ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ህዳር 1–7። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 125–128 “ለህያውና ለሙታን የደስታ ድምፅ”


“ህዳር 1–7። ትምህትና ቃል ኪዳኖች 125–128፥ ‘ለህያውና ለሙታን የደስታ ድምፅ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ህዳር 1–7። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 125–128፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ ከቅድመ አያቶች ጋር ያለ ቤተሰብ

እኛ ከእነርሱ ጋር እና እነርሱ ከእኛ ጋር፣ በኬትሊን ኮኖሊይ

ህዳር 1–7

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 125–128

“ለህያውና ለሙታን የደስታ ድምፅ”

እናንተ ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 125–28 በምታጠኑበት ጊዜ በእነሱ ላይ ማሰላሰል እና ለሌሎች ማጋራት እንድትችሉ ስሜታችሁን መመዝገብ ያስታውሱ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በነሐሴ 1840 (እ.አ.አ) በሐዘን የተደቆሰችው ጄኒ ኒይማን ነቢዩ ጆሴፍ በጓደኛው ሲሞር ብረንሰን የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ንግግር ሲሰጥ አዳመጠች። የጄኒ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኘው ወጣት ወንድ ልጇ ሳይረስ እንዲሁ በቅርቡ ሞቶ ነበር። ሐዘኗን የጨመረውም ሳይርስ ፈጽሞ ያልተጠመቀ መሆኑ ነበር፣ እናም ጄን ለዘለዓለማዊ ነፍሱ ይህ ምን ማለት እንደሚሆን ተጨነቀች። ጆሴፍ ምን እንደተሰማት ያውቅ ነበር፤ የሚወደው ወንድሙ አልቪን ከመጠመቁ በፊት ስለሞተ ተመሳሳይ ሐሳብ ያሳስበው ነበር። እናም ነቢዩ የወንጌል ስርዓቶችን ሳይቀበሉ ስለሞቱት፣ እና እነርሱን ለመርዳት ምን ማድረግ እንደምንችል፣ ጌታ የገለጸለትን ከጄን እና በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከሚገኙት ሁሉ ጋር ለመካፈል ወሰነ።

ለሙታን የመጠመቅ ትምህርቶች ቅዱሳንን አስደሰታቸው፤ ሀሳባቸው ወዲያውኑ ወደ ሟች ወላጆች፣ አያቶች እና ሌሎች የቤተሰብ አባሎች ተመለሰ። አሁን ለእነሱ ተስፋ ነበረ! ጆሴፍ ደስታቸውን ተጋራ፣ እናም ጌታ ስለ ሙታን መዳን ምን እንዳስተማረው ለመግለጽ በደስታ እና በጋለ ስሜት ቋንቋ ተጠቀመ፥ “ተራሮችም በደስታ ይጩሁ፣ እና ሸለቆዎች ሁሉ በጎላ ድምፅ አልቅሱ፤ እና እናንት ባህሮች እና ደረቅ ምድራት ሁሉ የዘለአለም ንጉሳችሁን አስደናቂነት ተናገሩ!” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128:23)።

ቅዱሳን 1:415–27፤ “ለሙታን የጥምቀት የሚጠቅሱ ደብዳቤዎች፣” ራዕያት በአገባብ፣ 272–76 ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 126

ጌታ ቤተሰቦቼን እንድንከባከብ ይፈልጋል።

ከበርካታ ተልእኮዎች ውስጥ በቅርቡ ከእንግሊዝ አገር ወደ ቤት ከተመለሱ በኋላ፣ ብሪገም ያንግ ሌላ አስፈላጊ ጥሪ ከጌታ ተቀበሉ፣ ይህም ባልነበሩበት ጊዜ መከራን የነበረባቸውን “ቤተሰብህን በልዩ ሁኔታ እንድትንከባከባቸው” ነበር (ቁጥር 3)። በክፍል 126 ውስጥ ያሉት ይህ እና ሌሎች ምክሮች እንዴት እናንተ ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን በምታስቡበት ጊዜ፣ የሚከተሉትን ከቀዳሚው ወጣት ሴቶች አጠቃላይ ፕሬዝዳንት ከሆኑት ከፕሬዚዳንት ቦኒ ኤል. ኦስካርሰንን ቃላት አስቡባቸው፥

