2010–2019 (እ.አ.አ)
ለመፅናት ያለን ጥንካሬ
ኦክተውበር 2013


13:6

ለመፅናት ያለን ጥንካሬ

እስከመጨረሻ በጻድቅነት የመፅናት ችሎታችን ከምስካራችን ጥንካሬ እና ከተቀየርንበት ዝልቀት ጋር የተያያዘ ነው።

በጠዋ ስንነቃ፣ የህይወት ፈተናዎችን በየቀኑ ያጋጥሙናል። እነዚህ ፈተናዎች በተለያዩ ሁኔታዎች ይመጣሉ፥ የሰውነት ፈተና፣ የገንዘብ ችግር፣ የግንኙነት ችግር፣ የስሜት ፈተና፣ እናም የእምነት ትግል።

በዚህ ህይወት ለምናገኛቸው ፈተናዎች መፍትሄ ለማግኘት እና ለማሸነፍ እንችላለን፤ ነገር ግን፣ ሌሎችም ከዚህ ህይወት እስከምናልፍ ድረስ ለመረዳት የሚያስቸግሩና ለማሸነፍ የማይቻሉ ሊሆኑ ይችላሉ። መፍትሄ ለማግኘት የምንችላቸውን በጊዜው ስንጸናባቸው እናም መፍትሄ ለማግኘት በማንችልባቸውን በመፅናት ስንቀጥል፣ የምናገኛቸው መንፈሳዊ ጥንካሬዎች የህይወትፈተናዎች ሲያጋጥሙን በውጤታማነት ለመቋቋም እንድንችል እንደሚረዱን ማስታወሳችን አስፈላጊ ነው።

ወንድሞችና እህቶች፣ የምድር ፍጥረታችንን ነድፎ በእርሱ ፊት ለዘለአለም ህይወት ብቁ እንዲያደርጉን የሚያስፈልጉንን የግል ትምህርቶች ለመማር እንድንችል የሚያደርግ የሚወደን የሰማይ አባት አለን።

በጆሴፍ ስሚዝ ህይወት ላይ የነበረው ይህን እንደምሳሌ ያሳያል።፡ነቢዩ እና ጓደኞቹ በሊብቲ፣ ምዙሪ ለብዙ ወሮች ታስረው ነበር። በእስር ቤት እየተሰቃዩ እያሉ፣ ነቢዩ ጆሴፍ ጌታን በትሁት ጸሎት ቅዱሳን ከሚሰቃዩበት እረፍት እንዲያገኙ ለመነ። ጌታም ነቢዩ ጆሴፍን እና ሁላችንም የሚያጋጥሙን ፈተናዎች በውጤታማነት ከጸናንባቸው ለእኛ ጥቅም እንደሚሆኑ አስተማረ። የሚቀጥለውም ለጆሴፍ ልመና ጌታ መልስ የሰጠበት ነው፥

“ልጄ፣ ለነፍስህ ሰላም ይኑርህ፤ ጭንቀትህ እና ስቃይህ ለጥቂት ጊዜ ቢሆን ነው፤

“ከዚያም፣ በመልካም ይህን ብትጸና፣ እግዚአብሔርም ወደ ላይ ዘለአለማዊ ክብር።”1

የሰማይ አባት በህይወት የምንጓዝበት ማንነታችንን የሚፈትን እንዲሆን አድርጓል። መልካም እና ክፉ ተፅዕኖዎች ያጋጥሙናል እና ከዚያም የምንወስደውን መንገድ እንድንመርጥ ስጋሪ ነጻ ምርጫ ይሰጠናል። የጥንት ነቢይ ሳሙኤል እንዳስተማረው፣ “አሁንም እኔ በመንፈስ በተወሰድኩ ጊዜ ስላየኋቸው ነገሮች መናገሬን አቆማለሁ፤ እናም ምንም እንኳን ያየሁአቸው ነገሮች ሁሉ ባይፃፉም የፃፍኳቸው ነገሮች እውነት ናቸው”2

የሰማይ አባት ደግሞች በስጋዊነታችን ምክንያት ሁልጊዜ ትክክለኛ ወይም ጻድቅ ምርጫዎችን እንደማንሰራ ያውቃል። ፍጹም ስላልሆንን እና ስህተት ስለምንሰራ፣ ወደ እርሱ ለመመለስ እርዳታ ያስፈልገናል። የሚያስፈልገው እርዳታም የመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት፣ ሳሌ፣ እና በኃጥያት ክፍያ መስዋዕት በኩል ነው። የአዳኝ የኃጥያት ክፍያ መስዋዕት የወደፊት ደህንነታችን እና ከፍ ማለታችንን በንስሀ መግባት መሰረታዊ መርሆ በኩል ያረጋግጣል። በእውነት እና በልብ ንስሀ ከገባን፣ የኃጥያት ክፍያ ንጹህ እንድንሆን፣ ፍጥረታችንን እንድንቀይር፣ እና ፈተናዎቻችንን በስኬታማነት እንድንጸናባቸው ሊረዳን ይችላል።

መፅናት በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ የሚገኝ አስፈላጊ መሰረታዊ መርሆ ነው። ይህም አስፈላጊ የሚሆነው የወደፊት የዘለአለም ህይወታችን በጻድቅነት ለመፅናት ካለን ችሎታ ጋር የተያያዘ ነው።

2 ኔፊ 31ውስጥ ነቢዩ ኔፊ እንደሚያስተምረው፣ እኛ ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለውን አይነት የሚያድን የጥምቀት ስርዓትንን ከተቀበልን እና ከዚያም የመንፈ ቅዱስ ስጦታን ከተቀበልን በኋላ፣ “የክርስቶስን ቃል በመመገብ፣ እናም እስከመጨረሻው በመፅናት የምትቀጥሉ ከሆነ፣ እነሆ አብ እንዲህ ይላል፥ የዘለዓለም ህይወት ይኖራችኋል።”3

ስለዚህ፣ የዘለአለም ህይወት የሆነውን፣ ከሁሉም በላይ የሆኑ የሰማይ አባታችን በረከቶችን ለመቀበል፣ መፅናት የሚያስፈልገውን ስራ ማከናወን እና ከዚህ ጋር የተያያዘውን ቃል ኪዳን መጠበቅ አለብን። በሌላ አባባልም፣ በስኬታ መፅናት አለብን።

እስከመጨረሻ በጻድቅነት የመፅናት ችሎታችን ከምስካራችን ጥንካሬ እና ከተቀየርንበት ዝልቀት ጋር የተያያዘ ነው። ምስክርነታችን የጠነከሩ ሲሆኑ እናም ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በእውነትም የተቀየርን ከሆንን፣ ምር ጫዎቻችን በመንፈስ ቅዱስ የተነሳሱ፣ በክርስቶስ ላይ የተመሰረቱ፣ እና እስከመጨረሻ ለመፅናት ያለንን ፍላጎት የሚደግፉ ይሆናሉ። ምስክርነታችን ደካማ ከሆኑ እና የተቀየርንባቸው ዝልቅ ካልሆኑ፣ በአለም የሀሰት ባህል ተታለን ደካማ ምርጫዎች በማድረግ ላይ ለመውደቅ አደጋ ላይ እንገኛለን።

በሰውነት ለመፅናት ምንያህል ጥረት እንደሚያስፈልገን የሚያሳይ ምሳሌ ላሳያችሁ እፈልጋለሁ፣ ከዚያም በመንፈስ ለመፅናት ከሚያስፈልገው ጥረት ጋር አመዛዝነዋለሁ። ከሚስዮን በማገለግልበት ስመለስ፣ በካሊፎርኒያ ኮሌጅ ውስጥ በደንብ ለሚከበር አሰልጣኝ የቅርጫት ኳስ ለመጫወት እድል ነበረኝ። ይህም አሰልጣኝ የቅርጫፍ ኳስ መፎካከሪያ ጊዜ ከመምጣቱ በፊት የሚጫወቱት በሰውነት የተዘጋጁ እንዲሆኑ የሚፈልግ ነበር። የምንሰለጥንበት አንዱ ነገር ቢኖር በትምህርት ቤቱ አካባቢ በሚገኙ ኮርብታዎች ላይ በተወሰነ ሰዓት በመፈጸም የምንሮጥበት መመሪያ ነበረን። ከሚስዮን አገልግሎት ከተመለስኩኝበኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እዚህ ለመሮጥ የሞከርኩበት አስታውሳለሁ፥ የምሞት መስሎኝ ነበር።

አሰልጣኙ ሩጫውን ለመፈጸም ያለውን አላማ ለማሟላት ሁለት ሳምንት ወሰደብን። ሩጫውን ለመፈጸም ብቻ ሳይሆን ወደ መጨረሻው መስመር ለመድረስ በፍጥነት መሄዱ በጣም የሚያስደስት ስሜት ነበር።

የቅርጫት ኳስ በስኬት ለመጫወት፣ ሰውነት በመልካም ሁኔታ መሆን ነበረበት። ሰውነት በመልካም ሁኔታ እንዲሆን ለማስደረግ በአላማ የመስራት፣ ያለማቋረጥ መመኮር፣ እና ራስን መቆጣጠር የሆነ ዋጋ መከፈል ያስፈልገዋል። መንፈሳዊ ፅናት ደግሞም የሚከፈልበት ዋጋ አለው። ይህም እንደዚህ አይነት ዋጋ ነው፥ በአላማ መስራት፣ ያለማቋረጥ መመኮር፣ እና ራስን መቆጣጠር።

እንደ ሰውነታችሁ፣ ለመፅናት ምስክርነት በመልካም ሁኔታላይ መሆን አለበት። ምስክርነታችንን በመልካም ሁኔታ እንዴት ለመጠበቅ እንችላለን? የቅርጨት ኳስ ጨዋታን በቲቪ መመልከታችን ሰውነታችን የቅርጫት ኳስ ለመጫወት የሚያስችል ሁኔታ እንዲኖረን ለማድርገ አይችልም። በዚህ ተመሳሳይም፣ ምስክርነታችን መላክም ሁኔታ እንዲኖረው ማድረጊያው በቲቪ አጠቃላይ ጉባኤን መስማቱ አይደለም። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን መሰረታዊ መርሆ ማጥናትና መማር ያስፈልገናል፣ ከዚያም በሚቻለን ያህል በእነዚህ ለመኖር መጣር አለብን። የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙት የምንሆንበት ይህ ነው፣ እናም የሚጸና ምስክርነትን የምንገነባውን በዚህ ነው።

በህይወት ፈተና ሲያጋጥመን እና ፍላጎታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸባን ለመከተል ሲሆን፣ በመንፈስ መዘጋጀታችን በጣም አስፈላጊ ነው። በመንፈስ መዘጋጀት ማለት የመንፈስ ጥንካሪ አለን ማለት ነው---በመንፈስ መልካም ሁኔታ ላይ አለን። በመንፈስ በመልካም ሁኔታ ላይ ሆነን ሁልጊዜም ትክክለኛውን እንመርጣለን። በወንጌል የመኖር ፍላጎታችንና ችሎታችንም የማይነቃነቅ ይሆናል።የማይታውቀው ጸሀፊ እንዳለው፣ “ወንዙ አጥቦ ሊወስደው የማይችል አይነት ድንጋይ መሆን አለብን።”

በየቀኑ ፈተናዎች ስለሚመጡብን፣ በየቀኑ መንፈሳችንን ማጠናከሩ አስፈላጊ ነው። የመንፈሳዊ ጥንካሪ ስናገኝ፣ የአለም የሀሰት ባህሎች፣ እና የራሳችን የየቀኑ ግል ፈተናዎች፣ በጻድቅ ለመጽናት ያለንን ችሎታ ላይ ያለው ተፀዕ የቀነሰ ነው።

የመንፈስ ጥንካሬ ታላቅ ምሳሌዎች የሚገኙት ከቤተሰብ ታሪኮች ውስጥ፡ነው። ከቅድመ አያቶቻችን ብዙ ታሪኮች መካከል፣ የመፅናት መልካም ጸባይ የሆኑ ብዙ ምሳሌዎችን ለማግኘት እንችላለን።

በቤተሰቤ ታሪክ ውስጥ የሚገኘው ይህን መርሆ ለማሳየት ይችላል። የአያቴ አባት ጆሴፍ ዋትሰን ማይንስ የተወለደው በ1856 ዓ/ም በ ኸል፣ ዮርክሻየር እንግሊዝ ውስጥ ነበር። ቤተሰቡ የቤተክርስቲያኗ ባለ የሆኑት በእንግሊዝ ነበር፣ ከዚያም ወደ ሶልት ሌክ መጡ። ኤማ ኪፕን በ1833 ዓ/ም አገባ፣ እናም የስምንት ልጆች ወላጆች ሆኑ። ጆሴፍ በሙሉ የሚስዮን ስራ እንዲያገለግል በ53 አመቱ በሰኔ 1910 ዓ/ም ተጠራ። በባለቤቱና በስምንት ልጆቹ ድገፋ ወደተወለደበት እንግሊዝ በሚስዮን ለማገልገል ሄደ።

ለሁለት አመት በእምነት ካገለገለ በኋላ፣ ከጓደኛው ጋር በግሎክስተር ኢንግሊዝ ወደ ሰንበት ትምህርት በቢስክሌት ሲሄድ፣ ጎማው ፈነዳ። ከቢስክሌቱ ወረደ እና ጉዳቱ ምን እንደሆነ ተመለከተ። መጥፎ እንደነበረና ለመጠገን ብዙ ጊዜ እንደሚፈጅ ሲያውቅ፣ ጓደኛው ወደ እሁድ አገልግሎቱ እንዲሄድ እና ተቀትሎት እንደሚመጣ ነገረው። ይህን ማለቱን ሲጨርስ፣ ወደቀ። በልቡ ምክንያት ወዲያው ሞተ።

ጆሴፍ ዋትሰን ሜይንስ በዚህ ህይወት ልጆቹንና ባለቤቱን እንደገና አላየም። አስከሬኑን ወደ ሶልት ሌክ ከተማ ለመመለስ ችለው ነበር እናም ለቅሶውም በዋተርሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ነበር። የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ቡድን አባል ሽማግሌ አንተኒ ደብሊው. አይቭንስ በለቅሶው ላይ ስለህይወት፣ ሞት፣ እና መፅናት አስፈላጊ ትምህርትን አስተማሩን፥ “ወንጌሉ የሚሰጠን ይህን ነው - ከሞት የምናመልጥበት አይደለም፣ ግን በትንሳኤ ባለን ተስፋ በኩል ድልን ይሰጠናል።... ይህም [ስለጆሴፍ ሜይንስ] የሚያመለክት ነው። ... ሰዎች ህይወታቸውን በጻድቅነት፣ በእምነት፣ ለእምነት ታማኝ በመሆን ህይወታቸውን አሳልፈው እንደሚሰጡ ማወቅ የሚያስደስት፣ የሚያረካና ደስ የሚያሰኝ ነው።”4

በአያቴ አባት ይታይ የነበረውን የመፅናት እና የመንፈስ ጥንካሬ ምሳሌን እንድከተል ይህ የቤተሰብ ታሪክ ከምችለው በላይ እንድጥር አነሳሳኝ። ጆሴፍ በመሞቱ ምክንያት ህይወቷ ከባድ በሆነባት በባለቤቱ፣ በኤማ፣ እምነትም ተነሳስቻለሁ። ስምንት ልጆቿን እየረዳች የቀረውን ህይወቷን ለእምነቷ ታማኝ ሆና ስትኖር ምስክሯ ጠንካራ እናም የተቀየረችበትም ሙሉ ነበር።

ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳለው፣ “እንግዲህ... እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ ... በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ...።”5 በፊታችን ያለው ሩጫ በየጠዋቱ የምንነሳባቸው ፈተናዎች ናቸው። በምድር ያለነር ሩጫውን ለመሮጥ፣ የነጻ ምርጫ መብታችንን ለመጠቀም፣ እና በትክክለኛና በስህተት መካከል ለመምረጥ ነው። ሩጫውን በክብር እና በስኬት ለመጨረስ እና ወደ ሰማይ አባታችን ለመመለስ፣ በአላማ መስራት፣ ያለማቋረጥ መመኮር፣ እና ራስን መቆጣጠር የሆኑ ዋጋዎችን መክፈል ያስፈልገናል። በመንፈስ መልካም ሁኔታ ላይ መሆን አለብን። መንፈሳዊ ጥንካሪ ያስፈልገናል። ወደ እውነተኛ ቅያሬ የሚመራን ጠንካራ ምስካሬነት ያስፈልገናል፣ እናም በዚህም ምክንያት እኛ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ለመቋቋም የውስጥ ሰላም እና ጥንካሬ እያለን እናገኛለን።

ስለዚህ በየጠዋቱ የምትነቁባቸው ፈተናዎች ምንም ቢሆኑ፣ በምታሳድጉት የመንፈስ ጥንካሬ፣ ከጌታ እርዳታ ጋር ተያይዞ፣ በሩጫው መጨረሻ ላይ ሐዋሪያው ጳውሎስ እንዲህ ያለበይን ልበ ሙሉነት እንደሰትበታለን፥

“በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል።

“መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤

“ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።”6

ስለሚያፈቅረን የሰማይ አባት እና ወደ ምድር በዚህ ጊዜ እንድናመጣ የሚያደርገው የእርሱ የደስታ ታላቅ እና ዘለአለማዊ እቅድ እውነት እንደሆነ እመሰክራለሁ። በውስጣችን ለመፅናት ጥንካሬ እንዲኖረን የጌታ መንፈስ ያነሳሳን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።