“ጥቅምት 11–17። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115–120፥ ‘መስዋዕቱ ለእኔ ከፍሬው በላይ ቅዱስ ነው፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]
“ጥቅምት 11–17። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115–120፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 11–17
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115–120
“መስዋዕቱ ለእኔ ከፍሬው በላይ ቅዱስ ነው”
ጌታ ሊያናግራችሁ ይፈልጋል። ቅዱሳት መጻህፍትን በምታጠኑበት ጊዜ፣ለእናንተ የሚሰጠውን መልእክቶች እንድታውቁት እንዲረዳችሁ ጸልዩ እና ጠይቁት።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
በሐምሌ 1838 (እ.አ.አ) ቅዱሳን ስለተሰበሰቡበት ስለ አዲሱ መሰብሰቢያ ቦታ ፋር ዌስት ተስፋ የማድረግ ምክንያት ነበር። ከተማዋ በፍጥነት እያደገች ነበር፣ ምድሪቱ ለጋስ መስላ ነበር፣ እናም ወደ ሰሜን አንድ አጭር ርቀት ላይ የሚገኝ አዳም-ኦንዳይ-አማን የሚባል ታላቅ መንፈሳዊ ጠቀሜታ ያለው ቦታ መኖሩ ተገለጸ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥53–56፤116 ይመልከቱ)። አሁንም፣ ቅዱሳኑ ስላጡት ነገር ላለማሰብ አስቸጋሪ ሳይሆን አልቀረም ነበር። እነሱ የፅዮን ማእከል ስፍራ ከነበረው ከእንድፔንደንስ ተባረው ነበር፣ እናም በማንኛውም በቅርብ ጊዜ የመመለስ እድሉ ምናልባት አናሳ ይመስል ነበር። በተጨማሪም፣ ቅዱሳን የሚወዱትን ቤተመቅደሳቸውን ከሁለት ዓመት ቆይታ በኋላ ብቻ በመተው ከከርትላንድ፣ ኦሃዮ ለመሸሽ ተገድደው ነበር። እናም በዚህ ጊዜ ችግር የሚፈጥሩት ከቤተክርስቲያኑ ውጭ ያሉ ጠላቶች ብቻ አልነበሩም—ሶስቱ የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክሮችን እና አራት የአስራ ሁለቱ ምስክሮች አባላትን ጨምሮ ብዙ ታዋቂ አባላት ጆሴፍ ስሚዝን ተቃዋሚ ሆነው ነበር። እንዳንዶችም የእግዚአብሔር መንግሥት እየተጠናከረች ናት ወይንስ እየደከመች ናት? በማለት ተገርመው ተገርመው ሊሆን ይችላል።
ሆኖም ታማኞቹ እንደዚህ ያሉ ጥያቄዎች እንዲያቆማቸው አልፈቀዱም። ይልቁን፣ አዲስ የተቀደሰ ስፍራ፣ በዚህ ጊዜም በፋር ዌስት ውስጥ መገንባት ጀመሩ። ለአዲሱ ቤተመቅደስ ዕቅዶችን አወጡ። ከጊዜ በኋላ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘዳንት የሚሆኑትን ሁለቱን፣ ጆን ቴይለር እና ዊልፎርድ ውድሩፍ፣ ጨምሮ አራት አዲስ ሐዋርያት ተጠርተው ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 118፥6 ይመልከቱ)። የእግዚአብሔርን ስራ በመሥራት ሂደት በጭራሽ አትወደቅም ማለት ሳይሆን ፤ “እንደገና ትነሳለህ” ማለት እንደሆነ ቅዱሳን ተማሩ። ምንም እንኳን አንዳንድ ነገሮችን መተው ቢኖርባችሁም፣ እነዚያ መስዋዕትነቶች ለእግዚአብሔር እንዲያውም “[ከፍሬአችሁ] በላይ … ቅዱስ ናቸው” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 117፥13)።
ቅዱሳን 1፥296–99፤ “ፋር ዌስት እና አዳም-ኦንዳይ-አማን፣” ራዕያት በአገባብ፣ 235–73 ይመልከቱ።
ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
የቤተክርስቲያኗ ስም በጌታ የተሰጠ ነበር።
ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን የቤተክርስቲያኗ ስም “እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው” ብለዋል። (“የቤተክርስቲያኑ ትክክለኛ ስም፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ) 87)። እናንተ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥4–6ን በምታነቡበት ጊዜ ይህ ለምን እውነት እንደሆነ አስቡበት። የቤተክርስቲያኗ ስም ከስራዋ እና ተልዕኮዋ ጋር ምን ግንኙነት አለው?
