“ጥቅምት 18–24 ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121–123፥ ‘እግዚአብሔር ሆይ፣ የት ነህ?’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]
“ጥቅምት 18–24 ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121–123፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 18–24
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121–123
“እግዚአብሔር ሆይ፣ የት ነህ?”
ግባችሁ እውነትን ለመግለጥ ከሆነ ቅዱሳት መጻህፍትን በማጥናት ተሞክሯችሁ የበለጠ የበለፀገ ይሆናል። በጸሎት ጀምሩ፣ መንፈሱን አድምጡ፣ እና ግንዛቤአችሁን መዝግቡ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
በሊብሪቲ፣ ምዙሪ ካውንቲ ውስጥ ያለው እስር ቤት የታችኛው ክፍል ጉድጓዱ በመባል ይታወቅ ነበር። ግድግዳዎቹ ወፍራም ነበሩ፣ የድንጋይ ንጣፉ ቀዝቅዛ እና ቆሻሻ ነበር፣ ምግቡ—ያለውም ቢሆን—የተበላሸ ነበር፣ እና ብቸኛው ብርሃንም በጣሪያው አጠገብ ባለ ሁለት ጠባብ የብረት የተዘጉ መስኮቶች የሚገባው ነበር። ይህም ጉድጋድ ጆሴፍ ስሚዝ እና ጥቂት ወንድሞቹ በምዙሪ ግዛት ላይ በአገር ክህደት ለነበረባቸው ክስ ለፍርድ ለመቅረብ ይጠብቁ የነበሩበትን አብዛኛውን የእስር ጊዜያቸውን—እንዲህም በ1838–39 (እ.አ.አ) መካከል በነበሩት ለአራት በጣም ቀዝቃዛ የክረምት ወራት—ያሳለፉበት ቦታ ነው። በዚህን ጊዜ ጆሴፍ ስለ ቅዱሳን ስቃይ ዘወትር ዜና ይሰማ ነበር። የፋር ዌስት ሰላምና ብሩህ ተስፋ የቆየው ለጥቂት ወራት ብቻ ነበር፣ እና እንደገና ለመጀመር ሌላ ቦታ ለመፈለግ ወደ ምድረ በዳ ተሰድደው፣ አሁንም ቅዱሳን እንደገና ቤት አልባ ነበሩ—በዚህም ጊዜ ነቢያችው በእስር ቤት ነበር።
ጆሴፍ ስሚዝ “እግዚአብሔር ሆይ፣ የት ነህ?” ብሎ ማልቀሱ ምንም አያስገርምም። የተቀበለው መልሶች፣ በእዚያች አሰቃቂ እስር ቤት ውስጥ “በወረደ” የመጣው “የሰማይ እውቀት”፣ ምንም እንኳን እንደዚያ ባይመስልም፣ እግዚአብሔር መቼም ሩቅ እንዳልሆነ ያሳያል። ምንም ሀይል “ሰማያትን ሊያቆም” እንደማይችል ነቢዩ ተማረ። እግዚአብሔር [ ከታማኝ ቅዱሳኑ] ጋር ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ነውና።” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥1፣ 33፤ 122፥9።)
ቅዱሳን፣ 1፥323–96፤ “በሊበርቲ እስር ቤት ግድግዳዎች ውስጥ፣” ራዕያት በአገባብ፣ 256–63 ይመልከቱ።
ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥1–10፣ 23–33፤ 122
መከራ “ለእኔ ጥቅም” ሊሆን ይችላል።
እኛ ወይም የምንወዳቸው በመከራ ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ስላለንበት ሁኔታ ያውቃልን ብሎ መጠየቅ አይደንቅም። እናንተ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 121፥1–6ን ስታነቡ፣ ከጆሴፍ ስሚዝ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ጥያቄዎች ወይም ስሜቶች ስለነበሯችሁ ጊዜ አስቡ። በጌታ ምላሽ ውስጥ እነዚያ ጥያቄዎች ወይም ስሜቶች ሲኖሯችሁ ሊረዳችሁ የሚችሉት ምን አግኝታችኋል? ለምሳሌ፣ በቁጥሮች 7–10፣ 26–33፣ “በመልካም [መከራን ለሚጸኑት]” እርሱ ቃል የገባቸውን በረከቶች ልብ በሉ። እናንተ ክፍል 122ን በምታነቡበት ጊዜ፣ ጌታ መከራችሁን እንዴት እንድትመለከቱ እንደሚፈልግ አስቡ።
