2010–2019 (እ.አ.አ)
ቃል ኪዳን የመጠበቅ ፍቅር ደስታ ሀይል
ኦክተውበር 2013


15:27

ቃል ኪዳን የመጠበቅ ፍቅር ደስታ ሀይል

አዳኛን ምን ህል እንደምንወደው፤ እናም በደስታ እንዴት ቃልኪዳናችንን እንደጠበቅን እራሳችንን እንድንገምት እያንዳንዳችንን እጋብዛችኋለሁ።

ልቤን የነካውን ታሪክ በማካፈል ለመጀመር እወዳለሁ።

አንድ ምሽት አንድ ሰው አምስት በጎቹን ለምሽት ወደ መጠለያ እንዲመጡ ጠራቸው። ይህ ሰው ኑ በማለት አምስቱን ሲጠራቸው በፍጥነት ወደፊት አቅጣጫውን ተከትለው ሲመጡ ቤተሰቦቹ በታላቅ ስሜት ይከታተሉት ነበር። አራቱ በፍጥነት ተከተሉት በፍቅርም ራሳቸውን መታ መታ አደረጋቸው በጎቹም ድምጹን ያውቁታል እናም ይወዱታል።

ነገር ግን አምስተኛው በግ በፍጥነት አልመጣም ነበር። ከመካከላቸው ያልተገራች አንዲት ተለቅ ያለች ሴት በግ ሌሎችን ታሳስታለች በማለት የበጓ ባለቤት በጓን ለጥቂት ቀናት በራሱ ቦታ ላይ በማሰር እንድትረጋጋ አስተማራት ቀስ በቀስም አጠር ያለች ገመድ በአንገቷ ላይ በማስቀረት እና እንድትፈታ በማድረግ እርሱን እና ሌሎች በጎችን እነድትወድ በትዕግስት አስተማራት።

ለመጥፋት ተቃርባ የነበረችውን በግ ይህ ሰው በመንከባከብ አንደገና በብልህነት ከእንግዲህ ወዲህ አልታሰርሽም ነጻ ነሽ ነይ ብሎ ሲመልስ ያን ምሽት ቤተሰቦቹ ከታተሉት ነበር። እጁን እራሷ ላይ በፍቅር በማድረግ ከእርሷ እና ከሌሎች በጎች ጋር ወደ መጠለያ ተመለሰ።1

በዚያ ታሪክ መንፈስ፡ ቃልኪዳናችንን ለመጠበቅ መንፈስ ቅዱስ ይረዳን ያስተምረን ዘንድ ጸሎቴ ነው። ቃልኪዳንን ማድረግ እና መጠበቅ ማለት ራሳችንን ከሰማይ አባታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ማስተሳሰርን መምረጥ ማለት ነው። አዳኝን መከተል ቃል መግባት ነው ከልክ ባለፈ ሁኔታ እኛን ነጻ ለማውጣት ለከፈለልን ዋጋ ውለታችንን ማሳየት ነው።

ሽማግሌ ጄፍር አር ሆላንድ እንዳስረዱት፣ ቃል ኪዳን የሚያጣብቅ መንፈሳዊ ስምምነት ነው፣ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ በመኖር እና በማሰብ ከሰማይ አባታችን ጋር መለኮታዊ ቃል ኪዳን እናደርጋለን። በተመላሹ አብ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እና መንፈስ ቅዱስ ሙሉ ድምቀት ያለው ዘላለማዊ ህይወት ቃል ገብቶልናል።2 በዚያ ተበምያጣብቀው ስምምነት ጌታ የመፈፀምያ ጊዜን ስቷል፣ እኛም ለመጠበቅም ተስማምተናል። ቃል ኪዳን ማድረግ እና መጠበቅ እንደ አዳኝ ለመሆን መግለፃችን ነው።3 አስተሳሰቡ በጥቂት ተወዳጅ መዝሙር የተገለፀውን መከተል ነው። የፈለክበት ቦታ እሄዳለሁ፣ ማለት የፈለከውን እላለሁ.... የፈለከውን እሆናለሁ።4

ለምን ቃልኪዳንን እንገባለን እና እንጠብቃለን?

