤተክርስቲያኗ ያለ የክህነት ስልጣን አጠቃቀም ሁሉ የሚመራው እንደ ካስማ ፕሬዚዳንት፣ ኤጲስ ቆጶስ እና እና የቡድን ፕሬዚዳንቶች ባሉ የክህነት ቁልፎችን በያዙ ግለሰቦች ነው። የክህነት ቁልፍ፣ የጌታን ሥራ በመስራት ሂደት የክህነት አጠቃቀምን ለመምራት የሚያስችል ሥልጣን ነው።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • ማርቆስ 3፥14–15 ከልጆቹ ጋር አንብቡ፣ እንዲሁም በዚያ የተገለፀውን ክስተት ሥዕል (ለምሳሌ የወንጌል ስዕሎች፣ ቁጥር 38) አሳዩዋቸው። አንድ ሰው በክህነት ክፍል ሲሾም ወይም ለጥሪ ሲለይ አይተው ያውቁ እንደሆነ ልጆቹን ጠይቋቸው (ወይም ያሏችሁን ተሞክሮዎች ልትነግሯቸው ትችላላችሁ)። ያ አዳኙ ከሐዋርያቱ ጋር ካደረገው ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? ልጆቹ ለቤተክርስቲያን አባላት ሊሠጡ የሚችሉ እንደ አስተማሪ ወይም የድርጅት መሪ የመሳሰሉ የክህነት ጥሪዎችን ወይም የክህነት ክፍሎችን በሰሌዳው ላይ እንዲዘረዝሩ እርዷቸው። ከእያንዳንዱ ጥሪ ወይም ክፍል አጠገብ በዚያ ጥሪ ወይም ክፍል ያለ አንድ ሰው ምን የማድረግ ሥልጣን እንዳለው ልትፅፉ ትችላላችሁ። በክህነት ቁልፎች አመራር በአንድ ግለሠብ ለጥሪ መለየታችሁ ለማገልገል እንዴት እንደረዳችሁ ለልጆቹ ንገሯቸው።

    ምስል
    Christ with the twelve men chosen by Him to be His Apostles. Christ has His hands upon the head of one of the men (who kneels before Him) as He ordains the man to be an Apostle. The other eleven Apostles are standing to the left and right of Christ.
  • እንደ መኪና ወይም በር ያሉ ለመክፈት ቁልፍ የሚያስፈልጋቸው ነገሮችን እንዲያስቡ ልጆቹን ጋብዟቸው። ቁልፉ ከሌላችሁ ምን ይሆናል? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 65፥2ን አብራችሁ አንብቡ፣ ከዚያም የክህነት ቁልፎችን በምድር ላይ የመኖር አስፈላጊነትን በተመለከተ ምስክርነታችሁን አካፍሉ። “Where Are the Keys? [ቁልፎች የት አሉ]” (የወንጌል ቤተ መጻህፍት) የሚለውን ቪዲዮ ልትመለከቱ እና ሽማግሌ ጌሪኢ.ስቲቨንሰን ስለክህነት ቁልፎች ምን እንዳስተማሩ ልትፈልጉ ትችላላችሁ።

ቤተመቅደስና እና የደስታ እቅድ

ቤተመቅደስ የጌታ ቤት ነው።

ቤተመቅደሶች የሰማይ አባት ለልጆቹ ያለው ዕቅድ አካል ናቸው። በቤተመቀደስ ውስጥ ከእርሱ ጋር የተቀደሱ ቃል ኪዳኖችን እንገባለን፣ በክህነት ሃይልም የቤተመቅደሥ ቡራኬን እንቀበላለን፣ መገለጥን እንቀበላለን፣ ለሞቱ ቀድመ ዓያቶቻችን ሥርዓቶችን እናከናውናለን እንዲሁም ከቤተሰቦቻችን ጋር ለዘለአለም እንታተማለን። ይህ ሁሉ የሚቻለው በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው አማካኝነት ነው።