“አንዳንድ በጣም አስፈላጊ ፍላጎቶች በፊታችሁ ያሉት እንደሆኑ አስታውሱ። በቤታችሁ እና በቤተሰባችሁ ውስጥ አገልግሎትን ጀምሩ። እነዚህ ዘለዓለማዊ ሊሆኑ የሚችሉ ግንኙነቶች ናቸው። ምንም እንኳን የቤተሰባችሁ ሁኔታ ፍጹም ካልሆነ፣ ለማገልገል፣ እናንተም ከፍ ለማድረግ እና ለማበረታታት መንገዶችን መፈለግ ትችላላችሁ። ባላችሁበት ጀምሩ፣ እንደሆኑም ውደዷቸው፣ እና ለወደፊቱ እንዲኖራችሁ ለምትፈልጉት ቤተሰብ ተዘጋጁ” (ከእኛ በፊት ያሉ ፍላጎቶች፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 27)።

በተጨማሪም “ለቤተሰባችሁ ልዩ እንክብካቤ ያድርጉ፣” ራዕያት በአገባብ፣ 242–49 ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 127፥2–4

ጌታ ደስታዬን እና ሀዘኔን ያውቃል።

የሐሰት ክሶች እና የመያዝ ስጋት ጆሴፍ ስሚዝ በነሐሴ 1842 (እ.አ.አ) እንደገና እንዲደበቅ አስገድደውታል። ነገር ግን በዚህን ጊዜ ለቅዱሳን የፃፋቸው ቃላቶች (አሁን ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 127) በተስፋና በደስታ ተሞልተዋል። እናንተን ቁጥሮች 2–4 ስለ እግዚአብሔር ምን ያስተምራችኋል? የግል ፈተናዎችን እንዴት መቋቋም እንደምትችሉ ምን ያስተምራችኋል?

ጌታ በህይወታችሁ “ጥልቅ ውሀ” ውስጥ እንዴት እንደሚጠብቃችሁ ለመመዝገብ ልብ በሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 127፥5–8128፥1–8

“በምድር የመዘገባችሁት ሁሉ በሰማይ የተመዘገበ ይሆናል።”

እናንተ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 127፥5–8128፥1–8ን ስታነቡ፣ ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ እንዲህ ላሉት የሙታን ጥምቀቶች ምዝገባን አስመልክቶ መመሪያ የሰጠበትን ምክንያት ፈልጉ። ስለ ጌታ እና ስለ ስራው ይህ ምን ያስተምራችኋል?

የቤተሰብ ስም ካርዶች ያለው ወጣት

ለቅድመ አያቶቻችን የቤተመቅደስ አገልግሎትን መስጠታችን ልባችንን ከእነርሱ ጋር ያስራል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥5–25

የቅድመ አያቶቼ መዳን ለእኔ መዳን አስፈላጊ ነው።

በዚህ ህይወት ያልተጠመቁ ቅድመ አያቶቻችን ለደህንነታቸው የእኛን እርዳታ የሚፈልጉት ለምን እንደሆነ እግዚአብሔር በጆሴፍ ስሚዝ በገለጠው በኩል ግልፅ ነው። ነገር ግን የቅድመ አያቶቻችን መዳን “ ለእኛ ደህንነት አስፈላጊ እና መሰረታዊ” የሆነው ለምን ይመስላቸኃል? (ይመልከቱ፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥15–18፤ ትኩረተ ተጨምሯል)።

ቁጥር 5 እንደሚያስተምረው ለሙታን የጥምቀት ሥርዓት “ከአለም መመስረት በፊት” ተዘጋጅቷል። ይህ እውነት ስለ እግዚአብሔር እና ስለ እቅዱ ምን ያስተምራችኋል? “የእግዚአብሔርን ቤተሰብ መሰብሰብ” የሚለው የፕሬዚዳንት ሄነሪ ቢ. አይሪንግ መልእክት ወደ ማስተዋላቸሁ ምን ይጨምራል? (ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 19–22)።

ጆሴፍ ስሚዝ ስለ ክህነት ስርዓቶች እና ስለ ሙታን ጥምቀት ሲያስተምር “የማሰር ኃይል”፣ “የመገጣጠሚያ አገናኝ” እና “ፍጹም አንድነት” የመሰሉ ሀረጎችን ተጠቅሟል። እናንተ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥5–25ን በምታነቡበት ጊዜ እነዚህን እና ተመሳሳይ ሐረጎችን ፈልጉ። በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለሙታን በክህነት ስርዓቶች ምክንያት ሊታሰሩ የሚችሉ አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው? ለሙታን የመዳንን ትምህርት ለመግለጽ “ደፋር” ጥሩ ቃል የሆነው ለምንድነው? (ቁጥሮች 9–11ን ይመልከቱ)።

