በክህነት ውስጥ ያለ ሀይል
ሰው መጋረጃውን በመክፈት ጸሀይ ወደ ክፍል እንዲገባ ለማድረግይችላል፣ ነገር ግን ያ ሰው ያንን ጸሀይ ወይም ብርሀን፣ ወይም የሚያመጣውን ሙቀት ባለቤት ለመሆን አይችልም።
የክህነት በረከቶች ለሁሉም ናቸው
“ፍቅር በዚህ ይነገራል” የሚለውን የመጀመሪያ ክፍል መዝሙር ልጆች በደስታ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ እየዘፈኑ እያሉ፣ ሁሉም ይህን አስደስቷቸው ፈገግ ብለው ነበር። አምስት ልጆች እያሳደገች ያለች ጎበዝ እናት ሁለተኛውን አንቀጽ አዳመጠች፥ “ቤቴም በክህነት ሀይል ጥንካሬ በየሰዓቱ የሚባረክ ቤት ነው።”1 በሀዘንም እንዲህ አሰበች፣ “ልጆቼ እንደዚህ አይነት ቤት አያውቁም።”2
ለዚህች ታማኝ ሴት እና ለሁሉም ያለኝ መልእክትም ቢኖር ጉዳያችን ምንም ቢሆን በየሰዓቱ “በክህነት ሀይል ጥንካሬ ለመባረክ” እንችላለን የሚል ነው።
አንዳንዴ በቤተክርስቲያኗ የሚገኘውን ክህነት በብዛት ከወንዶች ጋር እናያይዛለን። ክህነት ለሁሉም ወንዶች፣ ሴቶች፣ እና ልጆች ደህንነትና በረከት የተሰጠ የእግዚአብሔር ሀይል እና ስልጣን ነው።
ሰው መጋረጃውን በመክፈት ጸሀይ ወደ ክፍል እንዲገባ ለማድረግይችላል፣ ነገር ግን ያ ሰው ያንን ጸሀይ ወይም ብርሀን፣ ወይም የሚያመጣውን ሙቀት ባለቤት ለመሆን አይችልም። የክህነት በረከቶች ይህን ስጦታ እንዲሰጥ ከተጠየቀው በላይ በጣም ታላቅ የሆነ ነው።
የክህነት በረከቶችን፣ ሀይል፣ እና ቃል ኪዳኖችን በዚህ ህይወት እና በሚቀጥለው መቀበል የስጋዊነት ታላቅ እድል እና ሀላፊነት ነው። ብቁ ስንሆን፣ የክህነት ስርዓቶች በምድር ላይ ህይወታችንን ያበለጽጋል እናም ወደፊት ለሚመጣው አስደናቂ ቃል ኪዳን ያዘጋጀናል። ጌታ እንዳለው፣ “በስርዓቶች... የአምላክነት ሀይል ይገለጻል።”3
ለሚጠመቀው፣ መንፈስ ቅዱስ ለሚቀበለው፣እና በየጊዜው ቅዱስ ቁርባንን ለሚወስደው ለእያንዳንዱ ብቁ ሰው ከእግዚአብሔር የሚመጡ ልዩ በረከቶች አሉ። ቤተመቅደስም ተጨማሪ ብርሀንና ጥንካሪን ለትንሳኤና ለዘለአለም ህይወት የተስፋ ቃል ማረጋገጫ ትሰጣለች።4
እነዚህ ስርዓቶች በሙል በኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን እምነት እንድናሳድግና ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እንድንገባና እንድናከብር ይጋብዙናል። እነዚህን ቅዱስ ቃል ኪዳኖች ስናከብር፣ የክህነት ሀይልን እና በረከቶችን እንቀበላለን።
ይህን የክህነት ሀይል በህይወታችን ውስጥ አይሰማንምን እናም ቃል ኪዳን በሚጠብቁት የቤተክርስቲያኗ አባላት መካከል አናየውምን? አዲስ ተቀያሪዎች ከጥምቀት ውሀ ንጹህ እና ምህረት ያገኙ ሆነው ሲወቱ ይህንንም እንመለከታለን።፡ልጆቻችን እና ወጣቶቻችን ለመንፈስ ቅዱስ መነሳሻና መመሪያ ስሜት ሲኖራቸው እንመለከታለን። የቤተመቅደስ ስርዓቶች በአለም ዙሪያ ለሚገኙት ጻድቅ ወንዶችና ሴቶች የጥንካሪ ማሳያና ብርሀን ሲሆንም ተመልክተናል።
