“ጥቅምት 25-31 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች –124፥ ‘በስሜ ቤቴን፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]
“ጥቅምት 25-31 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ 2021 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 25-31 (እ.አ.አ)
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124
“ለስሜ ቤት”
እናንተ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124ን ስታነቡ፣ በናቩ የሚገኙትን ቅዱሳን እንዲቀበሉ ጌታ የሰጣቸውን በረከቶች እና ለእናንተ የሚስጣችሁንም በረከቶች አሰላስሉ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
ያለፉት ስድስት ዓመታት ለቅዱሳን አስቸጋሪ ቢሆኑም፣ በ1839 (እ.አ.አ) ፀደይ ላይ ነገሮች ቀና ማለት ጀመሩ፥ ስደተኞቹ ቅዱሳን ከኩዊንሲ፣ ኢሊኖይ ዜጎች መካከል ርህራሄን አግኝተዋል። ጠባቂዎች ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች የቤተክርስቲያኗ መሪዎች በሚዙሪ ምርኮን እንዲያመልጡ ፈቀዱላቸው። እና ለቅዱሳን እንደገና የሚሰበሰቡበትን መሬት ቤተክርስቲያኗ በኢሊኖይ ውስጥ ገዛች። አዎ፣ ረግረጋማ የሆነ፣ በትንኝ የተሞላ መሬት ነበር፣ ነገር ግን ቅዱሳን ቀድሞ ካጋጠሟቸው ፈተናዎች ጋር ሲወዳደሩ፣ ይህ የሚኖርበት ይመስል ነበር። ስለዚህ ረግረጋማውን መሬት አደረቁ እና ናቩ ብለው ለጠሯት አዲስ ከተማ መተዳደሪያን አዘጋጁ። ይህም ስም በእብራይስጥ “ቆንጆ” ማለት ነው፣ ምንም እንኳን በጊዜው ከቀጥተኛ አባባል ይልቅ ቢያንስም የእምነታቸው መግለጫ ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጌታ ነቢዩን በጥድፊያ ስሜት እየገፋፋው ነበር። በዳግም የሚመልሳቸው ብዙ እውነቶች እና ስርዓቶች ነበሩት፣ እናም ቅዱሳን እነሱን ለመቀበል የሚችሉበት ቅዱስ ቤተመቅደስ ያስፈልገው ነበር። በብዙ መንገዶች፣ እንደነዚህ ተመሳሳይ የሆኑ የእምነት እና አጣዳፊ ስሜቶች በዛሬው የጌታ ስራ አስፈላጊ ናቸው።
ናቩ ውበት ያላት እና ቤተመቅደስ የሚገኝባት ከተማ ብትሆንም፣ ሁለቱም በመጨረሻ ተትወው ነበር። ግን የጌታ እውነተኛ ያማረ ስራ፣ በአጠቃላይ፣ እናንተን “በክብር፣ ህያውነት፣ እና በዘለአለማዊ ህይወትንም ማጎናጸፉ” ነበር (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 124፥55)፣ እና ያም ስራ በጭራሽ አይጠናቀቅም።
በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥399–427፤ “ቤተክርስቲያንን በናቩ ማደራጀት፣” ራዕይ በአገባብ 264–71ን ይመልከቱ።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ጌታ የሚያምነው ደቀመዝሙር መሆን እችላለሁ።
ምንም እንኳን በርካታ ታዋቂ መሪዎች ቤተክርስቲያኗን በ1830 (እ.አ.አ) መገባደጃ ላይ ቢተዉም፣ እጅግ በጣም ብዙ አባላት ታማኝ ነበሩ። እነዚህ ታማኝ ቅዱሳን በምዙሪ ፈተናዎችን በጽናት የተቋቋሙትን እና በቅርብ ጊዜ ቤተክርስቲያኗን የተቀላቀሉትን ያጠቃልላል። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥12–21፣ ጌታ ከእነርሱ መካከል ስለጥቂቶቹ በአድናቆት ተናገረ። በእርሱ ቃላት ስለ ደቀመዝሙርነት ምን ግንዛቤዎችን አገኛችሁ? እንደነዚህ ታማኝ ቅዱሳን ለመሆን እንድትነሳሱ የሚያደርግ አንድ ነገር አለ? እንዲሁም ጌታ ለእናንተ ያለውን ፍቅር እንዴት እንደገለጸ ማሰላሰል ትችላላችሁ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥22–24፣ 60–61
