“ህዳር 22–28 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135–136፥ ‘እርሱ “ተልዕኮውን እና ስራዎቹን በደሙ አስሯል”’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]
“ህዳር 22–28 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135–136፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)
ህዳር 22–28 (እ.አ.አ)
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135–136
እርሱ “ተልዕኮውን እና ስራዎቹን በደሙ አስሯል”
ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 135–36ን ስታጠኑ፣ ያነበባችሁትን ለመተግበር እንዲረዳችሁ ጌታ ግንዛቤዎችን ይሰጣችሁ ይሆናል። ይህ በሚሆንበት ጊዜ፣ እርሱ የሚያስተምራችሁን ፃፉ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
በሰኔ 27 ቀን 1844 (እ.አ.አ) ከሰዓት በኋላ፣ ጆሴፍ እና ኃይርም ስሚዝ ከጆን ቴይለር እና ዊለርድ ሪቻርድ ጋር በመሆን በእስር ቤት ውስጥ በድጋሚ ይገኙ ።ነበር። ከማንኛውም ወንጀል ንጹህ እንደሆኑ ያምኑ ነበር፣ ነገር ግን በናቩ ውስጥ ባሉት ቅዱሳኖች ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት ለመከላከል ተስፋ በማድረግ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እራሳቸውን ሰጡ። የቤተክርስቲያኗ ጠላቶች ነቢዩ ጆሴፍን እስር ቤት ያስገቡበት ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አልነበረም፣ ነገር ግን በዚህ ጊዜ በህይወት እንደማይመለስ የተገነዘበ ይመስላል። እርሱ እና ጓደኞቹ ከመፅሐፈ ሞርሞን በማንበብ እና መዝሙር በመዘመር እርስ በእርሳቸው ለማጽናናት ሞከሩ። ከዚያ ተኩስ ድምጽ ተሰማ፣ እና በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የጆሴፍ ስሚዝ እና የወንድሙ ኃይርም ምድራዊ ሕይወት ተፈጸመ።
ነገር ግን ይህም ያቀፉት የመለኮታዊ ስራ መጨረሻ አልነበረም። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ዳግም መመለስ መጨረሻም አልነበረም። ተጨማሪ ስራ ነበር እናም ቤተክርስቲያኗን ወደ ፊት የሚመራ ተጨማሪ ራእይም ነበር። ነቢዩን መግደል የእግዚአብሔርን ሥራ ሊገድል አልቻለም።
ቅዱሳን፣ 1፥521–52 ይመልከቱ።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፤ 136፥37–39
ጆሴፍ እና ሃይረም ስሚዝ ምስክራቸውን በደማቸው አተሙ።
ጆሴፍ እና ሃይረም ስሚዝ ሲገደሉ በናቩ ውስጥ ብትኖሩ ኖሮ ምን ሊሰማችሁ እንደሚቻል ገምቱ (ቅዱሳን፣ 1፥554–55 ይመልከቱ)። የዚህን አሳዛኝ ክስተት ትርጉም ለመስጠት እንዴት ትሞክሩ ነበር? ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 135፣ ከሰማዕነታቸው ከሶስት ወር በኋላ ለመጀመሪያ የታተመው፣ ምናልባት የሚረዳ ሊሆን ይችላል። ማስተዋል እና ማበረታቻ ሊያመጣላችሁ የሚችሉ ቃላትን እና ሀረጎችን ምልክት ማድረግ ትችላላችሁ። “እግዚአብሔር ነቢዩ እንዲገደል ለምን ፈቀደ?” ብሎ ለሚጠይቅ ሰው ምን ምላሽ አላችሁ?
ደግሞም ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 5፥21–22፤ 6፥29–30፣ “ሰማዕትነትን ማስታወስ፣” ራዕያት በአገባብ፣ 299–306፤ የቤተክርስትያኗ ፕሬዘዳንቶች ትምህርቶች፥ ጆሴፍ ስሚዝ፣ 522–23፣ 529–40 ኤም. ራስል ባለርድ፣ “Shall We Not Go On in So Great a Cause?” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 8–11 ይመልከቱ።
ጆሴፍ ስሚዝ ከኢየሱስ ክርስቶስ በስተቀር ለእኛ መዳን ከማንም የበለጠ አድርጓል።
የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባልበመሆናችሁ ምክንያት ወደ እናንተ ስለመጡት በረከቶች አስቡ። ስንቶቹ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተከናወነው ተልእኮ ውጤት ናቸው? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፥3 የመጀመሪያውን ራዕይ ተከትሎ በ24 ዓመታት ውስጥ ጆሴፍ ስሚዝ ከፈጸማቸው ታላላቅ ነገሮች መካከል አንዳንዶቹን ይዘረዝራል። እነዚህ ነገሮች እናንተን ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለችሁን ግንኙነት እንዴት ተጽእኖ አሳድረዋል? የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ምስክርነታችሁን ለመቅዳት አስቡበት። ምስክርነትታችሁን መስማት የሚፈልግ ማን ነው?
በህይወት ውስጥ “ጉዞዎቼ” ጌታ ምክርን ይሰጠኛል።
ከናቩ ከተባረሩ በኋላ፣ ቅዱሳን ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ የሚወስደው ረጅም መንገድ ገጥሟቸው ነበር፣ እናም የመጀመሪያዎቹ ጥቂት መቶ ኪሎ ሜትሮች ዝግተኞች እና ተስፋ የሚያስቆርጡ ነበሩ። አሁን እንደ አስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን ፕሬዘደንት ቤተክርስቲያኗን የሚመሩት ብሪገም ያንግ ቅዱሳን የተቀሩትን ጉዞ እንዴት መትረፍ እንደሚችሉ ተጨነቁ። እርሳቸውም ዊንተር ኳርተር የተባለ ጊዜያዊ ሰፈር አቋቋሙ እናም መመሪያ ለማግኘት ተማጸኑ። በምላሽም፣ ጌታ በክፍል 136 ውስጥ የሚገኘውን ራእይ ሰጣቸው። ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ፣ ይህ መገለጥ ቅዱሳን “በጉዞአቸው ላይ የነበራቸው ባህሪ እንደ መድረሻቸው በጣም አስፈላጊ” እንደሆነ እና “ከአሳዛኝ አስፈላጊነት ወደ አስፈላጊ መንፈሳዊ ተሞክሮ ለመቀየር” እንደረዳቸው እንዲያስታውሱ አደረገ። (“ይህ ቃል ኪዳኖቻችን ይሆኑ፣” ራዕያት በአገባብ፣ 308)።
ይህንንም አግባብ ክፍል 136 በምታጠናበት ጊዜ ልብ በሉ። በሕይወት ውስጥ አስቸጋሪ ፈተናን ወደ “አስፈላጊ … መንፈሳዊ ተሞክሮ” ለመቀየር የሚረዳችሁን ምን ምክር አገኛችሁ? እንዲሁም የቀደሙት ቅዱሳን አስቸጋሪውን ወደ ምዕራብ ጉዞ እንዲፈጽሙ እንደረዳቸው፣ ምክሩ በራሳችሁ ሕይወት ውስጥ የጌታን ፈቃድ ለመፈፀም እንዴት እንደሚረዳ ማሰላሰል ትችላላችሁ።
ደግሞም “ይህ ቃል ኪዳኖቻችን ይሆኑ፣” ራዕያት በአገባብ፣ 307–14፤ የቤተክርስቲያን ታሪክ ርዕሰ ጉዳዮች፣ “የቤተክርስቲያን አመራር ስኬት፣” ChurchofJesusChrist.org/study/history/topics ይመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፥1፣ 3።የቤተሰብ አባሎች ጆሴፍ ስሚዝ “ተልእኮውን እና ስራዎቹን በእራሱ ደም ማተም” ምን ማለት እንደሆነ እንዲረዱ ለማገዝ፣ ቤተሰቦቻችሁ “የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክር” ቪዲዮን ማየት ትችላላችሁ (ChurchofJesusChrist.org፤ ደግሞም ጄፍሪ አር. ሆላንድንም፣ “ለነፍስ ደህንነት፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2009 (እ.አ.አ)፣ 88–90 ይመልከቱ)። ስለ እነዚህ ጥቅሶች ያስደነቀን ምንድን ነው? ሕይወታችንን ለእነርሱ እንድንሰጥ ባንጠየቅም እንኳን፣ ለምስክርነቶቻችን የበለጠ ታማኝ እንዴት ለመምሆን እንችላለን?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፥3።ጆሴፍ ስሚዝ “ከኢየሱስ በቀር፣ በዚህ ዓለም ላይ ለሰው ልጆች መዳን ከማንም ሰው ሁሉ” ባላይ ሰርቷል ብሎ የገለጸውን ምን ለማለት እንደሆነ ለመወያየት፣ ቤተሰቦቻችሁ በዚህ አመት ስለ ጆሴፍ ስሚዝ የተማሩትን ለመከለስ አስቡበት። የተማሩትን እንዲያስታውሱ ለማገዝ ከዚህ የጥናት ምንጭ ስዕሎችን መጠቀም እና የሚወዷቸውን ታሪኮች ወይም ትምህርቶች እንዲያጋሩ ለመጋበዝ ትችላላችሁ። ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ጌታ በእርሱ በኩል ላከናወነው ሥራ ለምን አመስጋኞች ነን? እንዲሁም “ጆሴፍ ስሚዝ፥ የዳግም መመለስ ነቢይ” የሚለውን ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ (ChurchofJesusChrist.org)።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 136።ጌታ ክፍል 136ን ሲገለጥ፣ ቅዱሳን በብሪገም ያንግ መሪነት ከፊት ለፊታቸው ረዥም አስቸጋሪ ጉዞ ነበራቸው (ምዕራፍ 58፣ 60፣ እና 62 በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 206–8፣ 211–16፣ 222–24 ይመልከቱ)። ክፍል 136ን በጋራ ስታነቡ፣ በቤተሰባችሁ ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉ አስቸጋሪ ነገሮች አስቡ። በዚህ ራዕይ ውስጥ የጌታን እርዳታ እና ሀይል እንድናገኝ የሚረዳን ምን ምክር እናገኛለን?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 136፥4።“በጌታ ሥርዓቶች ሁሉ እንሄዳለን” ሲባል ምን ማለት ነው? የተቀበልናቸው ስርዓቶች በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፥ “ለሰውየው ምስጋና፣” መዝሙር፣ ቁጥር 27።