ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
መስከረም 13–19 (እ.አ.አ)። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 102–105፥ “ከብዙ ስቃይ በኋላ … በረከት ይመጣል”


“መስከረም 13–19 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 102–105፥ ‘ከብዙ ስቃይ በኋላ … በረከት ይመጣል፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“መስከረም 13–19 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 102–105፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ወንዶች ከነሰረገላቸው

ሲ. ሲ. ኤ. ክሪስቲያንሰን [1831–1912 (እ.አ.አ)]፣ የፅዮን ሰፈር፣ በ1878 (እ.አ.አ) አካባቢ tempera on muslin፣ 198 × 290 ሴንቲ ሜትር። ብሪንግሀም ያንግ ዩኒቨርሲቲ የሥነጥበብ ሙዚየም፣ የ ሲ. ሲ. ኤ. ክሪስቲያንሰን የልጅ ልጆች ስጦታ፣ 1970 (እ.አ.አ)

መስከረም 13–19 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 102–105

“ከብዙ ስቃይ በኋላ … በረከት ይመጣል”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 102–5 ውስጥ ለእናንተ ትርጉም ያለው መርህ ምንድን ነው? ስለነዚህ መርሆዎች ሀሳቦቻችሁን እና ግንዛቤዎቻችሁን ለመመዝገብ አስቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በከርትላንድ የሚገኙት ቅዱሳን፣ በጃክሰን ካውንቲ፣ ምዙሪ ውስጥ ያሉ ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው ከቤታቸው መባረራቸውን ሲሰሙ እጅግ አዝነው ነበር። እንግዲያውስ ጌታ “የፅዮን መዳን” “በኃይል ይመጣል” ብሎ ሲናገር አበረታች ነበረ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 103፥ 15)። ያንን ተስፋ በልባቸው ይዘው፣ ከ 200 በላይ ወንዶች፣ እና ከ 25 በላይ ሴቶች እና ልጆች፣ በኋላ ላይ የፅዮን ሰፈር በመባል በሚጠራው የእስራኤል ሰፈር በተባለው ውስጥ ተመለመሉ። ተልዕኮው ወደ ምዙሪ በመሄድ ፅዮንን ማዳን ነበር።

ለሰፈሩ አባላት፣ ፅዮንን ማዳን ቅዱሳንን ወደ መሬታቸው መመለስ ማለት ነበር። ነገር ግን ሰፈሩ ጃክሰን ካውንቲ ከመድረሱ በፊት፣ ጌታ መሄድ እንዲያቆሙ እና የፅዮን ሰፈርን እንዲበትን ለጆሴፍ ስሚዝ ነገረው። አንዳንድ የሰፈር አባላት በዚህ አዲስ መመሪያ ግራ ተጋቡ እና ተበሳጩ፤ ለእነርሱ፣ ጉዞው አልተሳካም እና የጌታ ቃል ኪዳን አልተሟላም ማለት ነበር። ነገር ግን ሌሎች በተለየ መንገድ አዩት። ግዞተኞቹ ቅዱሳን ፈፅሞ ወደ ጃክሰን ካውንቲ ባይመለሱም፣ ተሞክሮው ለፅዮን በተወሰነ ደረጃ “ቤዛ” አመጣ፣ እናም ይህም የመጣው “በኃይል” ነበር። ታማኝ የፅዮን ሰፈር አባላት፣ ብዙዎች ከጊዜ በኋላ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች የሆኑት፣ ልምዱ በእግዚአብሔር ሀይል፣ በጆሴፍ ስሚዝ መለኮታዊ ጥሪ እና በፅዮን—ቦታው ፅዮን ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ህዝብ በሆኑት ፅዮን—ያላቸውን እምነት እንዳጠነከረ መስክረዋል። ያልተሳካለት የሚመስለውን ይዚህን ሥራ ዋጋ ከመጠራጠር ይልቅ፣ ምንም እንኳን ሁሉንም ነገር ባንረዳም እውነተኛው ተግባር አዳኛችንን መከተል መሆኑን ተምረዋል። በመጨረሻም ፅዮን የምትድነው በዚህ መንገድ ነው።

ቅዱሳን 1፥194–206፤ “ተቀባይነት ያለው የፅዮን ሰፈር መስዋት፣” ራዕያት በአገባብ፣ 213–18 ይመልከቱ።

ምስል
ትንሽ ወንዝ

እዚህ እንደሚታየው የፅዮን ሰፈር በትናንሽ የዓሣ ማጥመጃ ወንዝ ዳርቻዎች ላይ ቆይቷል፣ ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 102፥12–23

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉት መመሪያዎች ዓላማ ምንድነው?

