ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 20–26። ገና፥ ተወዳዳሪ የሌለው ስጦታ የሆነው የእግዚአብሔር መለኮታዊ ልጅ


“ታህሳስ 20–26። ገና፥ ተወዳዳሪ የሌለው ስጦታ የሆነው የእግዚአብሔር መለኮታዊ ልጅ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]።

“ታህሳስ 20–26። ገና፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
የማርያም እና የሕፃን ኢየሱስ ምስል

በመዳብ እና ኡምብር የተሰራ ልደት በጄ. ከርክ ሪቻርድስ

ታህሳስ 20–26

ገና

ተወዳዳሪ የሌለው ስጦታ የሆነው የእግዚአብሔር መለኮታዊ ልጅ

በዚህ የገና በዓል ሀሳባችሁን በአዳኝ ላይ ትኩረት የምታደርጉበት አንደኛው መንገድ “ሕያው ክርስቶስ፥ የሐዋሪያት ምስክርነትን” ማጥናት ነው። ይህ ዝርዝር ትንቢታዊ ምስክርነት የግል እና የቤተሰብ ወንጌል ጥናት ክፍል ማድረግ የምትችሉባቸውን መንገዶች ይጠቁማል።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በ1838 (እ.አ.አ) ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንደገለጸው፣ “የሐይማኖታችን መሰረታዊ መርሆች ቢኖሩ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በተመለከተ፣ እንዲሁም እርሱ እንደሞተ፣ እንደተቀበረ፣ እና በሶስተኛውም ቀን እንደተነሳ፣ እንዲሁም ወደ ሰማይ እንዳረገ የሚመሰክሩት የሐዋርያቶችና የነብያቶች ምስክርነቶች ናቸው፤ እናም ሁሉም ሐይማኖታችን የሚመለከቱ ሌላ ነገሮች በሙሉ የዛ አካል ቅጥያዎች ብቻ ናቸው።” (የቤተክርስትያኗ ፕሬዘዳንቶች ትምህርቶች፥ ጆሴፍ ስሚዝ፣ 49)። ከዓመታት በኋላ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳሉት “ለ15 ነቢያት፣ ባለ ራእዮች እና ገላጮች የጌታ ልደት 2 ሺህ ዓመት መታሰቢያን ለማክበር ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ እና እንዲፈርሙ ያበረታታቸው ይህ የነቢዩ ቃል ነበር። ያ ታሪካዊ ምስክርነት ‘ህያው ክርስቶስ‘ ይባላል። ብዙ አባላት የዚህን እውነቶች በቃላቸው ያስታውሳሉ። ሌሎቹ ደግሞ መኖሩንም በብዛት አያውቁም። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የበለጠ ለመማር ስትፈልጉ፣ ‘ህያው ክርስቶስን’ እንድታጠኑ አበረታታችኋለሁ” [“የኢየሱስ ክርስቶስን ሀይል ወደ ህይወታችን መሳብ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 40]።

እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ በዘመናችን ነቢያት እና ሐዋርያት በኩል ቀጣይነት ባለው መገለጥ በረከት እንደሰታለን። በመንፈስ አነሳሽነት ለሚሰጡት የምክር፣ የማስጠንቀቂያ እና ማበረታቻ ቃላት አመስጋኞች ነን። ነገር ግን ከሁሉም በላይ፣ በገና እና ዓመቱን በሙሉ፣ ስለኢየሱስ ክርስቶስ በሚሰጡት ጠንካራ ምስክርነታቸው ተባርከናል። እነዚህ የተካኑ ጸሐፊዎች ወይም የሕዝብ ተናጋሪዎች ቃላቶች ወይም ከቅዱሳት መጻህፍት ሊቃውንት የተገኙ ግንዛቤዎች ብቻ አይደሉም። እነርሱ በእግዚአብሔር ከተመረጡ፣ “በዓለም ሁሉ ውስጥ የክርስቶስ ስም ልዩ ምስክሮች” ተብለው ከሚጠሩና ስልጣን ካላቸው የመጡ ቃላት ናቸው (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 107፥23)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

“ይህን ያህል ተጽዕኖ ያሳደረ ሌላ ማንም የለም።”