1. ቃልኪዳን ማድረግ ያበረታል: ከፍ ያደርጋል እናም ይጠብቃል።

ኔፊ በራዕይ ቃልኪዳን በሚጠብቁ ላይ ጌታ ታላቅ በረከትን እንደሚሰጥ ተመለከተ። እንዲህም ሆነ፡ እኔ፡ ኔፊ በታላቅ ደስታ በቃልኪዳን ህዝብ ላይ የእግዚአብሔር በግ ሐይል ሲወርድ እና በታላቅ ክብር በእግዚአብሔር ሓይል እና ቅድስና ሲጣጠቁ አየሁ። በቅርቡ አንድ አዲስ ሴት ጓደኛ ተዋወቅሁ፡ ይህቺ ወጣት ሴት ከዚህ በፊት ይታገላት የነበረውን ፈተና በኃይል የቤተመቅደስ ስጦታ ዋን ከተቀበለች በኋላ መቋቋሟን መሰከረችልኝ።5

በቅርብ ጊዜ ውድ ጓደኛዬ ከሆነችው ጋር ተገናኘሁ፡የቤተመግደስ በረከትን ከተቀበለች በኋላ ትታገልባቸው የነበረፈተናዎችን ለመቋቋም ሀይል እንደተቀበለች መሰከረች።

ቃልኪዳናችንን ስንጠብቅ እኛም አንዱ የአንዱን ሸክም ለመሸከም ብርታት እና ጥንካሬን እናገኛለን። አንዲት ልቧ የተሰበረ እህት ችግር የነበረበት ልጅ ነበራት። በሴቶች መረጃ ማሕበር እንደ ቃልኪን ጠባቂነት ባላት በህቶች አምነት ለልጇ ጾመው እንዲጸልዩ በብርታት ጋበዘቻቸው። ሌላኛዋም ሴት ተመሳሳይ ጸሎት እህቶች እንዲያደርጉላት ምኞቷ እንደሆነ ገለጸች። ከዓመታት በፊት የራሷ ልጅ ትግል ላይ ነበር እናም ይህን ሸክሟን ቤተሰቧ ይረዷት ዘንድ ለመጋበዝ ምኞቷ እንደሆነ ገለጸች። አዳኛችን እንዲህ ብሏል እርስ በእርሳችሁ ብትዋደዱ ሰው ሁሉ ደቀመዝሙሬ እንደሆናችሁ ያውቃል። 6

ኦ እህቶች ሁላችንም የተሸከምናቸው ሸክሞች እንዲሁም የምነሸከማቸው ሸክሞች አሉ። ሉሲ ማክ ስሚዝ ለመጀመሪያ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አማካሪ ያደረጉት ንግግር ከመቼውም በላይ የአሁኑ አግባብ ያለው ነው። በሰማይ አብረን እንሆን ዘንድ ሁላችንም እንደጋገፍ አንዱ አንዱ ያጽናና እናም እንማማር።7 ይህ የቃልኪዳን መጠበቅ እና የጉብኝት ትምህርት ነው።

መጽሐፈ ሞርሞርን ነብዩ አልማ በአመጸኛ ልጁ ምክንያት ታላቅ ሸክም መሸከሙን ያስታውሰናል። ነገር ግን አልማ አንዱ የአንዱን ሸክም መሸከም ማለት በገባቸው እና ከልብ በጌታ ወንጌል በተለወጡ ወንድሞች እና እህቶች በመባረኩ እድለኛ ነበር። ስለልጁ የታላቅ እምነት የአልማ ጸሎት በሞዛያ መጽሐፍ የተጻፈውን እናውቀዋለን። ጽሑፉ እንዲህ ይገለጻል፤ ጌታ…. የህዝቡን እንዲሁም የአገልጋዩን አልማን ጸሎት ሰምቷል።8

ዘወትር ንስሐ በሚገባ 9ነፍስ ጌታ እንደሚደሰት እናውቃለን ነገርግን ከምንም በላይ የፕሬዚዳንት ሄንሪ ቢ አይሪንግ ፤ ቀድሞ መጀመር እና መጽናት የሚለውን መመሪያ ልጆቻችን እንዲከተሉ እንፈልጋለን።10 ከጥቂት ጊዜያት በፊት የሚያስቆጣ እና ከልብ የሆነ ጥያቄ በካህናት እና በረዳት መሪዎች መሃከል ተነሳ። በእርግጥ የ 8 ዓመት ልጆች ቃልኪዳናቸውን እንዲጠብቁ እናሳስባለን አብረን ስንመክ፤ የተቀደሰ የጥምቀት ቃልኪዳናቸውን እንዲጠብቁ እና ቀለል ባለ መንገድ ቃለመሃላ እንዲገቡ እና እንዲያደርጉ ስንረዳቸው ልጆችን የማዘጋጃ አንድ መንገድ ይሆናል የሚል አንድ ሀሳብ ቀረበ።

ታማኝ ወላጆች የልጆቻቸውን ፍላጎት ለሟሟላት በተሻለ ሁኔታ ለማስተማር የተሰጡ ናቸው። ወላጆች በግል ራዕይ፤ በህብረት ምክር፤ እና አገልግሎት እንዲሁም ቀላሉን የወንጌል መርሆ ለማስተማር ሲፈልጉ፤ ቤተሰቦቻቸውን የሚከላከል እና የሚያበረታ ኃይል ይኖራቸዋል። ሌሎች የቤተሰብ አባላትም ይረዷቸዋል:: ትሁቱ ኃያቴ በሚከተለው መዝሙር ቀላል ቃለመኃላ ጥበቃ ጥቅም አስተምሮናል። ቃለመኃላ ከማድረግ በፊት ጥቅሙን በሚገባ አስተውሉ። ከዚያም ሲደረግ በልባችሁ ቅረጹት። በልባችሁ ቅረጹት። ያ ትንሽ መዝሙር በፍቅር ፤ በእምነት፤ እና በኃይል ይሰጥ ነበር ምክንያቱም ኃያታችን የራሱን ቃለ መሃላ በልቡ ቀርጾት ነበርና።

አንዲት ብልህ እናት ሆን ብላ የራሷን ልጆች ቃልኪዳኗን በጥረት እንዲጠብቁ ታደርግ ነበር። ጎረቤቶችዋን፤ ጓደኞችዋን፤ እናም የዋርድ አባላትን ሸክም በደስታ ትሸከማለች እናም መጽናናት የሚሹትንም ታጽናናለች፡፤ ሴት ልጇ አባቷን በሞት የተነጠቀችውን ጓደኟዋን ማጽናናት ማየት የሚደንቅ አልነበረም። ጓደኛዋን የማጽናናት ድርጊት እና ፍላጎት አንዱ የጥምቀት ቃልኪዳኗን የመጠበቅ መልካም መንገድ መሆኑ ነበር። የመጀመሪያ ቃልኪዳናቸውን የጥምቀት ቃልኪዳናቸውን እንዲጠብቁ ካልጠበቅናቸው እንዴት ልጆች የቤተመቅደስን ቃልኪዳን ይጠብቃሉ ብለን እናስባለን;

ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ ስኮት አንዱ ታላቅ በረከት ክርስቶስን ያማከለ ወንጌል የሚሰበክበት፤ ቃልኪዳን የሚጠበቅበት፤ እናም በፍቅር የተከበበ ቤት ለአለም ስናበረክት ነው።11 ልጆቻችን የቤተመቅደስ ቃልኪዳንን እንዲጠብቁ እና እንዲያደርጉ ለማዘጋጀት መፍጥር የምንችለው አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው?

  • ለቤተመቅደስ ብቁ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ አብረን እናያለን።

  • መንፈስ ቅዱስን ማዳመጥ እንዴት እንደሆነ አንድ ላይ ማወቅ እንችላለን። የቤተመቅደስ ስጦታ የሚገኘው በራዕይ ስለሆነ፤ ያንን አስፈላጊ ጥበብ ማወቅ አለብን።

  • ከጥምቀት እና ቅዱስ ቁርባን የተቀደሱ ምልክቶች በመጀመር በምልክቶቹ ጥቅም አማካይነት እንዴት መማር እንደምንችል አንድ ላይ ማወቅ እንችላለን፡፤

  • አካል የተቀደሰ፤ አንዳንዴም ቤተመቅደስ ለምን እንደተባለ፤ እናም አለባበሳችንም አግባብ ያለው ከቤተመቅደስ የተቀደሰ ተፈጥሮ ጋርም እንዴት እንዲስማማ አንድ ላይ ማወቅ እንችላለን።

  • በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የደስታዎችን እቅድ ማየት እንችላለን። ከሰማይ አባት እቅድ ጋር የበለጠ በተቀራረብን እና በቅዱሳን መጽሐፍት በተሰጠን ቁጥር የቤተመቀደስ አምልኮ የበለጠ ዋጋ ይሰጠናል።

  • የቀድሞ ኃያቶቻችን ታሪኮች፤ የቤተሰብ ታሪክ ምርምር፤ ማውጫ፤ እና በህይወት ለሌሉት የቤተመቅደስ ስርዓት ማስፈጸም መማር እንችላለን።

  • ስጦታ፤ ስርዓት፤ ማተም፤ክህነት፤ ቁልፍ እና ከቤተመቅደስ አምልኮ ጋር የተመሳሰሉ ቃላቶችን ትርጉም አብረን ማየት እንችላለን።

  • ወደ ቤተመቅደስ የምንሄደው ስርአቶችን ለመፈጸም እና ልንጠብቃቸው ወደ ቤት እንደምንመለስ ማስተማር እንችላለን።12

ጥሩ፤ የተሸለ እናም በጣም ጥሩ ሚለውን ሃሳብ እስቲ ስናስተምር እናስታውስ።13 ልጆቻችንን ስለቤተመቅደስ ማስተማር መልካም እንደሆነ እናስተምራቸው ቃለ፤ኪዳናቸውን እንዲጠብቁ የቤተመቅደስ መሃላችንን እንደምንጠብቅ በምሳሌ ማሳየት የተሸለ ነው። እህቶ ፤ ልጆች በቃልኪዳን ጎዳና እንዲጓዙ በደህንነት ስራ ስንመግብ፤ ስናስተምር እና ስናዘጋጅ አስፈላጊ ስራ እየሰራን እንደሆን አስታውሰነው እናውቃለን፤ ኃይል ሊመጣ የሚችለው ቃልኪዳናችንን ስናከብር እና ስንጠበቅ ብቻ ነው።

2. ቃልኪዳንን መጠበቅ ለእውነተኛ ደስታ አስፈላጊ ነው

ፕሬዚዳንት ሞንስን የተቀደሰ ቃልኪዳን በእኛ መከበር እንዳለባቸው እና ለህጎችም ታማኝነት አንዱ የደስታ መለኪያ ነው በማለት አስተምረዋል።14 በ 2  ኔፊ በቀላሉ እንዲህ ይገለጻል፤ በደስታ ሁኔታ ውስጥ እንኖራለን።15 ቀደም ብሎ በዚሁ ምዕራፍ ላይ ኔፊ እና ህዝቦቹ ቤተመቅደስ መገንባታቸውን እንማራለን። በእርግጥ ደስተኛ ቃልኪዳን ጠባቂዎች ነበሩ በአልማ መጽሐፍ ይህን እናነባለን፤ ከሞሮናይ ጊዜ በላይ በኒፋይ ጊዜ በኒፋይ ህዝቦች መካከል የደስታ ጊዜ አልነበረም።16 ለምን፤ ደግሞ በቀድሞው ቁጥር ይህን እናነባለን የጌታን ትዕዛዛት በመጠበቅ ደስተኞች ነበሩ።17 ቃልኪዳን ጠባቂዎች ትዕዛዛት ጠባቂዎች ናቸው።

ይህን ጥቅስ እወደዋለሁ እናም ህዝቦች የጥምቀት ቃልኪዳን የሚለውን ስሰሙ፤ በደስታ፤ እናም በመደነቅ እጆቻቸውን አጨበጨቡ። ይህ የልባችን መሻት ነው።18 የልባቸውን መሻት ወደድኩት። በደስታ ቃልኪዳናቸውን ለመጠበቅ እና ለማድረግ ተስማሙ።

አንድ እሁድ አንድ ወጣት እህት በደስታ እንዲህ ተናገረች ዛሬ ወደ ቅዱስ ቁርባን መጣሁ በዚያ አይነት ሁኔታ የተደሰትንባቸው ጊዜያት መቼ ነበሩ፤ እንዴትስ እንገልጻውለን፤ የሰንበት ቀንን በመቀደስ እናም አዳኛን በማስታወስ፤ ዘወትር ቅዱሳን መጻሕፍትን ስናጠና፤ እናም የሳምንቱ የቤተሰብ ምሽት ሲኖረን ዘወትር እሱን በማስታወስ እንኖር እናሳያለን። በግዴለሽነት ከእነዚህ አስፈላጊ ነገሮች ስንርቅ፤ ንስሐ በመግባት እንደገና መጀመር ይገባናል።