ጌታ ሌሎችን እንድቀበል ይፈልጋል።
ቅዱሳን በምዙሪ የተሰቃዩበትን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ በናቩ ውስጥ እራሳቸውን ለማግለል እና ጎብኚዎች እንዳይመጡ ለመከልከል በመፈለግ ስሜት ተፈትነው ሊሆን ይችላል። እናንተም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥22–24፣ 60–61ን በምታነቡበት ጊዜ ያንን አስታውሱ። ጌታ “ማረፊያ ቤት፣” ስለመገንባት የሰጠው መመሪያ ያስደነቃችሁ ምንድነው? (ቁጥር 23)። ስለ ቤተክርስቲያኗ ተልዕኮ የእርሱ ቃላት ምን ያስተምሯችኋል? እነዚህ መመሪያዎች ለእናንተ እና ለቤታችሁ እንዴት እንደሚተገብሩ አሰላስሉ።
በተጨማሪም “የሁሉም ጓደኛ” የሚለውን ቪዲዮ ይመልከቱ፣ ChurchofJesusChrist.org።
ቅዱስ ስርአቶችን ለመቀበል እንድንችል ቤተመቅደሶችን እንድንገነባ ጌታ አዝዞናል።
በናቩ ላሉት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ኦሃዮ እና ሚዙሪ እንዳደረገው ጌታ ቤተመቅደስ ስለመገንባት መመሪያ መስጠቱ አያስደንቅም። ጌታ ለምን “ለቅዱስ ስሜ ህዝቤ ሁልጊዜ [ቤተመቅደስ] እንዲገነቡ” ታዝዘዋል እንዳለ ለመረዳት በበትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥ 25–45፣55 ውስጥ ምን አገኛችሁ? (ቁጥር 39)።
የናቩ ቤተ መቅደስ ከተገነባ ጀምሮ፣ ከ200 በላይ ቤተመቅደሶች ተገንብተዋል ወይም እንደሚገነቡ ማስተዋወቂያ ተሰጥቷል። ፕሬዘደንት ራስል ኤም ኔልሰን እንዳስተማሩት፥ “በቤተመቅደስ ውስጥ የምናሳልፋቸው ጊዜዎች ለእኛና ለቤተሰቦቻችን ደህንነት እና ከፍ ለመደረግ አስፈላጊ እንደሆኑ እናውቃለን። … የጠላት ጥቃቶች፣ በትልቅነት እና በአይነት፣ በብዙ እጥፍ እያደጉ ናቸው። በቤተመቅደስ ውስጥ በየጊዜው ለመገኘት ያለን ፍላጎት ከዚህ በፊት ከነበረው በላይ ታላቅ ነው” (“ምሳሌአዊ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መሆን፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 114)። ቤተመቅደስ “የጠላትን ጥቃቶች” ለመቋቋም የረዳችሁ እንዴት ነው? የፕሬዚዳንት ኔልሰንን ምክር ለመከተል ምን አይነት ነገር የማድረግ ስሜት ይሰማችኋል?
ደግሞም የቤተክርስቲያን ታሪክ ርዕሶችንም፣ “የናቩ ቤተመቅደስ፣” ChurchofJesusChrist.org/study/church–history ይመልከቱ።
ጌታ በሕይወቴ ውስጥ ልዩ የሆነ ምክር ሊሰጠኝ ይፈልጋል።
ቁጥሮች 84–118 ለተወሰኑ ግለሰቦች በሚሰጡ ምክሮች ተሞልተዋል፣ እናም የተወሰኑት ለህይወታችሁ ተገቢ ላይመስሉ ይችላሉ። ነገር ግን መስማት የሚያስፈልጋችሁን ነገርም ልታገኙ ትችላላችሁ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ጌታ ለእናንተ ምን መልእክት እንዳለው መጠየቅን አስቡበት፣ እናም ይህን ለማግኘት የመንፈስን መመሪያ ፈልጉ። ከዚያ በእዛ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ምን እንደምታደርጉ ወስኑ። ለምሳሌ፣ የበለጠ ትሁት መሆን መንፈስን ለመቀበል እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል? (ቁጥር 97ን ይመልከቱ)።
እንዲሁም ጌታ የሰጣችሁን ሌሎች ምክሮችንም ማሰላሰል ትችላላችሁ። በዚህ ላይ እንዴት እየተገበራችሁ ናችሁ?
