ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 6–12። የእምነት አንቀጾች እና አስተዳደራዊ አዋጆች 1 እና 2፥ “እናምናለን”


“ታህሳስ 6–12። የእምነት አንቀጾች እና አስተዳደራዊ አዋጆች 1 እና 2፥ ‘እናምናለን’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]።

“ታህሳስ 6–12። የእምነት አንቀጾች እና አስተዳደራዊ አዋጆች 1 እና 2፥” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
የብዙ የቆዳ ቀለሞች እጆች የሚያሳይ የአልጋ ልብስ

ለሁሉ ብቁ ለሆኑ ወንዶች አባላት፣ በ ኤማ ኦልቢስ

ታህሳስ 6–12

የእምነት አንቀጾች እና አስተዳደሪያዊ አዋጆች 1 እና 2

“እናምናለን”

የእምነት አንቀጾች እና አስተዳደሪያዊ አዋጆች 1 እና 2ን ሰታጠኑ፣ በቤተክርስቲያኗ ላይ ያደረጉትን ተጽዕኖ አስቡባቸው። ስለሚያስተምሩት እውነት አናንተን የሚያስደንቃችሁ ምንድን ነው?

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ከጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ራዕይ ከ200 ዓመታት በኋላ፣ እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያኑ መሪዎች “በራዕይ ላይ ራዕይን፣ በእውቀት ላይ እውቀትን” መስጠቱን ቀጥሏል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥61)። በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ያ ራዕይ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች “እንደ ጌታ ፈቃድ፣ እንደ ሰው ልጆች ሁኔታዎች ምህረቱን በማመቻቸት” በቤተክርስቲያኗ ፖሊሲዎች እና ልምምዶች ላይ ለውጦችን እንዲያመጡ መመሪያ ሰጥቷቸዋል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥15)። አስተዳደራዊ አዋጆች 1 እና 2 እንደዚህ አይነት ራዕዮችን ይወክላሉ—አንደኛው ከአንድ ሚስት በላይ የማግባትን ልምምድ እንዲያበቃ ያደረገ ሲሆን፣ ሌላኛው ክህነት በረከቶችን፣ እንዲሁም የቤተመቅደስ በረከቶችን፣ ለሁሉም ዘሮች እንዲገኝ አድርጓል። እንደነዚህ ያሉ ለውጦችም፣ ከእውነተኛ እና ህያው ነቢይ ጋር፣ “እውነተኛ እና ህያው ቤተክርስቲያን” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥30) አለች የማለት ክፍል ነው።

ነገር ግን የማይቀየሩ ነገሮችም፣ እንዲሁም መሰረታዊ፣ ዘላለማዊ እውነቶች አሉ። እናም አንዳንድ ጊዜ የራዕይ ዓላማ እነዚያን እውነቶች የበለጠ እንድናይለመርዳት ተጨማሪ ብርሃንን ለመስጠት ነው። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የሚያምኑትን ጆሴፍ ስሚዝ የዘረዘራቸው 13 አጭር መግለጫዎች የእምነት አንቀጾች፣ ለዚህ ዓላማ የሚያገለግሉ ይመስላሉ። ሁለቱም አይነት ራዕያት ቤተክርስቲያኗን ይመራሉ እናም ይባርካሉ፣ ይህችም ቤተክርስቲያን በዘለአለማዊ እውነት ላይ የተመሠረተች ግን ጌታ በዛሬው ጊዜ የሚያጋጥሙንን ፈታኝ ሁኔታዎች ለማለፍ እንዲረዳን ማስተዋላችንን በሚያሳድግበት ጊዜ ለማደግና መለወጥ የምትችል ነች። በሌላም አባባል፣ “እግዚአብሔር እስካሁን በገለጣቸው ሁሉ፣ አሁንም በሚገልጣቸው ሁሉ እናምናለን፣ እናም የእግዚአብሔርን መንግስት በተመለከተ ወደፊትም እርሱ በሚገልጣቸው ታላቅና አስፈላጊ ነገሮችም እናምናለን” (የእምነት አንቀጾች 1፥9)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

የእምነት አንቀጾች

የእምነት አንቀጾች በዳግም የተመለሰው ወንጌል መሰረታዊ እውነቶችን ይዘዋል።

የእምነት አንቀጾች ማጥናት የምትችሉበት አንዱ መንገድ በእያንዳንዱ ውስጥ የሚገኙትን እውነቶች በመዘርዘር እና ከዚያም ከእውነቶቹ ጋር የተዛመዱ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶችን በመፈለግ ነው። እነዚህ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች በእምነት አንቀፅውስጥ ስለእውነት ያላችሁን ግንዛቤ የሚያበለፅጉት እንዴት ነው?

