2010–2019 (እ.አ.አ)
ሌሎች አምላኮች
ኦክተውበር 2013


16:44

ሌላ እግዚአብሔር የለም

ከእግዚአብሄር ቅድምያ ተቀዳምነት ላለው ወይም ጣኦትን ጎንበስ በማለት እናገለግላለን?

አሥሩ ትእዛዛት ለክርስትያን እና አይሁዳን እምነት መስረታዊ ነው። በነቢይ ሙሴ አማካኝነት እእግዚአብሔር ለኢስራኤል ልጆች ሰጥተዋል። የመጀመሪያ ሁለቱ ትእዛዝ እንዴት መስገድ እንዳለብን ያሳያል። በመጀመሪያ ጌታ ይህን አዘዘ።(ዘጸአት 20:3) ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። ከዘመናት በኃላም መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም እንዲህ አለው። ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።(ማቴዎስ 22:36–37)

ከአሥሩ ሁለተኛው ትእዛዝ ሌላ እእግዚአብሔር እንደማይኖረን አቅጣጫን በማስረዳት እንደ እእግዚአብሔር ልጅነታችን በህይወታችን የትኛው የመጨረሻተቀዳሚነት እንዳለው ይለያል። በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።(ዘጸአት 20:4) ትእዛዙም በመቀጠል አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ ይህ የአካል ጣኦትን የሚከለክል ከማንኛውም ጊዜ የበለጠ መሰረታዊ ተቀዳሚነት ያለውን ይስረዳል።(ዘጸአት 20:5) ጄሆቫም አስረዳ፣ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።(ዘጸአት 20:5–6) መቅናት የሚለው ትርጉም የሚያነቃቃ ነው። በህብራዊያን መነሻ ትርጉም የራስ ስሜት ምድረግ እና የጥልቀት ስሜት ማለት ነው። (Exodus 20:5, footnote b) ሌሎች እእግዚአብሔር ስንሰግድ እእግዚአብሔርን እናስቀይማለን።1

፩.

በዘመናችን የሀይማቶት ሰው እንኳ ቢሆን ከእግዚአብሔር ቅድሚያ ለየትኛው ነው መስገድ ወይም ማገልገል ያለብን? በአለም የጋራ የሆነውን ይህን አስተውሉ፤

  • ባህላዊ እና የቤተሰብ ልምዶች

  • ሌሎችን ያለማስቀየም

  • ለሙያ የመነሳሳት ስሜት

  • አለማዊ ሀብት

  • የመዝናኛ ክትትሎች

  • ዝና፣ ሀይል እና ክብር

እነኝህ ምሳሌዎች እኛን የማይመለከተን ከሆነ ምናልባት ሌሎችን እንድምመለከት ሀሳብ መስጠት እንችላለን። መሪሁ ከግላዊ ምሳሌዎች የበለጠ ጠቃሚ ነው። ይህ መሪህ ሌላ ቀደምትነት መኖራችን አይደለም። በሁለተኛው ትእዛዝ የቀረበው ጥያቄ የመጨረሻ ቀደምትነታችን ምንድነው? ተቀዳምነት ላለው ጎንበስ በማለት ማገልገል ወይም ከእእግዚአብሔር ቅድምያ ጣኦትን መምለክ ነው? የሚትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ጠብቁ ብሎ ያስተማረን አዳኝ ረስተናል? ከሆነ ተቀዳምነት ያለው በመንፍሳዊ ደንታ ቢስነት ተገልብጠዋል።(ዮሀንስ 14:15) በዘመናችን የስድነት ፍላጎት የተለመደ ነው።

፪.