ክፍል 102 የመጀመሪያው የቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ ሸንጎ በተደራጀበት በከርትላንድ ኦሃዮ ውስጥ የተካሄደውን ስብሰባ ቃለጉባኤ ይይዛል። ቁጥሮች 12–23 ከፍተኛ ሸንጎ ከባድ መተላለፍ ላደረጉ ሰዎች የፀባይ ማረሚያ ሸንጎ እንዴት እንደሚያካሂዱ ይገልጻል።

ፕሬዘደንት ኤም. ራስል ባላርድ እንዳስተማሩት፣ አንዳንድ ጊዜ አባላት የቤተክርስቲያኗ የዲሲፕሊን ካውንስል ለምን እንደሚካሄድ ይጠይቃሉ። ዓላማው ሦስት እጥፍ ነው፣ የተላለፈውን ነፍስ ለማዳን፣ ንጹሁን ለመጠበቅ፣ የቤተክርስቲያኗን ንፅህና፣ ታማኝነት እና መልካም ስም ለመጠበቅ (”ለመጀመር ዳግም እድል፤፟ የቤተክርስቲያኗ የዲሲፕሊን ካውንስል እና የበረከት መመለስ፣” ኤንዛይን፣ መስከረም 1990 [እ.አ.አ]፣ 15)።

በተጨማሪም ከየወንጌል ርዕሶች፣ “የቤተ ክርስቲያን የዲሲፕሊን ካውንስል፣” topics.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ፥።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 103፥1–12፣ 36105፥1–19

ፅዮን መገንባት የምትችለው በፅድቅ መርሆዎች ላይ ብቻ ነው።

ቅዱሳናት በምዙሪ በቃል ኪዳን የተሰጣቸውን ምድር ለምን አጡ? እና ለምንድን ነው ጌታ የፅዮን ሰፈር ሰዎቹን ወደ መሬታቸው እንዲመልሷቸው ያልፈቀደው? በእርግጠኝነት የምዙሪ አመፅኞ ድርጊቶች ሚና ተጫውቷል፣ እናም የምዙሪ ገዢ ለቅዱሳኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል ግን ምንም አልደረገም። ጌታም “በህዝቤ መተላለፍ ባይሆን ኖሮ” ፅዮን “አሁንም ይድኑ ነበር” ብሏል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 105፥2)። እናንተ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች103፥1–2፤ 36105፥1–19ን በምታነቡበት ጊዜ፣ በምዙሪ ውስጥ ፅዮንን ለማቋቋም እንቅፋት የሚሆኑ እና ሌሎች ሊረዱ የሚችሉ አንዳንድ ነገሮችን አስተውላችሁ ይሆናል። ፅዮንን በልባችሁ እና በቤተሰባችሁ ውስጥ ለመመስረት ሊረዳችሁ የሚችል ምን ትማራላችሁ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 103፥12–13105፥1–6፣ 13–19

በረከቶች ከመከራዎች እና ከእምነት ፈተናዎች በኋላ ይመጣሉ።

በብዙ መንገዶች፣ በፅዮን ሰፈር ውስጥ መሳተፍ የእምነት ፈተና ነበር። ጉዞው ረጅም ነበር፣ አየሩም ሞቃት ነበር፣ እንዲሁም ምግብ እና ውሃ አንዳንድ ጊዜ እጥረት ነበረ። እናም ከዚህ ሁሉ ፅናት በኋላ፣ ቅዱሳን ወደ ሃገራቸውቸው መመለስ አልቻሉም። በ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 103፥12–13 እና 105፥1–6፣ 13–19 ውስጥ ያሉት መርሆች እንዴት የፅዮን ሰፈር አባላት ለማደራጀት የተሰጠው ትእዛዝ በእርግጥ በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ መሆኑን እንዲገነዘቡ ረድቷቸው ይሆናል። በእናንተ የእምነት ፈተናዎች ውስጥ እነዚህ መርሆዎች እንዴት ሊረዷችሁ ይችላሉ?