ሉቃስ 2፥10–11ን “ከህያው ክርስቶስ” መጀመሪያው አንቀፅ ጋር ስታነቡ ምን ሀሳቦች ወደ እናንተ ይመጣሉ? “ከዚህ በፊት ከኖሩት እና በዚህ ምድር ላይ ከሚኖሩት ሁሉ በላይ [እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ] ትልቅ ተጽዕኖ ያሳደረ ማንም የለም” የሚለውን አባባል በመደገፍ ምን ትላላችሁ? “በህያው ክርስቶስ” ውስጥ የአዳኙን ጥልቅ ተጽዕኖ የሚገልጹ እውነቶችን ፈልጉ። እናንተ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው እና “ታላቅ ደስታ” ያመጣላችሁ እንዴት ነው? (ሉቃስ 2፥10)።

“እሱ ከመቃብር ተነስቷል።”

“በህያው ክርስቶስ” ውስጥ፣ ሐዋሪያቱ ከሞት ስለተነሳው ጌታ ሦስት እይታዎችን በመግለጽ ስለ አዳኝ ትንሳኤ መስክረዋል (አንቀጽ አምስትን ይመልከቱ)። ስለ እነዚህ ጉብኝቶች ዮሐንስ 20–213 ኔፊ 11–26፤ እና ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥14–20ን ለማንበብ ያስቡበት። በእነዚህ ትዕይንቶች ወቅት ከአዳኝ ቃላት እና ተግባሮቹ ምን ትማራላችሁ?

”ክህነቱ እና ቤተክርስቲያኑ ዳግም ተመልሰዋል።”

በዚህ አመት የትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን ጥናታችሁ ወቅት፣ የአዳኙ “ክህነት እና ቤተክርስቲያኑ እንዴት በዳግም እንደተመለሱ” የበለጠ ለመማር እድል አግኝታችኋል። ዳግም ከተመለሱት እውነቶች ወይም መርሆዎች በተለይ ለእናንተ ጠቃሚ የሆኑት ማንኛው ናቸው? ስለ ዳግም መመለስ የሚያስተምሩ የሚቀጥሉትን ጥቅሶች ለመከለስ አስቡ፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥17–231320፥1–1265110112፥30–32124፥39–42128፥19–21። ዳግም የተመለሰው ወንጌል እውነቶች ኢየሱስ ክርስቶስን ለማወቅና ለማምለክ እንዴት እንደሚረዷችሁ አሰላስሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥19 ይመልከቱ)።

“አንድ ቀን ወደ ምድር በዳግም ይመለሳል።”

የገና በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበትን ቀን ወደኋላ የምንመለከትበት እና እርሱም የሚመጣበትን ቀን በጉጉት የምንጠባበቅበት ጊዜ ነው። “በህያው ክርስቶስ” ውስጥ ከመጨረሻውሁለት አንቀጽ በፊት በሚገኘው ስለ ዳግም መመለሱ ምን ትማራላችሁ? እንደ “ደስታ ለዓለም” ወይም “እኩለ ሌሊት ላይ መጥቷል” (መዝሙር፣ ቁጥር 201፣ 207) አይነት ስለ ዳግም ምጽአቱ የሚያስተምሩ የገና ዝማሬዎችን ማንበብ፣ መዘመር ወይም ማዳመጥም አስደሳች ሊሆን ይችላል።

“እርሱ የአለም ብርሀን፣ ህይወት፣ እና ተስፋ ነው።”

“በህያው ክርስቶስ” መጨረሻው አንቀጽ ላይ፣ ለአዳኝ የተሰጡ ባህሪያትን እና ርዕሶችን ልብ በሉ። የሚቀጥሉት ጥቅሶች ኢየሱስ ክርስቶስ “የአለም ብርሃን፣ ሕይወት እና ተስፋ” እንዴት እንደሆነ እንድታሰላስሉ ሊረዳችሁ ይችላሉ፥ ሉቃስ 2፥25–321 ቆሮንቶስ 15፥19–23ሞሮኒ 7፥41ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥2484፥44–4693፥7–10። እርሱ የእናንተ ብርሃን፣ ሕይወት እና ተስፋ የሆነው እንዴት ነው? ለእናንተ የበለጠ ትርጉም ያላቸው ሌሎች የአዳኝ ባህሪዎች ወይም ስሞች ምንድን ናቸው?