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥2–11።ጌታ ለቤተሰባችሁ “ለምድር አገሮች አስተዳዳሪዎች” “ወንጌሌን በቅድስና እንድታውጁ” ቢል፣ (ቁጥሮች 2–3) የእናንተ አዋጅ ምን ይላል? በጋራ አንድ ለመፍጠር አስቡ፣ እና የቤተሰብ አባላት ማካተት የሚፈልጉትን የወንጌል እውነት እንዲጠቁሙ ጋብዙ።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥15።ሀቀኝነት መኖር ማለት ምን ማለት ነው? ጌታ ሀቀኝነትን ከፍ አድርጎ የሚመለከተው ለምንድን ነው? ቤተሰባችሁ ምን የሀቀኝነት ምሳሌ አይተዋል? (በተጨማሪ ለወጣቶች ጥንካሬ፣ 19ን ይመልከቱ።)
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥28–29፣ 40–41፣ 55።ጌታ ቤተመቅደሶችን እንድንገነባ ያዘዘን ለምን እንደሆነ ከእነዚህ ጥቅሶች ምን እንማራለን? ቤተሰባችሁ የቤተመቅደስን ስዕል መሳል ወይም ከአንድ ድህረ ገጽ ወይም ሌሎች ግብአቶች መገንባት ይፈልጉ ይሆናል። ይህን ስታደርጉ፣ ዛሬ ቤተመቅደሶች ስላሉን ለምን አመስጋኝ እንደሆንን እና በቋሚነት በእነርሱ ውስጥ ማምለክ ለምን እንደሚያስፈልገን መወያየት ትችላላችሁ።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥91–92።ስለ ፓትሪያርክ በረከቶች ውይይት ቤተሰባችሁን ሊጠቅማችሁ ይችላሉን? የፓትርያርክ በረከታቸውን የተቀበሉ የቤተሰብ አባላት ይህን መቀበል ምን እንደ ሆነ እና እንዴት ይህም እንደባረካቸው ለመካፈል ይችላሉ። እንዲሁም “የፓትርያርክ በረከቶች” መከለስ ይችላሉ (የወንጌል ርዕሶች፣ topics.ChurchofJesusChrist.org)።
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፥ “ቤተመቅደስን ማየት እወዳለሁ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 95።
በዳግም የመመለስ ድምጾች
የሴቶች መረዳጃ ማህበር
በ1842 (እ.አ.አ)፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር በናቩ፣ ኢሊኖይ ውስጥ ከተደራጀ በኋላ፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ “ሴቶቹ እንደዚህ እስከተደራጁበት ጊዜ ድረስ ቤተክርስቲያኗ በፍፁም አልተደራጀችም” ብሏል።1 በተመሳሳይም፣ የጌታ ቤተክርስቲያን እና የክህነቱ የዳግም መመለስ ጥናት (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107 ይመልከቱ) የሴቶች መረዳጃ ማህበር ጥናትን እስኪያካትት ድረስ አልተጠናቀቀም፣ ይህም የሴቶች ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት የመሆን “የጥንት ንድፍ በዳግም መመለሱ” ነው።2
እላይዛ አር. ስኖው በዚያ ዳግም መመለስ ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውታለች። የሴቶች መረዳጃ ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ በተደራጀበት ጊዜ ተገኝተው ነበር እናም፣ እንደ ማህበሩ ጸሐፊ፣ በስብሰባዎቹ ወቅት ማስታወሻዎችን ይይዙ ነበር። የሴቶች መረዳጃ ማህበር “በክህነት ንድፍ” የተደራጀ መሆኑን በቀዳሚነት መሰከረች።3 ከዚህ በታች የሚገኙትም እርሳቸው የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ሆነው በሚያገለግሉበት ጊዜ ለቃል ኪዳን የእግዚአብሔር ሴት ልጆቹ የሰጠውን መለኮታዊ ስራ እንዲገነዘቡ ለመርዳት የሰጡት ቃላት ናቸው።
የሴቶች መረዳጃ ማህበር እንዴት እንደተደራጀ የበለጠ ለማወቅ፣ ሴት ልጆች በመንግሥቴ፥ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ታሪክ እና ስራ [2017 (እ.አ.አ)]፣ 1–25፤ የሴቶች መረዳጃ ማህበር የመጀመሪያው አምሳ ዓመታት [2016 (እ.አ.አ)]፣ 3–175ን ይመልከቱ።
እላይዛ አር. ስኖው
“ምንም እንኳን [የሴቶች መረዳጃ ማህበር] ስም የዘመናዊ ሊሆን ቢችልም፣ ተቋሙ ጥንታዊ አመጣጥ አለው። [በጆሴፍ ስሚዝ] እንደተነገረን፣ ይህ ድርጅት በቤተክርስቲያን ውስጥ በጥንት ዘመን እንደነበር፣ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በተመዘገቡት አንዳንድ ደብዳቤዎች ውስጥ “የተመረጠች እመቤት” በሚል ርዕስ ተጠቅሷል [ይመልከቱ፥ 2 ዮሀንስ 1:1፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥3]።
“ይህ ድርጅት ያለ ክህነት መኖር አይችልም፣ ምክንያቱም ስልጣኑን እና ሀይሉን ሁሉ የሚያገኘው ከዚያ ምንጭ ነውና። ክህነት ከምድር በተወሰደ ጊዜ፣ ይህ ተቋም እንዲሁም በምድር ላይ ያሉት ተቀጣይ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እውነተኛ ስርዓቶች ሁሉ ጠፍተዋል። …
“በናቩ ‘የሴቶች መረዳጃ ማህበር’ ድርጅት መቋቋም ጊዜ በመገኘቴ፣ … እናም በዚያ ማህበር ውስጥ ትልቅ ተሞክሮ በማግኘቴ፣ ምናልባት የፅዮን ሴት ልጆች ባለው በዚህ በጣም አስፈላጊ ቦታ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚረዱትን ጥቂት ፍንጮችን ልናገርባቸው እችል ይሆናል። ማንኛዎቹም የእስራኤል ሴት ልጆች እና እናቶች በአሁኑ ሁኔታቸው የተገደቡ እንደሆኑ ቢሰማቸው፣ ለሀይሎች በሙሉ እና በደንብ በመንፈስ በረከት በተሰጣቸው መልካም ለማድረግ ብቁ ችሎታ እንዳላቸው ያገኛሉ። …
“በማንኛውም፣ በአእምሯቸው ውስጥ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ዓላማ ምንድን ነው? የሚል ጥያቄ ቢነሳም፣ መልሴም—መልካም ለማድረግ—ድሆችን ለማዳን ብቻ ሳይሆን ነፍሳትን ለማዳን እኛ ያለንን አቅም ሁሉ ወደተጠየቀው ለማምጣት ነው። የትብብር ጥረት በጣም ውጤታማ ከሆኑ የግለሰቦች ጉልበት ጥረት በላይ እጅግ በጣም በተሳካ ሁኔታ ያከናወናል። …
“ድሆችን በመርዳት፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አካላዊ ፍላጎትን ከማስታገስ በላይ ሌላ የሚያከናውኑት ሀላፊነት አለ። የአእምሮ ድህነት እና የልብ ህመምም ትኩረትን ይጠይቃሉ፤ እና ብዙ ጊዜ የደግ አገላለፅ—ጥቂት የምክር ቃላት ወይም አልፎ ተርፎም ሞቅ ያለ እና በፍቅር የሚሰጥ የእጅ መጨበጥም ከወርቅ ሻንጣ የበለጠ ጥሩ ይሰራል እና ምስጋናም ይሰጠዋል። …
“ለሁሉም እንግዶች ሆነው፣ ለመዋሸት እና ለማታለል በሚጠብቁት ሰዎች በመጋለጥ፣ ቅዱሳን ከውጭ አገር ሲመጡ፣ [የሴቶች መረዳጃ] ማህበር [እነርሱን] በመጠበቅ መፋጠን እና እነሱንም ወደሚያነጻ እና ከፍ ከፍ ወደሚያደርግ፣ እና ከሁሉም በላይ በወንጌል እምነታቸው ወደሚያጠናክረው ማህበረሰብ እነርሱን ማስተዋወቅ ይገባዋል፣ እና ይህን በማድረግም ብዙዎችን ለማዳን ጠቃሚ መሳሪያ ሊሆን ይችላል።
በማኅበሩ እይታ ውስጥ የሚመጡ ተግባሮችን፣ መብቶችን እና ሀላፊነቶችን ለመግለፅ የመጽሃፍ ይዘቶች ያስፈልጋሉ። … (በኤጲስ ቆጶሱ አመራር ስር) በቀስታ፣ ሆን በማለት፣ በኃይል፣ በአንድነት እና በጸሎት ሂዱ እናም እግዚአብሔር ጥረቶቻችሁን ስኬትነት ይሰጠዋል።”4