ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 4–10። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111–114፥ “ሁሉንም ነገሮች ለእናንተ መልካምነት አዝዛለሁ”


“ጥቅምት 4–10። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111–114፥ ‘ሁሉንም ነገሮች ለእናንተ መልካምነት አዝዛለሁ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ጥቅምት 4–10። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111–114፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ ሲሰብክ

ጥቅምት 4–10

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111–114

“ሁሉንም ነገሮች ለእናንተ መልካምነት አዝዛለሁ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111–114ን በምታነቡበት ጊዜ፣ የመንፈስን ምሪት በጸሎት ጠይቁ እና ግንዛቤአችሁን መዝግቡ። ከዚያ በእነዚያ ግንዛቤዎች ላይ እርምጃ መውሰድ የምትችሉባቸውን መንገዶች አስቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በእምነታችሁ ልበሙሉ እና ጥብቅ የመሆን ስሜት እንዲሰማችሁ የሚያደርግ መንፈሳዊ ልምምድ አጋጥሟችህ ያውቃል—ግን ከዚያ የህይወት ችግሮች እምነታችሁን ፈተኑት፣ እና ከዚህ በፊት የተሰማችሁን ሰላም ለመመለስ ስትታገሉ ራሳችሁን አግኝታችሁት? በከርትላንድ ውስጥ ቅዱሳን ተመሳሳይ ነገር አጋጥሟቸው ነበር። ከከርትላንድ ቤተመቅደስ ምረቃ ጋር የተገናኘው የመንፈስ ፍስት ከሆነ ከአንድ አመት በታች በሆነ ጊዜ ውስጥ፣ ችግሮች ተነሱ። የገንዘብ ቀውስ፣ በአስራ ሁለቱ ቡድን ውስጥ አለመግባባት፣ እና ሌሎች ፈተናዎች አንዳንዶች በእምነታቸው እንዲንገዳገዱ አደረጓቸው።

ፈተናዎችን ለማስወገድ አንችልም፣ ስለሆነም በእምነታችን እና በምስክርነታችንን ላይ ስጋት እንዳይፈጥሩ እንዴት መከላከል እንችላለን? ምናልባት የመልሱ ክፍል ጌታ በከርትላንድ ያለው ችግር እየተባባሰ በነበረበት ጊዜ በሰጠው ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112 ምክር ውስጥ ይገኛሉ። ጌታም “በፊቴ ልባችሁን አፅዱ” (ቁጥር 28)፣ “አታምጹ” (ቁጥር 15)፣ “ለስራውም ወገብህን አጥብቅ” (ቁጥር 7)፣ እና “ትሁት ሁን” (ቁጥር 10) አለ። ይህንን ምክር ስንከተል፣ ጌታ በችግር ውስጥ እና ወደ ፈውስ እና ሰላም “[እጃችንን] ይዞ ይመራናል” (ይመልከቱ፥ ቁጥሮች 10፣ 13)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111

ጌታ “ሁሉንም ነገሮች [ለእኔ] መልካምነት [ለማዘዝ]” ይችላል።

በ 1836 (እ.አ.አ)፣ የጌታን ሥራ ለማከናወን ቤተክርስቲያኗ ከባድ ዕዳዎችን ሰብስባ ነበር። ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎችም ስለ እነዚህ ዕዳዎች ሲጨነቁ እና እነሱን ለመክፈል መንገዶችን ሲያስቡ፣ ወደ ሴለም፣ ማሳቹሴትስ ተጓዙ፣ ምናልባትም በዚያ ቤት ውስጥ የተወሰነ ገንዘብ ተትቶ ሊሆን ይችላል በሚል ወሬ ተነሳ። (የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111ን ክፍል መግቢያ ይመልከቱ)። ወደ ሴለም ከደረሱ በኋላ፣ ጌታ “በዚህ ከተማ ውስጥ ከአንድ በላይ ሀብቶች አሉአችሁና” (ቁጥር 10)፣ እንዲሁም “ለፅዮን ጥቅም [በጊዜው ሰብስቦ የሚያወጣቸውን” ሰዎችን ያካተቱ ሀብቶች (ቁጥር 2፤ ደግሞም ዘጸአት 19፥5ን በተጨማሪ ይመልከቱ)። በሳሌም ምንም ገንዘብ ባይገኝም፣ ከዚህ በኋላ ከሚስዮናዊነት ጥረት የመጡ ተቀያሪዎች ለጌታን የተስፋ ቃል ፍፃሜዎች ነበሩ።

ክፍል 111ን ስታነቡ፣ ስለምትጨነቁበት ነገሮች አስቡ። ጌታ ለጆሴፍ የተናገረው ቃል ለእናንተ እንዴት እንደሚሠራ አስቡ። ያልተጠበቁ “ሀብቶችን” ጌታ እንዴት እንድታገኙ ረድቷችኋል? (ቁጥር 10)። እሱ “ሁሉንም ነገሮች ለእናንተ መልካምነት” ስላደረገው ነገር አስቡ (ቁጥር 11)። “እናንት ልትቀበሉ በምትችሉት ፍጥነትም፣” የሚለው ሐረግ ስለሰማይ አባት ምን ያስተምራችኋል?

በተጨማሪም ማቲዎስ 6፥19–21፣ 33፤ “ከአንድ በላይ የሆኑ ሀብቶች፣” ራዕያት በአገባብ 229–34 ይሞልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥3–15

ጌታ በትህትና ፈቃዱን የሚፈልጉትን ይመራቸዋል።

በ1837 (እ.አ.አ) የበጋ ወቅት የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ሸንጎ አንድነት እየተዳከመ ነበር። ሀላፊነቶችን በተመለከተ አለመግባባቶች ነበሩ፤ እና አንዳንድ አባላት ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝን በመቃወም ይናገሩ ነበር። በዚያን ጊዜ የአስራ ሁለቱ ሸንጎ ፕሬዘደንት የነበሩት ቶማስ ቢ. ማርሽ ጉዳዩ ያሳስብው ነበር፣ እናም የነቢዩን ምክር ለማግኘት ከሚዙሪ ወደ ኦሃዮ መጣ። ወንድም ማርሽ ይህንን በክፍል 112 ውስጥ በነበረው ራዕይ በኩል ተቀበለ። የጌታ ምክር እሱን እና ሸንጎውን እንዴት ረድቶት ይሆን ? አለመግባባትን እና መከፋትን ለማሸነፍ በምትፈልጉበት ጊዜ ይህ ለእናንተ ምን ትምህርት አለው?

በተለይም፣ በቁጥር 10 ላይ ለማሰላሰል ትችላላችሁ። ጌታ “እጅህን ይዞ ይመራሀል” ማለት ምን ማለት ነው? ለዚህ ዓይነቱ መመሪያ ትሕትና አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

በተጨማሪም ዮሊሰስ ሶሬስ፣ “የዋህ እና ትሑት ሁን፣“ ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 9–11፤ “የቶማስ ማርሽ እምነት እና ውድቀት፣” ራዕያት በአገባብ፣ 54–60 ይመልከቱ።

ምስል
ሁለት ሰዎች እየጸለዩ

ትሑት ከሆንን ጌታ ይመራናል እንዲሁም ጸሎታችንን ይመልሳል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 113

ጆሴፍ ስሚዝ “የክርስቶስ እጆች አገልጋይ” ነበር።

ኢሳያስ ከእሴይ ዘር መካከል አንዱን “በትር” እና “ሥር” ሲል ጠርቶታል (ኢሳያስ 11፥1፣ 10)። በክፍል 113ም ውስጥ፣ ይህ የዘር ሐረግ፣ የክርስቶስ አገልጋይ፣ የጌታን ህዝቦች በመጨረሻው ቀን ለመሰብሰብ መጠቀሚያ እንደሚሆን ጌታ ገልጿል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 113:4፣ 6ን ይመልከቱ)—ይህም ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝን በትክክል የሚገልፅ ትንቢት ነበር። ይህ እና ሌሎች በክፍል 113 ውስጥ የሚገኙ እውነታዎች በከርትላንድ ውስጥ ሁከት ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ለቅዱሳኑ እንዴት ማበረታቻዎች ሊሆኑ ይችላሉ? በዚህ ራዕይ ውስጥ ዛሬ በጌታ ሥራ ውስጥ እንድትሳተፉ የሚያነቃቃችሁ ምን ታገኛላችሁ?