ቁጥሮች 19–25 ውስጥ ስላሉት የጆሴፍ ስሚዝ ቃላት ያስገረማችሁ ምንድነው? እነዚህ ጥቅሶች ለቅድመ አያቶቻችሁ ስለምታደርጉት የቤተመቅደስ አገልግሎት በሚሰማችሁ ስሜት ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ? ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም? ምን ለማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል? (ለሀሳቦች FamilySearch.org/discovery ይመልከቱ)።

በተጨማሪም 1 ቆሮንቶስ 15፥29፤ ዲል ጂ. ሪንላንድ “የቤተሰብ ታሪክ እና የቤተመቅደስ ሥራ፥–መታተም እና ፈውስ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 46–49፤ “የጊዜ መሥዋዕት” እና “ልባቸው ከእናንተ ጋር ተሳስረዋል፣ ቪድዮዎች፣ ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክቶች

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 126ለብሪግሃም ያንግ የተሰጠን ይህንን ምክር ማንበብ እርስ በርሳችሁ የበለጠ “በልዩ ሁኔታ እንድትንከባከቡ” (ቁጥር 3) እንዴት ጊዜ ለማሳለፍ እንደምትችሉ ቤተሰባችሁ እንዲነጋገሩ ሊያነሳሱ ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥15–18የቤተሰብ ታሪክ ስራ አንዳንድ የማዳን እና ፍጹም የማድረግ በረከቶች ምንድን ናቸው? “የቤተሰብ ታሪክ በተስፋ የተሰጠ በረከቶች” በተሰኘው ቪዲዮ ውስጥ (ChurchofJesusChrist.org) በማየት ወይም እንደ “የቤተሰብ ታሪክ እኔ እየተገበርኩት ነው”ወይም (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 94) አይነት መዝሙርን ስለ የቤተሰብ ታሪክ በመዘመር አንዳንድ ሀሳቦችን ልታገኙ ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥18የቤተሰብ ታሪክ እና የቤተመቅደስ ስራ ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር የሚያገናኘንን “የሚያስተሳስር ግንኙነት” እንዴት እንደሚፈጥር ለማሳየት በእያንዳንዱ አገናኝ ላይ ከቤተሰብ አባላት እና ቅድመ አያቶች ስሞች ጋር የወረቀት ሰንሰለት መስራትን አስቡበት። ምናልባት ተጨማሪ የቤተሰብ አባላትን ለማግኘት እና የእናንተን ሰንሰለት ለምን ያህል ጊዜ እንደሚያድግ ለማየት አንዳንድ ጥናትን በFamilySearch.org ውስጥ ማድረግ ትችሉ ይሆናል ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥19–23ምናልባት የቤተሰብ አባሎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እና ስለ ሙታን መዳን ጆሴፍ ስሚዝ ስለነበረው ደስታ የሚያሳዩ ቃላትን ለማግኘት እነዚህን ጥቅሶች መፈተሽ ትችሉ ይሆናል። የቤተሰብ አባላትም በዚህ ሥራ እንዲደሰቱ ያደረጓቸውን ልምዶች ማካፈል—ወይም እነዚህን የመሳሰሉ ልምምዶች በFamilySearch.org/discovery ውስጥ አብረው መፈለግ ትችላላችሁ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር: “የቤተሰብ ታሪክ—እየተገበርኩት ነው፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 94።

የዳግም መመለስ ድምጾች ተምሳሌት

የዳግም መመለስ ድምጾች

ለሙታን መጠመቅ፣ “አዲስ እና ታላቅ ርዕሰ”

በናቩ ቤተመቅደስ ውስጥ የጥምቀት ገንዳ ንድፍ

ይህ ንድፍ የናቩ ቤተመቅደስ የጥምቀት ገንዳ በአሥራ ሁለት በሬዎች ላይ አርፈው ያሳያል።

ፌቤ እና ውልፈርድ ውድረፍ

ፌቤ ውድሩፍ ጆሴፍ ስሚዝ ስለ ሙታን ጥምቀት ማስተማር በጀመረበት ጊዜ በናቩ አቅራቢያ ትኖር ነበር። በእንግሊዝ በሚስዮን እያገለገለ ለነበረው ለባልዋ ለዊልፎርድ ስለዚህ ጉዳይ ጻፈች፥

“ወንድም ጆሴፍ … ለሞቱት እና ይህንን ወንጌል የመስማት እድል ለሌላቸው ዘመዶቻቸው፣ ለልጆቻቸው፣ ለወላጆቻቸው፣ ለወንድሞቻቸው፣ ለእህቶቻቸው፣ ለአያቶቻቸው፣ ለአጎቶቻቸው እና ለአክስቶቻቸው በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ መጠመቅ እንደሚችሉ በራዕይ ተምሯል። … ለጓደኞቻቸው እንደተጠመቁ ከእስር ወዲያው ይለቀቃሉ እናም በትንሳኤ ውስጥ የእነርሱ ያደርጓቸዋል እና ወደ ሰለስቲያል መንግሥትም ያመጧቸዋል—ይህ ትምህርት በቤተክርስቲያን ውስጥ በጥሩ ሁኔታ ተቀባይነት አግኝቷል እናም በብዛት ወደፊት እየሄዱ ናቸው፣ አንዳንዶች በአንድ ቀን እስከ 16 ጊዜያት ተጠመቁ።”1