በዚህ ወር ልጃቸው ቢወለድም ለአንድ ሳምንት ብቻ የኖረላቸው ወላጆች በቤተመቅደስ መተሳሰር በነበራቸው ቃል ኪዳን ላይ ታላቅ ጥንካሬን ለማግኘት ሲችሉ ተመልክቼ ነበር። በክህነት ስርዓቶች በኩል መፅናኛ፣ ጥንካሬ፣ ጥበቃ፣ ሰላም፣ እና የዘለአለም ቃል ኪዳን ለመቀበል እንችላለን።5
ስለክህነት የምናውቀው
አንዳንዶች “የክህነት ሀይል እና በረከቶች ለሁሉም የሚገኙ ከሆኑ፣ የክህነት ስርዓቶች ማስተዳደር ለወንዶች ብቻ ይሰጣል?” ብለው ይጠይቃሉ።
መልአኩ “እናም የእግዚአብሔርን ትህትና ታውቃለህ?” ብሎ ኔፊን ሲጠይቀው፣ ኔፊ በታማኝነት እንዲህ መለሰ “እርሱ ልጆቹን እንደሚወድ አውቃለሁ፣ ይሁን እንጂ፣ የሁሉን ነገሮች ትርጉም አላውቅም”6
ስለክህነት ስንናገር፣ የምናውቃቸው ብዙ ነገሮች አሉ።
ሁሉም አንድ አይነት ናቸው
እግዚአብሔር ልጆቹን በሙሉ እንደሚያፈቅርና ሰውን እንደማይፈራ እናውቃለን። “የሚመጡትን ማንንም፣ ... ሴትና ወንድን አይክድም፤… ሁሉም ለእግዚአብሔር አንድ ናቸው።”7
የእግዚአብሔር ፍቅር ለወንድና ለሴት ልጆቹ “አንድ አይነት” እንደሆነ በእርግጥ ስናውቅም፣ ወንዶችንና ሴቶችን አንድ አድርጎ እንዳልፈጠረም እናውቃለን። ጾታ በስጋዊ እና በዘለአለማዊ ማንነት እና አላማ አስፈላጊ የሆነ ጸባይ እንደሆነ እናውቃለን።፡ቅዱስ ሀላፊነቶች ለእያንዳንዱ ጾታ ተሰጥቷል።8
ከመጀመሪያ
ከመጀመሪያ ጀምሮ ጌታ ክህነቱ እንዴት እንደራጅ እንደመሰረተ እናውቃለን። “ክህነት መጀመሪያ ለአዳም ተስጥቷል።”9 ኖኅ፣ አብርሐም፣ እና ሙሴም በክህነት ስርዓቶችን አገልግለዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁሉም ታላቅ የሆነ ሊቀ ካህን ነበር እናም ነው። ሐዋሪያትን ጠራ። “እናንተ አልመረአችሁኝም፣” አለ፣ “ነገር ግን እኔ መርጫችኋለሁ፣ እናም ቀብቻችኋለሁ።”10 በቀናችን፣ መጥምቁ ዮሀንስ፣ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሀንስ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ክህነትን ወደምድር በዳግም መልሰዋል።11 በዚህ ነው የሰማይ አባታችን ክህነቱን የሚያስተዳድረው።12
ከእግዚአብሔር የመጡ ስጦታዎች
የቅዱስ ክህነት ሀይል ከእምነት፣ ከመንፈስ ቅዱስ፣ እና ከመንፈስ ስጦታ ተለይቶ እንደማይሰራ እናውቃለን። ቅዱሳን መጻህፍት እንደሚያስጠናቅቁን፣ “የእግዚአብሔር ስጦታዎች እንዳትክዱአቸው አጥብቄ እመክራችኋለሁ፣ ብዙ ናቸውና ፤ እና እነርሱም የሚመጡት ከአንድ እግዚአብሔር ነው። እናም እነዚህ ስጦታዎች የሚገለጡበት የተለያዩ መንገዶች አሉ፤ ነገር ግን ሁሉን በሁሉ የሚያደርገው እግዚአብሔር አንድ ነው፤ እናም ለሰው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መገለጥ ለጥቅሙ ይሰጠዋል።”13
