በእምነት አንቀጽ ውስጥ ያሉት ትምህርቶችና መርሆች
እያንዳንዱ የእምነት አንቀጾች የተለየ ዋጋ በወንጌል መረዳታችን ላይ ይጨምሩልናል።
በዚ የክህነት የጠቅላላ ጉባኤ እንድናገር ስራዉ ሲሰጠኝ ስለ አንድ የህጻናት ክፍል መምህር አሰብኩ።የሷ ታላቁ ፍላጎት አኛን ክህነትን ለመቀበል ብቁ ማድረግ ነበር።ከ ህጻናት ክፍል ለመመረቅ በሚያበቁን መስፈርቶች ላይ የአስራሁለቱን ሃዋሪያት አባላት ሰም እና የእምነት መሰረቶችን እንድንሸመድድ በማድረግ አዘጋጀችን።ቃል ኪዳንም ገባችላን አስራሶስቱንም የእምነት መሰረቶች በቃላችን የምናዉቅ ከሆነ የፈለግንበት ቦታ በኛ ምርጫ እንደምትወስደን።
እኛም በሎጋን ግደብ መግቢያ አካባቢ ባለዉ ድንጋያማ ቦታ ላይ ወሰንን።ለጥ ያለ ሃት ዶግ እና ማርሽ ሜሎ ለማብሰል የሚሆን የ ማብሰያ ቦታ ነበር።ቦታዉን ሰንመርጥ ግን፤ትላቅ የሆነችዉን እና የስፖርተኛ አቅዋም የሌላትን መምህራችንን ከ ግምት ዉስጥ አልከተትንም ነበር።በደንብ ብናስብበት ኖሮ ጉዞውን ለማድረግ እንደሚያስቸግራት ይመጣልን ነበር።ቃልዋ ግን አጥንቷ ነበር እናም ተከተለችን።
በመጀመሪያ ትንሹን ተራራ ወጣን።በኛ ግዜ ምንም አይነት መንገድ የሚያሳጣ የአኤሌትሪክ መስመር አልነበረም።በትንሽ እርዳታ መምህራችን ተራራዉን ወጣች።አንዴ ከወጣን ብህዋላ የ “ኤሊ ጀርባ” ብለም በሰየምነዉ ቦታ ደረስን።
ከደረስን ብኋላ መምህራችን ትንፍሽዋን እስከምተሰበስብ ተንሽ ግዜ ወሰደባት።ምግባችንን አዘጋጅተን እንደተቀመጥን የመጨረሻዉን ትምህርታችንን ለማስተማር ተዘጋጅታ ነበር።በህጻናት ክፍል እኛን ለ ሁለት አመት ሰታስተመር ምን ያህል እንደተደሰተች ነገረችን።የ እምነት መሰረቶቹን ምን ያህል እንደተጠበብንባቸዉ አሞገሰችን።ከዛም የእምነት መሰረቶቹን በቻ ማዉቅ በዉስጡ የያዙትን ትምህርቶች እና መርህዎች ካልተረዳን ብዙ ቃላቶችን ከማወቅ የዘለለ ትርጉም እንደሌለዉ ተናገረች።በያንዳንዱ የእምነት መሰረቶች ውስጥ ያሉትን የወንጌል ትምህርቶችን እንድናጠና አበረታታችን።በ እምነት መሰረቶቹ ዉስጥ ያሉት ትምህርቶች በ ክፍሎች እንደሚከፋፈሉ አብራራችልን።
፩. አምላክ እና የክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ ትምህርት
በመጀመሪያዉ የእምነት አንቀጽ ዉስጥ የ እግዚአብሄር ሶስት አካላት እንዳሉት እንማራለን፡ እግዚአብሄር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እና መንፈስ ቅዱስ።
ሁለተኛዉ የእምነት አንቀጽ ደግሞ በምድር ላይ ለድርጊታችን ሃላፊነት እንዳለብን ያሰተምረናል።
ሶስተኛዉ ለሰማይ አባት ልጆች ደህንነት የአዳኝ ተለኮ ራእይ ይሰጣል።
አራተኛዉ መሰረታዊ መርህዎችን እና ስነስራቶችን ያሰተምራል።
የመምህራችን ትምህርት ሃይል በወንጌል ጥናት ጥቅም ላይ ያደረገችዉ አትክሮት የመነሳሳት ምንጭ ሆኖልኛል።ቅዱሳት መጽሃፍት የምንቀበለዉን እዉቀት የእውነተኛነት መሰረት ለመፍረድ በምሪት ያስቀምጣሉ፣እዉነትም የሁኑ ውሸት።እዉነተኛ ትምህርት ከእግዚአብሄር ይመጣል፣የሁሉም የእዉነታ ምንጭ እና መሰረት።የእዉነተኛ ትምህርት ትምህርት እና ሃሳብ በጌታ እና በአዳኝ ወንጌል ውስጥ ይገኛሉ።የውሽት ትምህርት ከሰይጣን ይመጣል፣የውሸቶች አባት ከሆነዉ።የሱ ፍላጎት እዉነታን መቀየር እና ማበላሸት ነው።እኛን በማታለል ወደ ሰማዩ ቤታችን የምናደርገዉን ጉዞ እንዲሰናከል ያደርጋል።
