ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ህዳር 15–21። ትምህትና ቃል ኪዳኖች 133–134፥ “ለሙሽራው ምጻት ተዘጋጁ”


“ህዳር 15–21። ትምህት እና ቃል ኪዳኖች 133–134፥ ‘ለሙሽራው ምጻት ተዘጋጁ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ህዳር 15–21። ትምህት እና ቃል ኪዳኖች 133–134” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

አምስት ብልህ ደናግል

ሙሽራው መጣ፣ በኤልሳቤት ጊብንስ

ህዳር 15–21

ትምህት እና ቃል ኪዳኖች 133–134፥ “ለሙሽራው ምጻት ተዘጋጁ”

“ለሙሽራው ምጻት ተዘጋጁ”

ፕሬዘደንት ሄነሪ ቢ. አይሪንግ እንዳስተማሩት፥ “ወንጌሉ ዳግም መመለስ የተጀመረው በትሁት ቤት ውስጥ በጥልቀት በተሰላሰለው ትሁት ጥያቄ ነበር፣ እና ይህም በእያንዳንዱ ቤታችን ውስጥ መቀጠል ይችላል” [“የጌታ መንፈስ የሚኖርበት ቤት፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 25]።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ቤተክርስቲያኗ ገና 19 ወር ብቻ በነበረችበት ጊዜ፣ ​​ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች የቤተክርስቲያኗ መሪዎች የእግዚአብሔርን የኋለኛ ቀን መገለጥን ወደ አንድ ጥራዝ ለማጠቃለል እና 10 ሺህ ቅጂዎችን ለማተም የታቀደ ታላቅ እቅድ አውጥተው ነበር—ይህም የመፅሐፈ ሞርሞን የመጀመሪያ እትምን በላይ በእጥፍ ለማተም ነበር። እንደ አለመታደል ሆኖ፣ ከፍተኛ ወጪዎች እነዚህን እቅዶች ገለል አደረገ፣ እና ህትመቱ በሂደት ላይ እያለ የቤተክርስቲያኗን ማተሚያ አመጸኛ ሰዎች አጠቁ። ያልተጠረዙ ገጾችን በታተኑ፣ እና ምንም እንኳን ደፋር ቅዱሳን ጥቂቶቹን ቢያተርፉም፣ ምንም የተሟላ የትእዛዝ መጽሐፍ ቅጂዎች እንደተረፈ አይታወቅም።

አሁን ክፍል 133 ብለን የምናውቀው የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል በትእዛዛት መጻህፍት ውስጥ ተጨማሪ መግለጫ፣ እንዲሁም በጌታ በታተሙ ራእዮች ላይ እንደ አንክሮ ነጥብ እንዲሆን የታሰበ ነበር። እሱ የሚመጣውን የፍርድ ቀን ያስጠነቅቃል እናም በዘመናዊው መገለጥ ሁሉ ውስጥ የሚገኘውን ጥሪ ያስተጋባል፥ በባቢሎን ከተመሰለው ዓለማዊነት ሽሹ፤ ፅዮንን ገንቡ፤ ለዳግም ምፅዓት ተዘጋጁ፤ እናም ይህንን መልእክት “ለሕዝብ፣ ለነገድ፣ ቋንቋ፣ እና ወገንም” አሰራጩ” (ቁጥር 37)። የትእዛዝ መጻህፍት የመጀመሪያ ዕቅዶች የተሳኩ ባይሆኑም፣ ይህ መገለጥ የጌታ ሥራ ሊከሽፍ እንደማይችል አስታዋሽ እና ምስክር ነው፣ “የተቀደሰውን ክንዱን … ይገልጣልና፣ እና በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካቸውን መድኃኒት ያያሉ” (ቁጥር 3)።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133

በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ያሉ እውነቶች የእግዚአብሔርን ስራ እንድሰራ ሊያዘጋጁኝ ይችላሉ።