“ህያው ክርስቶስን” ማጥናት በአዳኝ ላይ ባላችሁ እምነት እና ፍቅር ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው እንዴት ነው?

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ

የአለም ብርሃን፣ በሀዋርድ ሊዮን

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክቶች

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

“ህያው ክርስቶስ።”ቤተሰቦቻችሁ “በህያው ክርስቶስ” ስለአዳኝ የተማሩትን እውነቶች እንዲገነዘቡ ለማገዝ፣ የተወሰኑ ቁልፍ ሐረጎችን ለመምረጥ እና እነዚያን ሐረጎች የሚያብራሩ ስዕሎችን ለማግኘት ወይም ለመሳል አብራችሁ ለመስራት ትችላላችሁ። ከዚያም እነዚያን ስዕሎች እና ሐረጎች በመፅሀፍ ውስጥ ማቀናበር ትችላላችሁ።

“ምስክራችንን እናቀርባለን።”ምስክርነት መስጠት ምን ማለት እንደሆነ “ከህያው ክርስቶስ” ምን እንማራለን? የአዳኝን ልደት ለማክበር ስለክርስቶስ ያላችሁን ምስክርነት ለመመዝገብ አስቡበት።

“እሱ መልካምን በማድረግ ሄደ።”ቤተሰቦቻችሁ በዚህ የገና በዓል ላይ የአዳኝን አገልግሎት ምሳሌ ለመከተል እንዴት ይችላሉ? በቤተሰቦቻችሁ እና በማህበረሰባችሁ ውስጥ “ሰላምና በጎ ፈቃድ” እንዴት ይሰራጫሉ? “ለታመሙ ፈውስን” ለማምጣት እንዴት ልትረዱ ትችላላችሁ? በወንጌል ማህደረ አፕሊኬሽን ውስጥ ወይም በወንጌል ማህደረ ቤተ-መጽሐፍት ውስጥ በሚገኙት የገና ቪዲዮዎች ውስጥ አንዳንድ ሀሳቦችን ልታገኙ ትችላላችሁ (medialibrary.ChurchofJesusChrist.org)።

“ተወዳዳሪ ለሌለው መለኮታዊ ልጁ ስጦታው እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።”በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ምን ስጦታዎች ተቀበልን? ምናልባትም የቤተሰብ አባላት “በህያው ክርስቶስ” ውስጥ መልስ ማግኘት ይችሉ ይሆናል እና ከዚያም እነዚያን የአዳኝ ስጦታዎች የሚወክሉ ነገሮችን በስጦታ መጠቅለያ ያዘጋጁ። ቤተሰባችሁ በገና ቀን ወይም በዚያ ሳምንት በሙሉ ስጦታዎችን መክፈት እና ከእያድዳንዳቸው ጋር የሚዛመዱ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶችን ማንበብ ይችላሉ። ምንም እንኳን ቤተሰብዎ ብዙ ሌሎችን ሊያገኙ ቢችሉም፣ አንዳንድ ሊጠቅሙ የሚችሉ ጥቅሶች እዚህ አሉ፤ ሉቃስ 2፥10–141 ጰጥሮስ 2፥21ሞዛያ 3፥8አልማ 11፥42–43ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10–12። ከእሱ የሚመጡ ሌሎች ስጦታዎች ለማግኘት እንደ “ልጁን ልኮታል” (የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 34–35) አይነት ስለአዳኝ የሚናገሩ መዝሙርን ለመዘመር ትችላላችሁ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “አዳምጡ መልእክተኛ መላእክት ይዘምራሉ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 209።

የግል ጥናትን ማሻሻል

በአዳኝ ላይ ትኩረት ይደረግ። “‘ህያው ክርስቶስን’ በጸሎት ማንበብ የማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ የሉቃስ፣ የዮሐንስ እና የመፅሐፈ ሞርሞን ነቢያት ምስክሮችን እንደማንበብ ነው። በአዳኝ ላይ ያላችሁን እምነት ይጨምራል እናም በእርሱ ላይ ትኩረት እንድታደርጉ ይረዳችኋል” [ኤም. ራስል ባለርድ፣ ”መመለስ እና መቀበል፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና ግንቦት 2017 (እ.አ.አ) 65]።

አትም