ወደላይ ተመልከቱ
ዛሬ ወደላይ ተመልክተን የእዉነታዉ ምንጭ ለማየት አቅንተን አይተን ምስክረነታችን ጠንካራ መሆኑን የምናረጋግጥበት ነው።
ስምንት አመቴ እያለ፣እኔና ሁለት የአጎቶቼ ልጆች ለ 10 ሰዉ የሚሆን የ 15 ቀን ቀለብ እንደንገዛ ተላክን። ወደኋላ ስመለከት ሴት አያቴ እና አክስቴ እና አጎቴ ምን ያህል በእኛ መተማመን እንዳላቸዉ ሳስብ ያስገርመኛል። የጠዋቱ ሰማይ ብሩህ እና አንጸባራቂ ነበር ተንሹን ጋሪያችንን ይዘን ለ 16 ኪሎሜትር ጉዞ ስንነሳ።
በጉዞ ላይ ሃሳብ መቶልን ከጋሪዉ ወርደን ዳማ ለመጫወት ወሰንን። በጨዋታዉ በጣም ተዉጠን እየመሸ መሆኑን እንኳ ከላያችን ያለዉን ሰአት ማየት አልቻልንም። መን እየሆነ እያለ በተረዳን ሰአት፣ፌረሶቻችንን የመዉጫ ሰአት አልነበረንም። ከባዱ ዝናብ እና በረዶ ሲወርድብን ማሰብ የምንችለዉ ነገር ሁሉ ፈረሶቹን ፈቶ በፈረሶቹ መቀመጫ መጠለልን ነበር።
ፈረስ አልባ፣እርጥብ እና ብርድ ጉዞአችንን ቀጠልን፣በቻልነው መጠን እየፈጠንን። መድረሻችን ስንደርስ፣ወደከተማዉ የሚወስደዉ መንገድ በጎርፍ ተጥለቅልቆ አየነው። ያለን አማራጭ የለበስነዉን ጨርቅ ጥለን ከተማዉን ያጠረዉን በ ሽቦ ያታጠረዉን አጥር መዝለል ብቸኛዉ አማራጭ ነበር። መሽቶ ነበር ደክሞን፣ጨቅይተን ከተማው መግቢያ ላይ ያለን ቤት እንዲያስጠልሉን በፈለግንበት ሰአት። ጥሩ ቤተሰቦቹ አደረቁን፣የሚጣፍጥ ምግብም መገቡን ከዛም በክፍላችን እንድንተኛ አደረጉን። ባጭር ግዜ ዉስጥ ከፍሉ ዉስጥ ቆሻሻ መሬት መኖሩን ደረስንበት፣ከዛብ ሃሳብ መጣልን። ክብ ሰረተን መሬቱ ላይ ወድቀን እስከምንተኛ ደረስ ዳማ መጫወታችንን ቀጠልን።
እንደልጅነታችን ስለራሳችን ብቻ ነበር እናስብ የነበረዉ። ሰለተወደዱን ቤት እየፈለጉን ስላሉት አላሰብንም። ብልሆች ብንሆን ኖሮ ሰማዩን እናይ ነበር ፣ደመናዉን እናይ ነበር እናም ከ ነጎድጉዋዱ ለመቅደም ፍጥነት እንጨምር ነበር። አሁን ትንሽ ልምድ አልኝ፣ሁሌም እራሴን አስታዉሳለሁኝ፡ወደላይ ማየትህን አትርሳ።
ከአጎቶቼ ልጆች ጋር ያሳለፍኩት ልምድ ለአሁኑ ግዚያችን ምልክቶች ትኩረት እንድሰጥ አስተምሮኛል። ፓውሎስ እንደገለጠዉ በነጎድጓድ ዘመን ነው ምንኖረዉ፡ “ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ። ”(2 ጢማቴዎስ 3:2–4)