ስለፅዮን ሰፈር አባላት አጋጣሚም “በዳግም የመመለስ ድምጾች” የሚለውን በዚህ ክፍል በስተመጨረሻ ያለውን ለማንበብ ትችላላችሁ። በእነርሱ አስተያየት ምን ያስደነቀቃችሁ ነገር አለ? ከእነሱ ምሳሌ ምን ትምህርት ማግኘት ትችላላችሁ?

በተጨማሪም ዴቪድ ኤ. ቤድነር “በጌታ ጎን፥ ከፅዮን ሰፈር የምናገኛቸው ትምህርቶች፣” ኤንዛይን ሃምሌ 2017 (እ.አ.አ)፣ 26–35 ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 104፥11–18፣ 78–83

እኔ “የምድር በረከቶች በመጋቢነት ተጠያቂ” ነኝ።

በምዙሪ ከተከሰቱት ፈተናዎች በተጨማሪ፣ በ1834 (እ.አ.አ) ቤተክርስቲያኗ፣ ከባድ እዳዎችን እና ወጪዎችን ጨምሮ፣ የገንዘብ ችግሮች አጋጥሟት ነበር። በክፍል 104 ውስጥ ጌታ በቤተክርስቲያኗ የገንዘብ ሁኔታ ላይ ምክር ሰጥቷል። በቁጥሮች 11፟፟–18 እና 78–83 ላይ ያሉትን መሰረታዊ መርሆዎችን ወደ ራሳችሁ የገንዘብ ውሳኔዎች እንዴት ተግባራዊ ማድረግ ትችላላችሁ?

ቤተክርስቲያኗ ከእዳ ባርነት ነፃ እንድትወጣ ጌታ ካዘጋጃቸው መንገዶች ውስጥ ለመማር፣ “በመንግሥተ ሰማይ ውስጥ የሚገኝ ሀብት፤ የጆን ታነር ታሪክ” የሚለውን ቪዲዮ እዩ፣ (ቪድዮ፣ ChurchofJesusChrist.org)።

ለቅዱሳኑ ለማቅረብ ስለሚያደርገው የጌታን “የራሱን መንገድ”(ቁጥር 16) የበለጠ ለማወቅ፣ የፕሬዚዳንት ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍን መልእክት “በጌታ መንገድ ማቅረብ” ማጥናት ትችላላችሁ (ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2011 (እ.አ.አ)፣ 53–56)።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 103፥12፣ 36105፥9–13የእናንተ ቤተሰብ (ወይም ከቅድመ አያቶቻችሁ አንዱ) እናንተ እንደጠበቃችሁት ያልሆነ አንድ ነገር እንዲያደርግ ተጠይቆ ያውቃል? ጉዞአቸው እንደጠበቁት ስላልተሳካ ከፅዮን ሰፈር አባላት ስለነበራቸው ስሜት ምን መማር ትችላላችሁ? (“በዳግም የመመለስ ድምጾች” በዚህ ዝርዝር መጨረሻ ላይ ይመልከቱ)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 104፥13–18ጌታ ምን ሰጥቶናል? በእነዚህ ነገሮች ምን እንድናደርግ ይጠብቅብናል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 104፥23–46ለሚያምኑ ጌታ ምን ያህል ጊዜ “በረከትን እንደሚያበዛ” ቃል እንደገባ ለማግኘት ቤተሰባችሁ እነዚያ ጥቅሶች ሊፈትሹ ይችላሉ (ቁጥር 23)። ምናልባት “በረከቶቻችሁን ለመቁጠር” (“በረከታችሁን ቁጠሩ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 241) እናም በችግር ጊዜ እንዲህ ማድረጋችን እንዴት እንደሚረዳን ለመወያየት ይህ ጥሩ ጊዜ ሊሆን ይችላል። ትትንሽ ልጆች በተለይ ለሚያመሰግኗቸው በረከቶች ስዕሎችን መሳል ይወዳሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 105፥38–41ሌሎች ደግነት በጎደለው ሁኔታ ወይም ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ ሲይዙን “የሰላም ሀሳብ” (ቁጥር 40) ማቅረብ የምንችለው እንዴት ነው? በቤታችን ውስጥ “የሰላም አርማ” (ቁጥር 39) ለመሆን ምን ማድረግ አለብን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት ይህን ይመልከቱ፥ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል።

የሚመከር መዝሙር፥ “በረከቶቻችሁን ቁጠሩ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 241።

ምስል
የዳግም መመለስ ድምጾች ተምሳሌት

የዳግም መመለስ ድምጾች

የፅዮን ሰፈር

የፅዮን ሰፈር ቅዱሳንን በጃክሰን ካውንቲ ወደ መሬት ንብረታቸው በጭራሽ ስላልመለሳቸው፣ ብዙ ሰዎች ጥረታቸው ከንቱ እንደሆነ ተሰምቷቸው ነበር። ሆኖም፣ በርካታ የፅዮን ሰፈር ተሳታፊዎች ልምዶቻቸውን ወደ ኋላ ተመልሰው በመመልከት፣ ጌታ በህይወታቸው እና በመንግሥቱ እንዴት ከፍ ያለ ዓላማ እንደ ፈፀመ አዩ። የተወሰኑ ምስክርነቶቻቸውም እነሆ።

ጆሴፍ ስሚዝ

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ

ከፅዮን ሰፈር ከ40 ዓመታት በላይ በኋላ፣ የሰፈሩ አባል የነበረው ጆሴፍ ያንግ፣ ጆሴፍ ስሚዝ የሚከተሉትን እንደተናገረ ዘግቧል፥

“ወንድሞች፣ አንዳንዶቻችሁ በምዙሪ ስላልተዋጋችሁ ተናዳችሁብኛል፣ ነገር ግን ልንገራችሁ፣ እግዚአብሔር እንድትዋጉ አልፈለገም። ልክ እንደ አብርሓም ታላቅ መስዋትነት ከከፈሉ፣ ህይውታቸውን በመሰዋት ካዘጋጁት ሰዋች ካልወሰደ በቀር፣ በአስራ ሁለት ሰዎች፣ እናም የእነርሱን መሪነት የሚከተሉ በስራቸው በሚገኙ ሰባዎች ለምድር ህዝብ የወንጌልን በር ለመክፈት አይችልም።

አሁን ጌታ አሥራ ሁለቱን እና ሰባዎቹ አግኝቷል፣ እናም መስዋዕትን የሚያደርጉ፣ ሌሎች የሰባዎች ጉባኤም ይጠራሉ፣ እናም መስዋዕታቸውን እና ምፅዋታቸውን አሁን ያላደረጉም እነዚያ ከዚያ በኋላ መስዋዕትን ያደርጋሉ።”1

ብሪገም ያንግ

ምስል
ብሪገም ያንግ

“ወደ ምዙሪ ስንደርስ ጌታ አገልጋዩን ጆሴፍ ስሚዝ አነጋገረው እናም እንዲህ አለው፥ “መሰዋዕትህን ተቀብያለሁ” እና እንደገና የመመለስ መብት አግኝተናል። ስመለስ ብዙ ጓደኞች በድካም ወደ ምዙሪ በመሄድ ከዚያም ምንም ስለማካሰት ተመልሶ መምጣት ምን ጥቅም እንደነበረው ጠየቁኝ። ‘ማንን ጠቀመ?’ ብለው ጠየቁ። ‘ጌታ ይህን እንዲከናወን ካዘዘ፣ ይህን ሲያደርግ ምን ዓይነት አላማ ነበረው?’ … ለእነዚያ ወንድሞች ጥሩ እንደተከፈለኝ፣ ከከፍተኛ ወለድ ጋር እንደተከፈለኝ፣ አዎን መለኪያዬ ከነቢዩ ጋር በመጓዝ የተቀበልኩትን እውቀት ተትረፈርፎ ሞልቶልኝ ነበር ብዬ ነገርኳቸው።”2

ውልፈርድ ውድረፍ

ምስል
ውልፈርድ ውድረፍ

“ከእግዚአብሔር ነቢይ ጋር በፅዮን ሰፈር ውስጥ ነበርኩ። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያደረገውን ግንኙነት አየሁ። የእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋር አየሁ። እርሱ ነቢይ መሆኑን አየሁ። በእዚያ ተልእኮ ላይ በእግዚአብሔር ኃይል ለእሱ የታየው ነገር ለእኔም ሆነ መመሪያውን ለተቀበሉ ሁሉ ትልቅ ዋጋ ነበረው።”3