እንዲሁም 3 ኔፊ 27፥1–11ን ይመልከቱ።
ፅዮን እና ካስማዋ “ከአውሎ ነፋስ መሸሸጊያ” ይሰጣሉ።
በ1838 (እ.አ.አ) ቅዱሳኑ ከባድ ችግሮች ቢያጋጥሟቸውም፣ ጌታ አሁንም ለእነርሱ ከፍተኛ ተስፋ ነበረው። ጌታ ቤተክርስቲያኑ እና አባላቶቹ በዓለም ውስጥ እንዲያሟሉ የሚፈልገውን ሀላፊነት የሚያጎሉ ቃላትን በ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥5–6 ውስጥ ፈልጉ። ለምሳሌ፣ “ለመነሳት እና ለማብራት” (ቁጥር 5) ምን ማድረግ እንደሚያስፈልጋችሁ ይሰማችኋል? በአካባቢያችሁ ምን ዓይነት መንፈሳዊ ማዕበሎች ታስተውላላችሁ? እኛ በመሰባሰብ በኩል “መሸሸጊያ” (ቁጥር 6) እንዴት እናገኛለን?
በተጨማሪም 3 ኔፊ 18፥24ን ይመልከቱ።
የእኔ መስዋዕትነቶች በጌታ ዘንድ የተቀደሱ ናቸው።
በተለይም በዚያ ለቤተሰቦቻቸው የበለፀገ ኑሮ ለመሰረቱት እንደ ኒውል ኬ. ውትኒ አይነት ሰዎች፣ ከርትላንድን ለቅቆ መውጣት ከባድ ሊሆንባቸው ይችል ነበር። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 117፥1–11 ውስጥ ይህንን መስዋዕትነት እንዲከፍሉ ሊያግዛቸው የሚችልን ምን ታገኛላችሁ? እነዚህ ጥቅሶች በእውነት በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ነገር ያላችሁን አመለካከት እንዴት ይለውጣሉ?
ለኦሊቨር ግሬንጀር የተጠየቀው መስዋዕትነት የተለየ ነበር፥ በከርትላንድ ውስጥ እንዲቆይ እና የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ እንዲያስተካክል ጌታ ጥሪ ሰጠው። ከባድ ሥራ ነበር፣ እናም ቤተክርስቲያኗን በታማኝነት ቢወክልም፣ በመጨረሻም ብዙ ገንዘብ አላስመለሰም። በቁጥሮች 12–15 ያሉት የጌታ ቃላት ጌታ ለጠየቃችሁ ነገሮች እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆኑ ተመልከቱ።
በተጨማሪም ማቴዎስ 6፥25–33፤ ቦይድ ኬ ፓከር፣ “ከእነዚህ ያነሰው፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2004 (እ.አ.አ)፣ 86–88፤ “ሩቅ ምዕራብ እና አዳም-ኦንዳይ-አማን፣” ራዕያት በአገባብ፣ 239–40 ይመልከቱ።
አስራትን በመክፈል፣ “የጽዮንን ምድር” ለመገንባት እና “ለመቀደስ” እረዳለሁ።
በክፍሎች 119 እና 120 ያሉት መመሪያዎች በእኛ ጊዜ የጌታ ሥራ በገንዘብ ከሚደራጅበት መንገድ ጋር ተመሳሳይ ነው። ዛሬ ቅዱሳን “በየአመቱ የትርፋቸውን ሁሉ [ዛሬ የገቢያቸውን አንድ አስረኛ በሚል ነው ግንዛቤ የሚወሰደው] በየዓመቱ” ያበረክታሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 119–4)፣ እናም እነዚህ ገንዘቦች የሚተዳደሩት ቀደም አመራርን፣ አስራ ሁለቱ ጉባኤን፣ እና ኤጲስ ቆጶስ አመራርን በሚያካትት ሸንጎ ነበር። እነዚህን ክፍሎች ስታጠኑ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስቡባቸው፥
-