የምታስተምሯቸውን ልጆች ስለጌታ ቤት ቅድስና እንዲገነዘቡ እንዲሁም በቤተመቅደስ ሥርዓቶች ውስጥ ለመሳተፍ ብቁ ለመሆን እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው? እነዚህን ግብዓቶ መከለስን አስቡ፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥15–17፤ ራስል ኤም. ኔልሰን “የመዝጊያ ንግግር፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019፣ 120–22፤ “Why Latter-day Saints Build Temples [የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተመቅደሶችን ለምን እንደሚገነቡ፣” temples.ChurchofJesusChrist.org

ምስል
ወጣቶች ከቤተመቅደስ ውጪ

ቤተመቅደሶች የሰማይ አባት ለልጆቹ ያለው ዕቅድ አካል ናቸው።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • አንድ ወይም ከአንድ በላይ የቤተመቅደስ ሥዕሎችን አሳዩ። ቤተመቅደስን ልዩ ቦታ የሚያደርገው ምን እንደሆነ ልጆቹን ጠይቋቸው። እያንዳንዱ ቤተመቅደስ “ቅድስና ለጌታ— የእግዚአብሔር ቤት” የሚሉ የተቀረፁ ቃላት እንዳሉት ጥቀሱ። “ቅድስናን ለጌታ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንደሚያስቡ ልጆቹን ጠይቋቸው። ቤተመቅደስ የጌታ ቤት ተብሎ የሚጠራው ለምንድን ነው? ይህ ስለቤተመቅደስ ምን ያስተምረናል? ከልጆቹ አንዳቸው በቤተመቅደስ ተሣትፈው የሚያውቁ ከሆነ፣ እዚያ በነበሩበት ጊዜ እንዴት እንደተሰማቸው ሊያካፍሉም ይችላሉ። በቤተመቅደስ ተሳትፋችሁ የምታውቁ ከሆነ፣ የጌታ መገኘት እንዴት ተሰምቷችሁ እንደነበረ አካፍሉ እንዲሁም ቤተመቅደስ ለእናንተ ለምን የተቀደሰ ሥፍራ እንደሆነ ተናገሩ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥15–17 አብራችሁ አንብቡ። ጌታ ወደ ቅዱስ ቤቱ ከሚገቡ ሰዎች ምን እንደሚጠብቅ እንዲፈልጉ ልጆቹን ጠይቋቸው። ወደ ቤተመቅደስ ለመግባት ብቁ መሆን የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? እንደዚህ ውይይት አካል ስለ ቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ እንዲሁም እንዴት ማግኝት እንደሚቻል ከልጆቹ ጋር ተነጋገሩ። የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ቃለመጠይቅ ምን እንደሚመስል እና ስለሚጠየቁት ጥያቄዎች ለእነርሱ እንዲያካፍል አንድን የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል ልትጋብዙ ትችላላችሁ።

በቤተመቅደስ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እንገባለን።

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን “ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤታችን የሚመልሰንን የቃል ኪዳን መንገድ ተከትለን ከሰማያዊ ወላጆቻችንና ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር እንድንሆን ይጋብዘናል” ሲሉ አስተምረዋል። (“ኑ፤ ተከተሉኝ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 91)። የቃል ኪዳን መንገድ ጥምቀትን፣ ማረጋገጫ መቀበልን እና የቤተመቅደስ ቡራኬን እና እትመትን እንደሚያካትት እንዲገነዘቡ ልጆቹን እርዷቸው።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • ስንጠመቅ ከእግዚአብሔር ጋር የምንገባውን እንዲሁም ቅዱስ ቁርባን በምንወስድበት ጊዜ የምናድሰውን ቃል ኪዳን እንድትከልሱ እንዲረዷችሁ ልጆቹን ጠይቋቸ (ሞዛያ 18፥10ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77፣ 79 ተመልከቱ)። የቤተመቅደስን ምስል አሳዩና የሰማይ አባት በቤተመቅደስ ውስጥ ለእኛ ሊሰጠን የሚፈልጋቸው ተጨማሪ በረከቶች እንዳሉት አብራሩ።

