“ታህሳስ 13፟–19 (እ.አ.አ)። ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣ ‘ቤተሰብ ለፈጣሪ እቅድ ማዕከላዊ ነው፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]
“ታህሳስ 13፟–19 (እ.አ.አ)። ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ 2021 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 13፟–19 (እ.አ.አ)
ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ
“ቤተሰብ ለፈጣሪ እቅድ ማዕከላዊ ነው”
ፕሬዝዳንት ዳለን ኤች. ኦክስ እንዳሉት፥ “ስለቤተሰብ አዋጁ ያለን አመለካከት እና አጠቃቀማችን ለዚህ ትውልድ [ፈተና] እንደሆነ አምናለሁ። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን በዚያ ፈተና ውስጥ ጸንተው እንዲቆሙ እፀልያለሁ” (“ዕቅዱ እና አዋጁ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ሀዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 31)። በዚህ ሳምንት የቤተሰብ አዋጅን በምታጠኑበት ጊዜ እነዚህን ቃላት አሰላስሉ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
ከመወለዳችን በፊት፣ የቤተሰብ፣ እንዲሁም የሰማይ ወላጆቻችን ቤተሰብ አካል ነበርን። ከእነሱ ፊት የመውጣት ጊዜ ሲመጣ፣ የምድር ቤተሰቦችም የእግዚአብሔር እቅድ አካል እንደሚሆኑ ማወቁ የሚያጽናና ይሆንም ነበር። በምድር ላይ ያለው ንድፍ በሰማይ ፍጹም የሆነውን ንድፍ ለማሳየት ነው።
ምድራዊ ቤተሰቦች በጣም ጥሩ ወይም ተግባራዊ እንደሚሆኑ ዋስትና የለም። ነገር ግን ፕሬዘዳንት ሔነሪ ቢ. አይሪንግ እንዳስተማሩት፣ ቤተሰቦች “የእግዚአብሔር ልጆች ወደ አለም ሲመጡ በሰማይ የተሰማቸውን ብቸኛ የወላጃዊ አቀባበል ፍቅር እድልን ይሰጣሉ” [“የእግዚአብሔርን ቤተሰብ መሰብሰብ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 20]። ቤተሰቦች ፍጽምና የጎደላቸው እና ለጠላት ጥቃቶች የተጋለጡ መሆናቸውን አውቆ፣ እግዚአብሔር ውድ ልጁን ቤዛችን እንዲሆን እና ቤተሰባቻችንን እንዲፈውስ ልኳል። እንዲሁም የኋለኛውን ቀን ነቢያትን በአዋጅ ቤተሰቦችን ለመጠበቅ እና ለማፅናናት ልኳል። ነቢያትን የምንከተል እና እምነታችን በአዳኛችን ላይ ከሆነ፣ ምንም እንኳን ሟች ቤተሰቦች ለመለኮታዊነት ጉድለት ቢኖራቸውም፣ በምድርም ይሁን በሰማይም ለቤተሰቦች ተስፋ አለ።
ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
“ቤተሰብ ለፈጣሪ እቅድ ማዕከላዊ ነው።”
“ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ” በግልፅ ስለ ቤተሰቦች ነው። ነገር ግን በእኩል ደረጃ ስለ እግዚአብሔር የደህንነት ዕቅድ ነው። አዋጁን ለማጥናት አንዱ መንገድ ስለ ቅድመ ህይወት፣ የምድር ህይወት እና ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወታችን የሚያስተምረውን መፈለግ ነው። አዋጁን በዚህ መንገድ ስታጠኑ ምን ትማራላችሁ? ጋብቻ እና ቤተሰብ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ለምን አስፈላጊ እንደሆኑ እንድታውቁ እንዴት ይረዳችኋል?
በተጨማሪም ዳሊን ኤች. ኦክስ፣ “ዕቅዱ እና አዋጁ፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 28–31 ይመልከቱ።
“በቤተሰብ ህይወት ውስጥ ደስታ የሚገኘው ቤተሰብ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት በኩል ሲገነባ ነው።”
የቤተሰብ አዋጅን አንቀጽ ስድስት እና ሰባትን “በቤተሰብ ሕይወት ደስታን” እንደሚያስገኝንድፍ አስቡ። እነዚህን አንቀጾች በምታነቡበት ጊዜ “የስኬታማ ትዳሮች እና ቤተሰቦች” መሰረታዊ መርሆችን ለዩ። ከዚያም ለማጠናከር ስለምትፈልጉት የቤተሰብ ግንኙነት አስቡ። ምን ለማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል? በምታደርጉት ጥረት ላይ አዳኝን እንዴት ታሳትፉታላችሁ?
እንዲሁም ሪቻርድ ጄ. ሜይንስ፣ “ክርስቶስን ያማከለ ቤት ማቋቋም፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2011 (እ.አ.አ.)፣ 37–39፤ “ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ነገር፣” ቪድዮ፣ ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ፥።
ቤተሰቦቼን በምንከባከብበት “በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂ እሆናለሁ።”
የቤተሰብ አዋጁ የሰማይ አባት ምክሩን ለሚከተሉት ቃል የገባቸውን አስደናቂ በረከቶች ያካትታል። እንዲሁም ለማይከተሉትም ጠንካራ ማስጠንቀቂያዎችን ያካትታል። ያገኛችሁትን በረከቶች እና ማስጠንቀቂያዎች ዝርዝር ለመመዝገብ አስቡ።
በአዋጁ ውስጥ በተሰጠው የእግዚአብሔር ምክር ላይ እንዴት እርምጃ እየወሰዳችሁ ናችሁ? ዛሬ በእግዚአብሔር ፊት ብትቆሙ፣ ስለቤተሰባችሁ ግንኙነት ከእሱ ጋር ለመወያየት እርገጠኞች የምትሆኑት ምንድን ነው? ምን ማሻሻል ያስፈልጋችኋል?
በተጨማሪም አልማ 5፥15–22፤ ትምህርትና ቃልኪዳኖች 42፥22–25፣ 33፤ 93፥39–44 ይመልከቱ።
የቤተሰቤ ሁኔታ ከታሰበው በታች ከሆነ ቃል የተገቡትን በረከቶች ማግኘት እችላለሁን?
ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን እንዳስተማሩት፥ “ከጋብቻ እና ከቤተሰብ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መሠረታዊ እውነቶች ማወጅ ትክክለኛው መንገድ በአሁን ጊዜ ተጨባጭ ላልሆነላቸው የሰጡትን መስዋእት እና አሁን የሌለ ስኬትን መዘንጋት ወይም መቀነስ አይደለም። … ሁሉም ሰው ስጦታዎች አሉት፤ ሁሉም ተሰጥኦ አለው፤ በእያንዳንዱ ትውልድ ውስጥ ለሚከናወነው መለኮታዊ እቅድ አፈፃፀም አስተዋፅኦ ማበርከት ይችላል። ብዙ መልካም እና አስፈላጊ ነገር—እንዲሁም አልፎ አልፎም እንኳ ለአሁን አስፈላጊ የሆነው ሁሉ—ከተገቢው ሁኔታ ባነሰ ሁኔታ ውስጥ ሊከናወን ይቻላል። … የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ወደ እርሱ ለሚዞሩት ላጡት እና ለተሰቃዩበት ሙሉ ክፍያ እንደሚሰጥ በልበ ሙሉነት እንመሰክራለን። አብ ለልጆቹ እንዲወርሱ ካሰበው በታች ለመቀበል አስቀድሞ የተወሰነበት ማንም የለም” [“ለምን ትዳር፣ ለምን ቤተሰብ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 52]።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
“ጾታም አስፈላጊ የሆነ የግለሰብ ቅድመ ምድራዊ፣ ሟች፣ እና ዘለአለማዊ መለያ እና አላማ እና ባህሪ ነው።”ከቤተሰብዎ ጋር ከጾታ ጋር በተዛመደ እና ስለ ተመሳሳይ ጾታ ስበት መሠረተ ትምህርቶችን መወያየት ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት፣ የሚከተሉት ምንጮች ሊረዷችሁ ይችላሉ፥ ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “እውነት እና ዕቅዱ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 25–28፤ የወንጌል ርዕሶች፤ “የተመሳሳይ ጾታ ስበት፣ ” topics.ChurchofJesusChrist.org።
-
“ መለኮታዊ የደስታ እቅድ”ቤተሰቦች በሰማይ አባት እቅድ ውስጥ አስፈላጊነታቸውን ለቤተሰባችሁ ለማስገንዘብ፣ ቅድመ ህይወት፣ ሟች ህይወት፣ ከሞት በኋላ ያለ ህይወት ብላችሁ በወረቀት ሶስት ክፍሎች ላይ መጻፍ ትችላላችሁ። አዋጁን አብራችሁ መርምሩ፣ እና ስለእያንዳንዳንዱ የእግዚአብሔር እቅድ አካላት ምን እንደተማራችሁ በወረቀቱ ላይ ጻፉ። ቤተሰቦች ለእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው?
-
“ቤተሰቦች ለዘለዓለም አንድ መሆን [ይችላሉ]።”“የደህንነት ዕቅድ—አሁንም ቤተሰብ ነን” የሚለውን ቪድዮ (ChurchofJesusChrist.org) ለመመልከት ትችላላችሁ። በቪዲዮው ውስጥ ወጣቱ የተገነዘበውን እና እምነት እንዲኖረው የረዳውን እውነት የቤተሰብ አዋጁ ላይ ይፈልጉ።
-
“በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ ደስታ።”“[በቤተሰባችሁ] ሕይወት ውስጥ [የበለጠ] ደስታን” እንዴት ማግኘት እንደምትችሉ ለመወያየት፣ ለምሳሌ ስለቤተሰብ አንድ ላይ “ቤት በምድር ላይ ገነት ሊሆን ይችላል” (መዝሙር፣ ቁጥር 298) የሚለውን መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ። ከመዝሙር እና ከቤተሰብ አዋጅ ምን ለቤተሰቦቻችን የበለጠ ደስታን እንደሚያመጣ እንማራለን? ቤተሰባችን “በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ላይ የተመሠረተ” መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? በዚህ ሳምንት ልትተገብሩት ስለምትፈልጉት አንድ ትምህርት መምረጥ አስቡ።
-
“እንደ የኅብረተሰቡ መሠረታዊ ክፍል ቤተሰቦችን አጠናክሩ።”ሰይጣን በዓለም ያሉትን ቤተሰቦች የሚያዳክመው እንዴት ነው? ቤተሰቦችን ለማጠንከር የበኩላችንን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ሀሳቦችን ለማግኘት፣ የእህት ቦኒ ኤል. ኦስካርሰን መልዕክትን “የቤተሰብ አዋጅ ተከላካዮች” [ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 14–17] ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት ይህን የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፥ “ቤት በምድር ገነት ሊሆን ይችላል፣” መዝሙር፣ ቁጥር 298።