አሥራትን መክፈል “የፅዮንን ምድር [የሚቀድሰው]” እንዴት ነው? ይህ ሕግ የምትኖሩበትን ስፍራ “ለእናንተ የፅዮን ምድር” እንዲሆን እንዴት ሊረዳ ይችላል? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 119፥6)።
-
በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 120 ውስጥ “በምሰጣቸውም በራሴ ድምጽ” የሚለው ሐረግ ለእናንተ ምን ልዩ ትርጉም አለው?
በተጨማሪም ሚልክያስ 3፥8–12፤ ዴቪድ ኤ. ቤድነር፣ “የሰማይ መስኮቶች፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር፣ 2013 (እ.አ.አ)፣ 17–20፤ “የህዝቤ አስራት፣” ራዕያት በአገባብ፣ 250–55 ይመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥4–6።ፀሐይ ስትወጣ እያዩ ቤተሰባችሁ እነዚህን ጥቅሶች ማንበባቸው ይመቻል? “ተነሱ እና አብሩ” ምን ማለት እንደሆነ ለመወያየት ሊረዳችሁ ይችላል (ቁጥር 5)። ወይም ደግሞ በአውሎ ነፋሱ ወቅት መጠለያ መፈለግ ምን ማለት እንደሆነ መወያየት ትችላላችሁ። ያ ተሞክሮ በቤተክርስቲያን ውስጥ “መጠጊያ” እንደማግኘት እንዴት ሊሆን ይችላል? (ቁጥር 6) ከዚህ በኋላ ቤተክርስቲያኗ የምትሰጠውን መጠለያ እንዲያገኙ ቤተሰባችሁ ሌሎች ሰዎችን መርዳት ስለሚችልበት መንገዶች መነጋገር ትችላላችሁ።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 117፣1–11።ቤተሰባችሁ የውሃ “ጠብታን” አንድ “ብዛት” (ቁጥር 8) ካለው የጆግ ውሀ አይነት ጋር ሊያወዳድሩ ይችላሉ። ይህ በሕይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔርን የተትረፈረፉ በረከቶች እንዳናስተናግድ እንቅፋት ሊሆኑብን ስለሚችሉ አስፈላጊ ወዳላልሆኑ ነገሮች ውይይት ሊያመራ ይችላል።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 119።እንደ “እኔ አንድ አሥረኛውን ለጌታ መስጠት እፈልጋለሁ” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 150) አይነት መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ። መዝሙሩ እና ክፍል 119 አስራት ለምን እንደምንከፍል ምን ያስተምራሉ? ትንንሽ ልጆችም በነገሮች ምሳሌ በሚያሳይ ትምህርትም ሊጠቀሙ ይችላሉ፥ እናንተም ትንንሽ ነገሮችን መስጠት፣ አንድ አሥረኛውን እንዲያሰሉ መርዳት እና ለምን አስራትን እንደምትከፍሉ ልትነግሯቸው ትችላላችሁ። (በተጫማሪም ለእምነት እውነትነት፣ 180–82 ይመልከቱ)።
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝር በ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፥ “እኔ አሥረኛውን ለጌታ መስጠት እፈልጋለሁ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 150።