እንዲሁም የቅዱሳት መጻሕፍት መመሪያን፣ “እሴይ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org2 ኔፊ 21፥10–12ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥40 ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክቶች

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111፥2፣ 9–11እነዚህ ቁጥሮች ቤተሰባችሁ ምን ነገሮችን እንደ ዘለአለማዊ “ሀብቶች” እንደሚመለከቷቸው ለመወያየት ሊያበረታቱ ይችላሉ። ጌታ እንደ ሀብት ወይም ዋጋዎች እንዳላቸው የሚመለከታችውን የሚወክሉ ነገሮችን በቤቱ ዙሪያ በመደበቅ ሀብትን የመፈለግ ጨዋታ ልትጫወቱ ትችላላችሁ። ቤተሰባችሁ እያንዳንዱን ዕቃ ሲያገኙ፣ ከፍ አድርገው እንደሚመለከቱት ለማሳየት ምን ማድረግ እንደሚችሉ ተወያዩበት።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥10ሽማግሌ ዮሊሰስ ሶሬስ ትሁት የሆኑ ሰዎችን በዚህ መንገድ ገልፀዋል፥ “ትሁቶች ለመማር የሚችሉ፣ በእግዚአብሔር ላይ ምን ያህል ጥገኛ እንደሆኑ የሚያውቁ እና ለፈቃዱ መገዛት የሚሹ ናቸው። ትሁቶች የዋሆች እና ሌሎች ተመሳሳይ እንዲሆኑ ተጽእኖ የማድረግ ችሎታ ያላቸው ናቸው።” (“የዋህ እና ትሑት ሁን፣” ኤንዛየን ወይም ሊያሆና፣ ሀዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 10)። ቤተሰባችሁ ትህትና ምን ማለት እንደሆነ እንዲገነዘቡ ለማገዝ መንገዶችን አስቡበት። አንድ የቤተሰብ አባል ሌሎቹን “በእጁ” ወስዶ በቤትታችሁ ዙሪያ ሲመራ፣ ለምሳሌ “ትሑት ሁን” (መዝሙር፣ ቁጥር 130) አይነት ስለ ትህትና መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ። ወይም ጌታ የቤተሰብ አባላቶቻችሁን “በእጁ” የመራበትን እና “[ለጸሎታቸው] መልስ” የሰጠበትን ልምዶችን አካፍሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥11–14፣ 26የአንድን ሰው ስም በማወቅ እና እነሱን በማወቅ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? ከ ቁጥሮች 11–14 ውስጥ ጌታን ማወቅ ምን ማለት እንደሆነ ምን እንማራለን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥15በነቢዩ ላይ “ማመፅ” ምን ማለት ነው? በዚህ ቁጥር ውስጥ ነቢዩን ለመደገፍ እንድንፈልግ የሚረዳን ምን እናገኛለን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 113፥7–8ቁጥር 8 ውስጥ “ፅዮንን ዳግም ለማምጣትና” እና እስራኤልን ለማዳን የሚረዳ ምን እንማራለን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፥ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ትሑት ሁን፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 130 ።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ምስክርነታችሁን ኑሩ። ሽማግሌ ኔል ኤ. ማክስዌል እንዳስተማሩት፣ “‘እናንተ የሆናችሁትን ታስተምራላችሁ፣’ ‘ባህሪዎቻችሁ ከአንድ የተወሰነ ትምህርት ውስጥ ከነበረ የተወሰነ እውነት የበለጠ ይታወሳሉ’” (በአዳኝ መንገድ ማስተማር፣ 13)።

ምስል
ቶማስ ቢ. ማርሽ እና ጆሴፍ ስሚዝ

ቶማስ ቢ ማርስ በጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠውን ራዕይ ይመዘግባል። ትሑት ሁን፣ በጁሊ ሮጀርስ።

አትም