በተጨማሪም ይመልከቱ፥ ሄንሪ ቢ. አይሪንግ “ድንኳኑ የት አለ?” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2012 (እ.አ.አ)፣ 72–75።
“የሰማይ ኃይላትን” ማግኘት እንችላለን።
በሊብረቲ እስር ቤት ውስጥ ምንም ኃይል የሌለው በሚመስል ሁኔታ፣ ጆሴፍ ስለ ስልጣን ራዕይ ተሰጠው—በቅዱሳን ላይ ሲሠራ የነበረው የፖለቲካ ወይም የወታደራዊ ኃይል ሳይሆን “የሰማይ ኃይላት” ነው። በ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥34–46ን ስታነቡ፣ ስለ እግዚአብሔር ኃይል ምን ትማራላችሁ? ከዓለማዊ ኃይል እንዴት ይለያል? ለምሳሌ፣ በቁጥሮች 41–43 ውስጥ ጌታ “ኃይል ወይም ተፅዕኖን” ለመግለጽ የሚጠቀምባቸውን ቃላት ተመልከቱ። እግዚአብሔር የእርሱን ‘ኃይል ወይም ተፅዕኖ’ እንዴት እንደሚጠብቅ እነዚህ ምን ያስተምራሉ? ምናልባትም እነዚህ ጥቅሶች ህይወታችሁን እና ከሌሎች ጋር በሚኖራችሁ ግንኙነቶች ውስጥ በጎ ተጽዕኖ ለማሳደር ምን ለማድረግ እንደምትችሉ እንድታሰላስሉ ያነሳሱ ይችላሉ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁሉም ነገሮች በታች ወርዷል።
ጆሴፍ ስሚዝ ጓደኞቹ እና ቤተሰቦቻቸው ከቤታቸው እየተባረሩ በነበረበት ጊዜ ከአራት ወራት በላይ በግፍ እንዲታሰር ተደርጓል። ህይወቱን የወሰነበት ሥራ እየፈረሰ እያለ ይመስላል። በ ክፍል 122ለጆሴፍ በሰጠው ቃል ውስጥ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን ትማራላችሁ? ስለ ጆሴፍ ምን ትማራላችሁ? ስለ ራሳቸሁ ምን ትማራላችሁ?
ደግሞም አልማ 7፥11–13፤ 36፥3፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥6 ይመልከቱ።
“በሀይላችን ያሉትን ነገሮች ሁሉ በደስታ እናድርግ።”
በመጋቢት 1839 (እ.አ.አ)፣ ቅዱሳን ያጋጠማቸውን አስከፊ ሁኔታ ለመቀየር ብዙ ማድረግ የሚችሉበት እንደሌለ ይመስል ነበር። ግን ከሊብረቲ እስር ቤት በፃፋቸው ደብዳቤዎች ውስጥ፣ ጆሴፍ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ነገራቸው፥ “ተጨባጭ ነገሮች እውቀት ሁሉ [ሰብስቡ]” እና “በእርግጠኝነት የእግዚአብሔር የሚያደርገውን ለማዳን ለማየት [ቁሙ]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 123፥1፣ 17)። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ውስጥ ያሉትን የሰዎችን አታላይነት እና “[አጭበርባሪነት]” ስታስቡ፣ ለማድረግ ስለምትችሏቸው “[በኃይላችሁ] ያሉትን” አስቡ (ቁጥሮች 12፣ 17)። እነዚህን ነገሮች “በደስታ” ማድረጉ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ቁጥር 17)። “እውነትን እንዳያገኝ የተደረገ” ማንን ታውቃላችሁ (ቁጥር 12)፣ ይህ ሰው እንዲያገኘው እንዴት ለመርዳት ትችላላችሁ?