ብቁነት
የግል ብቁነት የክህነት ስርዓትን ለማከናወንና ለመቀበል አስፈላጊ እንደሆኑ እናውቃለን። እህት ሊንዳ ኬ. በርተን እንዳሉት፣ “የክህነት ሀይልን ወደ ህይወታችን ለማምጣት ጻድቅነት ብቁ የሚያደርግ ነው።”14
ለምሳሌ፣ በአለም በብዛት የሚገኘውን የወሲብ ነገሮችን ስለሚያሳዩ ነገሮች አስቡባቸው። የጌታ ብቁነት መሰረት በክህነት ስርዓት ለሚያገለግሉት ምንም ፈቃድ አይሰጥም።ጌታ እንዳለው፥
“…ለርኩሰታችሁ ሁሉ ንሰሃ ግቡ።”15
“የሰውነትህ መብራት ዓይንህ ናት። ...ዓይንህ ታማሚ በሆነች ጊዜ ግን ሰውነትህ ደግሞ የጨለመ ይሆናል።”16
“ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።”17
ብቁ ሳይሆኑ ቅዱስ ቁርባንን መባረክ ወይም መስጠት፣ በሽተኞችን መባረክ፣ ወይም በሌሎች የክህነት ስርዓቶች መሳተፍ ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር እንዳሉት የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መትራት ነው።18 አንድ ሰው ብቁ ካልሆነ፣ በክህነት ስርዓት ከመሳተፍ ይውጣ እናም በጸሎት እንደ ንስሀ መግባት እና ወደ ትእዛዛት መመለስ የመጀመሪያ እርምጃዎች ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር ይነጋገር።
ትሁት
ጻድቅ አባት እና እናት ልጆቻቸውን በመምራት አንድ በሚሆኑበት ቤተሰቦች ውስጥ የክህነት በረከቶች እንደሚበለጽጉ እናውቃለን። ነገር ግን እግዚአብሔር እንደነዚህ አይነት በረከቶች በሌሎች ጉዳዮች በጉጉት እንደሚሰጥም እናውቃለን።19
በመንፈስና በስጋ የሚያስፈልጋቸውን የምትሰጥ እናት የቤት ለቤት አስተማሪዎች መጥተው አንዷን ልጇን እንዲባርኩላት ለመጠየቅ ትህትና ያስፈልጋት እንደነበር ተናግራለች። ነገር ግን በዝልቅ አስተያየት ይህ የቤት ለቤት አስተማሪዎቿ ልጇን ለመባረክ ሲዘጋጁ ከሚያስፈልጋቸው ትህትና በላይ እንዳልሆነም ጨምራ ተናግራለች።20
የክህነት ቁልፍ
በቀዳሚ አመራር እና በአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት የተያዙት የክህነት ቁልፎች የጌታን ስራ በምድር ላይ እንደሚመሩ እናውቃለን። ለካስማ ፕሬዘደንቶች እና ኤጲስ ቆጶሶች በክልላቸ ላላቸው ሀላፊነት ልዩ የክህነት ቁልፎች ይሰጧቸዋል።፡ወንዶችንና ሴቶችን በራዕይ ይጠራሉ እናም በወኪል የተሰጣቸውን የማስተማርና የማስተዳደር ሀላፊነት እንዲያከናውኑ ይደገፋሉ እናም ይለያሉ።21
ስለክህነት ብዙ ብናውቅም፣ በስጋዊ አይኖች መመልከቱ ሁልጊዜም ስለ እግዚአብሔር ስራ ሙሉ መረጃ አይሰጥም። ነገር ግን “ሀሳቦቼ የእናንተ ሀሳቦች አይደሉም፣ መንገዴም የእናንተ መንገድ አይደለም”22 ብሎ እንድናስታውስ በማድረግ በጊዜ እና በዘለአለማዊ አስተያየት “ነገሮች እንደሆኑ”23 ለማየት እንደምንችል እናም በሙሉ ፍጹም ፍቅሩን ለመረዳት እንደምንችል ማረጋገጫ ሰጥቶናል።
ሁላችንም በፈቃደኛነት እናገለግላለን። አንዳንዴ በጥሪአችን ከምንችለው በታች የሚጠበቅብን ይመስለናል፣ እናም ተጨማሪ ለማድረግ እንመኛለን። በሌሎች ጊዜ ከጥሪአችን ስንለቀቅ ምስጋና ይሰማናል። የምንቀበለውን ጥሪ እኛ ልንወስንባቸው አንችልም። 24ይህን የተማርኩት በጋብቻዬ ወዲያው ነው። ካቲ እና እኔ በፍሎሪዳ እንኖር ነበር። አንድ እሁድ የካስማው አመራር አማካሪ ባለቤቴ የጠዋት የሴሚነሪ አስተማሪ እንድትሆን መነሳሻ ስሜት እንዳላቸው ነገሮኝ።
“እንዲት ልናደርገው እንችላለን?” በማለት ጠየቅኹኝ። “ትትንሽ ልጆች አሉን፣ ሰሚነሪ የሚጀመረው በጠዋት 11 ሰአት ነው፣ እናም እኔ የዎርዳችን የወጣት ወንዶች ፕሬዘደንት ነኝ።”
አማካሪው ፈገግ አለና እንዲህ አለኝ፣ “ወንድም አንደርሰን፣ ይህም መልካም ነው።፡እንጠራታለን፣ እናም አንተን ከጥሪህ እንለቅሀለን።”
እንዲዚህም ነበር የደረሰው።
ሴቶች የሚያቀርቡት
በህይወት፣ በጋብቻ፣ እና የእግዚአብሔርን መንግስት በመገንባት ውስጥ የሲቶችን ሀሳቦችና ድምጾችን መጠየቅና ማዳመጥ አስፈላጊ ነው።
ከሀያ አመት በፊት በአጠቃላይ ጉባኤ፣ ሽማግሌ ኤም. ራስል ባለርድ ከሴቶች መረዳጃ ማህበት አጠቃላይ ፕሬዘደንት ጋር የነበራቸውን ንግግር ተናግረውበትነበር። በሚስዮን ለማገልገል የሚዘጋጁትን ወጣቶች ስለማጠናከር ጥያቄ ነበር። እህት እሌን ጃክሰን በፈገግታ እንዲህ አሉ፣ “እንደሚያውቁት፣ ሽማግሌ ባለርድ፣ የቤተክርስቲያኗ ሴቶች የሚያቀርቡት ጥሩ የሆነ ሀሳብ አላቸው ... ከተጠየቁ። ...እኛ እናቶቻቸው ነን።”25
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን ከሴቶች የሚያስጨንቃቸውን የመጠየቅ እና ስለሚያስጨንቃቸው መልስ የመስጠት ልምድ አላቸው። ከሴቶች ሁሉ በላይ ተፅዕኖ ያደረጉባቸውን እህት ፍራንሲስ ሞንሰንን ነበሩ። በጣም እንናፍቃቸዋለን። ደግሞም፣ ፕሬዘደንት ሞንሰን ከዎርዳቸው ውስጥ ከነበሩት ባለቤት ከሞተባቸው 84 ሴቶች እንዴት እንደተማሩ እንድናስታውን አድርገው ነበር። በኤጲስ ቆጶስ አግልግሎታቸው እና በህይወታቸው በሙሉ ታላቅ ተፅዕኖ ነበራቸው።
በማያስደንቅ ሁኔታም፣ ፕሬዘደንት ሞንሰን በጸሎት ስለሚስዮን አገልግሎት እድሜ ቅያሬ ከመወሰናቸው በፊት፣ ከሴቶች መረዳጃ ማህበር፣ ከወጣት ሴቶች፣ እና ከመጀመሪያ ክፍል አጠቃላይ አመራሮች ውይይት ነበር።
ኤጲስ ቆጶሶች፣ የፕሬዘደንት ሞንሰንን ምሳሌ ስትከተሉ፣ የሚመራው የጌታ እጅ ቅዱስ ስራችሁን በተጨማሪ ሲባርክ ይሰማችኋል።