ለኃላኛው ቀን ቅዱሳን የእግዚአብሔር ትእዛዝ እእግዚአብሔር ለልጆቹ ካለው የደህንነት ዕቅድ ጋር የሚለያዩ አይደለም። ይህም ዕቅድ አንዳንድ ጊዜ ታላቁ የደስታ ዕቅድ ይባላል። ይህም እንደ እእግዚአብሔር ልጆች መነሻና(አልማ 42:8) መድረሻችን እና ከየት እንድመጣን፣ የት እንደምንሄን ያስረዳል። የፍጥረትን አላማ እና የሟችነትን ሁነታ እናም የእእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጭምር ያስረዳል። እናም አዳኝ ለምን እንድምያስፈልገን እና የሟችነት ሚና እና ዘላለማዊ ቤተሰብን ያስረዳል። እኛ የኃላኛው ቀን ቅዱሳን ይህ እውቀት የተሰጣን ብዚህ እቅድ ቀድምትነት ያለውን ካልመሰረትን ሌላ እእግዚአብሔር በማገልገል አደጋ ላይ እንወድቃለን።

እግዚአቤር ለልጆቹ ያለውን እቅድ ማወቅ ለኃላኛው ቀን ቅዱሳኖች ስለ ጋብቻና ቤተስብ ልዩ ገፅታን ይሰጣል። ቤበተሰብ ላይ ትኩረት የምንሰጥ ቤተክርስትያን በመባል በትክክል ታውቀናል። መንፈሳዊ ትምህርታችን የሚጀምረው በሰማይ ወላጆች ነው። ከፍተኛው ፍላጎታችን ሙሉ የሆነ ዘላለማዊ ህይወት ለማግኘት ነው። ይህም የሚገኘው በቤተሰብ ግንኙነት መሆኑን እናውቃለን። የእእግዚአብሔር እቅድን ለሟሟላት በወንድና በሴት መሀከል ያለው ጋብቻ አስፈላጊ እንደሆነ እናውቃለን። ይህ ጋብቻ ብቻ ነው አግባብ ያለው በምድር መውለድን እና የቤተሰብ አባሎችን ለዘላለማዊ ህይወት ልያዘጋጅ የሚችለው። ጋብቻ የመውለድ እና ልጆችን የማሳደግ የእእግዚአብሔር እቅድ አካል መሆኑ እንመለከታለን። ይህንንም እንድናደርግ ቅዱስ የሆነ የሥራ እድል ተሰቶናል። የምድርና ሰማይ ሀብታችን ልጆቻችን እና የልጅ ልጅ ዘራችን መሁኑን እናምናለን።

፫.

የቤተስብ ዘላለማዊ ሥራ በመረዳታችን ምክንያት በታሪካዊ ባህል ክርስትያን እና አይሁዳ በሆኑት ብዙ ምዕራባዊያን ህዝቦች የልደት ቁጥር ጎልቶ ማሽቆልቆል ያሳዝናል።

  • አሜሪካ አሁን በታሪክ አነስተኛ የውልደት መጠን አለው።,2 በብዙ አውሮፓ እና ያደጉት ሀገሮች የውልደት መጠን ከሚፈለገው በታች ነው።.3 ይህ የባህል መትረፍን እና ህዝቦችን ያስፈራል።

  • በአሜሪካ የወጣት ጎልማሶች ዕድሜ ከ18 እስከ 29 ዓመት በ1960 ያገቡት አሁን በ2010 ዓ/ም ሀያ ከመቶ ዝቅ ብለዋል።4 የመጀመሪያ ጋብቻ አሁን በታሪክ ከፍተኛ ደርጃ ላይ ደርሶ ይገኛል። ለሴቶች 26 ዓመት፣ ለወንዶች 29 ዓመት ነው።5

  • በብዙ ሀገሮችና (1)ባህል የቤተስብ ባህላዊ ጋብቻ እናት፣ አባት እና ልጆች ከልማድ ለየት እየሆነ መጥተዋል። (2)ከጋብቻ ይልቅ የሥራ ሙያ ክትትል እና ልጆችን የመውለድ ምርጫ የብዙ ወጣት ሴቶች እየጨመረ በመሄድ (3)የአባቶች አስፈላጊ ነገር ሥራ መረዳት እየቀነሰ ሄደዋል።