በኋላ ውልፈርድ ውድረፍ ስለዚህ መርህ እንዲህ ብለዋል፥ “ይህን በሰማሁበት ቅጽበት ነፍሴ በደስታ ዘለለች። … ወደ ፊት ቀረብኩ እናም ላስታወስኳቸው ለሞቱ ዘመዶቼ ሁሉ ተጠመቅሁ። … ስለ ሙታን መጠመቅ ለእኛ ራእዩ ሲገለጥ ሃሌሉያ ለማለት ፈልጌ ነበር። በመንግሥተ ሰማይ በረከቶች የመደሰት መብት እንደነበረን ተሰማኝ።”2

ቪሌት ኪምቦል

እንደ እህት ውድሩፍ፣ ቪሌት ኪምቦል ስለ ባለቤቷ ሒበር ወንጌልን በሩቅ እየሰበከ በነበረበት ጊዜ ስለ ሙታን ጥምቀት ሰምታ ነበር። እሷም ጻፈችለት፥

“ፕሬዘደንት ስሚዝ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ታላቅ መነቃቃት እንዲፈጠር ያደረገ አዲስ እና የተከበረ ርዕሰ ጉዳይ ከፍተዋል። … ያም፣ ለሞቱ መጠመቅ ነው። ጳውሎስ ስለዚህ ጉዳይ፣ በአንደኛ ቆሮንቶስ 15ኛ ምዕራፍ 29ኛ ቁጥር ውስጥ ተናግሯል። ጅሴፍም በራዕይ የበለጠ የተሟላ ማብራሪያ አግኝቷል። … ይህ ወንጌል ከመምጣቱ በፊት ለሞቱት ዘመዶቻቸው፣ እስከ ሴት እና ወንድ ቅድመ አያቶቻቸው ድረስ፣ ሁሉ የመጠመቅ ትልቅ መብት የዚህች ቤተክርስቲያን እድል ነው። … እንዲህ በማድረግ ለእነርሱ ወኪሎች እንሆናለን፤ እናም በመጀመሪያው ትንሳኤ የመነሳትን እድል እንሰጣቸዋለን። እሱ ወንጌል እንደሚሰበክላቸው ተናግሯል … ግን ነፍሳት ይጠመቃሉ የሚል ምንም ነገር የለም። … ይህ ትእዛዝ እዚህ ስለተሰበከ፣ ውሃው ያለማቋረጥ ተረብሿል። በስብሰባው ወቅት አንዳንድ ጊዜ ከስምንት እስከ አስር ሽማግሌዎች በወንዙ ውስጥ ያጠምቁ ነበር። … ለእናቴ መጠመቅ እፈልጋለሁ። ወደ ቤት እስክትመለስ ድረስ መጠበቅን አሰላሁ፣ ነገር ግን ጆሴፍ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ በተነጋገረ ጊዜ፣ እያንዳንዳቸው እንዲነሱ እና እንዲያከናውኑት፣ እንዲሁም ጓደኞቻቸውን በተቻለ ፍጥነት ከባርነት ነፃ እንዲያወጡ መክሯል። ስለዚህ ብዙ ጎረቤቶች ይህን ስለሚያደርጉ በዚህ ሳምንት እኔም አደርገዋለሁ ብዬ አስባለሁ። አንዳንዶች ቀድሞውንም ቢሆን ብዙ ጊዜ ተጠምቀዋል። … በዚህ መንገድ ለሁሉም እድል እንዳለ ታያለህ። ይህ ታላቅ ትምህርት አይደለምን?”3

ፌቤ ቼዝ

በናቩ ቤተመቅደስ ውስጥ የጥምቀት ገንዳው ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ለሙታን መጠመቅ የሚከናወነው በወንዙ ውስጥ ሳይሆን በእዚያ ነበር። የናቩ ነዋሪ የሆነችው ፌቤ ቼስ የጥምቀቱን ገንዳ “ለሞቱብን የምንጠመቅበት እና በፅዮን ተራራ አዳኞች የምንሆንበት ቦታ” በማለት ለእናቷ ስለ ቤተመቅደስ ጽፋለች። እንዲህም በማለት ገለጸች፥ በዚህ ገንዳ ላይ “ለውዱ አባቴና ለተቀሩት የሞቱት ጓደኞቼ በሙሉ ተጠምቄያለሁ። … አሁን እነርሱን ለማስለቀቅ ስለምፈልግ የአባትሽ እና የእናትሽ ስሞች ምን እንደ ሆነ ማወቅ እፈልጋለሁ፣ ሙታንን ለማዳን እፈልጋለኁና። … ጌታ እንደገና ተናግሯል እናም የጥንታዊ ስርዓቱን ዳግም መልሷል።4

ሳሊ ራንዳል

ለጓደኞቻቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ስለ ሙታን መጠመቅ ስትጽፍ፣ ሳሊ ራንዳል የልጇን ጆርጅ ህልፈት አስታውሳለች፥

“አቤቱ ለእኔ ምንኛ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር እና አሁንም ይህን ለመቀበል አልቻልኩም፣ ነገር ግን … አባቱ ለእርሱ ተጠምቋል እናም እኛ የምናምነው እና የተቀበልነው አሁን እንደተሰበከ የወንጌሉ ሙላት ምን ታላቅ ነገር ነው እናም ለሁሉም ለሞቱት ጓደኞቻችን መጠመቅ እና እነርሱን እስከምናውቃቸው ድረስ ልናድናቸው እንችላለን።

“በየትኛውም ደረጃ እስከ የወንድ አያቶች እና የሴት አያቶች ድረስ የሞቱት የሁሉም ግንኙነቶች ስሞች እንድትፅፉልኝ እፈልጋለሁ። ጓደኞቼን ለማዳን የቻልኩትን ሁሉ ለማድረግ አስቤአለሁ እና አንዳንዶቻችሁም ብትመጡና ብትረዱኝ በጣም ደስ ይለኛል፣ ይህም አንድ ሰው ብቻውን ለማድረግ ትልቅ ስራ ነውና። … ይህ እንግዳ የሆነ ትምህርት ነው ብላችሁ ታስቡ ይሆናል ብዬ እጠብቃለሁ ነገር ግን እውነት እንደሆነ ታገኙታላችሁ።”5

ማስታወሻዎች

  1. ፌቤ ውድሩፍ ደብዳቤ ለውልፈርድ ውድረፍ፣ ጥቅምት 6 ቀን 1840 (እ.አ.አ)፣ የቤተክርስቲያኗ ታሪክ ቤተመጻሕፍት፣ ሶልት ሌክ ሲቲ፤ የፊደል አጻጻፍ እና ሥርዓተ–ነጥቡ ዘመናዊ ተደርጓል።

  2. ውልፈርድ ውድረፍ፣ “ንግግሮች፣” ዴዘረት ኒውስ፣ ግንቦት 27፣ 1857 (እ.አ.አ)፣ 91፤ ሥርዓተ–ነጥቡ ዘመናዊ ተደርጓል።

  3. ቪሌት ኪምቦል ደብዳቤ ለሂበር ሲ. ኪምቦል ጥቅምት 11፣ 1840 (እ.አ.አ)፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጻሕፍት፣ ሶልት ሌክ ስቲ፤ የፊደል አጻጻፍ እና ሥርዓተ–ነጥቡ ዘመናዊ ተደርጓል።

  4. የፌቤ ቼስ ደብዳቤ፣ ቀኑ ያልታወቀበት፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጻሕፍት፣ ሶልት ሌክ ሲቲ፣ የፊደል አጻጻፍ እና ሥርዓተ–ነጥቡ ዘመናዊ ተደርጓል። ቅዱሳን ለሙታን መጠመቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጀምሩ፣ ግለሰቦች አንዳንድ ጊዜ የሁለቱም ጾታዎች ቅድመ አያቶችን በመወከል ይጠመቁ ነበር። በኋላ ለወንዶች ወንዶች እና ለሴቶች ደግሞ ሴቶች መጠመቅ እንዳለባቸው ተገለጠ።

  5. ሳሊ ራንዳል ደብዳቤ ሚያዝያ 21፣ 1844 (እ.አ.አ)፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጻሕፍት፣ ሶልት ሌክ ስቲ፤ የፊደል አጻጻፍ እና ሥርዓተ–ነጥቡ ዘመናዊ ተደርጓል።

የጥምቀት ገንዳ በኦግደን ዩታ ቤተመቅደስ ውስጥ

በኦግደን ዩታ ቤተመቅደስ ውስጥ የጥምቀት ገንዳ በአስራ ሁለት በሬዎች ጀርባ ላይ ይቀመጣል።