መጽሐፍት አንዳንድ ጊዜ የመጽሐፉን ዋና ዋና ነጥቦችን በሚደግፍ ወይም በማጠቃለያ መደምደሚያ ይጠናቀቃሉ። ክፍል 133 መጀመሪያ የታሰበው የትእዛዛት መጽሐፍ መደምደሚያ እንዲሆን ነበር፣ ይህንን በግምት ውስጥ በማስገባት ይህንን ክፍል ማንበብ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ጌታ ስለ ሥራው የትኛውን ነጥብ ላይ ትኩረት አደረገ? ቁጥሮች 57–62 ጌታ በሥራው ውስጥ እንድትጫወቱ ስለሚፈልግበት ሚና ምን ያስተምሯችኋል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥1–19

ለዳግም ምፅዓቱ እንድዘጋጅ ጌታ ይፈልግብኛል።

ሁለቱም ክፍል 1፣ የጌታ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች መቅድም፣ እና ክፍል 133፣ የመጀመሪያው መጽሐፍ ተጨማሪ መግለጫ፣ በጌታ በተሰጡ ተመሳሳይ ልመና ይጀምራሉ፥ “የቤተክርስቲያኔ ህዝብ ሆይ፣ አድምጡ፣” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥1133፥1)። ማድመጥ ማለት ምን ማለት ነው? (ለቅዱሳት መጻህፍት መመሪያን፣ “አዳምጡ” ይመልከቱ፣ scriptures.ChurchofJesusChrist.org)። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥1–19 ውስጥ ምን ዓይነት ግብዣዎች ወይም ትዕዛዞች እንድታደምጡ ጌታ ይፈልጋል? ለእሱ ምፅዓት በተሻለ ለመዘጋጀት ምን ምሪት አገኛችሁ? በአካባቢያችሁ ያሉ ሰዎችን እንዲዘጋጁ እንዴት ትረዷቸዋላችሁ?

በተጨማሪም ማቴዎስ 25፥1–13፣ ዲ ቶድ ክርስቶፈርስን “ለጌታ መመለስ መዘጋጃትኤንዛይን ወይም ሊያሆና ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 81–84ን ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥19–56

ዳግም ምፅዓት ለጻድቃን አስደሳች ይሆናል።

የአዳኝን ዳግም ምጽዓት ስለሚከተሉ ክስተቶች በ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥19–56 ውስጥ ስታነቡ፣ የእነዚህ ክስተቶች መግለጫዎች ስለአዳኝ እና ስለ ስራው ምን እንደሚጠቁሙ ልታሰላስሉ ትችላላችሁ። በእነዚህ መግለጫዎች ውስጥ ምን ሊሆኑ የሚችሉ መንፈሳዊ መተግበሪያዎችን ታገኛላችሁ?

ቁጥሮች 32–56ን ስለ አዳኝ ምፅዓት መግለጫ ስታነቡ፣ ያንን ታላቅ ቀን በጉጉት እንድትጠብቁ የሚያደርጋችሁ ምንድን ነው? ጌታ ለህዝቡ ያለውን ፍቅር የሚገልፁት ቃላት ወይም ሀረጎች የትኞቹ ናቸው? “[የጌታችሁን] አፍቃሪ ደግነትን፣ እና በመልካምነቱም መሰረት፣ … [በእናንተ] ላይ ስላፈሰሰው” (ቁጥር 52) ያላችሁን የግል ልምዶች ለመመዝገብ ያስቡበት።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 134

“መንግስታት እግዚአብሔር ለሰው ጥቅም የመሰረታቸው [ናቸው]።”

የቀድሞ ቅዱሳን ከመንግስት ጋር የነበራቸው ግንኙነት ውስብስብ ነበር። ቅዱሳኑ በጃክሰን ካውንቲ፣ ሚዙሪ በ1833 (እ.አ.አ) ተገድደው ሲወጡ፣ በአከባቢው ወይም በብሔራዊ መንግሥት እርዳታን ለማግኘት ቢለምኑም ድጋፍም ሆነ ካሳ አልተሰጣቸውም። በተመሳሳይ ጊዜም፣ ከቤተክርስቲያን ውጭ ያሉ አንዳንድ ሰዎች ስለ ፅዮን ያለው ትምህርት ቅዱሳን የምድራዊ መንግስታት ስልጣንን አልተቀበሉም ማለት ነው ብለው ተረጎሙ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 134 በክፊልም የተጻፈው ቤተክርስቲያኗ ስለመንግስት ያላትን አቋም ለማብራራት ነበር።

