ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
መስከረም 20–26። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 106–108፥ “ሰማያት … እንዲከፈቱ”


“መስከረም 20–26። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን 106–108፥ ‘ሰማያት … እንዲከፈቱ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) (2020 (እ.አ.አ))

“መስከረም 20–26። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 106–108” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ፀሀይ በደመናዎች አልፋ ስታበራ

መስከረም 20–26

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 106–108

“ሰማያት … እንዲከፈቱ”

ሽማግሌ ዩልሲስ ሶሬስ እንዳስተማሩት፣ “[በአዳኝ] ውስጥ መኖር፣ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ እራሳችንን ማስመጥ፣ በእነሱ መደሰት፣ ትምህርቱን መማር፣ እንዲሁም እሱ እንደኖረበት ለመኖር ጥረት ማድረግ አለብን” (“እንዴት ልረዳው እችላለሁ?ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 7)። በትምህርት እና ቃልኪዳኖች 106–8 ውስጥ ራሳችሁን ስታሰምጡ ባገኛችኋቸው እውነቶች ለመኖር ጥረት የምታደርጉባቸውን መንገዶች መዝግቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በመጀመሪያ እይታ፣ ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 107 የክህነት ሀላፊነቶችን በጌታ ቤተክርስቲያን አመራር መዋቅር ስለማደራጀት ብቻ የሚናገር ሊመስል ይችላል። በእርግጥም ይህ ራዕይ በታተመ ጊዜ፣ የቤተክርስቲያኗ አባልነት ቀድሞውኑ የነበራቸውን ጥቂት መሪዎችን አቅም እያለፈ ይገኝ ነበር። ስለዚህም የቀዳሚ አመራር፣ የአስራ ሁለቱ ሸንጎ፣ ሰባዎች፣ ኤጲስ ቆጵሳት፣ እና የሸንጎ አምራሮች ሚናዎችን እና ሀላፊነቶችን መዘርዘር በእርግጥ አስፈላጊ እና አጋዥ ነበሩ። የክህነት ስልጣኖችን እና ሸንጎዎችን እንዴት ማደራጀት ከሚቻልበት በላይ የሆኑ በጣም ብዙ መለኮታዊ መመሪያዎች በክፍል 107 ውስጥ አሉ። በዚህም “በአዳም ዘመን [ስለተቋቋመ]” አንድ ጥንታዊ የክህነት ሥርዓት ጌታ ያስተምረናል (ቁጥር 41)። አላማው ከመጀመሪያ ጀምሮ፣ እናንተን ጨምሮ፣ የእግዚአብሔር ልጆች የወንጌልን የማዳን ስርዓቶች እንዲቀበሉ እና “በቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ በረከቶች ላይ ሁሉ—የመንግስተ ሰማያትን ሚስጥራት ለመቀበል ልዩ መብት [ባላቸው]፣ [እና] ሰማያት ለእነርሱ [በሚከፈቱላቸው]” እንዲደሰቱበት ነው (ቁጥሮች 18–19)።

በተጨማሪም “የጥንት ስርዓትን በዳግም መመለስ፣” ራዕይ በአገባብ፣ 208–12ን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክቶች

ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 106108

ጌታ እንዲያገለግሉ የሚጠራቸውን ያስተምራል፣ ያበረታታል፣ እንዲሁም ይደግፋቸዋል።

ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 106 እና 108 ውስጥ፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ እንዲያገለግሉ ለተጠሩ ሁለት አባላት ጌታ ምክር እና የተስፋ ቃል ሰጠ። በእነዚህ ራዕዮች ውስጥ ማበረታቻችን እና በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ስላለው አገልግሎታችሁ ግንዛቤን የሚሰጡት ሀረጎች ምንድን ናቸው? ሊታሰብባቸው የሚገቡ ሁለቱ እነሆ፥

ክፍሎች 106 እና 108 ውስጥ ሌሎች ለእናንተ ትርጉም ያላቸው ሃረጎች የትኞቹ ናቸው?

በተጨማሪም ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “በእግዚአብሔር ሀይል እና ስልጣን ማገልገል፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 68–75፤ “ዋረን ኮውደሪ፣” ራእዮች በአገባብ፣ 219–23፤ “‘በሰሩት’ ራዕይን መሻት፣” ራእዮች በአገባብ፣ 224–28።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107

ጌታ ቤተክርስቲያኗን በክህነት ስልጣን ይመራታል።

የወንጌል ዳግም መመለስን ስላጠናችሁ፣ ጌታ ብዙውን ጊዜ በአንድ ራእይ ውስጥ አንድን ትምህርት ሙሉ በሙሉ እንደማያብራራ አስተውላችሁ ይሆናል። በዚህ ምትክ፣ ነገሮችን ሁኔታዎች ባስፈለጉበት ጊዜ “በስርዐት ላይ ስርዐት” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥12) ይገልጻል። ምንም እንኳን ከዚህ በፊት እስከ 1829 (እ.አ.አ) መጀመሪያ ድረስ ጌታ ስለ ክህነት መመሪያ ቢሰጥም (ለምሳሌ፣ ክፍሎች 20 እና 84ን ይመልከቱ)፣ በማደግ ላይ ያሉትን መንጋዎቹን ለማስተዳደር እና ለመምራት ስለሚያስፈልጉ ልዩ የክህነት ሀላፊነቶች በሚመለከት በ1835 (እ.አ.አ) ለቅዱሳኑ ተጨማሪ መመሪያ ሰጣቸው።