ቃል ኪዳን መግባትና በደስታ መጠበቅ ዋነኛው የሆነውን ቅዱስ የማዳኛ ሥረኣቶችን ለመጠበቅ ለህይወት ተገቢነትን በመስጠት አባት ያለውን ሁሉ እንድንቀበል ያደርጋል።19 ትእዛዝና ቃል ኪዳን ለመንፈሳዊ ጉዞ ወሳኞች ናቸው። ፕሬዝዳንት ሄነሪ ቢ አይርንግ ስያስተምሩ ይህን ተጠቅመዋል። የኃለኛው ቀን ቅዱሳኖች የቃል ኪዳን ህዝቦች ናቸው። ከተጠመቅን ቀን ጀምሮ እስከ ህይወታን መንፈሳዊ ጉዞ ከግዚአብሄር ጋር ቃል ኪዳን እናደርጋለን፣ እሱም ከኛ ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋል። እሱ ሥልጣን ባለው አገልጋዩ አማካኝነት የተሰጠን ቃል ኪዳኞች ሁል ጊዜ ይጠብቃል። ነገር ግን ቃል ኪዳን ገብተን የምንጠብቅ መሆናችን በህይወታችን ዋነኛ ፈተና ነው።20

3. ቃልኪዳናችንን መጠበቅ ለአዳኛችን እና ለሰማይ አባታችን ያለንን ፍቅር ይገልጻል።

የበለጠ ቃልኪዳናችንን በመጠበቅ ትጉ ከሚያደርጉን ምክንያቶች ከከሁሉም ፍቅር የበለጠ ይህ ምክንያት ያስገድዳል። በብሉ ኪዳን የፍቅርን መርሆ ሳስብ አንድ ቁጥር ልቤን ይነካል። በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ማናችን ነን የያዕቆብን እና የራሄልን ታሪክ ስናነብ ያልተነካን፤ ያዕቆብ ራሄልን ለ7ዓመታት አገለገለ፤ ለእርሷ ከነበረው ፍቀር የተነሳ ለእርሱ ግን ጥቂት ጊዜያቶች ይመስሉት ነበር?21 እህቶች ቃልኪዳናችንን እንዲህ በመሰለ ጥልቅ እና ታማኝ ፍቅር መጠበቅ እንችላል።

አዳኝ ከአብ ጋር ቃልኪዳኑን ለመጠበቅ እና አለምን ከሀጢአት ለማንጻት መለኮታው ተልዕኮውን ለማሟላት ለምን ተስማማ ለአብ እና ለእኛ ስላለው ፍቅር ነበር። በዚህ ምድር ትክክለኛ ወይም አግባብ ያልሆነውን የአለም ደካማነትን፤ በሽታን፤ የልብ ህመምን መግለጽ የማይቻለውን ሐጢያትን ህመምን አንድያ ፍጹም የሆነው ልጁ እንዲሸከም አብ ለምን ፈቀደ፤በዚህ ቃል መልሱን እናገኛለን። እግዚአብሄር አለምን ስለወደደ፤ አንዲያ ልጁን እንዲሁ ሰጠ።22

በሙላት ከእኛ የተሰጠውን በርካታ በረከቶች ካደነቅን በጉጉት እና በፍቃደኝነት ማድረግ የማንችለውን ነገር ጌታ አልጠየቀም።23 በፕሬዚዳንት ጆሴፍ ፊልዲንግ ስሚዝ አገላለጽ ቃልኪዳንን መጠበቅ ማለት ከምንም በላይ የሆነውን የማይቆጠረውን የአዳኛችንን እና የቤዛችንን እንዲሁም ፍጹም የሰማይ አባታችንን ፍቅር አንዱ የመገለጫ መንገድ ነው።