በዚህ ደብዳቤ ውስጥ ጆሴፍ የጠየቃቸው ብዙ ጥያቄዎች ለመንግሥት የተረከቡ እናም በናቩ ጋዜጣ ውስጥ ባለ 11–ክፍል ተከታታይ ጋዜጣ፣ ጊዜያት እና ወቅቶች ውስጥ የታተሙ ነበሩ (ይመልከቱ፥ “በምዙሪ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የስደት ታሪክ፣ ታህሳስ 1839–ጥቅምት 1840፣” [josephsmithpapers.org])።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥1–10።በሊበረቲ እስር ቤት የሚገኘው “ጉደጓድ” ስፋቱ 4.2 በ4.4 ሜትር ብቻ ነበር። ለአራት ቀዝቃዛ ወራት ያህል መጠኑ አነስተኛ በሆነ ቦታ ውስጥ መኖር ምን እንደሚመስል ለመገመት እንዲችሉ ቤተሰባችሁን መርዳት ትችላላችሁ? ስለ ሊብረቲ እስር ቤት ሁኔታዎችን በተመለከተ ሌሎች ዝርዝሮችን በ“ምዕራፍ 46፥ ጆሴፍ ስሚዝ በሊበርቲ እስር ቤት ውስጥ” (የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 172–74) ውስጥ ለማግኘት ትችላላችሁ። በዚህ ዝርዝር መጨረሻ ላይ “የዳግም መመለስ ድምጾች፥ የሊብረቲ እስር ቤት” ማንበብ ትችላላችሁ ወይም ጆሴፍ በሊብረቲ እስር ቤት ውስጥ የነበረበትን በቪዲዮ የሚያሳይ ቪዲዮ ይመልከቱ ጆሴፍ ስሚዝ፥ የዳግም መመለስ ነቢይ (ChurchofJesusChrist.org፣ ከ43:00 በመጀመር)። ይህ መረጃ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥1–10 ውስጥ ላሉ መርሆዎች እንዴት ስሜታችንን ይነካል?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥34–36፣ 41–45።ምናልባት ቤተሰባችሁ “የሰማይ ሀይላትን” ለማስረዳት ምሳሌን መጠቀም ሊረዳ ይችላል። ለምሳሌ፣ የእግዚአብሔርን ኃይል ከኤሌክትሪክ ሀይል ጋር ማነፃፀር ትችላላችሁ፤ የኤሌክትሪክ መሳሪያ ኃይል እንዳይቀበል ምን ሊከለክለው ይችላል? ይህ ምሳሌ፣ ከቁጥሮች 34–36፣ 41–45 ጋር፣ መንፈሳዊ ሀይላችንን እንዴት ከፍ ማድረግ እንደምንችል ያስተምሩናል? ምናልባት የቤተሰብ አባላት እነዚህን ባህሪዎች ምሳሌ ከሚሆኑባቸው የአዳኝ ህይወት ታሪኮችን ሊያጋሩ ይችላሉ።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 122፥7–9።ምናልባት የቤተሰብ አባላት ከእነዚህ ጥቅሶች የሚያነቃቁ ሐረጎችን የሚያመለክቱ ትትንሽ ምልክቶችን በመስራት ይደሰቱ ይሆናል። እነዚህን ምልክቶች በቤታችሁ ውስጥ ለማሳየት ይቻላል። “የሰው ልጅ ከሁሉም በታች [መውረዱን]” ማወቁ አስፈላጊ የሆነው ለምን ነው?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 123፥12።ሰዎች እውነትን “የት እንደሚያገኙ” እንዲገነዘቡ እንዴት ልንረዳቸው እንችላለን?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።
የተጠቆመ መዝሙር፥ “ለሰላም የት መሄድ እችላለሁ?” መዝሙር፣ ቁጥር 129።
የዳግም መመለስ ድምጾች
ሊብረቲ እስር ቤት
በሊብረቲ ሚዙሪ ውስጥ ታስሮ በነበረበት ጊዜ ጆሴፍ ስሚዝ በአገረ ገዢው ትእዛዝ ከክልሉ እየተባረሩ ስላሉት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሁኔታ የሚገልጽ ደብዳቤ ደረሰው። ከባለቤቱ ከኤማ የሚነካ ደብዳቤም መጣ። የእርሷ ቃላቶች፣ እና በምላሹ የጆሴፍ ደብዳቤዎች፣ በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ስቃያቸውን እና እምነታቸውን ይገልፃሉ።
ከኤማ ስሚዝ ወደ ጆሴፍ ስሚዝ የተላከ ደብዳቤ፣ መጋቢት 7፣ 1839 (እ.አ.አ)
“ውድ ባለቤቴ
“በጓደኛ ለመላክ አጋጣሚ ሳገኝ፣ ለመጻፍ ሙከራ አደርጋለሁ፣ ግን ሁሉንም ስሜቴን ለመፃፍ አልሞክርም፣ ምክንያቱም ባለህበት ሁኔታ፣ ግድግዳዎች፣ መወርወሪያዎች እና መቀርቀሪያዎች፣ ወንዞቹ፣ የሚሽከረከሩ ጅረቶች፣ ከፍ ያሉ ኮረብቶች፣ ተንሸራታቾች ሸለቆዎች እና የሚለያዩን ውዳሴዎች፣ እና በመጀመሪያ አንተን በእስር ቤት ውስጥ የጣለህን እና በዚያ የሚያስቆይህ በጭካኔ የተሞላው ኢፍትሀዊነት፣ ከብዙ ሌሎች ጉዳዮች ጋር፣ ስሜቴን ለመግለፅ እጅግ ከባድ ያደርገዋል።