በዚህ በምያሳስበን አዝማምያ መሀከል እያለን የእእግዚአብሔር እቅድ ለሁሉም ልጆቹ መሆኑን እንገነዘባለን።6 እናም እእግዚአብሔር በየትኛውም ቦታ ሁሉንም ልጆቹን ይወዳል። የመጀመሪያው ምዕራፍ መፅሀፈ ሞርሞን እንደምገልፀው የእግዚአብሔር ኃይል፣ ቸርነትህና ምህረትህ በምድር ባሉ ፍጡራን ሁሉ ላይ ነው፤በኃላም ምዕራፉ እንድምገልፀው ደህንነቱን ለሰዎች ሁሉ በነፃ ሰጥቶአል።(1 ኔፊ 1:14) ሁሉም ሰው እንደሌላው ታድሏል፤ እናም ማንም አልተከለከለም።(2 ኔፊ 26:27–28) ቅዱስ መጽስሀፍ እንድምያስተምረው ለሁሉም ሰዎች ለሌጋሽነት እና ርህራሄ እንድኖረን ሀላፍነት አለብን (1 ተሰሌንቆ 3:12; 1 ዮሀንስ 3:17; ት. እና ቃ. 121:45)።

፬.

የሁሉንም ሰዎች ሀይማኖት እምነት ክብር መስጠት ይኖርብናል፤ ምንም እንኳ ብዛት ያላቸው በእግዚአብሔር የማያምኑትን ጭምር። እእግዚአብሔር በሰጣቸው የምርጫ ኃይል ብዙዎቹ ከኛ እምነት ተቃራኒ ናቸው። ነገር ግን ሌሎችም የሀይማኖታችን እምነት በእኩል ክብር መስጠት እንዳለባቸው ምኞታችን ነው። እምነታችን ለአንዳንድ ልዩ ምርጫዎችና ባህሪይ ከነርሱ የበለጠ እንደምያስገድደን መረዳት አለባችሁ። ለምሳሌ ለደህንነቱ እቅድ መሰረታዊ አካል እእግዚአብሔር የግብረ ሥጋ ግንኙነት በተጋቡ ባልና ሚስት መካከል መሆን እንዳለበት ዘላለማዊ ደንብ መመስረቱን እናምናለን።

ነፍስን የመፍጠር ሀይል እእግዚአብሔር ለልጆቹ ከሰጠው ስጦታውች የበለጠ የተሞገስ ሀይል አለው። እእግዚአብሔር በመጀመሪያ ትእዛዝ ለአዳምና ሔዋን (ዘፍጥረት 1:28) እንድጠቀሙ ግዴታ ሰጣቸው (ዘጸአት 20:14; 1 ተሰሌንቆ 4:3)። ነገር ግን አለአግባብ አለመጠቀማቸው ሌላ አስፈላጊ የሆነ ትእዛዝ ተሰጥቶ ነበር። በንፅህና ህግ ላይ ትኩረት የሚንሰጠው የእግዚአብሔርን እቅድ ለሟሟላት ነፍስን የመፍጠር ሀይልመረዳታችን ላይ ተረድተዋል። ከጋብቻ ውጭ በወንድና ሴት መሀከል ንፍስን የመፍጠር ሀይል በየትኛውም ደረጃ ሀጢያትና እእግዚአብሔር ለልጆቹ ላለው ዘላለማዊ ህይወት እቅድ ተቃራኒ ነው።

የንፅህና ህግ አስፈላጊነት አያያዛችን የጋብቻ ምሳሌ በአዳምና ህዋን የተመሰረተ እንደሆነ እና በእግዚአብሔር ደንብ ወንድና ሴት መሀከል ያለው ነፍስን የመፍጠር ግንኙነት ለዘመናት እየቀጠለ በመሆኑ ነው። እናም ልጆቹን ለመንከባከብ ነው። ከሌላ ሀይማኖት ወይም ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ያላቸው ብዙ ሰዎች የጋብችን ተፈትሮአዊ አስፈላጊነት ከኛ ጋር ይስማማሉ፣ አንዳዶቹ በሀይማኖት መሰረታዊ ህግጋት እና ለሎችለህዝብ የተሻለ መሆኑ በማሰብ ነው።

እእግዚአብሔር ለልጆቹ ያለውን እቅድ መረዳታችን ከጋብቻ ውጭ ስለተወለዱት ልጆች7 ብዛት ለምን ጭንቀት እንደደረስብን ይስረዳል። በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ 41% የተወለዱ ልጆች እና ያለጋብቻ አንድ ላይ የሚኖሩ ባለፉት ግማሽ ዘመን በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው8። ባለፉት 50 አመታት ሳይጋቡ አብሮ መኖር በጣም አነተኛ ነበር። አሁን ሳይጋቡ አብሮ መኖር ወደ 60% እይበለጠ ነው።9 ይህም በተለይም በወጣቶች ዘንድ ተቀባይነት አለው። በቅርቡ ጥናት እንድምያስረዳው 50% በተለይም ከ13–19 አመት እድሜ ያለቸው ከጋብቻ ውጭ የተወልዱ መሆናቸውን ያስረዳል።10

፭.

ብዙ የፖለቲካ እና ሚድያ ግፍት ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ጋር ተቃራኒ የሆነውን ስለ ግብረገብነት ባህሪይን የጋብቻ አላማና ልጅ መውለድን ለወለወጥ ግፍት ላይ ናቸው። ይህም ግፍት በአንዳንድ ግዛት እና ሀገር አንድ አይነት ፆታዎች እንድጋቡ አድርገዋል። ሌላው ግፍት ፆታን ግራ ያጋባል ወይም የእእግዚአብሔር ታላቅ የደስታ እቅድን ለሟሟላት አስፈላጊ የሆነውን በወንዶች እና ሴትች መካከል ያለውን ልዩነት ተመሳሳይ ያደርጋል።

የእእግዚአብሔር እቅድ እና ህግጋት መረዳታችን የዝህን አይነት ባህሪይን ቻላ አለማለት ወይም ይህን የምፈቅድ ህግ ትክክል ነው ማለት ዘላለማዊ አመለካከትን ይሰጠናል። ሌሎች ድርጅቶች ደንቦችን እና ህግጋቶችን እንደምለውጡ የኛ ደንብ በእእግዚአብሔር እውነታ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ልለወጥ አይችልም።

የአሥራ ሁለተኛው የእምነት አንቀጾችን ለመንግሥት እና ህግ ታዛዥ መሆን እንዳለብን ይገልፃል። ነገር ግን እእግዚአብሔር ግብረገባዊ ያለሆነ ያለውን የሰው ህግ ግብረገብ ነው ማለት አይችልም። ከፍተኛ ደርጃ የሆነው ለእግዚአብሔር አገልግሎት ፍቅር የሚያስፈልገው ለተለመደው ባህሪያችን ህጉን እንመለከታለን። ለምሳሌ እኛ ዝሙት አለመፈፀም በመልኮታዊ ትእዛዝ ሥር ነን። ምንም እንኳ ይህ በግዛት ወይም በሀገር በህግ ፍት ወንጄል ባይሆንም ዝሙት ከጋብቻ ውጭ መለኮታዊ ትእዛዝ ነው። በተመሳሳይም የአንድ አይነት ፆታ ጋብቻ ህግ የእግዚአብሔር የጋብቻ ህግን ወይም ትእዛዙን አይለውጥም። እኛ እእግዚአብሔርን ለመውደድ እና ተዛዙን ለመጠበቅ እናም ሌሎች ጣኦትችን ወይም በዘመናችን ጊዜና ቦታ ታዋቂ የሆኑትን እንኳ አለማምለክ በቃል ኪዳን ሥር ነን።

በዚህ ቁርጥ ሀሳብ አለመረዳት ምናልባትም ስሞታ፣አክራሪነት ወይም የአድሎት ስቃይ ልያጋጥመን ይችላል። ወይም የሀይማኖት ነፃነት ልምምድ ወረራ ልያጋጥመን ይችላል። ይህ ከሆነ መጀመሪያ ተቀዳሚ የሆነውን እእግዚአብሔርን መገልገል ማስታውስ አለብን። የቀድሞ ሰፋሪዎቻችን በፅናት እንዳሳዩን የግል ጋሪያችን ወደ ፍት መግፋት አለብን።