ሽማግሌ ሆላንድ በመቀጠልም እንዲህ ይገልጻሉ፤ በፍርድ ቀን ልምምዳችን ምን እንደሚሆን እርግጠኛ አይደለሁም፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ክርሰተስ ጴጥሮስን ትወደኛለህ ብሎ የጠየቀውን በትክክለኛነት ካልጠየቀ በጣም አደንቃለሁ።24 ዛሬ ምሽት አዳኛን ምን ህል እንደምንወደው፤ እናም በደስታ እንዴት ቃልኪዳናችንን እንደጠበቅን እራሳችንን እንድንገምት እያንዳንዳችንን እጋብዛችኋለሁ። አዳኝ እንዲህ በሎ ነበር፤ ቃልኪዳኔ ያለው እና የጠበቀ እኔን ይወደኛል፤ እንዲሁም የሚወደኝ ቢኖር አባቴንም ይውደድ። እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም አሳዋለሁ።25 በዕለት ህይወታችን የአዳኝን ትክክለኛ መገለጫ ሁላችን እንዴት እናገኛለን፤

ሁላችንም እንደውም ባለፉት ግዜያትም ሆነ አሁን በተለየዩ ነገሮች የምትታገሉ የመልካም እረኛ እጅ በላያችን ላይ መነካት የሰማን። ፤ኑ፤ የሚለውን ድምጽም እንስማ ከእንግዲህ ነጻ ናችሁ፤ አትታሰሩም። አዳኛችን እንዲህ ብሏል፤ መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ ህይወቱን ለበጎቹ ይሰጣል፡፤ ይህን ያለው ቃልኪዳኑን በፍቅር ስለሚጠብቅ ነው።26 ጥያቄው እንግዳውስ እኛስ፤ በእምነት፤ በልብ ደስተኝነት፤ እና በታላቅ የቃልኪዳን ጠባቂነት ፍላጎት እንግፋ። በዚህ መንገድ ነው በሰማይ ላለው አባታችን እና አዳኛችን ያለንን ፍቅር የምናሳየው። በታላቅ ፍቅር እመሰክራለሁ፤ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. See D. Todd Christofferson, “You Are Free,” Ensign, Mar. 2013, 38, 40; or Liahona, Mar. 2013, 16, 18.

  2. Jeffrey R. Holland, “Keeping Covenants: A Message for Those Who Will Serve a Mission,” New Era, Jan. 2012, 3; or Liahona, Jan. 2012, 49.

  3. See “Understanding Our Covenants with God,” Ensign, July 2012, 25; or Liahona, July 2012, 23.

  4. “I’ll Go Where You Want Me to Go,” Hymns, no. 270; emphasis added.

  5. 1 ኔፊ 14:14.

  6. ዮሀንስ 13:35.

  7. Lucy Mack Smith, in Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society (2011), 25.

  8. ሞዛያ 27:14.

  9. ትምህርት እና ቃል ኪዳን 18:13.

  10. See Henry B. Eyring, “Spiritual Preparedness: Start Early and Be Steady,” Ensign or Liahona, Nov. 2005, 37–40.

  11. Richard G. Scott, “For Peace at Home,” Ensign or Liahona, May 2013, 30.

  12. See D. Todd Christofferson, “The Gospel Answers Life’s Problems and Challenges” (worldwide leadership training meeting, Feb. 2012); lds.org/broadcasts.

  13. See Dallin H. Oaks, “Good, Better, Best,” Ensign or Liahona, Nov. 2007, 104.

  14. Thomas S. Monson, “Happiness—the Universal Quest,” Ensign, Oct. 1993, 4; or Liahona, Mar. 1996, 5.

  15. 2 ኔፊ 5:27.

  16. አልማ 50:23.

  17. አልማ 50:22.

  18. ሞዛያ 18:11.

  19. ትምህርት እና ቃል ኪዳን 84:38.

  20. Henry B. Eyring, “Witnesses for God,” Ensign, Nov. 1996, 30; emphasis added.

  21. ዘፍጥረት 29:20.

  22. ዮሀንስ 3:16.

  23. Joseph Fielding Smith, “Importance of the Sacrament Meeting,” Relief Society Magazine, Oct. 1943, 592.

  24. Jeffrey R. Holland, “The First Great Commandment,” Ensign or Liahona, Nov. 2012, 84.

  25. ዮሀንስ 14:21.

  26. ዮሀንስ 10:11.