ስለሚከተሉት የክህነት ሀላፊነቶች ስታነቡ፣ በእነዚህ ጥሪዎች የሚያገለግሉትን “በእምነት፣ ታማኝነት፣ እና ጸሎ[ቶች]” እንዴት መደገፍ እንደምትችሉ አስቡበት (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥22)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥1–20

የክህነት ስርዓቶች ለሁሉም የሰማይ አባት ልጆች መንፈሳዊ እና ጊዜያዊ በረከቶችን ይሰጣሉ።

ሽማግሌ ኒል ኤል. አንደርሰን እንዳስተማሩት፥ “ክህነት ሁሉንም፣ ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ እና ልጆችን፣ ለመዳን እና ለመባረክ የተሰጠው የእግዚአብሔር ሀይል እና ስልጣን ነው። … ብቁ ስንሆን፣ የክህነት ስርዓቶች በምድር ላይ ህይወታችንን ያበለጽጋሉ እናም በወደፊት አለም ለሚመጡት አስደናቂ ተስፋዎች ያዘጋጁናል” (”በክህነት ውስጥ ያለ ኃይል፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 92)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥1–20 (በተለይ ቁጥሮች 18–20ን ይመልከቱ) እና የተቀረውን የሽማግሌ አንደርሰንን መልእክት ስታነቡ፣ የእግዚአብሔር ኃይል በምድር ላይ ሕይወታችሁን እንዴት እንደሚያበለፅገው እና ለዘለአለም እንደሚያዘጋጃችሁ ግንዛቤዎችን ለመጻፍ አስቡበት። እነዚያን በረከቶች ይበልጥ በሙሉ ለመቀበል—እና ሌሎች እንዲቀበሉት ለማገዝ—ምን እያደረጋችሁ ነው?

ደግሞም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥19–27፤ ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “የክህነት ቁልፎች እና ስልጣን፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 69–72 ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥41–57

ክህነት ቤተሰቦችን ይባርካል።

አዳም የእርሱ ዘሮች በክህነት እንዲባረኩ ይፈልግ ነበር። እሱ ምን የተስፋ ቃሎችን ተቀበለ? ( ቁጥሮች 4255ን ይመልከቱ)። አዳም ስላደረገው ነገር ሲታነቡ፣ ቤተሰባችሁ በክህነት በረከቶች እንዲደሰቱ የምትፈልጉትን የራሳችሁን ምኞቶች አስቡ። ቤተሰባችሁ እነዚህን በረከቶች እንዲያገኙ ለመርዳት ምን ለማድረግ ተነሳስታችኋል?

ምስል
አዳም ዘሮቹን ሲባርክ

አዳም ዘሮቹን ሲባርክ፣ በክላርክ ኬሊ ፕሪይስ

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 106፥6ቤተሰባችን “በሰማይ ደስታ” ለመፍጠር ምን ማድረግ ይችላል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥22መሪዎቻችንን “በእምነት፣ ታማኝነት፣ እና ጸሎት” ለመደገፍ ምን እያደረግን ነው?

ትምህር እና ቃልኪዳን 107፥27–31፣ 85የቤተክርስቲያኗ ሸንጎዎችን የሚመሩ መርሆዎች እንደቤተሰብ አንድ ላይ እንድንመክርም ሊረዱን ይችላሉ። ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የትኞቹን መርሆዎች በቤተሰብ ምክክር ላይ ተግባራዊ ማድረግ አንችላለን? (ኤም. ራስል ባላርድ፣ “የቤተሰብ ሸንጎዎች፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 63–65ን ይመልከቱ።)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥99–100ለአንድ የቤተሰብ አባል ስለቤት ስራ የጽሑፍ መመሪያዎችን ስጡ፣ እና ስራውን እንዴት ለማከናወን እንዲመርጥ ወይም እንድትመርጥ ጋብዙ፥ በትጋት፣ በዝግታ፣ ወይም መመሪያዎቹን ሳያነቡ። የተቀረው የቤተሰብ አባል ሥራውን ሲሰራ ወይም ስትሰራ ይመልከቱ እና የቤተሰብ አባሉ የትኛውን አቀራረብ እንደመረጠ/እንደመረጠች ይገምቱ። ከዚያ ሌሎች የቤተሰብ አባላት ተራ እንዲያገኙ ያድርጉ። ሀላፊነቶቻችንን እንድንማር እና በትጋት እንድንሠራ ጌታ ለምን ይፈልጋል? (ቤኪ ክሬቨን፣ “ጥንቃቄ እና ተለምዶ፣” ኢንዛይን ወይም ላያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 9–11 ይመልከቱ።)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 108፥7በንግግራችን ውስጥ አንዳችን ሌላውን እንዴት ማጠንከር እንችላለን? በጸሎታችን ውስጥስ? በማሳሰቢያችን ወይም በማበረታቻችንስ? በሁሉም ተግባሮቻችንስ? በቤተሰብ ደረጃ እንድትሰሩ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን መምረጥ ትችላላችሁ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “እኛ የነብያትን ድምጽ እንስማለን፣” መዝሙር፣ ቁጥር 22።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ። መንፈሳዊ እይታዎች ወይም ግንዛቤዎች ወደ እናንተ በሚመጡበት ጊዜ መዝግቧቸው። ይህን ሲታደርጉ፣ የእርሱን መመሪያ ከፍ አድርጋችሁ እንደምትመለከቱ ለጌታ ታሳያላችሁ። (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 1230ን ይመልከቱ።)

ምስል
መልከጼዴቅ አብራምን ባረከ

መልከ ጼዴቅ አብርሐምን ሲባርክ፣ በዋልተር ረኔ

አትም