ቅዱሳት መጻሃፍት የዉሸት ትምህርቶችን እንዴት እንደምናስወግድ ያስተምሩናል።ለምሳሌ፣ጳውሎስ ለ ጢምቲዎስ እንደጻፈዉ፡
“የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ፣
“ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል”(2 ጢማቴዎስ 3:16–17)።
ይህ ትምህርት ለቤተክርስቲያን ነው ልክ ባትሪ ለ ሞባይል ቀፎ እንደሆነዉ።ከ ሞባይላቹ ዉስጥ ቀፎዉን ስታወጡ ጥቅም አይኖረዉም።ትክክለኛ ትምህርት የማይሰጥበት ቤተክርስትያን ደግሞ በተመሳሳይ ሁኔታ ዋጋ አይኖረዉም።ወደሰማዩ አባታችን እና ወደ ዘላለማዊ ቤታችን አይመራንም።
፪. የክህነት ስነስራት እና መዋቅር
ሰለ ክርስቶስ መሰረታዊ ትምህርቶችን ስንረዳ፣ አምስተኛው እና ስድስተኛው የእምነት መሰረቶች ስለክህነት መዋቅር እና ስነስራቶች ያስተምሩናል።በጌታ ምሪት ዮሴፍ ስሚዝ በክህነት ስልጣን አማካኝነት የጌታን ቤተክርስቲያን አቋቋመ-የ እግዚአብሄር ሃይል።የኋለኛዉ ቀን ቅዱሳን የ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ክርስቶስ በምድር በነበረበት ወቅት አቋቁሞት እንደነበረዉ አይነት ነው።
ምን አይነት የክብር ቀን ነበር ለ ዮሴፍ ስሚዝ እና ለ አሊቨር ኩዋድሪ ግንቦት 1829 በጫካዉስጥ ሄደዉ ሰለ ጥምቀት የጸለዩበት በጸሃፈ ሞርሞንን እየተረጎሙ ባሉበት ሰአት።በ 1800 መጀመሪያ በተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ስለ ጥምቀት የተለያዩ ትምህርቶች ነበሩ ዮሴፍ እና አሊቨር ሁሉም እዉነት እንደማይሆኑ አወቁ።ስለ ትክክለኛ የጥምቀት ስነስራት እና የማጥመቅ ስልጣን ስላለዉ ለማወቅ ፈለጉ።
ለጸሎታቸዉ ምላች መጥምቁ ዩሃንስ ተገልጦላቸዉ።አንድ በአንድ እጁን ጭኖ በጭንቅላታቸዉ ላይ በዚ ቃል የማጥመቅ ስልጣንን ሰጣቸው “በእናንተ ላይ ውድ አገልጋዮች በ መሲው ስም የ አሮናዊ ክህነትን እጭናለዉ” (ት እና ቃ 13፡1)
በአለም ታሪክ ምን አይነት ድንቅ ቀን ነበር! ክህነት ዳግመኛ ወደምድር ተመለሰ።
ክህነትን ስንቀበል በእግዚአብሄር ስም ለመከወን እና ወደ እዉነታ እና ጽድቅና ይመራናል።ይህ ስልጣን የጻድቅ የሃይል ምንጭ እና ለእግዚአብሄር ልጆች ጥቅም የመጣ ነው።የ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ከመቋቋሙ በፊት ክህነት መመለስ አስፈላጊ ነበር። ይህንን መሰረታዊ ትምህርት ነው ከእምነት አንቀጽ አምስት እና ሰድስት የምንማረዉ።
፫. ዘላለማዊ ምንጮች በሞችነት ጉዞ
ቀጣዮቹ ሶስት የእምነት አንቀጾች-ሰባት፣ስምንት እና ዘጠኝ -በዚህ በሟችነት ጉዟችን የሚጠቅሙንን ጥቅሞችን ያስቀምጣል።መንፈሳዊ ስጦታዎች ተሰተዉናል የጌታን ትምህርቶች ስንከተል ከክፋት እንዲጠብቁን።ቅዱሳን መጻህፍት ሌላኛው ምሪቶች ናቸዉ-የእግዚአብሄርን ቃል አጠንክረን የምንይዝ ከሆነ ወደዘላለማዊ ህይወት ወደሚወሰደን መንገድ ላይ እንቆያለን።