በብራዚህ ለብዙ አመታት እንኖር ነበር። በዚይ እንደደረስኩኝ፣ እንደ ሰባ የሚያገለግሉትን አደልሰን ፓሬላ እና እንደ ካስማ አመራር ውስጥ የሚያገለግሉትን ወንድማቸውን አዲልሰን ጋር ተገናኘሁ። በኋላም በፍሎሪአኖፖሊስ እንደ ካስማ ፕሬዘደንት የሚያገለግሉትን ወንድማቸውን አዳልቶን እና እንደ ኤጲስ ቆጶስ የሚያገለግሉትን ሌላኛው ወንድማቸውን አዴልሞ አገኘሁ። በእነዚህ ወንድሞች እምነት ተደንቄ ነበር እናም ስለወላጆቻቸው ጠየኳቸው።
ቤተሰቡ በሳንቶስ ብራዚል ከ42 አመት በፊት ተጠምቀው ነበር። አዲልሰን ፓሬላ እንዳሉት፣ “በመጀመሪያ አባታችን የቤተክርስቲያኗ አባል ለመሆን የተደሰተበት ነበር። ነገር ግን፣ ወዲያውም ተሳታፊነትን አቆመ እና እናታችን ወደ ቤተክርስቲያን እንዳትሄድ ጠየቃት።”
አዲልሰን እንደነገሩኝ ልጆቹ ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄዱበት ለባስ እየሚከፍሉበት ገንዘብ ለማግኘት እናታቸው ልብስን ለጎረቤቶች ይሰፉ ነበር። አራቱ ትትንሽ ልጆች አብረው ለ2.2 ኪሎ ሜትር በእግር ይሄዱ፣ ለ45 ደቂቃ በባስ ይጓዘ፣ እና ለተጨማሪ 20 ደቂቃ በእግር ወደ ቤተክርስቲያኗ ይሄዱ ነበር።
ከልጆቻቸው ጋር ወደ ቤተክርስቲያን አብረው ለመሄድ ባይችሉም፣ እህት ፓሬላ ቅዱስ መጻህፍትን ለልጆቻቸው ያነቡ፣ ወንጌልን ያስተምሯቸው፣ እና አብረው ይጸልዩ ነበር። ትሁት ቤታቸው በክህነት ሀይል በረከት ተሞልቶ ነበር። ትትንሽ ልጆች አደጉ፣ በሚስዮንነት አገለገሉ፣ ተማሩ፣ እናም በቤተመቅደስ አገቡ። የክህነት በረከቶችም ቤቶቻቸውን ሞላ።
ከብዙ አመታት በኋላ፣ ያላገቡት እህት ቫኒ ጌ ፓኡላ ፐሬላ ለእራሳቸው የቤተመቅደስ በረከት ለማገኘት ወደ ቤተመቅደስ ገቡ፣ በኋላም በብራዚል ውስጥ ለሶስት ጊዜ በሚስዮንነት አገለገሉ።አሁን በ84 አመታቸው፣ እምነታቸው የሚከተሏቸውን ትውልዶች እየባረከ ነው።
ምስክር እና የተስፋ ቃል
የእግዚአብሔር የቅዱስ ክህነት ሀይል በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ይገኛል። በብቁነት በክህነት ስርዓት ስትሳተፉ፣ ገኢታ ታላቅ ጥንካሬ፣ ሰላም፣ እና ዘለአለማዊ አስተያየት ይሰጣችኋል። ጉዳያችሁ ምንም ቢሆን፣ ቤታችሁ “በክህነት ሀይል ጥንካሪ ይባረካል” እናም በእናንተ የሚቀርቡትም እነዚህን በረከቶች ለእራሳቸው ይፈልጋሉ።
እንደ ወንዶችና ሴቶች፣ እንደ እህቶችና ወንድሞች፣ እንደ እግዚአብሔር ወንድና ሴት ልጆች፣ አብረን ወደፊት እንገፋለን። ይህም የእኛ እድል፣ የእኛ ሀላፊነት፣ እናም የእኛ በረከት ነው። የእግዚአብሔርን መንግስት ወደ አዳኝ ለመመለስ ማዘጋጀትም የእኛ እጣ ፈንታ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።