ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ህዳር 29–ታህሳስ 5። ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 137–138፥ “ስለሙታን ቤዛነት ራዕይ”


“ህዳር 29–ታህሳስ 5። ትምህትና ቃል ኪዳኖች 137–138፥ ‘ስለሙታን ቤዛነት ራዕይ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ህዳር 29–ታህሳስ 5። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137–138፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
በመንፈሳዊው ዓለም ያሉ ሰዎች

ጆሴፍ አባቱን፣ እናቱን እና ወንድሙን በሰለስቲያል መንግሥት ውስጥ አየ (የጆሴፍ ስሚዝ የሰለስቲያል መንግሥት ራዕይ፣ ሮበርት ባረት)።

ህዳር 29–ታህሳስ 5

ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 137–138

“የሙታን ቤዛነት ራዕይ”

ፕሬዘደንት ኤም. ራስል ባላርድ እንዳስተማሩት፥ “በጥልቀት እና በጥንቃቄ [ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 138] እንድታነቡ እጋብዛችኋለሁ። ይህን ስታደርጉ፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ለልጆቹ ያለውን የደህንነት እና የደስታ እቅዱ ሙሉ በሙሉ እንድትረዱት እና በአድናቆት እንድትመሩ ጌታ ይባርካችሁ። [“የሙታን ቤዛነት ራዕይ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 73]።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137 እና 138 ውስጥ የተመዘገቡት ራዕዮች በ80 ዓመታት እና በ 2 ሺህ 414 ኪሎ ሜትሮች በመራራቅ ይለያዩ ነበር። ክፍል 137ን በ1836 (እ.አ.አ) ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ባልተጠናቀቀው የከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ነበር የተቀበለው እናም ክፍል 138ን በ1918 (እ.አ.አ) በሶልት ሌክ ሲቲ ውስጥ የተቀበሉትም ስድስተኛው የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ ነበሩ። ነገር ግን በትምህርት፣ እነዚህ ሁለት ራዕዮች ጎን ለጎን የሚሄዱ ናቸው። እነርሱም በሚቀጥለው ህይወት ውስጥ ስላለው ስለእግዚአብሔር ልጆች ዕጣ ፈንታ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ። የተቀበሉትን ነቢያት የሕይወት ልምዶች ስንመረምርም ሁለቱም ተጨማሪ ጥልቅ ትርጉም ይይዛሉ።

የጆሴፍ ስሚዝ ራዕይ የጥምቀት ስልጣን እንደገና ከመመለሱ ከስድስት ዓመት በፊት የሞተውን የወንድሙ አልቪንን የዘለአለም ዕጣ ፈንታን እንዲረዳ አግዞታል። የአልቪን ዘላለማዊ ደህንነት ጥያቄዎች ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከጆሴፍ ጋር ነበሩ። የጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ ራዕይም ስለ መንፈስ አለም አስደናቂ እውነቶችን ገልጿል—በእርግጥም የበርካታ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ሞት አዝኖ ለነበረ ሰው መፅናኛ የሚያመጣ ራዕይ ነበር። ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ አባታቸውን ኃይረም ስሚዝን በ5 ዓመታቸው እና እናታቸውን፣ ሜሪ ፊልዲንግ ስሚዝንም፣ በ13 ዓመታቸው አጥተው ነበር። በ1918 (እ.አ.አ) በራዕያቸው መገለጥ ወቅት፣ 13 ልጆች መሞትን እያዘኑበት ነበር።

ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት ብዙ ሰዎች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች በእነዚህ ራዕዮች ውስጥ ተመልሰዋል። ክፍል 137 ለእነዚህ አይነት ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ያብራራል፣ እና ክፍል 138 የእውቀት መጋረጃዎችን ይበልጥ በስፋት ይከፍታል። በአንድ ላይ፣ “አብ እና ወልድ ያሳዩትን ታላቅ እና አስደናቂ ፍቅር” ይመሰክራሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥3)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137

እያንዳንዷ ነፍስ የሰለስቲያል ክብርን የመምረጥ እድል ይኖራታል።

በ1836 (እ.አ.አ) አካባቢ በክርስቲያኖች መካከል የተለመደው መግባባት፣ ልክ እንደ ጆሴፍ ስሚዝ ወንድም አልቪን አይነት ያልተጠመቀ ሰው ወደ ሰማይ መሄድ እንደማይችል ነው። ሆኖም ጆሴፍ ስለሰለስቲያል መንግሥት ባየው ራዕይ ውስጥ አልቪንን አየ። እናንተ ክፍል 137ን ስታነቡ፣ ስለሰማይ አባት፣ ስለደህንነት እቅዱ እና ስለ ሰለስቲያል መንግስተ ምን እንደተማራችሁ አሰላስሉ።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥232–35ን ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥1–11፣ 25–30

ቅዱሳት መጻህፍትን ማንበብ እና ማሰላሰል መገለጥን እንድቀበል ያዘጋጀኛል።

አንዳንድ ጊዜ መገለጥ ባልፈለግንበትም ጊዜ ይመጣል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ የሚመጣው በትጋት በመፈለጋችን እና ለዚያ በመዘጋጀታችን ምክንያት ነው። እናንተ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥1–11፣ 25–30ን ስታነቡ፣ ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ “የመረዳት [አይናቸው ሲከፈቱ]” የአዳኝን የመቤዥት ተልእኮ በተሻለ ለመረዳት ምን እያደረጉ እንደበሩ አስተውሉ። ከዚያም የፕሬዚዳንት ስሚዝን ምሳሌ እንዴት መከተል እንደምትችሉ አስቡበት። ለምሳሌ፣ “በቅዱሳት መጻሕፍት ለማሰላሰል” እና የበለጠ “[የአዳኝን] ታላቅ የኃጢያት ክፍያ” ለማሰላሰል” እንድትችሉ በቅዱሳት መጻህፍት ጥናታችሁ ላይ ምን ለውጦች ማድረግ ትችላላችሁ? (ቁጥሮች 1–2)።