“የፅዮን ሰፈር አባላት በተጠሩ ጊዜ ብዙዎቻችን አንተዋወቅም ነበር፤ እኛ እርስ በእርሳችን እንግዳ ነበርን እናም ብዙዎች ነቢዩን በጭራሽ አይተውት አያቁም ነበር። እኛ ወደ ውጭ፣ እንዲሁም ልክ እንደ ተቆራረጠ በቆሎ ቅርፅ፣ በመላው አገሪቱ ተበታትነን ነበር። እኛ ወጣት ወንዶች ነበርን፣ እና በዚያ በመጀመሪያው ጊዜያት ሄደን ፅዮንን እናድን ዘንድ ተጠርተን ነበር፣ እናም ማድረግ ያለብንን በእምነት ማድርግ ነበረብን። ከተለያዩ ግዛቶች ወደ ከርትላንድ ተሰበሰብን እናም የእግዚአብሔር ትእዛዝ በእኛ ላይ ተፈጻሚ እንዲሆን፣ ፅዮንን ለማዳን ሄድን። እግዚአብሔር የአብርሃምን ሥራ እንደተቀበለው ሥራችንን ተቀበለ። ከሃዲዎች እና የማያምኑ ብዙ ጊዜ ‘ምን ተደረገ?’ በለው ቢጠይቁም እንኳ፣ እኛ ብዙዎችን አከናወንን። በጭራሽ በሌላ መንገድ ፈፅሞ ማግኘት የማንችለው ተሞክሮ አግኝተናል። የነቢዩን ፊት የማየት እድል ነበረን፣ እናም አንድ ሺህ ማይሎችንን ከእርሱ ጋር አብረን የመጓዝ እድል ነበረን፣ ከእርሱም ጋር የእግዚአብሔርን መንፈስ ሥራ፣ የኢየሱስ ክርስቶስም ለእርሱ መገለጥን፣ እናም የእነዚያ መገለጦች ፍጻሜን አየን። ደግሞም በዚያች በመጀመሪያ ቀን ሁለት መቶ ሽማግሌዎችን ከየአገሩ ሁሉ ሰበስቦ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንድንሰብክ ወደ ዓለም ሁሉ ልኮናል። ከፅዮን ሰፈር ጋር ባልሄድ ኖሮ ዛሬ እዚህ [በአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ጉባኤ ውስጥ በማገልገል፤ በሶልት ሌክ ሲቲ] ውስጥ ባልሆን ነበር። ወደዚያ በመሄድ ወንጌልን ለመስበክ ወደ ወይኑ አትክልት ተላክን፣ እናም ጌታ ስራችንን ተቀበለ። በስራዎቻችን ሁሉ እና በስደታችን ሁሉ፣ ሕይወታችን ብዙውን ጊዜ አደጋ ላይ የተጋለጠ ሆኖ፣ በእምነት ለመስራት እና ለመኖር ነበረብን።”4

“በፅዮን ሰፈር በመጓዝ ያገኘነው ተሞክሮ ከወርቅ እጅግ የላቀ ነበር።”5

ማስታወሻዎች

  1. ጆሴፍ ያንግ ቀዳማዊ፣ History of the Organization of the Seventies [የሰባዎች ጉባኤ የምስረታ ታሪክ] [1878 (እ.አ.አ)]፣ 14።

  2. “ስብከት፣” ዴዘረት ኒውስ፣ ታህሳስ 3፣ 1862 (እ.አ.አ)፣ 177።

  3. የጉባኤ ሀተታ፣ ሚያዝያ 1898 (እ.አ.አ)፣ 29–30፤ በተጨማሪም Teachings of Presidents of the Church: Wilford Woodruff [የቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንቶች አስተምህሮ፥ ዊልፈርድ ዉድረፍ] [2004 (እ.አ.አ)፣ 135 ይመልከቱ።

  4. “ስብከት፣” ዴዘረት ኒውስ፣ ታህሳስ 22፣ 1869 (እ.አ.አ)፣ 543፤ በተጨማሪም Teachings: Wilford Woodruff [ትምህርቶች፥ ዊልፈርድ ዉድረፍ]፣ 138 ይመልከቱ።

  5. ዴዘረት ኒውስ፣ በሳምት ሁለት ጊዜ የሚታተም፣ ነሃሴ 27፣ 1880 (እ.አ.አ)፣ 2፤ እንዲሁም ይመልከቱ፥ Teachings: Wilford Woodruff [ትምህርቶች፥ ዊልፈርድ ዉድረፍ]፣ 138

ምስል
የፅዮን ሰፈር በወንዙ

ፅዮን ሰፈር (በአሳ ማጥመጃ ወንዝ የፅዮን ሰፈር)፣ በጁዲት ኤ. መኸር

አትም