ዘጠነኛው የእምነት አንቀጽ እግዚአብሄር እንደሚገልጥ፣እንደገለጥ እና ወደፊትም እንደሚገልጥ ብዙ ታላቅ እና ጠቃሚ እዉነታዎችን ለ ነብዮቹ ያስተምረናል።የተረጋጋዉን እና ትንሹን የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ ከመስማት በተጨማሪ ሌላኛው የምሪት ምንጭ የኛ የቤተክርስቲያን መሪዎች፣የተመረጡት፣የተጠሩት እና በሚያስተምሩት ትምርት ህይወታችንን እንዲባርኩ በተደረጉት ነው።
፬. የአባላት ሚስኖያዉያን
አስረኛዉ፣አስራደኛዉ እና አስራሁለተኛዉ የእምነት አንቀጽ ሰለ ምስዮናዊነት ሰራ ይመራናል።ለዳግመኛ ለአዳኝ ምጻት የእስራአኤል ልጆች መሰብሰብን እንማራለን።ወንዶች እና ሴቶች የራሳቸዉ ተወካዮች እንደሆኑ እና የእግዚአብሄርን ቃል በራሳቸዉ አ እምሮ በመጠቀም የመቀበል ወየም ያለመቀበል መብት እንዳላቸዉ እንማራለን።በስተመጨረሻም ወንጌልም በአለም በ አራቱም መአዘናት ስናዛምት የያንዳንዱን ሃገራት መንግስት እንድናከብር እንማራለን።በእዉነቱ የያንዳንዱን ሃገር ህግ በመታዘዝ፣በማክበር እና በመደገፍ እናምናለን።
፭. የሚያነሳሳ ጸባይ
አስራ ሶስተኛዉ የእምነት አንቀጽ ህይወታችንን እንዴት እንደምንመራ እና እራሳችንን እንደምናቀርብ ያሳያል። እንዲ ይነበባል “በታማኝነት፣በእውነተኛነት፣በንጽህና እና ለሁሉም መልካም ነገሮችን በመሰራት እናምናለን፡ሁሉንም እናምናለን፣ሁሉንም ተሰፋ እናደርጋለን፣ብዙ ነገሮችን በጸናት አልፈናል ወደፊትም እንዲሁ።ጥሩ እና መልካም ነገሮች ካሉ እኛ እኚህን እንሻለን።
ሁላችንም እነዚህን ባህሪያት በዚ ተምሳሌነት እንያዛቸው።በእምነት አንቀጽ ዉስጥ ያሉት እዉነታዎች ልክ እንደ ስልክ ቀፎ እርስ በእርሳቸዉ የተደጋገፉ ናቸው።
የእኔ መምህር የመንግስቱን ትምህርት እንዳጠና በዉስጤ ውሳኔን አኖረች።በዚ የእምነት አንቀጽ ዉስጥ ያለዉን ወስጣዊ ትርጉም እንድሻ አስተማረችኝ።የህን የተቀደሰ እዉነታ ለማወቅ የምሻ ከሆነ የማገኘዉ እዉቀት ህይወቴን የተሻለ እንደሚያደርገዉ ቃል ገባችልኝ እናም እመሰክርላችህዋለዉ ለዉጦታል።
ከመምህሬ ምርጥ ትምህርት ብኋላ ካቀድነዉ በላይ እንደቆየን ታወቀን።ምሽቱ ወደ ማብቂያዉ እየቀረበ ነበር ከዛም ችግር እንዳለ ተረዳን።
መደዚ ልዩ ቦታ ለመድረስ መምህራችን ታግላለች፣መመለሱ ደግሞ ሌላ ችግር መሆኑ እዉን ሆነ።መመለሱ አስቸጋሪ ነበር ለኛ በሷ እደሜ ላለ ደግሞ በጣም አሰቸጋሪ።
ተራራዉን ለመዉረድ ስናግዛት፣ሁለት ፖሊሶች መጡ።የ ህጻናት ክፍሉ ፕሬዘዳንት የጠፋን መስሎት እኛን እንዲያገኙ ልኳቸዉ ነበር።ሁኔታዎችሁ እና የተማርናቸዉ ትምህርቶች በህይወታችን የማይረሱ ልምዶች አደረጉት።
እናንተ ወጣቶች-ይህን ብሩ አ እምሮአችሁን የ እምነት አንቀጾችን እና የሚያስተምሩትን ትምህርት ለመማር እንድትጠቀሙበት እጋብዛችኋለሁ።በቤተክርስቲያን ዉስጥ ጠቃሚ የትምህርት ቃላቶች ናቸዉ።የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለማጥናት የምትጠቀሟቸዉ ከሆነ የተመለሰዉን እዉነታ ለአለም ለመመስከር እንድትዘጋጁ ያደርጋችኋል።በቀላል፣ቀጥተኛ እና ልባዊ በሆነ መንገድ የኋለኛዉ ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በመሆናቹ የያዛችሁትን እምነት እንድትገልጹ ያደርጋችኋል።
ስለአስራ ሶስቱ የእምነት አንቀጾች እውነትነት ምስክሬን የምጨምረውም በጌታችን እና መዳኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣አሜን።