ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
መስከረም 27–ጥቅምት 3 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109-110፥ “ይህም ቤትህ፣ የቅድስናህ ስፍራ [ነው]”


“መስከረም 27–ጥቅምት 3 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109-110፥ ‘ይህም ቤትህ፣ የቅድስናህ ስፍራ [ነው]፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“መስከረም 27–ጥቅምት 3 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109–110፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021(እ.አ.አ)

የከርትላንድ ቤተመቅደስ

የከርትላንድ ቤተመቅደስ፣ በጃን ማክናውተን

መስከረም 27–ጥቅምት 3 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109–110

“ይህም ቤትህ፣ የቅድስናህ ስፍራ [ነው]”

ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥24–28ን በማጣቀስ እንዳሉት፣ “ሕይወታችሁ እና በቤተሰብችሁ ውስጥ እነዚህ የቅዱሳት መጻህፍት ጠቀሜታዎችን በጸሎት ደጋግማችሁ እንድታጠኑ እና እንደታሰላስሉ እጋብዛለሁ” (“በአክብሮት ስም እና አቋም መያዝ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2009 (እ.አ.አ)፣ 99)። በምታጠኑበት ጊዜ ይህንን ግብዣ ልብ በሉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የከርትላንድ ቤተመቅደስ በሮች እስከ መጋቢት 27 ቀን 1836 እሰከ 2 ሰዓት ድረስ ሊከፈቱ አልነበሩም። ነገር ግን በምረቃው አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ ተስፋ የሚያደርጉ ቅዱሳን ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ መሰለፈ ጀመሩ። መተላለፊያዎች እና ጥጋጥጎች በጉጉ ምዕመናን በፍጥነት በተሞሉ ጊዜ፣ ጆሴፍ ስሚዝ መቀመጫ ቦታ ላጡት ቦታ የሚሰጥበትሰጥ ሀሳብ አቀረበ። ያም ሲሞላ፣ ሁለተኛ ክፍለ ጊዜ ታቅዶ ነበር። እናም በቦታው ለመገኘት የተጨነቁ ህያዋን ብቻ አልነበሩም። ከምርቃቱ ግዜ እና በኋላ ላይም በቤተመቅደሱ ውስጥ እና በቤተመቅደሱ ጣራ ላይ ብዙ ምስክሮች መላእክቶችን እንዳዩ መስክረዋል። ከኋለኛው ቀን ቅዱሳን ጋር “የሰማይ ሠራዊቱ” “ለመዘመር እና ለመጮህ” የመጡም ይመስል ነበር (“የእግዚአብሔር መንፈስ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 2)።

በመጋረጃው በሁለቱም በኩል ለምን ታላቁ ደስታ ነበር? ቅዱሳኑ ወደ ኦሃዮ ከተሰበሰቡበት አንደኛው ምክንያት፣ “ከላይ የሚመጣ ኃይል ትቀበላላችሁ” የሚለው የተገባላቸው የተስፋ ቃል ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥32)። ለወደፊቱ ደግሞ ታላላቅ ነገሮች ተስፋ ተሰጥተዋል። ጌታ እንዳወጀው፣ “ይህም በህዝቤ ራሶች ላይ የሚፈሰው የበረከት መጀመሪያም ነው” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥10)። አሁን የምንኖርበት ዘመን፣ እንዲሁም በተፋጠነ የቤተመቅደስ ስራ እና ስነስርዓቶች በሕይወት ላሉናእና ለሞቱት ለሚሊዮኖች በሚገኙበት ዘመን፣ “ምድር የነበረባትን መጋረጃ መቀደድ በጀመረበት” በከርትላንድ ጅምር ነበረው (“የእግዚአብሔር መንፈስ”)።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥232-41፤ “ለአምላካችን የሚሆን ቤት፣” ራዕይ በአገባብ 169–72ን ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክቶች

ለግል ቅዱሳን ጽሁፍ ጥናት ጠቃሚ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109

ጌታ በቅዱስ ቤቱ ውስጥ እኔን ሊባርክልኝ ይፈልጋል።

በአንዳንድ መንገዶች፣ የከርትላንድ ቤተመቅደስ በአሁኑ ጊዜ ከምናውቃቸው ቤተመቅደሶች የተለየ ነበር። ምንም መሠዊያዎች እና የጥምቀት ገንዳ አልነበረም፣ እና ለሙታን መጠመቅ እና መታተም ያሉ ሥርዓቶች ዳግም አልተመለሱም ነበር። ነገር ግን በ ከፍል 109፣ እንዲሁም በከርትላንድ ቤተመቅደስ የምረቃ ጸሎት፣ ውስጥ የተገለጹት በረከቶች ዛሬ በጌታ ቤት ውስጥ የምንቀበላቸው በረከቶች ናቸው። ከእነዚህ በረከቶች ውስጥ የተወሰኑትን ለማግኘት የሚከተሉትን ጥቅሶች ይከልሱ። ስለእነሱ በምታነቡበት ጊዜ፣ እነዚህ ለእናንተ እና ለቤተሰባችሁ ለምን አስፈላጊ እንደሆኑ በጥንቃቄ አስቡ።

ቁጥሮች 5፣ 12–13 (በተጨማሪምትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥6–8ይመልከቱ)፥ በቤተመቅደስ ውስጥ ጌታ እራሱን ለእኛ ለመግለጥ ይችላል እንዲሁም እኛ የእሱ ሀይል ሊሰማን ይችላል።

ቁጥሮች 9፣ 17–19፣ 26፣ 78–79፥ በቤተመቅደስ ውስጥ የጌታን ስም በራሳችን ላይ እንወስዳለን።

ቁጥሮች22–23፥ የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን ስንገባ እና ስናከብር፣ ጌታ ስራውን እንድንፈጽም ኃይል ይሰጠናል።

ቁጥሮች 24–33፥ በቅድስና ወደ ቤተመቅደስ ስንሄድ፣ የጌታን ጥበቃ እንቀበላለን።

ሌሎች በረከቶች፥

እነዚህን በረከቶች ለመቀበል መንፈስ ምን እንድታደርጉ አነሳስቷችኋል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109

የከርትላንድ ቤተመቅደስ የምረቃ ጸሎት ስለ ጸሎት ሊያስተምረኝ ይችላል።

ክፍል 109 በራዕይ ለጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠው የምረቃ ጸሎት ነው (የክፍሉን መግቢያ ይመልከቱ)። ከዚህ ክፍል ስለ ፀሎት ምን ተምራችኋል? ስታነቡ ስለራሳችሁ ጸሎቶች አስቡ። ከሰማይ አባት ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለማሻሻል ሊረዱ የሚችሉ ምን ዓይነት ግንዛቤዎች ተቀብላችኋል? ለምሳሌ፣ ነቢዩ በዚህ ጸሎት ስለ ምን ጸልዮ ነበር?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥1–10

ጌታ እራሱን በቤተመቅደስ ውስጥ ለእኔ ለመግለጥ ይችላል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥1–10 ካነበባችሁ በኋላ ስለአዳኙ ምን ይሰማችኋል? በቤተመቅደስ ውስጥ እንዴት እራሱን ለእናንተ ገልጧል? ጥረቶቻችሁን እና መስዋእታችሁን እንደሚቀበል እንድታውቁ በየትኞቹ መንገዶች ይረዳችኋል?

የከርትላንድ ቤተመቅደስ የውስጥ ክፍል

እያንዳንዱ የከርትላንድ ቤተመቅደስ መጨረሻ ለክህነት መሪዎች የሚሆን የመስበኪያ ቦታ አለው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥11–16

የእግዚአብሔርን ሥራ ለማከናወን የሚያስፈልጉ የክህነት ቁልፎች ዛሬ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ አሉ።

በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ሙሴ፣ ኤልያ እና ኤሊያስ ለጆሴፍ ስሚዝ እና ለኦሊቨር ካውድሪ የሰጧቸውን የክህነት ቁልፎች ለመረዳት፣ የሽማግሌ ክውንተን ኤል. ኩክን መልዕክት “እግዚአብሔርን ለመገናኘት ይዘጋጁ” ለማንበብ ትችላላችሁ (ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 114–17)። ሽማግሌ ኩክ እነዚህ ቁልፎች ዛሬ ከቤተክርስቲያኗ ስራ ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ ገልጸዋል። በተጨማሪም ስለ እነዚህ ጥንታዊ ነቢያት ለመማር፣ “ሙሴ፣” “ኤልያ፣” እና “ኤሊያስ” በቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ ውስጥ (scriptures.ChurchofJesusChrist.org) ለማጥናት አስቡበት። ከእነዚህ ቁልፎች ጋር በተዛመደ ሥራ ውስጥ ለማገዝ ምን ማድረግ እንደምትችሉ አሰላስሉ።

በተጨማሪም “የክህነት ቁልፎች፣” ለእምነት እውነትነት 126–27፤ ሄንሪ ቢ. ኢይሪንግ፣ “ከእኛ ቀድሞ ይወጣል፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2020፣ 66-69 ይመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109ክፍል 109 ውስጥ በቤተመቅደስ ውስጥ ብዙ ጊዜ እንዲያሳልፉ የሚያነሳሳዎትን የተወሰኑ ጥቅሶችን ፈልጉ (ለምሳሌ፣ “ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች” በሚለው ስር የተዘረዘሩትን ጥቅሶች ይመልከቱ)። ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን የሰጡትን ሀሳብ እንዴት ማድረግ እንደምትችሉ ተነጋገሩበት፥ “በእርሱ ቅዱስ ቤት ለመገኘት፣ ከጌታ ጋር ዘወትር ቀጠሮ የምትይዙበትን መንገድ አግኙ፣ ከዚያም ይህን ቀጠሮ በትክክል እና በደስታ ጠብቁ። [“የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ምሳሌ መሆን፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 114]። እናንተ ወይም ቤተሰባችሁ ወደ ቤተመቅደስ ገና ያልገባችሁ ከሆነ፣ temples.ChurchofJesusChrist.org በመጎብኘት ለመሄድ እራሳችሁን አዘጋጁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥78–80የእግዚአብሔር መንፈስ” የሆነ ርዕስ ያለው መዝሙር (መዝሙር፣ ቁጥር 2) የተፃፈው ለከርትላንድ ቤተመቅደስ ምረቃ ነበር፣ እናም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በእያንዳንዱ የቤተመቅደስ ምረቃ ላይ እየተዘመረ ይገኛል። አንድ ላይ ሆናችሁ ይህንን መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ እናም ለኋለኛው ቀን ቤተመቅደሶች ያላችሁን ምስጋና የሚጨምሩ ሀረጎችን አግኙ። ይህ መዝሙር ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥78–80 መልእክት ጋር እንዴት ይዛመዳል?

temples.ChurchofJesusChrist.org ውስጥ በአቅራቢያችሁ ላለው ቤተመቅደስ የምርቃ ጸሎት ማግኘት ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110የቤተሰብ አባላታችሁ ክፍል 110ን ሲያነቡ እና በዚህ ገጽ መጨረሻ ላይ ያለውን ሥዕል ሲመለከቱ፣ ከጆሴፍ ስሚዝ እና ከኦሊቨር ካውዴይ ጋር አብረው በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ቢገኙ ኖሮ ምን ሊሰማቸው እንደሚችል እንዲገምቱ ጋብዟቸው። ቤተሰባችሁ ስለ አዳኝ የሚሰማቸውን እንዲያጋሩ እድል ስጡ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥15የልጆቻችሁን “ልብ ወደ” ቅድመ አያቶቻቸው “[ለመመለስ]” ምን ሊረዳ ይችላል? በFamilySearch.org/discovery ውስጥ አንዳንድ አስደሳች ሀሳቦችን ማግኘት ይችላሉ። የቤተመቅደስ ስርዓቶች የሚያስፈልጋቸውን ቅድመ አያቶች ለመለየት እና በቤተመቅደስ ውስጥ እነዚህን ስርዓቶች ለማከናወን ለማቀድ አብራችሁ መስራት ትችላላችሁ። እንዲሁም በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ በኤልያስ ዳግም የተመለሰው ስራ ለቅድመ አያቶቻችሁያላችሁ ፍቅር እንዲጨምር ስለሚያደርግበት መንገድ መነጋገር ትችላላችሁ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “የእግዚአብሔር መንፈስ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 2።

በዳግም የመመለስ ድምጾች ምልክት

በዳግም የመመለስ ድምጾች

መንፈሳዊ መገለጦች እና የከርትላንድ ቤተመቅደስ

ከርትላንድ የቤተመቅደስ ምረቃ

እንደሚነድ እሳት፣ በግሌን ኤስ. ሆፕኪንሰን

ከዚህ በታች የሚገኙት በምረቃው እና በሌሎችም ስብሰባዎች በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ የነበሩ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቃላት ናቸው። ብዙ ሰዎች ልምዶቻቸውን የጥንቶቹ ቅዱሳን በበዓለ ሃምሳ ቀን “ከላይ ኃይል [እስኪለብሱ]” ወቅት ከነበሩበት ሁኔታ ጋር አነፃፅረውታል (ሉቃስ 24፥49፤ ደግሞም የሐዋሪያት ሰራ 2፥1–4ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥36–37 ይመልከቱ)።

እላይዛ አር. ስኖው

“የምረቃው ሥነ-ሥርዓቶች ልምምድን ሊያካትቱ ይችላል፣ ነገር ግን ያንን የማይረሳ ቀን የሰማይ መገለጦችን ምንም የሰው ቋንቋ ሊገልጸው አይችልም። መላእክት ለአንዳንዱ ተገለጡ፣ በተገኙት ሁሉም ላይ የመለኮታዊ መገኘት ተረጋገጠ፣ እናም እያንዲንዱም ልብ መግለጽ በማይቻል እና በክብር ደስታ ተሞልቶ ነበር።”1

ሲልቨያ ካልትር ዌብ

“ከቀደምት ማስታወሻዎቼ ውስጥ አንዱ የቤተመቅደሱ ምረቃ ነው። አባቴ በጭኑ ላይ አስቀመጠን እና ለምን እንደምንሄድ እና የእግዚአብሔር ቤት ምረቃ ምን ማለት እንደሆነ ነገረን። ምንም እንኳን በወቅቱ በጣም ልጅ ብሆንም፣ ዝግጅቱን በግልፅ አስታውሳለሁ። ያለፉትን አመታት ወደኋላ መለስ ብዬ መመልከት እና በዚህ የማይረሳ ቀን ላይ ነቢዩ ጆሴፍ እጆቹን ወደ ሰማይ ከፍ አድርጎ፣ ፊቱ እንደ አመድ ነጭ ሆኖ፣ እንባውን በጉንጮቹ እየፈሰሱ ሲናገር እመለከታለሁ። ሁሉም በእንባ እያሉ ይመስላል። ቤቱ በጣም ተሞልቶ ልጆች በአብዛኛው በዕድሜ የገፉ ሰዎች እግር ላይ ተቀምጠው ነበር፤ እህቴ በአባቴ እናም እኔ በእናቴ እግር ላይ ተቀመጥን። የለበስናቸውን ቀሚሶችንም እንኳ አስታውሳለሁ። በዚያን ጊዜ እምሮዬ በጣም ወጣት በመሆኔ የሁሉንም ነገር አስፈላጊነት አልጨበጥኩም ነበር፣ ነገር ግን ከጊዜ በኋላ የበለጠ እተተጫነኝ መጣ፣ እናም እዚያ የመገኘት እድል በማግኘቴ በጣም አመስጋኝ ነኝ።”2

ኦሊቨር ካውድሪ

“ምሽት ላይ በጌታ ቤት ውስጥ ከሚገኙት የቤተክርስቲያን ኃላፊዎች ጋር ተገናኘሁ። መንፈሱ አብዝቶ ፈሰሰ—የእግዚአብሔር ክብር እንደ ታላቅ ደመና ሲወርድ እና በቤቱ ላይ ሲያርፍ፣ እናም እንደ ኃይለኛ ነፋስ ቤቱን ሲሞላው አየሁ። እንዲሁም እሳት በእነርሱ ላይ የሚያርፍ የሚመስል እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳኖችንም አየሁ፣ … በሌላ ቋንቋ ሲናገሩ እና ትንቢት እየተናገሩ ነብር።”3

ቤንጃሚን ብራውን

“ብዙ ራእዮች [ታዩ]። አንደኛው ፀሃይ በደመና ላይ ሲያበራ እንደ ወርቅ የሚያንጸባርቅ አይነት ብሩህ የሆኖ ትራስ ወይም ደመና በቤቱ ላይ ሲቀመጥ አየ። ሁለት ሌሎች ሰዎችም በእጆቻቸው ውስጥ ብሩህ ቁልፎች እና ብሩህ ሰንሰለት የያዙ ሶስት ሰዎች በክፍሉ ላይ ሲያንዣብቡ ተመለከቱ።”4

ኦርሰን ፕራት

“እግዚአብሔር እዚያ ነበር፣ መላእክቱ እዚያ ነበሩ፣ መንፈስ ቅዱስ በሰዎች መካከል ነበር … እናም ከጭንቅላታቸው አክሊል እስከ እግሮቻቸው ድረስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እና ምሪት ተሞሉ።”5

ናንሲ ናዮሚ አሌክሳንድር ትሬሲ

“ቤተመቅደሱ ተሠርቶ ሲጠናቀቅ እና ሲመረቅ … በህይወቴ በጣም ደስተኛ ከሆኑበት ሁለት ቀናት ውስጥ ነበሩ። ለበዓሉ የተዘጋጀው ተስማሚ መዝሙር ‘የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ እሳት ይቃጠላል’ የሚል ነበር። የሰማይ ተፅእኖ በዚያ ቤት ላይ ማረፉ በእውነቱ እውን ነበር። በምድር ላይ ያለ ሰማይ እንደሆነ ተሰማኝ።”6

ማስታወሻዎች

  1. ኤድዋርድ ደብሊው. ቱሊጅ የሞርሞን ሴቶች 1877 (እ.አ.አ)፣ 95።

  2. በካርል ሪክ አንደርሰን፣ ጆሴፍ ስሚዝ በከርትላንድ፤ የአይን እማኞች ታሪክ [1996 (እ.አ.አ)]፣ 182–83።

  3. የኦሊቨር ካውደሪ ማስታወሻ ደብተር፣ መጋቢት 27፣ 1836 (እ.አ.አ)፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጽሃፍት፣ ሶልት ሌክ ስቲ።

  4. የቤንጃሚን ብራውን ለባለቤቱ ሳራ የጻፈው ደብዳቤ፣ በሚያዚያ 1866 (እ.አ.አ) አካባቢ፣ የቤንጃሚን ብራውን ቤተሰብ ስብስብ፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጽሃፍት፣ ሶልት ሌክ ስቲ፤ አጻጻፉ ዘመናዊ ተደርጓል።

  5. ኦርስን ፕራት፣ “ንግግር፣” የዴዘሬት ጋዜጣ፣ ጥር 12፣ 1876 (እ.አ.አ)፣ 788።

  6. በሪቻርድ ኢ. ቱርሊ ዳግማዊ እና ብሪትኒ ኤ. ቻፕማን፣ በኋለኛው ቀን ያሉ አማኝ ሴቶች [2011 (እ.አ.አ)]፣ 1፥442።

ሙሴ፣ ኤልያ እና ኤሊያስ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ታዩ

ሙሴ፣ ኤልያ እና ኤሊያስ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ታዩ፣ በ ጌሪ ኢ. ስሚዝ