  • ወደ መንገድ የሚያመራ በር ሳሉ። የመሄጃ መንገድ መኖሩ ለምን ጠቃሚ እንደሆነ እንደሚያስቡ ልጆቹን ጠይቋቸው። ኔፊ የጥምቀትን ቃል ኪዳንን ከበር ጋር የሚያነጻጽርበትንና ከጥምቀት በኋላ በመንገዱ እንድንቀጥል የሚጋብዝበትን 2 ኔፊ 31፥17–20 አብራቸሁ አንብቡ። በቤተመቅደስ የሚገቡትን ቃል ኪዳኖች ጨምሮ ከጥምቀት በኋላ የምንገባቸው ብዙ ቃል ኪዳኖች አሉ። ፕሬዚዳንት ኔልሰን ይህንን መንገድ “የቃል ኪዳን መንገድ” ብለው እንደጠሩት አብራሩ።

በቤተመቅደስ ውስጥ ለሞቱ ቅድመ ዓያቶቻችን ልንጠመቅ እና ማረጋገጫ ልንቀበል እንችላለን።

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፣ ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች፣ ወንጌልን ሳያውቁ የሞቱ ቢሆኑም እንኳን፣ ከእርሱ ጋር ለመኖር መመለስ እንዲችሉ ያደርጋል። በቤተመቅደስ ልንጠመቅ እና የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል በመሆን ማረጋገጫ ልንቀበል እንችላለን።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • በራሳችሁ ልታደርጉት ያልቻላችሁትን አንድ ነገር አንድ ሰው ያደረገላችሁን ጊዜ ተናገሩ። ልጆቹ ተመሳሳይ ተሞክሮዎችን እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። ወደ ቤተመቅደስ ስንሄድ ለሌሎች ለሞቱ ሰዎች እንደ ጥምቀት ያሉ ቅዱስ ሥርዓቶችን ማከናወን እንደምንችል ግለፁ። ለሞቱ ሰዎች ሥራ ስንሰራ እንደ ኢየሱስ የምንሆነው እንዴት ነው? በራሳችን ልናደርገው የማንችለውን ምን አድርጎልናል?

  • ለቅድመ ዓያቶቻቸው የተጠመቁ አንድ ወይም ከአንድ በላይ ወጣቶች ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። የቤተመቅደስ ተሞክሯቸው እንዴት እንደነበር ጠይቋቸው። ለቅድመ ዓያቶቻቸው ይህንን ሥራ በመስራታቸው እንዴት እንደተሰማቸው እንዲያካፍሉ አበረታቷቸው።

  • ሥሮቹን እና ቅርንጫፎቹን ጨምሮ በሰሌዳው ላይ አንድ ዛፍ ሳሉ። ቤተሰብ እንዴት እንደ ዛፍ እንደሆነ እንዲያስቡ ልጆቹን ጠይቋቸው። ሥሮቹን ቅድመ ዓያቶች፣ ቅርንጫፎቹን ዘሮች፣ ግንዱን እኔ ብላችሁ ሥም ስጡ። ይህንን ዓረፍተ ነገር ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥18 ውስጥ አብራችሁ አንብቡ፦ “ያለ እነርሱ ፍጹም ልንሆን አንችልም፤ ወይም እነርሱም [ቅድመ አያቶቻችን] ያለእኛ ፍጹማን ሊሆኑ አይችሉም።” እንደሚከተሉት ያሉ ጥያቂዎችን ጠይቁ፦ “ቅድመ ዓያቶቻችንን የምንፈልጋቸው ለምንድን ነው? ዘሮቻችን የሚፈልጉን ለምንድን ነው? ወላጆቻችን፣ ዓያቶቻችን እና ሌሎች ቅድመ ዓያቶቻችን የረዱን እንዴት ነበር? በቀሪው የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥18 ውስጥ ቅድመ ዓያቶቻችንን እንዴት መርዳት እንደምንችል የሚገልጽ ሀረግ እንዲፈልጉ ልጆቹን ጋብዟቸው።

  • በቤተመቅደስ ውስጥ ሥርዓቶች እንዲከናወንለት የሚያስፈልገውን የአንድ ቅድመ ዓያት ሥም ለመፈለግ ከእያንዳንዱ ልጅ ወላጆች ጋር መሥራትን አስቡ (FamilySearch.org ተመልከቱ)።

አትም