“በንጹህ ቅንነት እና መለኮታዊ ምሕረት ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት ባይሆን ኖሮ፣ ያለፍኩትን የመከራ ትዕይንቶች መቼም ቢሆን በጽናት መቋቋም እንደማልችል እርግጠኛ ነኝ … ; ነገር ግን ለአንተ ስል እንዲህ እንድሰቃይ የደጉ ሰማይ ፍቃድ ከሆነ እኖራለሁ እና አሁንም ለመከራዬ የበለጠ መከራን ለመቀበል ፈቃደኛ ነኝ።
“በጣም ታማሚ ከሆነው ፍሬድሪክ በስተቀር አሁን ሁላችንም ደህና ነን።
“አሁን በእጄ ውስጥ ያለው ትንሹ አሌክሳንደር በሕይወትህ ውስጥ ከተመለከትካቸው በጣም ደስ የሚሉ ትንሽ ሰዎች አንዱ ነው። እሱ በጣም ጠንካራ ስለሆነ በአንድ ወንበር እገዛ በክፍሉ ዙሪያ ዙሪያውን በሙሉ ይሮጣል። …
“ከትንሽ ልጆቻችን በስተቀር ቤታችንን እና መኖሪያችንን ያገኘናቸውን ነገሮች ሁሉ ትተን፣ አንተንም ለብቻህ በዛ እስር ቤት ውስጥ እንደተዘጋብህ ትቼ ከምዙሪ ግዛት በምጣበት ጊዜ፣ የአእምሮዬን አስተሳሰብ እና የልቤን ስሜት ከእግዚአብሔር በስተቀር ማንም አያውቅም። ነገር ግን መታሰቢያው የሰው ልጅ ሊሸከም ከሚችለው በላይ ነው። …
“… አሁንም ወደ እኛ የሚመጡ የተሻሉ ቀናት እንደሚኖሩ ተስፋ አለኝ። … [እኔ] ሁል ጊዜ በፍቅር የአንተ ነኝ።
“ኤማ ስሚዝ”1
ከጆሴፍ ስሚዝ ወደ ኤማ ስሚዝ የተላከ ደብዳቤ፣ ሚያዚያ 4፣ 1839 (እ.አ.አ)
“ውድ—እና አፍቃሪ—ባለቤቴ።
“በሀሙስ ምሽት፣ በዚህ የብቸኝነት እስር ቤት ውስጥ አሾልከን የጸሃይን መጥለቅ ስንመለከት፣ ለአንቺ ያለሁበትን ሁኔታ ለማሳወቅ ደብዳቤ ለመጻፍ ቁጭ አልኩኝ። እኔ በሌሊትና በቀን በጠባቂዎች መኮሳተር፣ የሚሰቀጥጥ ድምጽ ያልው የብረት በር ባለው የብቸኝነት፣ ጨለማ እና ቆሻሻ እስር ቤት ግድግዳዎች ውስጥ ከሆንኩኝ አሁን አምስት ወር ከስድስት ቀናት2 ያህል እንደሆነ አምናለ። ይህንን ደብዳቤ የምጽፈው እግዚአብሔር ብቻ በሚያውቃቸው ስሜቶች ነው። በእነዚህ ሁኔታዎች ስር ያለው የአዕምሮ እይታ እኛ የሚያጋጥመንን በጭራሽ ላላጋጠመው የሰው ልጅ ለመግለጽ፣ ወይንም ለመሳል ብዕርን ወይም ምላስን፣ ወይ መላዕክትን ይከላከላል። እኛ ለማዳን በያህዌኽ ክንድ ላይ እንመካለን፣ እና በማንም አንመካም፣ እናም እሱ ካላደረገው አይከናወንም፣ በማንኛውም ነገር ጥፋተኞች ባንሆንም፣ በዚህ ስቴት ውስጥ ለደማችን ታላቅ ጥማት እንዳአለ እርግጥኛ ሁኚ። … ውዴ ኤማ ሁል ጊዜም ስለአንቺ እና ስለ ልጆቹ አስባለሁ። … ትንሹ ፍሬደሪክን፣ ጆሴፍን፣ ጁሊያን፣ አሌክሳንደርን፣ ጆአናን እና ኦልድ ሜጆርን (የቤተሰብ ውሻውን) ማየት እፈልጋለሁ። ከዚህ አንቺን ለማየት በባዶ እግሬ፣ በተጋለጠ ጭንቅላቴ፣ እንዲሁም ግማሽ ዕራቁቴን በመሆን ለመጓዝ ፈቃደኛ ነኝ እንም ይህን እንደ ታላቅ ደስታ እንጂ እንደ ስቃይ አላስበውም። … የእኔን ጭቆና ሁሉ በፅናት እሸከማለሁ፣ ከእኔ ጋር ያሉትም እንዲሁ ያደርጋሉ፤ ማንኛችንም ብንሆን ገና አልተንቀሳቀስንም። [ልጆቻችን] እንዳይረሱኝ እንድታደርጊ እፈልጋለሁ። አባታቻው በፍጹም ፍቅር እንደሚወዳቸው፣ እናም ከወንበዴዎች በማምለጥ ወደ እነርሱ ለመምጣት የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ነው ብለሽ ንገሪያቸው። … አባታቸውም ጥሩ ልጆች መሆን አለባችሁ እና እናታቸውንም ማክበር አለባችሁ ብሏል በያቸው። …
“የአንቺው፣
ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ”3