በተጨማሪም የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያን፣ “የእምነት አንቀጾች፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org፤ ኤል ቶም ፔሪ፣ “ትምህርቶች እና በእምነት አንቀጾች ውስጥ የተያዙ መሠረታዊ ሥርዓቶች፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 46–48፤ “ምዕራፍ 38፥ የዌንትወርዝ ደብዳቤ፣” በቤተክርስቲያን ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፥ ጆሴፍ ስሚዝ፣ 435–47 ይመልከቱ።

የእምነት አንቀጾች 1፥9አስተዳደራዊ አዋጆች 1 እና 2

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በራእይ ትመራለች።

ምንም እንኳን እነዚህ ነገሮች የቤተክርስቲያኗን ፖሊሲዎች እና ልምዶች መለወጥ ማለት ቢሆንም፣ “የእግዚአብሔርን መንግስት በተመለከተ ወደፊትም እርሱ በሚገልጣቸው ታላቅና አስፈላጊ ነገሮችም እናምናለን” (የእምነት አንቀጾች 1፥9)። ይህንን መርህ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ አስተዳደራዊ አዋጆች 1 እና2፣ ገምግሙ፣ እናም በመገለጥ ቀጣይነት እምነታችሁን የሚያጠናክሩ ቃላትን እና ሀረጎችን ፈልጉ። ለጌታ ነቢይ ቀጣይ ራዕይ መሰጠትን የሚያሳዩ ሊሎች ምን ምሳሌዎች ልታስቡ ትችላላችሁ? እነዚህ ራዕያት እንዴት በህይወታችሁ ላይ ተጽዕኖ አሳድረዋል? የሰማይ አባትን መንግሥት ሥራ እንዴት ወደፊት ገፍታችኋል?

በተጨማሪም ይመልከቱ፥ አሞፅ 3፥72 ኔፊ 28፥30

አስተዳደሪያዊ አዋጅ 1

የእግዚአብሔር ሥራ ወደፊት መጓዝ አለበት።

“ከፕሬዘደንት ዊልፈርድ ዉድረፍ ስለህዝባዊ መግለጫ ከሰጡት ሶስት ንግግሮች የተወሰደ ምንባብ” (በአስተዳደራዊ አዋጅ 1 መጨረሻው ላይ)፣ ከአንድ በላይ ሚስቶች ማግባት ልምድን በቤተክርስቲያኗ ለማቆም ጌታ ለነቢዩ ምን ምክንያቶች ሰጠ? ስለ እግዚአብሔር ሥራ ይህ ምን ያስተምራችኋል?

ስለ አስተዳደሪያዊ አዋጅ 1፣ እና “መልእክተኛው እና ህዝባዊ መግለጫ” ታሪካዊ መነሻው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ (ራዕያት በአገባብ፣ 323–31) and “Plural Marriage and Families in Early Utah” (የወንጌል ርዕሶች፣ topics.ChurchofJesusChrist.org) ይመልከቱ።

ምስል
የዊልፈርድ ዉድረፍ ምሥል

ዊልፈርድ ዉድረፍ በ ኤች. ኢ. ፒተርሰን

አስተዳደራዊ አዋጅ 2

ፍጹም የሆነ መረዳት በማይኖረንም ጊዜ እንኳ በጌታ ልናምን እንችላለን።

ቅዱሳት መጻህፍት በጌታ እንድናምን ያስተምሩናል (ምሳሌ 3፥5 ይመልከቱ)፣ እና ቤተክርስቲያኗ የክህነት ስርዓትን እና የቤተመቅደስ ስነስርአቶችን በከለከለችበት ጊዜ ብዙዎቹ የአፍሪካ የዘር ሐረግ ያላቸው የቤተክርስቲያኗ አባላት ያደረጉት ይህንንም ነበር። ምንም እንኳን ይህ ፖሊሲ ለምን እንደነበረ ባይረዱም—እና ቤተክርስቲያኗ ዛሬ የምትወግዘውን ምክንያት በመማር ስሜታቸው የተጎዱ ቢሆኑም—በርካታ ቀናተኛ የአፍሪካ የዘር ሐረግ ያላቸው አባላት በጌታ አመኑ እና በህይወታቸው ሙሉ ታማኝ ሆነው ቀሩ። አስተዳደሪያዊ አዋጅ 2ን ስታነቡ፣ ምንም እንኳን ፍጹም የሆነ መረዳት ባይኖራችሁም እንኳን በጌታ ላይ እንዴት መታመን እንደቻላችሁ አሰላስሉ።

ስለ ጥቁር የቤተክርስቲያኗ አባላት እምነት መማር እናንተን የሚያነሳሳ ሊሆን ይችላል። ከታሪኮቻቸው ውስጥ የተወሰኑት፣ በhistory.ChurchofJesusChrist.org ውስጥ ይገኛሉ፥

  • ጄን ኤልዛቤት ማንኒ ጄምስ” (የቤተክርስቲያን ታሪክ ርዕሶች)

  • በአባቴ ቤት ውስጥ ብዙ መኖሪያዎች አሉ” (የግሪን ፍሌክ ታሪክ)

  • በመጨረሻ መጥተዋል” (የአንቶኒ ኦቢያን ታሪክ)

  • “መራራ አፈርን ይስበሩ” (የጁሊያ ማቪምቤላ ታሪክ)

  • በእምነት ይህን እወስዳለሁ” (የጆርጀ ሪከፎርድ ታሪክ)

ደግሞም “ታማኝነትን መመሥከር፣” ራዕያት በአገባብ፣ 332–41፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “ዘር እና ክህነት፣” ChurchofJesusChrist.org፤ አህመድ ኮርቢት፣ “በዘር እና በክህነት ስልጣን ላይ ያለ የግልዊ ጥናታዊ ጽሁፍ፣” ክፍሎች 1–4፣ ChurchofJesusChrist.orgBeOne.ChurchofJesusChrist.orgን ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክቶች

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

የእምነት አንቀጾችቤተሰብባችሁ ለየእምነት አንቀጾች “አጭር ትምህርቶችን” እንዴት ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ያስቡ። ለምሳሌ፣ በሳምንቱ ውስጥ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል አንድ አንቀጽ መምረጥ እና ተዛማጅ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅስ፣ ስዕል፣ መዝሙር፣ ወይም የልጆችን መዝሙር ማግኘት ወይም የግል ልምድ ለመካፈል ይችላል።

ወይም የቤተሰብ አባላት ተራ በተራ ስለ ቤተክርስቲያኗ እና ስለእምነቶቻችን አንዳቸው ሌላውን ጥያቄዎች መጠየቅ ይችላሉ፣ ከዚያም እነዚያን ጥያቈዎች የእምነት አንቀፅን በመጠቀም መመለስ ይችላሉ።

አስተዳደሪያዊ አዋጅ 1 እና 2አስተዳደሪያዊ አዋጅ 1 እና 2 በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ዘመናዊ ራዕያት ያላቸውን ሚና እንድንገነዘብ ይረዱናል። ከቤተሰባችሁ ጋር አብረው ስታነቡ፣ ነቢዩ “በሁሉም ገዢ እግዚአብሔር መነሳሳት” (አስተዳደሪያዊ አዋጅ 1) እንዴት እንደሚመራን ለመወያየት አስቡበት። እነዚህ ሁለት አዋጆች በግል ቤተክርስቲያኑን በሚመራው በህያው እግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት የሚያጠናክሩት እንዴት ነው? ዛሬ በቤተክርስቲያኗ ስራ ላይ እጁን እንዴት እናያለን? ከዚህ በላይ ባለው “ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች” ውስጥ ያሉትን አንዳንድ የጥናት ምንጮች በአንድ ላይ ለማሰስ መወሰን ትችላላችሁ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ትዕዛዛቱን ጠብቁ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 146–47።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

በተግባር እንዲውሉ የተደረጉ የግብዣ ጥሪዎችን ክትትል ያድርጉ። “እርምጃ እንዲወስዱ የቀረበላቸውን ግብዣ ሲከታተሉ፣ ለቤተሰባችሁ አባላት እንደምታስቡላቸው እና ወንጌል ህይወታቸውን እንደሚባርካቸው ታሳያላችሁ። ደግሞም ልምምዳቸውን እንዲካፈሉ እድሎችን ትሰጣችኋላችሁ“ (በአዳኝ መንገድ ማስተማር፣ 35)።

አትም