ስለዚ ግዜ ስናወራ፣ሽማግሌ ዳሊን አኤች ኦክስ ይህን አሉ “መንፈሳዊ እና አለማዊ ዝግጅቶችን ማድረግ አልብን…..ችላ የሚባለዉ ዝግጅት ብዙ ግዜ የሚታየዉ እና የሚያስቸግረዉ ነው-መንፈሳዊዉ (“Preparation for the Second Coming,” Ensign or Liahona, May 2004, 9)። በሌላ ቋንቋ ወደላን ማየትን ችላ አትበሉ።
የምንፈስ መዘጋጀትን በዚ በአስቸጋሪ ወቅት መሰጠት፣የማስጠንቀቂያ ቃል ስለሆነው ስለግዚያችን ምልክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁኝ። ሙያዮ መ ቴክኖሎጂ ግንባር ላይ እንድቀመጥ አድርጎኛል ስለዛ ስለጥቅሙ ተረዳሁ። ሰለሰዉ መረጃ መእጃችን ነው አሁን። ነገር ግን ኢንተርኔት በሚያሳስቱ ነገሮችም ጭምር የተሞላ ነው። የመናገር ነጻነታችንን አጠናክርዋል። ከመቼዉም በበለጠ ሁኔታ ይህንን ዘላለማዊ መርህዎችንን ማስታወስ አለብን “በፍሬያቸዉ ታዉቋችዋላችሁ” (ማቴዎስ ወንጌል 7:20)
በተለይ፣በተለይ የብልግና ምስሎችን እንዳትመለከቱ ወየም ክርስቶስን እና ነብዩን ዮሴፍ ስሚዝን በስህተት ለሚወነጅሉት ትኩረት እንዳትሰጡ አስጠነቅቃችዋለሁ። ተግባር ተመሳሳይ ወጤትን ይፈጥራል፡የመንፈስ ቅዱስ እና የሱን ጠባቂነት ሃይል ማጣት። ደስተኛ ያለመሆን ይከተላል።
ወድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣የወንጌል ምስክረነታችሁን እንድትጠራጠሩ ከሚያረጋቹ ነገሮች ስትመጡ፣ወደላይ እንድትመለከቱ እማጸናችዋለሁ። የሁሉንም የጥበብ ምንጭ እና እዉነታ ተመልከቱ። እምነታችሁን እና ምስክርነታችሁን በእግዚአብሄር ቃል መግቡት። በምድር ላይ እምነታችሁን በግማሽ እዉነታዎች ወሸቶች ጋር እየደባለቁ የሚያንኳስ ሱ አሉ። ለዛ ነው በ ዘሌቄታዊነት ለምንፈሱ ብቁ መሆን ያለባችሁ። የመንፈስ ቅዱስ ረዳትነን ለምቾት ብቻ አይደለም-ለመንፈሳዊ ህልዉናችሁ አስፈላጊ ነው (ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ 1:37)። የክርስቶስን ቃል እና የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ብትሰሙ አትታለሉም።
እየሱስ ክርስቶስ፣ፍጹም የነበረዉ፣እና ዮሴፍ እስሚዝ እንዳልሆነ ያመነዉ፣ሁለቱም የተገደሉን ምስክረነታቸዉን ባልተቀበሉ የዉሸት ከሳሾች ነው። እንዴት ነው ምስክረነታቸዉ እዉነት እንደሆነ የምናዉቀዉ-እየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅ ስለመሆኑ እና ዮሴፍ ስሚዝ እዉነተኛ ነብይ ስለመሆኑ?
“በፍሬያቸዉ ታዉቋችዋላችሁ” ጥሩ ፍሬ ከመጥፎ ዛፍ ማደግ ይችላል?ለራሴ አዉቃለሁኝ አዳኜ ሃጢያቴን ይቅር ብሎ የግላዊ ቀንበሬ ነጻ እንዳወጣኝ፣እንዳለ እንኳን ወደማላዉቀው ደስታ አምቶኝ። አዉቃለሁኝ ዮሴፍ ስሚዝ ነብይ እንደነበረ ምክንያቱም ቀላሉን የመጽሃፈ ሞርሞን ቃል ኪዳን ተግባራዊ አድርጊያለዉ…..”እናም እነዚህንም ነገሮች በምትቀበሉበት ጊዜ እነዚህ ነገሮች ሀሰት እንደሆኑ ዘለዓለማዊ አባታችሁ እግዚአብሔርን በክርስቶስ ስም እንድትጠይቁት እመክራችኋለሁ፤ እናም በንፁህ ልባችሁ፤ ከእውነተኛ ስሜት በክርስቶስ አምናችሁ ከጠየቃችሁት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እውነቱን ይገልፅላችኋል። ”(ሞሮኒ 10:4) በቀላል ቋንቋ ወደላይ ተመልከቱ።
አንዳንዶች አካላዊ ማስረጃ ያስፈልጋል ይላሉ በ ክርስቶስ ትንሳአኤ እና በተመለሰው ወንጌል ለማመን። ለነሱ አልማ ለ ቆሪሆር የተናገረዉን እጠቅሳለሁኝ “በቂ ምልክት አግኝተሃል፣ አምላክህን ትፈትናለህን?የወንድሞችህ ሁሉ፣ እናም ደግሞ የቅዱሳን ነቢያት ምስክርነትን ባገኘህ ጊዜ ምልክት አሳዩኝ ትላለህን? ቅዱሳን መፃሕፍት በፊትህ ቀርበውልሃል፣ አዎን፣ እናም ሁሉም ነገር እግዚአብሔር መኖሩን ያመለክታሉ” (አልማ 30:44)።
እናንተ እና እኔ የአዳኝ አዳኝነት ምስክሮች ነን። ህያዉ ምስክሮች ነን ስለ ዮሴፍ ስሚዝ ትምህርቶች እና በምስክረነታቸዉ ጸንተዉ ስለኖሩት ቅዱሳን። የእየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አሁን ከመቼዉም በላይ በአለም ላይ እየተሰፋፋች ነው-በየዋህ ሰዎች ለማመን መንካት እና ማየት በማያስፈልጋቸዉ።
ማንም ጌታ መቼ እንደሚመጣ አያዉቅም። የመጨረሻዎቹ ግዜዎች ግን ግልጥ እየሆኑልን ነው። ዛሬ ወደላይ ተመልክተን የእዉነታዉ ምንጭ ለማየት አቅንተን አይተን ምስክረነታችን ጠንካራ መሆኑን የምናረጋግጥበት ነው።
እኔ እና የአጎቴ ልጅ በጠዋት ተነሳን ጸሃያማ እና የሚያምር ሰማይ ነበር። አንድ ሰዉ በሩን አንኳኳ የጠፍ ሶስት ወንድ ልጆችን ፍለጋ። ፈረሰ ላይ አስቀምጦን በመጣንበት መንገድ ወደቤታችን አቀናን-በጣም በዙ ሰዎች ሌሊቱን ሙሉ ሲፈልጉን ሰለነበር ትራክተራቸዉ፣መኪናቸዉ ጭቃ ዉስጥ ተቀርቅረዉ ነበር። ኮርቻዎች እዚ ፈረሶች እዛ ሆነዉ አገኙ ስንመለስ ሲያዩ ፍቅራቸዉን እና የመረጋጋት ስሜታቸዉን ማየት እችል ነበር። በከተማዉ መግቢያ ላይ አንዱ የአጎቴ ልጅ ሮጦ ሰላም ሊለን መጣ ከነሱ ፊት ሴት አያቴ እና አጎቴ እና አክስቴ ነበሩ። አቅፈዉን አለቀሱ፣የጠፉትን ልጆቻቸዉን በማግኘታእዉ በጣም ተደስተዉ። ጌታችን ወደቤታችን እስክንመለስ እየጠበቅ ነው።
የነጎድጓድ ምልክቶች በአካባቢያችን አሉ። ወደላይ አየተን እራሳችንን እናዘጋጅ። ጥንቃቄ አለ በጠንካራ ምስክርነት ዉስጥ። ምስክርነታችንን ሁልግዜ እናጠንክረዉ።
ለዘላለሙ እንደቤተሰብ እንደምንኖር አዉቃለሁ፣የሰማይ አባታችን እየጠበቀን ነው፣የእርሱን ልጆች። እየሱስ ክርስቶስ አዳኚያችን ህያዉ ነው። ልክ እንደ ፒጥሮስ ስጋ ና ደም አልተገለጠልኝም፣ግን የሰማይ አባቴ (ማቴዎስ 16:15–19 ተመልከቱ)። በተቀደሰዉ ስም በ እየሱስ ክርስቶስ ስም፣አሜን።