በመልእክታቸው “የሙታን ቤዛነት ራዕይ” (ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ) 71–74) ውስጥ፣ ፕሬዘደንት ኤም. ራስል ባላርድ ፕሬዘደንት ስሚዝ ይህንን ራዕይ ለመቀበል የተዘጋጁባቸውን ሌሎች መንገዶችን ጠቁመዋል። አሁን ለሚኖራችሁ ወይም ወደፊቱ ለሚያጋጥማችሁ ልምዶች እንዴት እንደምትዘጋጁ ልብ ይበሉ።

በተጨማሪ “የጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ አገልግሎት፥ የሙታንን የመዳን ራዕይ፣” የሚለውን ቭድዮ በ ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

ምስል
የጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ ምስል

ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ በአልበርት ኢ. ሳልዝብረነር

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥25–60

የደህንነት ሥራ በመጋረጃው በሁለቱም በኩል እየተከናወነ ነው።

ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ “ለአለም ያለን መልእክት ቀላል እና ልባዊ ነው፥ በመጋረጃው ሁለት በኩል ያሉትን የእግዚአብሔር ልጆችን ሁሉ ወደ አዳኛቸው እንዲመጡ፣ የቤተመቅደስ በረከቶችን እንዲቀበሉ፣ በደስታ እንዲጸኑ፣ እናም ለዘለአለም ህይወት ብቁ እንዲሆኑ እንጋብዛለን” [“ወደፊት እንግፋ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 118–19]። እናንተም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥25–60ን ስታነቡ ይህንን መግለጫ አሰላስሉ። እንዲሁም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከግምት ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ፥

  • በመንፈሳዊው አለም ውስጥ የደህንነት ሥራ እንዴት እየተከናወነ እንደሆነ ከእነዚህ ጥቅሶች ምን ተማራችሁ? ይህ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ማወቅ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? እነዚህ ጥቅሶች በአዳኝ የኃጢያት ክፍያ ላይ ያላችሁን እምነት እንዴት ያጠናክራሉ?

  • እነዚህ ጥቅሶች በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ በደህንነት ሥራ ስለሚሳተፉ ሰዎች ምን ያስተምራሉ? የደህንነት ሥራው በመጋረጃው በሁለቱም በኩል እየተሠራ መሆኑን መረዳት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

በተጨማሪም ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “በጌታ ታምኑ፣“ ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 26–29፤ “ሱዛ ያንግ ጌትስ እና የሙታንን መዳን ራዕይ፣” ራዕያት በአገባብ፣ 315–22 ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክቶች

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137፥1–5ቤተሰባችሁ በእነዚህ ጥቅሶች ላይ በመመስረት የሰለስቲያል መንግሥት ምን እንደሚመስላቸው እንዲስሉ ይጋብዟችው። በእነዚህ ጥቅሶች እዚያ ለመኖር ተስፋ ለማድረግ የሚረዷችሁን ምን ታገኛላችሁ? በሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ለመኖር ለመዘጋጀት አሁን ምን እያደረግን ነን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137፥5–10ጆሴፍ ስሚዝ ብዙ የቤተሰብ አባላቱን በሰለስቲያል መንግስተ ውስጥ ማየት መቻሉ ለእርሱ ምን ትርጉም እንደነበረው ለመማር፣ ቤተሰባችሁ “የጆሴፍ ስሚዝ ትምህርት፥ ቤተመቅደሶች” (ChurchofJesusChrist.org) የተሰኘውን ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ። ምናልባትም ለመጠመቅ እድሉ ሳይኖረው ስለሞተ ስለ አንድ ሰው ማውራትም ትችላላችሁ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137፥5–10 ስለዚህ ሰው ምን አስተምረውናል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥12–24ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥12–24 አዳኙ በመንፈስ አለም ስለጎበኛቸው ሰዎች ምን ያስተምራሉ? ምን በረከቶች ተቀበሉ? ከእነርሱ ምሳሌ ምን እንማራለን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥38–55እነዚህ ጥቅሶች ፕሬዘዳንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ በመንፈስ አለም ውስጥ ያዩአቸውን እና ስለእነሱ አጭር ዝርዝሮችን ይገልፃሉ። ምናልባት ቤተሰባችሁ በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ያሉ ቅድመ–አያቶቻችሁን ለመዘርዘርና የሕይወት ዘመናቸውን በዝርዝር ማዘጋጀት ትችሉ ይሆናል።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ይፈልጉ፣ አሰላስሉ እና ይጸልዩ፣” የልጆች መዝሙር መፅሐፍ፣ 109።

ማስተማርን ማሻሻል

በቅዱሳት መጻህፍት ላይ ማሰላሰል። ፕሬዘደንት ዴቪድ ኦክ. መኬይ ማሰላሰልን “ወደ ጌታ ፊት በማለፍ የምንገባበት በጣም ቅዱስ ከሆኑ በሮች አንዱ ነው” ብለው ጠርተውታል (የቤተክርስቲያን ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፥ ዴቪድ ኦ. መኬይ [2003 (እ.አ.አ)]፣ 32)።

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ዓለም

ተልዕኮ የተሰጠው፣ በ ሃሮልድ አይ. ሆፕኪንሰን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ዓለም ውስጥ ወንጌልን እንዲሰብኩ ጻድቅ መንፈሶችን ተልዕኮ ሰጣቸው።

አትም