የፕሬዝዳንት ቶምስ ኤስ ሞንሰን ትምህርት ይህን ሁኔታ ይመለከታል። የዛሬ 27 አመት ጉባኤ ላይ ይህን በድፍረት ገልፀዋል፤ በሀሳብ ለማያይስማሙት እምብተንነት ለማሳየት ጉብዝና ይኑረን፣ ለመሪህ ለመቆምም ጉብዝና ይኑረን። የእግዚአብሔርን ማፅደቅ ፈገግታ ለምያመጣ እንጂ ለድርድር ጉብዝና አያስፈልግም። ጉብዝና ኗሪ ነው፣እናም በፍቃደንነት እንደ ወንድ መሞት ብቻ ሳይሆን አግባብ ባለው ቆራጥነት መሞት የሚማርክ ምግባር ነው። የሞራል ፈሪ የምያውቀውን ትክክለኛ የማያደርግ ነው ምክንያቱም ሌሎች ስለማያፀድቁ ወይም ስለምስቁበት ነው። ሁሉም ሰዎች ፍራቻ እንዳለባቸው አስታውሱ፣ ነገር ግን ፍራቻን በክብር የሚጋፈጡት ጉብዝናም አላቸው።11

የምድር ጊዜያዊ ችግሮች ታልቁን ትእዛዝ እና በፈጣሪ አምላካችን የተሰጠን ተቀዳሚነት እንዳንረሳ ያድርገን ዘንድ ፀሎቴ ነው። ሰዎችን ለማክበር ብለን በፍፁም ልባችን በአለማት ላይ ማድረግ የለብንም። እኛ ነን እእግዚአብሔር ለልጆቹ ያለውን እቅድ የምናውቅ፣ እኛ ቃል ኪዳን ያደርገነው ግልፅ የሆነ ሀላፍነት አለብን።( ት. እና ቃ. 121:35) ዘላለማዊ ህይወት ለሟሟላት የሚረዳን ጠቀሜታ ያለው ፍላጎታችን በፍፁም መርሳት የለብንም። በቀደምትነት ሌላ ጣኦት እንዳይኖረን ያስፈልጋል።12 ከእግዚአብሔር አባት እና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማገልገል ቅድሚያ የሚመጣ ነገር አይኖርም።

ይህን ቀደምትነት እንድንረዳ እግዛሄር ይርዳን ዘንድ እናም ይህንን በጥበባዊና ፍቅር መንገድ ስንከተል ሌሎችም እንድረዱን ዘንድ ፀሎቴ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ለምሳሌ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124:84 ተመልከቱ።

  2. See Joyce A. Martin and others, “Births: Final Data for 2011,” National Vital Statistics Reports, vol. 62, no. 1 (June 28, 2013), 4; Gloria Goodale, “Behind a Looming Baby Bust,” Christian Science Monitor Weekly, Feb. 4, 2013, 21, 23.

  3. See Population Reference Bureau, “2012 World Population Data Sheet,” www.prb.org/Publications/Datasheets/2012/world-population-data-sheet/data-sheet.aspx.

  4. See D’Vera Cohn and others, “Barely Half of U.S. Adults Are Married—a Record Low,” Pew Research Center, Social and Demographic Trends, Dec. 14, 2011, available at www.pewsocialtrends.org/2011/12/14/barely-half-of-u-s-adults-are-married-a-record-low; “Rash Retreat from Marriage,” Christian Science Monitor, Jan. 2 and 9, 2012, 34.

  5. U.S. Census Bureau, “Estimated Median Age at First Marriage, by Sex: 1890 to the Present,” available at www.census.gov/population/socdemo/hh-fam/ms2.xls.

  6. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “All Men Everywhere,” Ensign or Liahona, May 2006, 77–80 ተመልከቱ.

  7. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “The Great Plan of Happiness,” Ensign, Nov. 1993, 72–75 ተመልከቱ.

  8. Martin, “Births: Final Data for 2011,” 4 ተመልከቱ።

  9. The State of Our Unions: Marriage in America,2012 (2012), 76 ተመልከቱ።

  10. The State of Our Unions, 101, 102 ተመልከቱ።

  11. ተማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “Courage Counts,” Ensign, Nov. 1986, 41።

  12. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “Desire,” Ensign or Liahona, May 2011, 42–45።