የቤተክርስቲያን አባላት ስለ መንግስታት ምን ሊሰማቸው ይገባል? ክፍል 134ን ስታጠኑ፣ ሁለት ዝርዝሮችን ለመዘርዘር አስቡበት፥ አንደኛው ስለ መንግስት የምትማሩት መሰረታዊ መርሆዎችን እና ሌላኛው ስለ ዜጎች ኃላፊነትን ይዘርዝር። እነዚህ ሀሳቦች ለቀደሙት ቅዱሳን እንዴት ጠቃሚ ይሆኑ ነበር? እናንተ በምትኖሩበት ቦታ እንዴት ይተገበራሉ?

በተጨማሪም የእምነት አንቀጾች 1፥11–12፤ “የሃይማኖት ነፃነት፣” topics.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ፥።

የቤተሰብ ጥናት ምልክቶች

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥4–14ከጽዮን መንፈሳዊ ተቃራኒ የሆነችው ባቢሎን ናት—በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ሁሉ ክፋትንና መንፈሳዊ ባርነትን የሚያመለክታት ጥንታዊት ከተማ ናት [የሚቀጥሉትን ይመልከቱ፥ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርስን፣ “ወደ ፅዮን ኑ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና ህዳር 2008 (እ.አ.አ)፣ 37፤ ቅዱሳት መጻሕፍት መመሪያ፣ “ባቤል፣ ባቢሎን፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org]። በቤተሰብ ደረጃ በመንፈሳዊ አባባል “ከባቢሎን [ለመውጣት]” (ቁጥር 5) እና “ወደ ፅዮን … [ለመሄድ]”? (ቁጥር 9) የሚባለውን ለማድረግ የሚያስፈልጋችሁ ምን አለ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥20–33እነዚህን ጥቅሶች በጋራ ስታነቧቸው፣ ዳግም ምፅአት ምን እንደሚመስል የሚያስቡትን ስዕሎች ቤተሰቦቻችሁ መሳል ይችላሉ። እንዲሁም ስለ ዳግም ምፅዓት፣ እንደ “እንደገና ሲመጣ” (የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 82–83) አይነት መዝሙርን ለመጫወት ወይም ለመዘመር፣ እና ቤተሰባችሁ ለእርሱ ምፅዓት ለመዘጋጀት ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለመወያየት ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥37–39ቤተሰቦቻችሁ እነዚህን ጥቅሶች “በታላቅ ድምፅ” (ቁጥር 38) በማንበብ ይደሰታሉን? በታላቅ ድምፅ ወንጌልን ማካፈል ማለት ምን ማለት ነው? የትኞቹን እውነቶች ማጋራት እንችላለን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 134፥1–2ቤተሰቦቻችሁ ስለመንግስት አስፈላጊነት እንዲገነዘቡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መወያየት ትሽላላችሁ፥ ህግ በመኖሩ ቤተሰባችን የሚባረከው እንዴት ነው? ህግ በመኖሩ አገራችን እንዴት የተባረከች ናት? እንዲሁም የአገራችሁን ሰንደቅ ዓላማ በስዕል መስራት ወይም ማቅለም ወይም አስራ አንድኛ እና አስራ ሁልተኛ የእምነት አንቀጾችን በቃል መያዝ ትችላላችሁ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ይመልከቱ።

የተጠቆመ መዝሙር፥ “ኑ፣ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች ሆይ፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 58።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ግልፅ እና ቀላል ትምህርትን አስተምሩ። ጌታ ወንጌሉን “ግልጽ” እና “ቀላል” በሚሉት ቃላት ይገልፃል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥57)። ወንጌልን ለቤተሰቦቻችሁ ስለማስተማር እነዚህ ቃላት ምን ይጠቁሙላችኋል?

ክርስቶስ በቀይ ልብስ

ክርስቶስ በቀይ ልብስ፣ በሚኔርቫ ቲችርት